THIQAH
በምያንማር "መንግስት በፈጸመው ጥቃት" 30 ሰዎች ሲሞቱ፣ 70 የሚሆኑት ቆሰሉ። ምያንማርን የሚያስተዳድረው ወታደራዊ መንግስት (ጁንታ) የአማፂዎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በራኪን ግዛት የአየር ጥቃት ፈጽሟል። መንግስት የፈጸመው የድሮን ጥቃት በማሩክ ሆስፒታል በማረፉ ንፁሃን ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል። ሆስፒታሉ ባለ 300 አልጋ ሲሆን፣ በሁሉም አልጋዎች ህሙማን እንደሚገኙበት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተናግረዋል።…
"የሞቱት ንጹሐን አይደሉም፣ የአሸባሪው ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው" - መንግስት
የማይናማር መንግስት "ከ30 በላይ ንጹሐን" የቀጠፈውን ጥቃት አስተባብሏል።
የወቅቱ የማይናማር መንግስት በራኪን ግዛት በሚገኘው ሆስፒታል ላይ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጦ፣ ነገር ግን "ጥቃቱ ንጹሐን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ አልነበረም" ብሏል።
ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ጁንታ "የሞቱት ንጹሐን አይደሉም፣ የአሸባሪው ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው" ሲል የደረሰበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።
መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ "የራኪን ግዛት ከ2024 ጀምሮ በአርካን አማፂ ኃይሎች (AA) ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው፣ ሆስፒታሉን የሚገለገሉበትም የታጠቁ ሀይሎች ናቸው" ነው ያለው።
ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ በተፈጸመው የአየር ላይ ጥቃት 33 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ፣ 76 መቁሰላቸውና 27 የሚሆኑት በጽኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኙ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። #anadoluagency
@ThiqahETH

❤8💔2🤔1🕊1
ቤላሩስ ለ123 የፖለቲካ እስረኞች ምህረት አደረገች።
መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው አሜሪካ ቤላሩስ ወደ ውጭ በምትልከው የማዳበሪያ ምርት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተከትሎ ነው።
በይቅርታ ከወጡት መካከል በ2020 የተደረገውን ፀረ መንግስት ተቃውሞ የመራችው ማሪያ ኮላስኒኮቫ እና የሰላም ኖቤል ተሸላሚው አሌስ ቢያሊያትስኪ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
አሜሪካ የፕሬዝዳንት ሉካሽንኮ መንግስት በ2021 ያካሄው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ አይደለም በሚል የቤላሩስ መንግስት ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
ፕሬዚዳንት ሉካሽንኮ በዩክሬን ጦርነት ሀገራቸው ለሩሲያ እንደምትወግን በግልጽ ድጋፍ ማሳየታቸው ተገልጿል። #radiofreeeurope #skynews

❤11👏2🙏2🤔1😭1
"የበቀል እርምጃ እንወስዳለን" - ዶናልድ ትራምፕ
በሶሪያ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው ተነግሯል።
አይኤስአይኤስ (ISIS) በማዕከላዊ ሶሪያ ባደረሰው ጥቃት ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች እና አስተርጓሚ የነበረ የሀገሪቱ ዜጋ ሲገደሉ ሌሎች ሶስት ወታደሮች ተጎድለዋል።
ጥቃቱን ያደረሰው የቡድኑ አባል የነበረ ግለሰብ ፓልምይራ ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በፈጸመው ጥቃት ነው።
ስለክስተቱ አስተያየታቸውን የሰጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ጥቃት የደረሰበት አደገኛ ቦታ በሶሪያ መንግስት ስር አይደለም" ብለዋል።
"የሶርያ ፕሬዚዳንት አልሻራም ሀዘኑን ገልጿል" ያሉ ሲሆን "በወታደሮቻችን ላይ ለተፈፀመው ጥቃት የበቀል እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉም አክለዋል። #euronews

❤8👏3🤔2😱1😢1
ተመድ በሱዳን የባንግላዴሽ ወታደሮች ላይ የተፈፀመውን ግድያ አወገዘ።
ስድስት የባንግላዴሽ የሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን የገለፀው ድርጅቱ፣ የሟቾችን ማንነት በምስል ይፋ አድርጓል ተብሏል።
የሰላም አስከባሪዎቹ በተልዕኮ ላይ በነበሩበት ወቅት የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በፈጸመው የድሮን ጥቃት ተገድለዋል።
ወታደሮቿ የተገደሉባት ባንግላዴሽ ሀዘኗን በመግለፅ፣ ከተመድ ጋር አብራ መስራቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። #aljazeera

💔5❤2😱1😢1
በአውስትራሊያ በጀዊሽ ማህበረሰብ በዓል ላይ በተፈጸመ ጥቃት 11 ሰዎች ሲገደሉ፣ 29 ቆሰሉ።
በቦንዲ ቢች ከተማ ሲከበር በነበረው የሀኑካህ በዓል ላይ ሁለት ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸውን የከተማዋ ፖሊስ ኦፊሰር ማል ላንዮን ገልጸዋል።
ጥቃቱ የጸረሴማዊነት አካል ነው ቢባልም የአውስትራሊያ መንግሥት "የሽብር ድርጊት" ሲል ፈርጆታል።
ከጥቃት አድራሾቹ አንዱ በተወሰደበት እርምጃ ህይወቱ ሲያልፍ፣ ሌላኛው በቁጥጥር ስር መዋሉን ኦፊሰሩ ተናግረዋል። #rns

👏15💔9❤2🤔1😭1
"የሁሉም የስፓርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከዛሬ ጀምሮ ተሰርዟል" - አገልግሎቱ
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሁሉም የስፓርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከዛሬ (ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም) ጅምሮ መሰረዙን አስታውቋል።
የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የህዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑንም ገልጿል።
ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ብሏል አገልግሎቱ።
ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ እንዲያቋርጡ አዟል።
ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ፣ አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ እንደማይቻል አስታውቋል። #ELS
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

👏22❤5😱1😢1😭1
ጆዜ አንቶኒዮ የቺሊ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።
የቀኝ ዘመም ሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይዋ አንቶኒ በምርጫው 58.17% ድምፅ አግኝተዋል።
ተፎካካሪዋ የቀድሞው የሰራተኛ ሚኒስትር ጃራ ጎት በበኩላቸው፣ 41.8 ድምፅ አግኝተዋል። #anadoluagency

❤5😱1🕊1
ዝምባብዌ የውጭ ሀገራት ዜጎች በታክሲ እና በዳቦ ቤት ስራዎች እንዳይሰማሩ ከለከለች።
14 የስራ ዘርፎች የስራ እድል ለመፍጠር በማሰብ ለሀገር ውሰጥ ዜጎች ቅድሚያ እንድሰጥ ተወስኗል።
ከእነዚህም ውስጥ የፀጉር ቤት፣ የውበት ሳሎን፣ የጥበቃ አገልግሎት፣ የቅጥር ኤጀንሲዎች፣የማስታወቂያ ኤጀንሲዎች፣ የብረታብረት ምርት እና የመድኃኒት ችርቻሮ ተካተዋል።
ከዚህ ባለፈም በውጭ ዜጎች የበላይነት የተያዘው የኢንዱስትሪ ዘርፍ 75% የሚሆነው በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች እንድንሸጋገር መወሰኑ ተገልጿል።
ዝምባብዌ ከፍተኛ ስራ አጥነት ከሚስተዋልባቸው የአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። #zbc #iol
@ThiqahEth

❤15👏4🤔3
ብሌስ ማትረወሊ የዩናይትድ ኪንግደም የስለላ ድርጅት (M16) ዋና ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
ማትረወሊ ተቋሙን ለመምራት የተሾሙ የመጀመሪዋ ሴት ዳይሬክተር መሆናቸው ተገልጿል።
አዲሷ ኃላፊ የምዕራቡ ዲሞክራሲ ላይ ስጋት ላሏቸው የውጭ አካላት ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።
ብሌስ ማትረወሊ ሪቻርድ ሞሬን በመተካት ነው የሀገሪቱ የውጭ የስለላ ድርጅት ኤም 16 ለመምራት ሀላፊነት የተረከቡት። #politico

👏5❤2🤔1
የናይጄሪያ ፖሊስ 161 ህገወጥ የእፅ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ህገወጥ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎቹ የተያዙት በደልታ ክልል አግቦር ከተማ እንደሆነ ገልጿል።
ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ 110 ወንዶች እና 51 ሴቶች መሆናቸውን የደልታ ክልል ፖሊስ ቃል አቀባይ ብራይት እዳፍ ተናግረዋል።
በኢንተለጀንስ በተደገፈው ዘመቻ ብዛት ያላቸው የአደንዛዥ እፆች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዛቸውን ገልጸዋል።
ከተያዙት ውስጥ የካናዳ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች እንደሚገኙበት ቃል አቀባዩ አብራርተዋል። #dailypost

❤5🙏2😢1💔1😡1
የአሜሪካ ጦር በፓስፊክ ውቅያኖስ በፈጸመው ጥቃት የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።
ሦስት ጀልባዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ያረጋገጠው የአሜሪካ የደቡብ ኮማንድ "ምክንያቱም አደገኛ እፅ እያዘዋወሩ ነበር" ብሏል።
ጦሩ "የእፅ አሸባሪዎችም እርምጃ ተወስዶባቸዋል" በማለት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች የወንጀል ተባባሪ እንጂ ንጹሐን አለመሆናቸውን አስታውቋል።
ዘመቻው በአሜሪካ ጦር ዋና ኃላፊ ፔት ሄጌት ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ተገልጿል።
ስለደረሰው ጥቃት ገለልተኛ ሪፖርት ማግኘት አልተቻለም። #yenisafaq

😡5❤4🕊3🤔1
በሞሮኮ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ37 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር "ድንገተኛ ጎርፍ በአንድ ሌሊት 70 መኖሪያ መንደሮችን እና 10 ተሽከርካሪዎችን አውድሟል" ብሏል።
ሚኒስቴሩ "ትምህርትቤቶች ለሶስት ቀናት ዝግ ሆነዋል" ሲል ገልጿል።
አደጋው የተከሰተው ከዋና ከተማዋ ራባት በ320 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሳፊ ከተማ ነው።
በከተማዋ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ተገልጿል። #hurriyetdailynews

😭6❤1
"አሁንም በእስር ላይ ያሉ ከ10 ሺሕ በላይ የግፍ እስረኞች እንዲለቀቁ ጫና ማሳደር ይገባል" - ድርጅቱ
ተመድ የኤርትራ መንግስት እስረኞችን መልቀቁን በበጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።
ድርጅቱ፣ ይሁን እንጅ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች እንዲፈቱም ጫና ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።
ኤርትራ በቅርቡ ለ18 አመት በእስር ላይ ለነበሩ 13 ዜጎች ምህረት አድርጋለች ተብሏል።
እርምጃውን "አበረታች" ሲል የገለፀው የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ(OHCHR) "አሁንም በእስር ላይ ያሉ ከ10,000 በላይ የግፍ እስረኞች እንዲለቀቁ ጫና ማሳደር ይገባል" ብሏል።
"እስር ላይ ከሚገኙት መካከል ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሀይማኖት አባቶችና ተማሪዎች ይገኙበታል" ሲል አስታውቋል። #unnews #As
@ThiqshEth

❤3🕊1
ቡርኪናፋሶ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን የናይጄሪያ ወታደሮች አለመልቀቋ ተገለጸ።
11 የሚደርሱ የናይጄሪያ አየር ሀይል አባላት በሲ-130 የጦር ጄት የአየር ላይ ቅኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት በቡርኪናፋሶ ግዛት ውስጥ ማረፋቸው ተገልጿል።
የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት "የአየር ክልሌን ጥሰዋል" በማለት ወታደሮቹን እና የጦር ጄቱን በቁጥጥር ስር አውሏል።
የቡርኪናፋሶ መንግስት ስለ ክስተቱ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ሁለቱ ሀገራት ላለፉት ስድስት ቀናት ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ቢያደርጉም ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። #dw #politicsnigeria

❤3🙏1
የቀድሞው የኮንጎ "አማፂ ቡድን" መሪ ሮጀር ሉምባላ የ30 አመት እስር ተፈረደባቸው።
ሉምባላ ከ2002 እስከ 2003 በምስራቅ ኮንጎ ለተፈጸመው ወንጀል በፈረንሳይ ፍርድቤት እስር ተፈርዶባቸዋል።
ሁለተኛው የኮንጎ ጦርነት እየተባለ በሚጠራው ዘመን በጎረቤት ኡጋንዳ እየታገዘ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደፈጸመ ተገልጿል።
ሉምባላ "የፈረንሳይ ፍትህ የእኔን ጉዳይ የመመልከት ስልጣን የለውም" በማለት ፍርድቤት ሳይቀርብ ቆይቷል። #bbc

❤4👏2😱1
THIQAH
#ለጥንቃቄ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ #አደጋ ላይ የጣለ አዲስ የክሮም #Chrome ክፍተት ተገኝቷል። ይህን ተከትሎም ጎግል ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያው #Browser በአስቸኳይ ሊተገበሩ የሚገባቸው ለሶስት አደገኛ ክፍተቶች መድፈኛ አዲስ ማሻሻያ #Patch መልቀቁን አስታውቋል። ከእነዚህ ክፍተቶች መካከል አንዱ በተለይ እጅግ አደገኛ ሲሆን፣ የግል መረጃዎችን ለመጥለፍ በመረጃ ጠላፊዎች…
ለመረጃ መንታፊዎች የሚያጋልጡ ጎጅ የስልክ አጠቃቀሞች ምንድን ናቸው?
-ያልተረጋገጡ አፕሊኬሽኖችን በስልካችን መጫን፦ ብዙዎቻችን ከዋናው የሶፍትዌር መደብር (Play Store/App Store) ውጭ ያሉ አፕሊኬሽኖች በተለያዩ ድረ-ገጾች አማካኝነት እንጭናለን። እነዚህ አፕሊኬሽኖች ስልካችንን ለመሰለል/መረጃ ለመሰረቅ የተዘጋጁ ቫይረሶችን ሊይዙ ይችላሉ።
-የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን (Updates) አለማድረግ፦ የስልክ አምራቾች በየጊዜው የደህንነት ማሻሻያዎችን ይለቃሉ። እነዚህን ማሻሻያዎች ችላ ማለት ጠላፊዎች በድሮው የሶፍትዌር ስሪት ያሉ ክፍተቶችን ተጠቅመው ወደስልካችን ሰርገው እንዲገቡ ያጋልጣል።
-ለሁሉም አፕሊኬሽኖች "ፈቃድ" መስጠት፦ አንድ አፕሊኬሽን ስንጭን "Allow" የሚል ምርጫ ይጠይቀናል። ለአንድ ፎቶ ማቀናበሪያ አፕሊኬሽን ስልክ ቁጥሮችን፣ ያሉበትን ቦታ እንዲያይ ፈቃድ መስጠት አላስፈላጊ እና ለመረጃ ስርቆት ያጋልጣል።
-ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የዋይፋይ (Public Wi-Fi) አጠቃቀም፦ ነፃ የዋይፋይ ኔትዎርኮች በቀላሉ ለመጠለፍ የተመቹ ናቸው። በእነዚህ ኔትዎርኮችን ተጠቅመን የባንክ አካውንት መክፈት/ሚስጥራዊ መረጃዎችን መላላክ ከፍተኛ አደጋ አለው።
-አጠራጣሪ ሊንኮችን መክፈት፦ "ሎተሪ ደርሶዎታል"፣ ወይም "ነፃ የኢንተርኔት ጥቅል" በሚሉ አሳሳች መልዕክቶች ያሉ ሊንኮችን መጫን ስልካችንን ለጠላፊዎች አሳልፎ ይሰጣል።
-ቀላል የይለፍ ቃላትን መጠቀም፦ እንደ "1234"፣ "0000" ወይም የልደት ቀንን የመሳሰሉ በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃላትን መጠቀም ስልካችን በእጃችን ቢሆን እንኳ በሩቅ ሆኖ ለመገመት ለሚሞክር የመረጃ መንታፊ ስራውን ያቀልለታል። #INSA

❤12👏4🙏3😢1
የቦትስዋና ወጣቶች ለዩክሬን ጦርነት እየተመለመሉ እንደሚላኩ ተገለጸ።
ብዛት ያላቸው የሀገሪቱ ወጣቶች በስራ ቅጥር እና በስልጠና ሰበብ ወደ ሩሲያ መላካቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
የቦትስዋና መንግስት ወጣቶችን እየመለመሉ በሚልኩ ኤጄንሲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ዜጎች ከሀሰተኛ መረጃ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት፣ የስራ አጥነት ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልጿል። #outlook

❤2🤔2😱1