ዝምባብዌ የውጭ ሀገራት ዜጎች በታክሲ እና በዳቦ ቤት ስራዎች እንዳይሰማሩ ከለከለች።
14 የስራ ዘርፎች የስራ እድል ለመፍጠር በማሰብ ለሀገር ውሰጥ ዜጎች ቅድሚያ እንድሰጥ ተወስኗል።
ከእነዚህም ውስጥ የፀጉር ቤት፣ የውበት ሳሎን፣ የጥበቃ አገልግሎት፣ የቅጥር ኤጀንሲዎች፣የማስታወቂያ ኤጀንሲዎች፣ የብረታብረት ምርት እና የመድኃኒት ችርቻሮ ተካተዋል።
ከዚህ ባለፈም በውጭ ዜጎች የበላይነት የተያዘው የኢንዱስትሪ ዘርፍ 75% የሚሆነው በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች እንድንሸጋገር መወሰኑ ተገልጿል።
ዝምባብዌ ከፍተኛ ስራ አጥነት ከሚስተዋልባቸው የአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። #zbc #iol
@ThiqahEth

❤15👏4🤔3
ብሌስ ማትረወሊ የዩናይትድ ኪንግደም የስለላ ድርጅት (M16) ዋና ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
ማትረወሊ ተቋሙን ለመምራት የተሾሙ የመጀመሪዋ ሴት ዳይሬክተር መሆናቸው ተገልጿል።
አዲሷ ኃላፊ የምዕራቡ ዲሞክራሲ ላይ ስጋት ላሏቸው የውጭ አካላት ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።
ብሌስ ማትረወሊ ሪቻርድ ሞሬን በመተካት ነው የሀገሪቱ የውጭ የስለላ ድርጅት ኤም 16 ለመምራት ሀላፊነት የተረከቡት። #politico
@ThiqahETH

👏5❤2🤔1
የናይጄሪያ ፖሊስ 161 ህገወጥ የእፅ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ህገወጥ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎቹ የተያዙት በደልታ ክልል አግቦር ከተማ እንደሆነ ገልጿል።
ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ 110 ወንዶች እና 51 ሴቶች መሆናቸውን የደልታ ክልል ፖሊስ ቃል አቀባይ ብራይት እዳፍ ተናግረዋል።
በኢንተለጀንስ በተደገፈው ዘመቻ ብዛት ያላቸው የአደንዛዥ እፆች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዛቸውን ገልጸዋል።
ከተያዙት ውስጥ የካናዳ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች እንደሚገኙበት ቃል አቀባዩ አብራርተዋል። #dailypost

❤5🙏2😢1💔1😡1
የአሜሪካ ጦር በፓስፊክ ውቅያኖስ በፈጸመው ጥቃት የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።
ሦስት ጀልባዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ያረጋገጠው የአሜሪካ የደቡብ ኮማንድ "ምክንያቱም አደገኛ እፅ እያዘዋወሩ ነበር" ብሏል።
ጦሩ "የእፅ አሸባሪዎችም እርምጃ ተወስዶባቸዋል" በማለት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች የወንጀል ተባባሪ እንጂ ንጹሐን አለመሆናቸውን አስታውቋል።
ዘመቻው በአሜሪካ ጦር ዋና ኃላፊ ፔት ሄጌት ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ተገልጿል።
ስለደረሰው ጥቃት ገለልተኛ ሪፖርት ማግኘት አልተቻለም። #yenisafaq

😡5❤4🕊3🤔1
በሞሮኮ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ37 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር "ድንገተኛ ጎርፍ በአንድ ሌሊት 70 መኖሪያ መንደሮችን እና 10 ተሽከርካሪዎችን አውድሟል" ብሏል።
ሚኒስቴሩ "ትምህርትቤቶች ለሶስት ቀናት ዝግ ሆነዋል" ሲል ገልጿል።
አደጋው የተከሰተው ከዋና ከተማዋ ራባት በ320 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሳፊ ከተማ ነው።
በከተማዋ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ተገልጿል። #hurriyetdailynews

😭6❤1
"አሁንም በእስር ላይ ያሉ ከ10 ሺሕ በላይ የግፍ እስረኞች እንዲለቀቁ ጫና ማሳደር ይገባል" - ድርጅቱ
ተመድ የኤርትራ መንግስት እስረኞችን መልቀቁን በበጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።
ድርጅቱ፣ ይሁን እንጅ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች እንዲፈቱም ጫና ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።
ኤርትራ በቅርቡ ለ18 አመት በእስር ላይ ለነበሩ 13 ዜጎች ምህረት አድርጋለች ተብሏል።
እርምጃውን "አበረታች" ሲል የገለፀው የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ(OHCHR) "አሁንም በእስር ላይ ያሉ ከ10,000 በላይ የግፍ እስረኞች እንዲለቀቁ ጫና ማሳደር ይገባል" ብሏል።
"እስር ላይ ከሚገኙት መካከል ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሀይማኖት አባቶችና ተማሪዎች ይገኙበታል" ሲል አስታውቋል። #unnews #As
@ThiqshEth

❤3🕊1
ቡርኪናፋሶ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን የናይጄሪያ ወታደሮች አለመልቀቋ ተገለጸ።
11 የሚደርሱ የናይጄሪያ አየር ሀይል አባላት በሲ-130 የጦር ጄት የአየር ላይ ቅኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት በቡርኪናፋሶ ግዛት ውስጥ ማረፋቸው ተገልጿል።
የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት "የአየር ክልሌን ጥሰዋል" በማለት ወታደሮቹን እና የጦር ጄቱን በቁጥጥር ስር አውሏል።
የቡርኪናፋሶ መንግስት ስለ ክስተቱ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ሁለቱ ሀገራት ላለፉት ስድስት ቀናት ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ቢያደርጉም ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። #dw #politicsnigeria

❤3🙏1
የቀድሞው የኮንጎ "አማፂ ቡድን" መሪ ሮጀር ሉምባላ የ30 አመት እስር ተፈረደባቸው።
ሉምባላ ከ2002 እስከ 2003 በምስራቅ ኮንጎ ለተፈጸመው ወንጀል በፈረንሳይ ፍርድቤት እስር ተፈርዶባቸዋል።
ሁለተኛው የኮንጎ ጦርነት እየተባለ በሚጠራው ዘመን በጎረቤት ኡጋንዳ እየታገዘ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደፈጸመ ተገልጿል።
ሉምባላ "የፈረንሳይ ፍትህ የእኔን ጉዳይ የመመልከት ስልጣን የለውም" በማለት ፍርድቤት ሳይቀርብ ቆይቷል። #bbc

❤4👏2😱1
THIQAH
#ለጥንቃቄ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ #አደጋ ላይ የጣለ አዲስ የክሮም #Chrome ክፍተት ተገኝቷል። ይህን ተከትሎም ጎግል ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያው #Browser በአስቸኳይ ሊተገበሩ የሚገባቸው ለሶስት አደገኛ ክፍተቶች መድፈኛ አዲስ ማሻሻያ #Patch መልቀቁን አስታውቋል። ከእነዚህ ክፍተቶች መካከል አንዱ በተለይ እጅግ አደገኛ ሲሆን፣ የግል መረጃዎችን ለመጥለፍ በመረጃ ጠላፊዎች…
ለመረጃ መንታፊዎች የሚያጋልጡ ጎጅ የስልክ አጠቃቀሞች ምንድን ናቸው?
-ያልተረጋገጡ አፕሊኬሽኖችን በስልካችን መጫን፦ ብዙዎቻችን ከዋናው የሶፍትዌር መደብር (Play Store/App Store) ውጭ ያሉ አፕሊኬሽኖች በተለያዩ ድረ-ገጾች አማካኝነት እንጭናለን። እነዚህ አፕሊኬሽኖች ስልካችንን ለመሰለል/መረጃ ለመሰረቅ የተዘጋጁ ቫይረሶችን ሊይዙ ይችላሉ።
-የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን (Updates) አለማድረግ፦ የስልክ አምራቾች በየጊዜው የደህንነት ማሻሻያዎችን ይለቃሉ። እነዚህን ማሻሻያዎች ችላ ማለት ጠላፊዎች በድሮው የሶፍትዌር ስሪት ያሉ ክፍተቶችን ተጠቅመው ወደስልካችን ሰርገው እንዲገቡ ያጋልጣል።
-ለሁሉም አፕሊኬሽኖች "ፈቃድ" መስጠት፦ አንድ አፕሊኬሽን ስንጭን "Allow" የሚል ምርጫ ይጠይቀናል። ለአንድ ፎቶ ማቀናበሪያ አፕሊኬሽን ስልክ ቁጥሮችን፣ ያሉበትን ቦታ እንዲያይ ፈቃድ መስጠት አላስፈላጊ እና ለመረጃ ስርቆት ያጋልጣል።
-ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የዋይፋይ (Public Wi-Fi) አጠቃቀም፦ ነፃ የዋይፋይ ኔትዎርኮች በቀላሉ ለመጠለፍ የተመቹ ናቸው። በእነዚህ ኔትዎርኮችን ተጠቅመን የባንክ አካውንት መክፈት/ሚስጥራዊ መረጃዎችን መላላክ ከፍተኛ አደጋ አለው።
-አጠራጣሪ ሊንኮችን መክፈት፦ "ሎተሪ ደርሶዎታል"፣ ወይም "ነፃ የኢንተርኔት ጥቅል" በሚሉ አሳሳች መልዕክቶች ያሉ ሊንኮችን መጫን ስልካችንን ለጠላፊዎች አሳልፎ ይሰጣል።
-ቀላል የይለፍ ቃላትን መጠቀም፦ እንደ "1234"፣ "0000" ወይም የልደት ቀንን የመሳሰሉ በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃላትን መጠቀም ስልካችን በእጃችን ቢሆን እንኳ በሩቅ ሆኖ ለመገመት ለሚሞክር የመረጃ መንታፊ ስራውን ያቀልለታል። #INSA

❤12👏4🙏3😢1
የቦትስዋና ወጣቶች ለዩክሬን ጦርነት እየተመለመሉ እንደሚላኩ ተገለጸ።
ብዛት ያላቸው የሀገሪቱ ወጣቶች በስራ ቅጥር እና በስልጠና ሰበብ ወደ ሩሲያ መላካቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
የቦትስዋና መንግስት ወጣቶችን እየመለመሉ በሚልኩ ኤጄንሲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ዜጎች ከሀሰተኛ መረጃ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት፣ የስራ አጥነት ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልጿል። #outlook

❤2🤔2😱1
ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ሀገራት ብዛት 39 ደረሰ።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ20 ሀገራት ላይ የጣሉትን የጉዞ እገዳ አራዝመዋል።
ከሀገራቱ በተጨማሪ የፍልስጤም ባለስልጣናትም የጉዞ ክልከላው እንደሚመለከታቸው ተናግረዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ሌሎች አምስት ሀገራትን ሙሉ በሙሉ ያገደ ሲሆን ተጨማሪ 15 ሀገራት ከፊል እገዳ እንደተጣለባቸው ተገልጿል።
በዚሁ ውሳኔ መሰረት ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ሀገራት ጠቅላላ ብዛት 39 ደርሷል።
ሙሉ በሙሉ ከታገዱት ውስጥ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ የመን፣ ኢራ፣ ማይናማር ይገኙበታል።
አዲስ ሙሉ እገዳ የተጣለባቸው አምስት ሀገራት ደግሞ ሶርያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማሊ እና ኒጀር ናቸው።
ከፊል እገዳ ከተጣለባቸው 15 ሀገራት ውስጥ ደግሞ አንጎላ፣ ቤኒን እና ሴኔጋል ተካተዋል። #euronews

❤11😢1😡1
በሱዳን ከ100 የሚበልጡ ንጹሐን በድሮን ጥቃት ተገደሉ።
በኮርዶፋ ግዛት የተፈጸመው ይህ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሏል።
የሀገሪቱ ጦር ለተፈፀመው የድሮን ጥቃት የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉን ተጠያቂ ቢያደርግም፣ አማፂ ሀይሉ የሰጠው ምላሽ እንደሌለ ተገልጿል።
ጥቃቱ በህፃናት ትምህርትቤት እና በሆስፒታል ላይ በመከሰቱ የአደጋው መጠን ከፍተኛ ሊሆን ችሏል ተብሏል። #aljazeera

😭18🕊2❤1🤔1
የአሜሪካ ሴኔት ለ2026 የመከላከያ በጀት 901 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ።
ሴኔቱ በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የመከላከያ በጀት አፅድቋል።
ከበጀቱ ውስጥ 4 በመቶው ለዩክሬን የሚሰጥ ድጋፍ ነው። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዋጁን በፊርማቸው ህግ አድርገው ያፀድቁታል ተብሏል። #samaatv

❤9😡8🤔3👏2
"እስራኤል በታሪኳ ትልቁን የነዳጅ ሽያጭ ስምምነት ፈጽማለች" - ኔታንያሁ
እስራኤል እና ኢራን የ35 ቢሊየን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ ስምምነት ማድረጋቸው ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ "ለግብጽ የጋዝ አቅርቦት ለማሟላት ስምምነት ላይ ተደርሷል" ብለዋል።
"እስራኤል በታሪኳ ትልቁን የነዳጅ ሽያጭ ስምምነት ፈፅማለች" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የቀጠናው የሀይል ምንጭ በመሆን ለቀጠናው መረጋጋት የበኩላችንን ሚና እንጫወታለን" ሲሉ ገልጸዋል።
"እስራኤል እስከ 2040 የነዳጅ አቅርቦቱን ለማሟላት ዝግጁ መሆኗን ለመግለጽ እወዳለሁ" ብለዋል ኔታንያሁ።
የተፈጥሮ ነዳጁ 600 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ያመነጫል ተብሎ ከሚጠበቀው የሌቪያታን የነዳጅ ማመንጫ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
እስራኤል እና ግብፅ ባሳለፍነው ነሐሴ ተመሳሳይ የኢንቨስትመንት ስምምነት ቢፈራረሙም በጋዛው ጦርነት ሳቢያ በሳምንታት ውስጥ ፈርሷል ተብሏል። #theindependent

🤔44❤11😢3🕊3😡3😱1
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቬኔዙዌላን የነዳጅ ታንከሮች ላይ እገዳ ጣሉ።
ፕሬዝዳንቱ እገዳውን አስመለክቶ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ "ቬንዙዌላ እስከዛሬ በደቡብ አሜሪካ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ጦር ተከባለች" ሲሉ አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንቱ "ሁሉንም ነዳጅ፣ መሬት እና ካሁን በፊት ከእኛ የሰረቋቸውን ሁሉንም ንብረቶች ለዩናይትድስቴትስ ካልመለሱ ከዚህም በላይ አይተውትይጨመራል፣ በማያውቁት ሁኔታ ይደነግጣሉ" በማለት ገልጸዋል።
አክለው "ህጋዊ ያልሆነው የማዱሮ መንግስት ከተሰረቁ ጣቢያዎች የመነጩ ነዳጆችን እየተጠቀመ ራሳቸውን፣ የእፅ አሸባሪዎችን፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ ግድያ እና እገታን እየደገፈበት ነው" ብለዋል።
"የእኛን ንብረት በመዝረፍና በሽብር፣ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሌሎችም ወንጀሎች የቬኔዙዌላ መንግስት በውጭ የአሸባሪ ድርጅቶች ውስጥ ተካቷል" ሲሉ አስታውቀዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ አስተያየታቸው "በመሆኑም ዛሬ ሁሉም ከቬንዙዌላ የሚገቡ እና የሚወጡ የነዳጅ ታንከሮች እንድቆሙ እና ሙሉ ማዕቀብ እንድጣልባቸው አዝዣለሁ" ነው ያሉት።
"ወንጀለኛው የማዱሮ አገዛዝ በደካማው የባይደን አስተዳደር ዘመን ወደአሜሪካ የላካቸው በፍጥነት ወደ ቬንዙዌላ እየተመለሱ ነው" በማለት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ መቋረጡን አስረድተዋል።
"አሜሪካ ወንጀለኞችን፣ አሸባሪዎችን ወይም ሌሎች ሀገራትን ለዘረፋ፣ ለስጋት እና ለየትኛውም ጥፋት አትፈቅድም" ያሉት ትራምፕ "በተመሳሳይ መልኩ ጥፋተኛ አገዛዝ ነዳጃችንን፣ መሬታችንን እና ሌሎች ሀብታችንን እንዲወስድብን አንፈቅድም፣ ሁሉም ወደአሜሪካ መመለስ አለባቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

😡13❤6🤔4
የቤልጅየም አርሶአደሮች የአውሮፓ ህብረት የፈጸመውን ስምምነት ተቃወሙ።
የአውሮፓ ህብረት ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር " የግብርና ምርት ስምምነት(EU Mercosur)" ፈጽሟል።
በቤልጅየም ዋና ከተማ ብራሰልስ የተሰባሰቡት አርሶአደሮቹ ስምምነቱን "ኢፍትሃዊ ውድድርን ይፈጥራል፣ የአውሮፓ ግብርናን ይጎዳል" ሲሉ ተቃውመዋል።
አርሶአደሮቹ የእርሻ ትራክተሮችን ይዘው በመውጣት ወደ ብራሰልስ የሚወስደውን መንገድ ዘግተውታል።
የአውሮፓ አርሶአደሮች ፌደሬሽን 10,000 ተቃዋሚዎች መሳተፋቸውን አስታውቋል። #aa

❤7👏5😱2🕊1
THIQAH
የቤልጅየም አርሶአደሮች የአውሮፓ ህብረት የፈጸመውን ስምምነት ተቃወሙ። የአውሮፓ ህብረት ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር " የግብርና ምርት ስምምነት(EU Mercosur)" ፈጽሟል። በቤልጅየም ዋና ከተማ ብራሰልስ የተሰባሰቡት አርሶአደሮቹ ስምምነቱን "ኢፍትሃዊ ውድድርን ይፈጥራል፣ የአውሮፓ ግብርናን ይጎዳል" ሲሉ ተቃውመዋል። አርሶአደሮቹ የእርሻ ትራክተሮችን ይዘው በመውጣት ወደ ብራሰልስ የሚወስደውን መንገድ…
የአውሮፓ ሀገራት በአርሶአደሮች ተቃውሞ ስለገጠመው የግብርና ምርት ስምምነት (EU Mercousur) ምን ምላሽ ሰጡ?
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "የአውሮፓ ህብረት በአባል ሀገራቱ አርሶአደሮች ጥቅም ላይ መደራደር የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል።
ጣሊያን በበኩሏ የስምምነቱ ፊርማ "የአርሶአደሮችን ደህንነት የሚያስጠብቁ አስተማማኝ ሁኔታዎች" እስኪሟሉ ድረስ እንዲዘገይ ጠይቃለች ተብሏል።
ጀርመን እና ስፔን "የአውሮፓን የወጪ ገበያ ያሳድገዋል" በማለት የስምምነቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ አርሶአደሮች አሁንም በአውሮፓ ፓርላማ አጠገብ በመገኘት ድንች እና ቲማቲም መንገድ ላይ በመጣል፣ እንጨት በማቃጠል፣ 150 የእርሻ ትራክተሮችን በማጓጓዝ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ተብሏል። #anadoluagency

🤔4❤2😭1
"ከ200 የሚበልጡ የህክምና ባለሙያዎች ተገድለዋል። 507 ባለሙያዎች ሲቆስሉ፣ 59 ጠፍተዋል" - ሪፖርት
በሱዳን ከ2023 ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህክምና ባለሙያዎች ህይወት ማለፉን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) ገልጿል።
ጥምረቱ ባወጣው ሪፖርት "ከ2023 ጀምሮ ቢያንስ 234 የህክምና ባለሙያዎች ተገድለዋል፣ 73 የሚደርሱት ዳርፉር ውስጥ በአር ኤስ ኤፍ ታግተዋል" ብሏል።
ሪፖርቱ አክሎ፣ "507 ባለሙያዎች ሲቆስሉ፣ 59ኙ ጠፍተዋል" ነው ያለው።
ጥምረቱ ባወጣው ሪፖርት አለማቀፍ ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ ድርጅቶች የህክምና ባለሙያዎች ደህንነት እንድጠብቅ ጫና እንዲፈጥሩ ጠይቋል።
በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ሀይሎች ግጭቱን እንዲያቆሙ ያሳሰበው ቡድኑ፣ የታገቱት እንዲለቀቁ እና የጠፉት መዳረሻቸው እንዲታወቅ አሳስቧል። #aa

💔8😭7❤2😱1🕊1
በባንግላዴሽ የወጣቶች ንቅናቄ መሪ መገደሉ ከፍተኛ ህዝባዊ አመፅ ተቀሰቀሰ።
ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የምትገኘው ባንግላዴሽ ለምርጫ ዕጩ ሁኖ የቀረበው የተማሪዎች ንቅናቄ አስተባባሪ ሻሪፍ ኡስማን ሀዲ ተገድሏል።
የ32 አመቱ ሀዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲናን ከስልጣን ባነሳው የተማሪዎች ንቅናቄ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።
ሀዲ በዋና ከተማዋ ዳካ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ለህክምና ወደ ሲንጋፖር ቢያቀናም ከስድስት ቀን በኋላ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
በአስተባባሪው ህልፈት የተበሳጩት ሰልፈኞች ስሙን በመጥራት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው ተብሏል። #keralanews

🙏5🤔3❤2💔1