ሩሲያ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት 12 የማዕድን ባለሙያዎች ተገደሉ።
ጥቃቱ በዩክሬን ኢነርጂ ካምፓኒ (DTEK) ንብረት በሆነ አውቶብስ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል።
ድርጊቱ "የሽብር ጥቃት" ሲሉ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ 16 ሰዎች መጎዳታቸውን በኤክስ ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።
የሩሲያ ጥቃት መፈጸም የተሰማው ሁለተኛው ዙር የአቡ ዳቢ ውይይት ረቡዕ ለማካሄድ ቀጠሮ በተያዘበት ወቅት ነው። #independent
@EyobTikuye @ThiqahETH

😢4🙏2
THIQAH
"ግድቡ አደገኛ ነገር ነው። የሆነ ነገር ማድረግ አለብን ብየ አስባለሁ" - አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ኢትዮጵያ እና ግብፅን ማደራደር ይቻላል" ሲሉ የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ እንደአዲስ ቀስቅሰውታል። ፕሬዝዳንቱ በስዊዘርላንድ በተካሄደው የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ከግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር ተወያይተዋል። ትራምፕ በዚህ ወቅት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውዝግብ…
"በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" - ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በዛሬ የፓርላማ ማብራሪያቸው አሜሪካ ስለህዳሴ ግድቡ በተደጋጋሚ ለምትለፍፈው ጉዳይ እክት ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ "ለህዳሴ ግድቡን በገንዘብ ረድታለች" በማለት ከሦስት ጊዜ በላይ መናገራቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በዋይትሃውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፣ "ዩናይትድ ስቴትስ የህዳሴ ግድብን በገንዘብ በማገዟ ኃላፊነት ትወስዳለች" ሲሉ ተደምጠው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ደግሞ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ "በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" ሲሉ እክት ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።
"በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ ጠቋም በሀገር ውስም በከሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨክነው በጋራ ቆመው ስለሰሩ የተከናወነ ፕሮጀክት ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
አቢይ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች እምብዛም ስለሌሉ ወጣቶች ለስራ አጥነት ጨምር እየተጋለጡ በመሆኑ ምላሽ እንዲሰጡ ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ሲሆን፣ ከዚህ ንግግራቸው አስከትለውም፣ "ግን በዚህ አላበቃም፤ ህዳሴ ከአፍሪካ አንደኛውን ሰርተናልና ሌላ አያስፈልግም እኮ አላለችም ኢትዮጵያ" ብለዋል።
"በአፍሪካ ሦስተኛውንም ኮይሻ እየገነባን ነው ያለነው። የንፋሱን ሳንጨምር። በርካታ ፕሮጀክቶች ይሰራሉ" ነው ያሉት።
"'ፕሮጀክቶ ቋሟል፤ ሜጋ፣ ሜጋ ፕሮጀክት የለም' ለተባለው። እውነት ነው ፕሮጀክት የለም። ግን ከአፍሪካ አንደኛው ኤርፓርት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀምሯል" ሲሉ መልሰዋል።

❤14🥰8
ሞሮኮ በከባድ ጎርፍ ተመታች።
በጎርፍ የተጎዳችው ሞሮኮ ከ50 ሺሕ በላይ ዜጎቿን ከአካባቢው አስወጥታለች።
የክሳር ኤልከቢር ከተማ ግማሽ የሚሆኑት ነዋሪዎች በአደጋው ምክንያት አካባቢውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል ተብሏል።
በከተማዋ ለሳምንት የጣለው ዝናብ ከባድ ጎርፍ ማስከተሉ ተገልጿል።
ክሳር ኤልከቢር ከተማ ከዋና ከተማዋ ራባት በሰሜን አቅጣጫ 190 ኪሎሜትር ርቃ ትገኛለች ተብሏል። #asiaone

❤6
THIQAH
"ስምምነት ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ብየ አስባለሁ፣ ያኔ ኩባ ነፃ ትሆናለች" - ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኩባ የሚገባው ነዳጅ መቆም በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ "ውይይት" ያስፈልጋል አሉ። "ስምምነት ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ብየ አስባለሁ፣ ያኔ ኩባ ነፃ ትሆናለች" ብለዋል። ትራምፕ "ኩባ ከዋሽንግተን ጋር መስማማት ከቻለች ሰብዓዊ ቀውስ አይፈጠርም" ሲሉ አብራርተዋል። "ኩባ ለአሜሪካ…
"ሀቫና ከዋሽንግተን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ናት ግን ለድርድር የማይቀርቡ ነገሮች አሉ" የኩባ ዲፕሎማት
ኩባ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ንግግር መጀመሯን ጠቆመች።
የኩባ የውጭ ሚኒስትር ዲዔታ ካርሎስ ፈርናንዴዝ ዲካሲዮ "ትርጉም ያለው እና ሀላፊነት የተሞላበት ድርድር ለማድረግ መዘጋጀታችንን የአሜሪካ መንግስት ያውቃል" በማለት የሀገራቸውን አቋም አንፀባርቀዋል።
ዲካሲዮ "ሀቫና ከዋሽንግተን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ናት፣ ግን ለድርድር የማይቀርቡ ነገሮች አሉ" ብለዋል።
"የህገመንግስት ለውጥ እና ሶሻሊስት መንግስት መቀየር በፍጹም ተቀባይነት የለውም" ሲሉም ተናግረዋል።
"ኤምባሲዎች አሉ፣ ንግግሮች አሉ፣ መልዕክት እንለዋወጣለን፣ ግን በጠረጴዛ ዙሪያ የተደረገ ውይይት አልተካሄደም" ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ'ለት ኩባ ለድርድር እንድትዘጋጅ ካልሆነ ግን ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። #aljazeera

❤6🥰2👏2
በፖላንድ መነሻው ያልታወቀ ድሮን በወታደራዊ ካምፕ አጠገብ ተከሰከሰ።
ከየት እንደተላከ ያልታወቀው ሰው አልባ ድሮኑ አሪየል ቬህክል (UAV) ስሪት መሆኑን የፖላንድ ጦር ገልጿል።
ጦሩ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ያረፈው በወታደራዊ ካምፕ አጠገብ መሆኑ ከፍተኛ ጥርጣሬ ተፈጥሯል ብሏል።
የድሮኑ መነሻ ቦታ እና የተላከበት አላማ በግልጽ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ነው ሲል አስታውቋል።
የፖላንድ ጦር ካሁን በፊት በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በድንበር አቅራቢያ ከሞስኮ የተላኩ ድሮኖችን መያዙ ይታወቃል። #aa

❤3🥰1👏1😢1🙏1🕊1
በናይጄሪያ በደረሰ የጭነት መኪና አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ።
ከሌጎስ ወደ ኢባዳን በሚወስደው መንገድ በደረሰው በዚህ አደጋ 23 መንገደኞች መጎዳታቸውን የፌደራል መንገድ ደህንነት ኮርፕ (FRSC) አስታውቋል።
የአደጋው ምክንያት ፍጥነት ያስከተለው መጋጨት እንደሆነ ተገልጿል። #naijanews
@EyobTikuye @ThiqahETH
ከሌጎስ ወደ ኢባዳን በሚወስደው መንገድ በደረሰው በዚህ አደጋ 23 መንገደኞች መጎዳታቸውን የፌደራል መንገድ ደህንነት ኮርፕ (FRSC) አስታውቋል።
የአደጋው ምክንያት ፍጥነት ያስከተለው መጋጨት እንደሆነ ተገልጿል። #naijanews
@EyobTikuye @ThiqahETH
😢5❤3🥰1👏1😭1
ጋና ለአፍሪካውያን የምትሰጠውን ዜግነት በጊዚያዊነት አቆመች።
አገልግሎቱ የቆመው "በጊዚያዊነት ነው" የተባለ ሲሆን፣ መቼ እንደሚመለስ ግን የተባለ ነገር የለም።
ውሳኔው የተላለፈው "ውድ፣ ውስብስብ እና ከባድ" ነበር የተባለውን አሰራር ዳግም ለመፈተሽ እንደሆነ ተገልጿል።
ከ2016 ጀምሮ አፍሪካዊ ዝርያ ያላቸው ተወላጆች ለዜግነት የሚያመለክቱበት አሰራር እንደነበር የሀገሪቱ መንግስት አስታውሷል።
ባርነትን ጨምሮ በተለያየ ምክንያቶች ከአፍሪካ የተሰደዱ ሰዎችን አፍሪካዊ ማንነት ለመስጠት በማለት መጀመሩም ተገልጿል።
በዚህ ፕሮግራም ከ1000 በላይ አፍሪካውያን የጋና ዜግነት ማግኘት መቻላቸው ተመልክቷል። #saharareporters

❤5😢3🙏1🕊1
THIQAH
ሩሲያ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት 12 የማዕድን ባለሙያዎች ተገደሉ። ጥቃቱ በዩክሬን ኢነርጂ ካምፓኒ (DTEK) ንብረት በሆነ አውቶብስ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል። ድርጊቱ "የሽብር ጥቃት" ሲሉ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ 16 ሰዎች መጎዳታቸውን በኤክስ ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል። የሩሲያ ጥቃት መፈጸም የተሰማው ሁለተኛው ዙር የአቡ ዳቢ ውይይት ረቡዕ ለማካሄድ ቀጠሮ በተያዘበት ወቅት ነው። #independent…
ሩሲያ በአንድ ሌሊት 450 ድሮን እና 70 ሚሳዔል ወደ ዩክሬን አስወነጨፈች።
ሞስኮ ከሁለተኛው ዙር ድርድር በፊት በዩክሬን ላይ ከባድ የአየር ላይ ጥቃት ፈጽማለች ተብሏል።
ጥቃቱ በአምስት የዩክሬን ክልሎች ላይ የተፈፀመ ሲሆን በዋናነት የሀይል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ተገልጿል።
የውሃ እና የኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫዎች ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል ተብሏል።
ጥቃቱ ሌሊት ላይ ከተፈፀመ በኋላ ዛሬ ጠዋት ላይ 1 ሺሕ 170 የመኖሪያ አፓርትመንቶች መብራት እንደተቋረጠባቸው ተገልጿል።
በዚህ ጥቃት የሞት ሪፖርት አለመኖሩ ቢገለጽም፣ 10 ሰዎች ግን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ሩሲያ በትናንትናው እለት በፈፀመችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት 12 የማዕድን ባለሙያዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል። #euronews
@EyobTikuye @ThiahETH

❤8😢5👏2😡2
የሱዳን ጦር ባደረሰው የድሮን ጥቃት ህፃናት ጨምር ተገደሉ።
የሱዳን ጦር ካዱግሊ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል።
የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች (RSF) ከተማዋን ለቀው ሲወጡ በፈፀሙት የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል።
ከሟቾቹ ውስጥ ሦስቱ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል።
የከተማዋ ነዋሪዎች የሀገሪቱ ጦር ሲገባ በአደባባይ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
ተመድ በካዱግሊ ከተማ የርሃብ አደጋ መከሰቱን ያወጀው ከአንድ አመት በፊት ቢሆንም ያለፉት ሁለት ወራት በተለየ መልኩ የምግብ እጥረት መፈጠሩን አስታውቋል። #dailysabah #swedenherald

😢8❤5👏4🙏2
"ከአሜሪካ ጋር ያለንን ትብብር ማሳደግ ፍላጎቴ ነው" - ጉስታቮ
"በቬኔዙዌላ የተፈጠረው ፔትሮ ሀሳቡን እንድቀይር አድርጎታል፣ ለውይይት ዝግጁ ሆኗል" - ትሪምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮን በዋይትሃውስ ጋብዘዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት "በሽተኛ ነው" ሲሉ ከጠሩት ፔትሮ ጋር ለመገናኘትና ውጥረቱን በውይይት ለማርገብ መወሰናቸው ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ጉስታቮ በበኩላቸው፣ በጋዛ ጦርነት "የተወዛገበ ዘር ጨፍጫፊ" ሲሉ ከወቀሱትና ፕሬዘዳንት ማዱሮ ላይ የወሰደውን እርምጃ "እገታ ነው የፈፀመው" ሲሉ ካወገዙት ትራምፕ ጋር "ከአሜሪካ ጋር ያለንን ትብብር ማሳደግ ፍላጎቴ ነው" ብለዋል።
መሪዎቹ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር እና በላቲን አሜሪካ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሏል።
ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ "በቬኔዙዌላ የተፈጠረው ፔትሮ ሀሳቡን እንድቀይር አድርጎታል፣ ለውይይት ዝግጁ ሆኗል" ሲሉ ተናግረዋል።
አሜሪካ እና በአለም ላይ ቀዳሚዋ የኮኬይን አምራች ኮሎምቢያ ላለፉት 30 አመታት የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል ተብሏል። #huffpost

🕊2😡2❤1🙏1
THIQAH
"አሜሪካ ኢራንን ካጠቃች ኢራናውያን ጠንካራ ምላሽ ይሰጣሉ፣ በአሜሪካ የተጀመረው ጦርነት ደግሞ በቀጠናው ይስፋፋል" - አያቶላሕ ኮሚኒ "ተስፋ አደርጋለሁ ስምምነት ላይ እንደርሳለን፣ ከተስማማን ጥሩ ነው፣ ካልተስማማን የሚፈጠረውን እናያለን" - ትራምፕ ኢራን ህይወታቸው ያለፈ 2 ሺሕ 986 ተቃዋሚዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደርጋለች። ለሦስት ሳምንታት በቀጠለው አመጽ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ጠቅላይ ድምር…
አሜሪካ የኢራንን ድሮን መትታ ጣለች።
አንድ የኢራን ድሮን በገልፍ ወደሚገኘው የአሜሪካ አየር ሀይል ሲበር ነው ጥቃቱ የተፈፀመው ተብሏል።
ኢራን ኢላማ ያደረገችው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ ያሰማሩት ዩኤስኤስ አብረሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ ነው ተብሏል።
ይሁን እንጂ ስለተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካም ይሁን የኢራን ባለስልጣናት የሰጡት ማረጋገጫ የለም ነው የተባለው።
የአሜሪካ ባህር ሀይል የኢራንን ጥቃት ማክሸፉ የተሰማው ኢራን እና አሜሪካ ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን በገለፁ ማግስት ነው።#ukdefencejournal #reuters

❤7😢3🙏1
"ዚንታን በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተፈጽሞ ነው ህይወቱ ያለፈው" ኮካድ
የፕሬዝዳንት ጋዳፊ ልጅ በታጣቂዎች ተገደለ።
የቀድሞው የሊቢያ ፕሬዚዳንት መሀመድ ጋዳፊ ልጅ ሰይፈ አል ኢስላም ጠበቃ ማርሴል ኮካድ በምዕራብ ሊቢያ "ዚንታን በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተፈጽሞ ነው ህይወቱ ያለፈው" ብለዋል።
የፈረንሳይ ዜግነት ያለው የአል ኢስላም ጠበቃ "አራት ሰዎች ናቸው እሱን ለመግደል የተሳተፉት" ሲሉ ተናግረዋል።
የቅርብ አማካሪው አብዱራህ አብዱራህማን በበኩላቸው፣ "የደህንነት ካሜራዎቹን በእሳት አደጋ አበላሽተው እሱን ገደሉት" ሲሉ ግድያው እንዴት እንደተፈጸመ አስረድተዋል።
የ53 አመቱ አል ኢስላም በዓለማቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት (ICC) "በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች" ክስ የእስር ትዕዛዝ አውጥቶበታል።
በ2011 በቁጥጥር ስር ውሎ በ2015 የሞት ፍርድ ቢፈረድበትም በይቅርታ መውጣት ችሎ ነበር።
በ2021 ለምርጫ እንደሚሳተፍ ቢያሳውቅም ምርጫው ተራዝሞ ሳይሳተፍ ቀርቷል። #legit #ndtv
@EyobTikuye @ThiqahEth

💔8❤7🕊2
ስፔን ከ16 አመት በታች በሆኑ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ገደብ ልትጥል ነው ተባለ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በቀጣይ ሳምንት ህጋዊ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።
ሳንቼዝ በዱባይ የመንግስታት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር "የጥላቻ ንግግር፣ የወሲብ ድረገጾች እና ሀሰተኛ መረጃ በወጣቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል" ብለዋል።
"ልጆቻችን መጓዝ በሌለባቸው መስመር እያለፉ ነው፣ ይህ ከዚህ በኋላ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ እድሜን መሠረት ያደረገ እርምጃ እንድወስዱ ጠይቀዋል።
አውስትራሊያ ባለፈው ህዳር ወር ከ16 አመት በታች ለሚገኙ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያን በመከልከል የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
ፈረንሣይ ተመሳሳይ ውሳኔ ለማሳለፍ መዘጋጀቷን ፕሬዚዳንት ማክሮን ጠቁመዋል። #theguardian
@EyobTikuye @thiqaheth

👏12❤7🥰1🙏1🕊1
THIQAH
አሜሪካ የኢራንን ድሮን መትታ ጣለች። አንድ የኢራን ድሮን በገልፍ ወደሚገኘው የአሜሪካ አየር ሀይል ሲበር ነው ጥቃቱ የተፈፀመው ተብሏል። ኢራን ኢላማ ያደረገችው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ ያሰማሩት ዩኤስኤስ አብረሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ስለተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካም ይሁን የኢራን ባለስልጣናት የሰጡት ማረጋገጫ የለም ነው የተባለው። የአሜሪካ ባህር…
"በኤፍ-35 ተዋጊ ጄት ነው ተመትቶ የወደቀው፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል" - የአሜሪካ ባህር ሀይል
የኢራን ድሮን በአሜሪካ ጦር መመታቱን አሜሪካ ማረጋገጫ ሰጥታበታለች።
የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን ወደ አብረሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ሲጓዝ እንደነበር የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ አስታውቋል።
የመርከቡ የባህር ኃይል ካፒቴን ቲም ሃውኪንስ፣ "የኢራን ሻህደድ-139 ድሮን ግልጽ ፍላጎቱ በማይታወቅበት ሁኔታ ወደ ጦር መርከቡ እየተጠጋ ነበር" ብለዋል።
"በኤፍ-35 ተዋጊ ጄት ነው ተመትቶ የወደቀው፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል" ሲሉም ገልጸዋል።
ካፒቴኑ፣ "መርከቡን እና በመርከቡ የሚገኙ የባህር ሀይል አባላትን ለመጠበቅ የወሰድነው እርምጃ ነው፣ የተጎዳብን ሰው የለም" በማለት አብራርተዋል።
ኢራን ተፈጽሟል ስለተባለው ጥቃት እና ስለወደመባት ድሮን የሰጠችው ማብራሪያ የለም። #thewashingtonpost

❤3🕊3😡1
"የምዕራባውያን 'ተኩስ አቁም የማስፈጸም' ዕቅድ የይስሙላ ነው" - ተንታኝ
-አሜሪካ፣
-አውሮፓ እና
- ዩክሬን ሩሲያ የዩክሬንን የሰላም ስምምነት "ከጣሰች" ተግባራዊ እናደርጋለን በሚል በቅንጅት አዘጋጅተውታል የተባለው የ" 'ወታደራዊ ምላሽ' "ዕቅድ፤ የዘለንስኪን አገዛዝ ለማባበል ያለመ ነው ሲሉ ሩሲያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ኮንስታንቲን ብሎኪን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እነዚህ ተስፋዎች ዩክሬንን ወደ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመገፋፋት የታሰቡ ሊሆኑ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ጉዳዩ ገጽታን የመጠበቅ ነው፤ ምዕራባውያን ዩክሬንን እየተዋት እንዳልሆነ እና "የተወሰኑ ቁርጠኝነት እያሳዩ" እንደሆነ ለማሳየት ነው ብለዋል።
"ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚገቡት ቃል የግድ በተባለው መሰረት ይፈጸማሉ ማለት አይደለም" ነው ያሉት።
ዩክሬን፤ ከምዕራባውያን ደጋፊዎቿ ጋር በመሆን ሩሲያ የሰላም ስምምነቱን "ከጣሰች" ለሚሰጠው ደረጃውን የጠበቀ ምላሽ መስማማቷን ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።
ዕቅዱ "የአሜሪካን ጦር የሚያካትት እና በምዕራባውያን የሚደገፍ የተቀናጀ ወታደራዊ ምላሽ" በመጨረሻ አማራጭነት አስቀምጧል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ የገለጸች ቢሆንም፤ ማንኛውም የኔቶ ጦር በሀገሪቱ ውስጥ መሰማራቱ ተቀባይነት እንደሌለው እና ውጥረቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቃለች። #Sputnik

❤4😢2🥰1🕊1
ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን የኤችአይቪ መድኃኒት በሰዎች ላይ ሙከራ አደረገች።
መድሃኒቱ ፍቃደኛ በሆኑ 20 ሰዎች ላይ በሙከራ መሰጠቱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሀገሪቱ 8 ሚሊዮን የሚደርሱ ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ዜጎች እንዳሉ ተገልጿል።
ይህም በአፍሪካ ትልቁ የቫይረስ ተጠቂ ቁጥር ያለባት ሀገር አድርጓታል ተብሏል።
በ2023 በተደረገ ጥናት በሰብ-ሰሀራ አፍሪካ 25.6 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካ የሞከረችው መድሃኒት ውጤታማ ከሆነ ለቀጠናው ተስፋ እንደሚሆን ተገልጿል። #eyewitnesnews

❤23👏4🙏3🥰1
በግሪክ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ስደተኞቹን ለማትረፍ አራት የባህር ጠባቂ ጀልባዎች እና በሄሊኮፕተር እገዛ 24 ሰዎች ከአደጋው ተርፈው ለህክምና ተወስደዋል ተብሏል።
ጀልባዋ ከየት እንደተነሳች እና ስንት ሰዎችን እንደጫነች ትክክለኛ መረጃ አለመገኘቱን የግሪክ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ስደተኞቹ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና አፍሪካ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ የሚመርጡት በግሪክ በኩል ያለውን መግቢያ በር እንደሆነ ተገልጿል። #novinite

😢5🕊3❤1