THIQAH
10.9K subscribers
4.42K photos
48 videos
1 file
38 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
ትልልቅ አየር መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያደርጉትን በረራ ለሳምንት አቆሙ።

ኤርፍራንስ፣ ብሪቲሽ ኤርዌይስ፣ እና ሉፍታንዛ አየር መንገዶች በረራ ለማቆም ከወሰኑት መካከል ይገኙበታል።

አየር መንገዶቹ በረራዎችን ያቆሙት በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በአዲስ መልኩ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ አሜሪካ ጥቃት ልትፈጸሸም ትችላለች በሚል የደህንነት ስጋት እንደሆነ ተገልጿል።

በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በበረራው መሰረዝ ምክንያት ተስተጓጉለዋል።

የአየር መንገዶቹ በረራ ማቆም ውሳኔ ለአንድ ሳምንት ፀንቶ እንደሚቆይ ተገልጿል።   #airlive

@EyobTikuye @ThiqahETH
7🕊3🤔2😱2
THIQAH
"እጃችን ምላጩ ላይ ነው" ኢራን "መላው የአየር ኃይላችን ዝግጅቱን ጨርሶ በተጠንቀቅ ቆሟል" - እስራኤል "ኢራን እጃችን ምላጩ ላይ ነው። በተጠንቀቅ ቆመናል" በማለት አሜሪካና እስራኤል ላይ ዝታለች። አሜሪካ በበኩሏ፣ በየትኛውም ያልተጠበቀ ሰዓት ኢራንን ለማጥቃት መዘጋጀቷ ተነግሯል። የጦር መርከቦቿ ወደ ኢራን ጉዞ መጀመራቸውም ታውቋል። የእስራኤል አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ቶመር ባር…
"አርማዳ የጦር መርከብ ወደ ኢራን እየተጓዘ ነው" - አሜሪካ

"ሁሉን ያቀፈ ጦርነት ይከሰታል። አሜሪካ የኢራንን ሉዓላዊነት ከጣሰች ምላሽ ለመስጠት እንገደዳለን" - ኢራን

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተቃዋሚዎች ግድያ እና በኑክሌር ፕሮግራም "ሰበብ" ወደ ኢራን የጦር መርከብ መላካቸውን ተከትሎ ኢራን አስጠነቀቀች።

ዶናልድ ትራምፕ "አርማዳ የጦር መርከብ ወደ ኢራን እየተጓዘ ነው፣ እንደማንጠቀመው ግን ተስፋ አለኝ" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ "ብዙ ሚሳዔል አውዳሚ መሳሪያዎች በቀጣይ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ይላካሉ" ነው ያሉት።

"አስፈላጊ ከሆነ ብቻ ነው የምንጠቀማቸው ሁኔታውን በቅርበት እንከታተለዋለን" በማለት ገልጸዋል።

ስማቸው ያልተጠቀሰ የኢራን ከፍተኛ የጦር አመራር በበኩላቸው፣ "ይህ የጦር ክምችት ለውጊያ ነው ብለን አናስብም፣ ግን የኢራን ጦር ዝግጁ ነው" ብለዋል።

"በዚህ ሰዓት የሚቃጣ የትኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት የሚያስችል ቁመና አለን" ሲሉ አብራርተዋል።

"ሁሉን ያቀፈ ጦርነት ይከሰታል" በማለት ጦርነቱ ቀጠናዊ እንደሚሆን የገለጹት እኒሁ አመራር፣ "አሜሪካ የኢራንን ሉዓላዊነት ከጣሰች ምላሽ ለመስጠት እንገደዳለን" በማለት አስታውቀዋል። #skynews

@EyobTikuye  @ThiqahETH
12🕊3🤔2👏1😱1😢1
THIQAH
ትልልቅ አየር መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያደርጉትን በረራ ለሳምንት አቆሙ። ኤርፍራንስ፣ ብሪቲሽ ኤርዌይስ፣ እና ሉፍታንዛ አየር መንገዶች በረራ ለማቆም ከወሰኑት መካከል ይገኙበታል። አየር መንገዶቹ በረራዎችን ያቆሙት በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በአዲስ መልኩ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ አሜሪካ ጥቃት ልትፈጸሸም ትችላለች በሚል የደህንነት ስጋት እንደሆነ ተገልጿል። በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች…
የመካከለኛው ምሥራቅ የፓለቲካ ውጥረት ተከትሎ በዋናነት የተቋረጡ በረራዎች መካከል ተከታዮቹ ተጠቃሽ ናቸው።

ስዊዝ አየር መንገድ (Swiss Airlines) በረራ ካቋረጡት አንዱ ነው። ወደ እስራኤል የሚደረጉ በረራዎችንም ሰርዟቸዋል።

የሆላንድ አየር መንገድ የሆነው KLM ሌላኛው ነው። በዚህም
-ወደሳዑዲ አረቢያ፣
-የተባበሩት አረብ ኢምሬስት
-እስራኤል የሚደረጉ በረራዎችን ሰርዟል።

ብሪቲሽ ኤርዌይስ (British Airways) በረራውን ሰርዟል። የሰረዘውም ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚደረጉ ጉዞዎችን ነው።

ኤር ፍራንስ (Air France) አየር መንገድም በተመሳሳይ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚያደረጉ በረራዎችን አቋርጧል።

ዩናይትድ አየር መንገድ (United Airlines) እና ኤር ካናዳ (Air Canada) በበኩላቸው፥ ወደ እስራኤል እና መካከለኛው ምስራቅ የሚያደጉ በረራዎችን አቋርጠዋቸል።

@EyobTikuye @ThiqahETH
🕊4🤔3🙏1
THIQAH
"ሶማሊያውያንን በእኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊያ ዜጎችን ከአሜሪካ ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቁ። ፕሬዝዳንቱ "እውነት ለመናገር በፖለቲካ ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ግን ሶማሊያውያንን በእኛ ሀገር ማየት አልፈልግም" ሲሉ ተደምጠዋል። "እነሱ (የሶማሊያ ዜጎች) በእኛ ሀገር ላይ የጨመሩት ነገር የለም፣ በአጋጣሚ ሀገራቸው ደግሞ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም" ብለዋል። የትራምፕ…
"ስደተኞች እየተያዙ ያሉት በስራ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ በገበያ ቦታዎች እና በመኖሪያ ቤታቸው መሆኑ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል" - ቮልከር ተርክ

ተመድአሜሪካ ስደተኞችን የምትይዝበትን መንገድ በብርቱ ተቃውሟል።

የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ፣ "የአሜሪካ ኢምግሬሽንና ጉምሩክ ኢንፎርስመንት (ICE) ስደተኞች የሚይዝበት መንገድ ሰብዓዊነት እንደመንፈግ ይታያል" ብለዋል።

ቮልከር በወቅታዊ የስደተኞች አያያዝ ላይ በሰጡት መግለጫ፣ "የህግ አግባብን ያልተከተለ፣ የቤተሰብ አንድነት የሚንድ እና መሰረታዊ የሰብዓዊ አያያዝ መርህን የጣሰ ነው" ሲሉ ተችተዋል።

"በአሜሪካ ሰነድ አልባ ስደተኞች በግድ መታደናቸው፣ መያዛቸው እና መታገታቸው አሳሳቢ ነው" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ "ስደተኞች እየተያዙ ያሉት በስራ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ በገበያ ቦታዎች እና በመኖሪያ ቤታቸው መሆኑ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል" ብለዋል።

የአሜሪካ ኢምግሬሽንና ጉምሩክ ኢንፎርስመንት (ICE) ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ የስደተኞች አያያዝን በሚቃወሙ ስደተኞች ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። #theauthiritynews

N.B አሜሪካ በሀገሯ የሚገኙ የየትኛውም ሀገር ሰነድ አልባ ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ካልወጡ እስራት በመፈጸም ጭምር በግዳጅ ለመባረር እንደምትገደድ መግለጿ ይታወሳል። ከ60 ቀናት በኋላም የማሳደድ ዘመቻው ተጀምሯል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH
12🤔2😡2🙏1
THIQAH
"አሜሪካ እና ኔቶ የተስማሙበትን ጉዳይ አላውቅም" - ግሪንላንድ የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሬድሪክ ኔልሰን የሀገራቸው አቋም እንደማይቀየር ገልጸዋል። ኔልሰን ዛሬ በዋና ከተማዋ ኑክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ "በኛ ጉዳይ ከኛ ውጭ እኛን ወክሎ ስምምነት መፈጸም የሚችል አካል የለም" ሲሉ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ያደረጉትን ስምምነት "ተቀባይነት…
የአውሮፓ ህብረት በግሪንላንድ ጉዳይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።

አስቸኳይ ስብሰባው የተጠራው ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ እንደሆነ ስማቸው ያልተገለጸ አምስት ዲፕሎማቶች ማረጋገጣቸው ታውቋል።

ህብረቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የታሪፍ እርምጃን ለመቀልበስ "ንግድን እንደ ጦር መሳሪያ ለመጠቀም ማቀዱ" ተገልጿል።

ትራምፕ ግሪንላንድን ለመቆጣጠር የያዙትን ውሳኔ ካልቀለበሱ ህብረቱ ምላሽ መስጠት ግዴታው እንደሆነ ያምናል ተብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ በውሳኔያቸው ላይ ተቃውሞ ባሰሙ ስምንት የአውሮፓ ሀገራት ላይ ሊጥሉት የነበረውን ታሪፍ ከኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ከተወያዩ በኋላ በጊዜያዊነት መተዋቸውን አስታውቀዋል ሲል ፓለቲኮ ዘግቧል።

ትራምፕ፣ ግሪንላንድን "የአሜሪካ አካል" የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ለዴንማርክ አቻቸው ሜቴ ፍሬድሪክሰን በደብዳቤ ካሳወቁ በኋላ አሜሪካና ግሪንላንድ ብርቱ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተዋል።

በአውሮፓ ፓርላማ የዴንማርክ ተወካይ አንደር ቪስትሰን "ግሪላንድ ለሽያጭ የቀረበች አይደለችም" ሲሉ የትራምፕን ሀሳብ ውድቅ ማድረጋቸውም አይዘነጋም።

ትራምፕ ሰሞኑን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረምን ለመታደም ወደ ስዊዘርላንድ ባቀኑበት ወቅትም "ትራምፕ እንኳን ደኀና መጡ መባል የለባቸውም" የሚል ተቃውሞ ከዙሪክ ከተማ ሰልፈኞች እንደገጠማቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የአውሮፓ ህብረት ለዚሁ ጉዳይ ስብሰባ የሰጠራ ሲሆን፣ ስብሰባው ከተካሄደ ውጤቱን በመከታተል ቲቃህ መረጃ ያቀርባል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH
8🤔2🕊2
የሶማሊያ ጦር "በ59 የአልሸባብ አባላት ላይ እርምጃ" መውሰዱን ገለጸ።

ጦሩ ለ24 ሰዓታት በቆየ ዘመቻ "42 የቡድኑ አባላት መቁሰላቸውን" እና "10 አልሸባብ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች" መያዙን አስታውቋል።

የሀገሪቱ ጦር "ወስጀዋለሁ" ባለው "ጠንካራ እርምጃ የኩዳይ ስትራቴጂክ ግዛት መልሶ መቆጣጠሩን" ገልጿል።

በዚህም ጦሩ ዘመቻውን ያከናወነው በሶማሊያ ከሚገኘው የአሜሪካ ጦር ጋር በመቀናጀት እንደሆነ አስታውቋል። #thenewarab

@EyobTikuye @ThiqahETH
14🕊2👏1🙏1
የ75 አመቱ የቻይና ከፍተኛ የጦር ጀነራል በ"ግልጽ የዲሲፕሊን ጥሰት" ወንጀል ተጠርጥረው ታያዙ።

ቻይና በማዕከላዊ ጦር ኮሚሽን (CMC) የጦር ጄነራሏ ላይ የሙስና ወንጀል ምርመራ ጀምርመራ መጀመራ ታውቋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ጄነራል ዣንግ ዪዢያ፣ "ግልጽ የዲሲፕሊን ጥሰት" በመፈጸም ተጥርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።

የ75 አመቱ ጄነራል ዪዢያ ከጦር አመራርነታቸው ባለፈ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ (CCP) ሥራ አስፈፃሚ አባል መሆናቸው ተገልጿል።

ጄነራሉ በቅርቡ በፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ አማካኝነት የተጠራ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል ተብሏል።

ቻይና ባለፈው ጥቅምት ከዪዢያ በፊት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ጄነራል ዣንግ ሸንግሚንን በተመሳሳይ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ማዋሏ ይታወሳል።  #thestraightstimes

@EyobTikuye @ThiqahETH
4🤔3👏1🕊1
በሱዳን የወርቅ ማዕድን ማውጫ በደረሰ አደጋ 6 ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች ተጎዱ።

በደቡብ ኮርዶፋ በተከሰተው በዚህ አደጋ 12 ሰዎች መጎዳታቸው እና በደርዘን የሚቆጠሩ መጥፋታቸው ተገልጿል።

ለተጎጂዎች የህክምና እርዳታ መሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን፣ መንግስት ለማዕድን አውጪዎች በቂ ስልጠና እና የደህንነት ዋስትና መስጠት አለበት ተብሏል።

በሀገሪቱ ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ በማዕድን ማውጣት ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንዳሉ፣ ነገር ግን 80% የሚሆኑት በቂ ስልጠና የሌላቸው እንደሆኑ ተገልጿል። #trtworld

@EyobTikuye @ThiqahETH
😢96🤔4👏1
በኢንዶኔዥያ በደረሰ የመሬት መንሸራተት 7 ሰዎች ሲሞቱ 82 ቆሰሉ።

በምዕራብ ጃቫ ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ ለመሬት መንሸራተት አደጋው መንስኤ መሆኑን የኢንዶኔዥያ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ (IDMA) አስታውቋል።

ኤጀንሲው የጠፉትን ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል። #onmanorama

@EyobTikuye @ThiqahETH
😢63😱1🙏1😭1
"በዌስት ባንክ ጊዜ የማይሰጥ ረሃብ ተከስቷል" - ፍሊፕ ላዛርኒ

የፍልስጤም አንዱ ግዛት የሆነው ዌስት ባንክ አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ እያስተናገደ መሆኑ ተሰምቷል።

በፍልስጤም የተመድ ዕርዳታ ስራ ኤጀንሲ (UNRWA) ኃላፊ ፍሊፕ ላዛርኒ፣ "በዌስት ባንክ ጊዜ የማይሰጥ ረሃብ ተከስቷል" ብለዋል።

"ዌስት ባንክ ከ1967 በኋላ ከባድ አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ ተጋርጦበታል" ሲሉ ያጋጠመውን የአቅርቦት ችግር አስረድተዋል።

"33,000 ፍልስጤማውያን በሰሜን ዌስት ባንክ ከሚገኙ የስደተኞች ካምፕ ተፈናቅለዋል" ሲሉም ገልጸዋል።

እንደ ላዛርኒ ገለፃ የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ የፍልስጤም ነዋሪዎችን ማፈናቀል አላቆመም። #gulftimes

@EyobTikuye  @ThiqahETH
😢4💔4😱3👏21😡1
THIQAH
Photo
"የሃይማኖት አባቶች በአየር መንገድ ተገኝተን ስደተኞች እንዳይመለሱ ለመማጸን ነው የመጣነው" - ቄስ ቶልጋርድ

"ፖሊስ በሚኒሶታ 100 የሚጠጉ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል" !

በአሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈፎች የስደተኞች አያያዝን በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

በሚኒሶታ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ ፉሮስ ቶልጋርድ፣ "ፖሊስ በሚኒሶታ 100 የሚጠጉ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል" ብለዋል።

"በከተማዋ 700 የሚደርሱ የንግድ ሱቆችና ትምህርት ቤቶች በአመፁ ምክንያት ተዘግተዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

"የሀይማኖት አባቶች በአየር መንገድ ተገኝተን ስደተኞች እንዳይመለሱ ለመማጸን ነው የመጣነው" በማለት ገልፀዋል።

"ሚኒሶታ አካባቢ የተፈጠረው ህሊና የማይፈቅደው ነገር ነው" ያሉት ቄስ ቶልጋርድ "በዚህ ሁኔታ መኖር ውስብስብ ችግር ፈጥሮብናል" ነው ያሉት።  

ቄስ ቶልጋርድ "ፖሊስ ወደመጣንበት እንድንመለስ ቢጠይቀንም እኛ ከስደተኞች ጎን መቆማችንን ለማሳየት እዚሁ ድምፃችንን እያሰማን ነው፣ ለውጥ ካላየን አንመለስም" ብለዋል።

የኢምግሬሽን እና ከስተም ኢንፎርስመንት (ICE) ፖሊስ የሁለት እና የአምስት አመት ህፃን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ስደተኞችን ይበልጥ ስጋት ላይ መደቀኑ ተገልጿል። #silive

@EyobTikuye   @ThiqahEth
19👏7😢5🥰2😡1