THIQAH
10.8K subscribers
4.46K photos
49 videos
1 file
38 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
"ከስልጣን እንድንለቅ ያቀረባችሁትን ቅሬታ ሰምተን ለቀናል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዘሊዝኮቭ

የቡልጋሪያ መንግስት መፍረሱ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሮሰን ዘሊዝኮቭ የመተማመኛ ድምጽ በማጣታቸው ከስልጣን ወርደዋል።

ከ100,000 በላይ ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ተስፋፍቷል ያሉትን ሙስና በመቃወም "ማፊያ መንግስት ይውደም" በማለት አደባባይ ወጥተዋል።

ዘሊዝኮቭ በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው "የህዝብ ድምጽ ሊደመጥ እና ሊበረታታ ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ከስልጣን እንድንለቅ ያቀረባችሁትን ቅሬታ ሰምተን ለቀናል" ብለዋል። #bbc #theindependent

@ThiqahETH
👏409🕊2🤔1💔1
"ኢጋድ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስፈን አስተዋጽኦ አላደረገም" - ኤርትራ

ኤርትራ ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ወይም ኢጋድ መውጣቷን አሳወቀች። በዚህም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀገሪቱ ከኢጋድ አባልነት መውጣቷን አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኤርትራ፣ "ህጋዊ ማንነቱን እና ስልጣኑን በአግባቡ ያልተረዳ" ካለው ተቋም መውጣን ይፋ አድርጓል።

በዚህም፣ "ስትራቴጂካዊ ጥቅም ማረጋገጥ አልቻለም" በማለት ኢጋድን ተችቷል። "ኢጋድ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስፈን አስተዋጽኦ አላደረገም" በማለት በብርቱ ወቅሷል።

ኢጋድ የኤርትራን መውጣት በተመለከተ የሰጠው አስተያየት የለም።  #thestateoferitreamofa

@ThiqahETH
7😢2
THIQAH
በታይላንድ እና ካምቦዲያ ጦርነት ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቀሉ። የሁለቱ ሀገራት ጦርነት እንደ አዲስ ማገርሸቱን ተከትሎ በሁለቱም ወገን ቢያንስ 20 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ካሁን በፊት የነበረውን ጦርነት ያሸማገሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግጭቱን ለማቆም ከሀገራቱ መሪዎች ጋር በስልክ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። #theweek @ThiqahETH
ከካምቦዲያ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኙ የታይላንድ መንግስት ፓርላማ ፈረሰ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርንቪራኩል ከሀገሪቱ ንጉሥ ማሃ ቫጅራሎንግኮርን ፍቃድ ካገኙ በኋላ ፓርላማውን ማፍረሳቸው ተገልጿል።

ሀገሪቱ ከ45 እስከ 60 ባሉት ቀናት ውስጥ ምርጫ ታካሂዳለች ተብሏል።

ታይላንድ በድንበር ውዝግብ ከካምቦዲያ ጋር ጦርነት ውስጥ እንደምትገኝ ተገልጿል። #euronews

@ThiqahETH
👏2🙏1
THIQAH
ትራምፕ ባቀረቡት የዩክሬን የሰላም እቅድ የተካተቱት የስምምነት ነጥቦች ምን ምን ይዘዋል? -የዩክሬን ሉዓላዊነት የተረጋገጠ ይሆናል። በሩሲያ፣ ዩክሬን እና አውሮፓ መካከል ወረራ ያለመፈጸም ስምምነት ይፈጸማል። -ሩሲያ የጎረቤት ሀገራትን እንደማትወር እና ኔቶ ከተጨማሪ መስፋፋት እንዲቆጠብ ይደረጋል። -በሩሲያ እና በኔቶ መካከል አለማቀፍ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታትና መረጋጋትን ለመፍጠር፣ ትብብርን በማጠናከር…
"በህዳር ወር ውስጥ ብቻ 226 ዩክሬናውያን ተገድለዋል፣ 952 ቆስለዋል" - ተመድ

በዩክሬን በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙ ጉዳቶች መጨመራቸው ተገለጸ።

ሩሲያ የምትፈጽመው ጥቃት እየተበራከተ መምጣቱን በዩክሬን የሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ቁጥጥር ተልዕኮ (UNHRMM) አስታውቋል።

ድርጅቱ ባወጣው አዲስ ሪፖርት "በህዳር ወር ውስጥ ብቻ 226 ዩክሬናውያን ተገድለዋል፣ 952 ቆስለዋል" ብሏል።

"የሩሲያ ፌደሬሽን በከባድ መሳሪያ የሚያደርሰው ጥቃት መሰረተ ልማቶችን አውድሟል" ያለው ተመድ፣ "በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የኤሌክትሪክ ሀይል ማግኘት አልቻሉም" ሲል ገልጿል።

የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ 12 ሺሕ 300 በላይ ንጹሐን ህይወታቸው ማለፉን የተመድ መረጃ ያመላክታል።

በቅርቡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት ባለ28 ነጥብ የሰላም እቅድ በዩክሬን ዘንድ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አላገኘም ተብሏል። #interfax

@ThiqahETH
7😢3👏2🕊2
THIQAH
"ኢጋድ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስፈን አስተዋጽኦ አላደረገም" - ኤርትራ ኤርትራ ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ወይም ኢጋድ መውጣቷን አሳወቀች። በዚህም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀገሪቱ ከኢጋድ አባልነት መውጣቷን አረጋግጧል። ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኤርትራ፣ "ህጋዊ ማንነቱን እና ስልጣኑን በአግባቡ ያልተረዳ" ካለው ተቋም መውጣን ይፋ አድርጓል። በዚህም፣ "ስትራቴጂካዊ ጥቅም…
ኢጋድ በኤርትራ ውሳኔ ማዘኑን ገለጸ

ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (IGAD) እራሷን ማግለሏ እንዳሳዘነው የኢጋድ ሴክሬታሪያት አስታውቋል።

ኢጋድ ምሽቱን ባወጣው መግለጫ፣ ኤርትራ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ራሷን ካገለለች በኋላ በ2023 በጅቡቲ በተካሄደው የተቋሙ 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ለቀጠናዊ አንድነትና ትብብር ድርጅቱን በድጋሚ ለመቀላቀል ያቀረበችውን ጥያቄ በአባል ሀገራቱ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቶ መጽደቁን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ፣ "ኤርትራ ከ2023 ጀምሮ በተቋሙ  ስብሰባዎች፣ ፕሮግራሞች እና ተግባራት ተሳትፎ አልነበራትም" ሲል ገልጿል።

"ባለፉት ሁለት አመታት በትዕግስት እና በተስፋ መሻሻሎች" እንዲመጡ ሲጠባበቅ እንደነበረ በመግለጫው ጠቅሷል።

ኢጋድ አክሎ ኤርትራ፣ "ተቋሙ ሊያሻሽለው ይገባል" የምትለውን  ሃሳብ ባላቀረበችበትና ከዚያም ባለፈ "ድርጅቱን ለቃ እንድትወጣ ያደረጋትን ምክንያት በግልጽ ባላስቀመጠችበት ሁኔታ ማግለሏን በማሳወቋ ማዘኑን ያሳዝናል" በማለት የኤርትራ መንግስት ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው አሳስቧል።

አሁንም ቢሆን ከኤርትራ መንግስት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

ኢጋድ ከኤርትራ መንግስት ጋር ንግግር እንደሚያደርግ ገልፆ፣ "ሀገሪቱ ድርጅቱን በድጋሚ በመቀላቀል በመተማመን እና በቀናነት ለጋራ አላማ፣ ለአካባቢው ለሰላም፣ መረጋጋት፣ ልማት ለመስራት እንደሚያበረታታ" ገልጿል።

ኢጋድ "ለአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ቀጠናዊ ትብብርን ለመፍጠር፣ ውይይትን ለማዳበር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ" ሀላፊነቱን እንደሚወጣ በመግለጫው አመላክቷል። #igadsecretariat

@ThiqahETH
🤔64😡3👏1😱1😭1
THIQAH
ካምቦዲያ "ከዲፕሎማሲ ጦርነት መርጣለች" ስትል ታይላንድን ወነጀለች። ሁለቱ ሀገራት በአሜሪካ አማካኝነት የሰላም ስምምነት ከፈጸሙ በኋላ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተገልጿል። እንደ አዲስ ባገረሸው ጥቃት የ10 ሰዎች ሞት መመዝገቡን እና 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የካምቦዲያ መንግስት አስታውቋል። ታይላንድ በበኩሏ፣ ሶስት ወታደሮቿ እንደተገደሉባት ገልፃለች። #themacaonews @ThiqahETH
ትራምፕ የተኩስ አቁም መደረጉን ቢገልጹም የታይላንድ እና ካምቦዲያ ጦርነት አለመቆሙ ተገለጸ።

የካምቦዲያ መንግስት "ታይላንድ ተዋጊ ጄቶችን ጨምሮ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ ጥቃት እያደረሰች ነው" ብሏል።

ታይላንድ በበኩሏ የካምቦዲያ ጦር "አለማቀፍ ህግን ጥሷል" በማለት የአፀፋ እርምጃ እየወሰደች እንደምትገኝ ተገልጿል።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ትናንት ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ ግጭቱን ለማቆም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የነበረ ቢሆን በሰዓታት ልዩነት ጥሰውታል ነው የተባለው። #asiaone

@ThiqahETH
3🙏1🕊1😭1
ኢራናዊቷ ኖቬል ተሸላሚ ያለቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ፋውንዴሽኗ ጠየቀ።

ኢራናዊቷ የኖቤል ተሸላሚ ናርገስ ሞሀመድ መታሰሯ ተነግሯል።

ናርገስ በአንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች መታሰቢያ ላይ በተገኘችበት ወቅት በኢራን መንግስት በቁጥጥር ስር መዋሏን በስሟ የተቋቋመው ፋውንዴሽን አስታውቋል።

በማሻድ ከተማ በደህንነት ሰዎች መያዟን የገለጸው ፋውንዴሽኑ፣ ያለቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ጠይቋል።  #theindependent

@ThiqahETH
🙏5🕊32
ተመድ በአልሸባብ ላይ የጣለውን ማዕቀብ አራዘመ

የተመድ የፀጥታው ምክርቤት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው "የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን" ላይ የተጣለበትን ማዕቀብ ገምግሟል።

ሁሉም 15ቱ አባላት የምክር ቤቱ አባላት የድጋፍ ድምፅ ሰጥተዋል።

አልሸባብ የሶማሊያን መንግስት ለመጣል ላለፉት 16 አመታት ሲታገል ቆይቷል።

ከ2024 ጀምሮ በቡድኑ ላይ ተደጋጋሚ ዘመቻዎችን እንደፈፀመ የገለጸው የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር፣ 220 ጥቃቶችን አድርሶ 868 የሚሊሺያ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። #aa

@ThiqahETH
6👏1
አማራ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 35.8 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገለጸ

ባንኩ በተያያዘው 2018 በጀት ዓመት በ5 ወራት ብቻ ከ 3.55 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እስከ ህዳር 2018 35.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ እድገቱም 82 በመቶ መሆኑንም አስረድቷል።

ካፒታል ጋዜጣ ደረሰኝ ባለው መረጃ መሰረት፤ ባንኩ ከታክስ በፊት 1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል። 591,884 አዳዲስ የደንበኞችን ሒሳብ በመክፈት አጠቃላይ የደንበኞችን ቁጥር 2.68 ሚሊዮን አድርሷል።

የውጭ ምንዛሪ በማሰባሰብ ረገድ፤ 76.58 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ313 በመቶ ብልጫ አለው የተባለ ሲሆን፣ ባንኩ ከተመሰረተ ጀምሮ ያቀረበው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያ ወደ 31.3 ቢሊዮን ብር በማሳደግ በ53.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። #Capital

@ThiqahETH
12🙏4🕊2😡1
ገዳ ባንክ የሀብት መጠኑን 10 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ገለጸ

የባንኩ የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ የተካሄደ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ 2024/ 2025 የበጀት ዓመት የስራ ሪፖርቱን አቅርቧል።

በሪፖርቱም ላይ ባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 10.1 ቢልየን ብር መድረሱን ያሳወቀ ሲሆን፣ ይህም የእቅዱን 94 በመቶ ያሳካው ነው። ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃጸር 80.4 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ሁሴን ሀሰን፣ አሁን ላይ ያለው የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 7.1 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸዋል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲወዳደር የ92.5 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ በበጀት ዓመቱ የ4.33 ቢልየን ብር ዝውውር ማድረጉን፣ በአሁኑ ወቅት የባንኩ አጠቃላይ ባለ አክሲዮኖችም 31 ሺህ 518 ማድረሱ ተገልጿል። #TiritaFm

@ThiqahETH
7🤔3🙏1💔1😡1
ከ30 የሚበልጡ የየመን ወታደሮች በአማፂ ሀይሎች ተገደሉ።

ከሟቾቹ በተጨማሪ 45 ወታደሮች መቁሰላቸውን አለማቀፍ እውቅና የተሰጠው የሊቢያ መንግስት አስታውቋል።

የሀገሪቱ መንግስት ለደረሰው ጥቃት በሀይደራባት ከተማ የሚንቀሳቀሱትን የኤስ ቲ ሲ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል ተብሏል። #reuters

@ThiqahETH
💔64😢3🙏1
THIQAH
ትራምፕ የተኩስ አቁም መደረጉን ቢገልጹም የታይላንድ እና ካምቦዲያ ጦርነት አለመቆሙ ተገለጸ። የካምቦዲያ መንግስት "ታይላንድ ተዋጊ ጄቶችን ጨምሮ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ ጥቃት እያደረሰች ነው" ብሏል። ታይላንድ በበኩሏ የካምቦዲያ ጦር "አለማቀፍ ህግን ጥሷል" በማለት የአፀፋ እርምጃ እየወሰደች እንደምትገኝ ተገልጿል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ትናንት ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ…
"በውይይታችን የሀይል እርምጃዎች እንዲቆሙና ንጹሐን ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች እንዲቀሩ አሳስቢያለሁ" - ማሌዥያ

ማሌዥያ ካምቦዲያ እና ታይላንድ የገቡበትን ጦርነት እንዲያቆሙ አሳሰበች።

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር የተናጠል የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "በውይይታችን የሀይል እርምጃዎች እንዲቆሙ እና በንጹሐን ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች እንዲቀሩ አሳስቢያለሁ" ብለዋል።

ኢብራሂም "በመጪው ማክሰኞ በሚካሄደው የእስያ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እልባት እንዲበጅለት በአጀንዳ መልክ ይነሳል" ሲሉ ጠቁመዋል።

አምስተኛ ቀኑን በያዘው የታይላንድ እና ካምቦዲያ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሟቾች ቁጥር 48 ሲደርስ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል።

ማሌዥያ ከወራት በፊት የነበረውን የሁለቱን ሀገራት ግጭት በማስቆም በዋና ከተማዋ ላምፑር የሰላም ስምምነት እንዲፈጾም ማድረጓ ይታወሳል። #straightstimes

@ThiqahETH
8👏1😱1😢1
THIQAH
በምያንማር "መንግስት በፈጸመው ጥቃት" 30 ሰዎች ሲሞቱ፣ 70 የሚሆኑት ቆሰሉ። ምያንማርን የሚያስተዳድረው ወታደራዊ መንግስት (ጁንታ) የአማፂዎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በራኪን ግዛት የአየር ጥቃት ፈጽሟል። መንግስት የፈጸመው የድሮን ጥቃት በማሩክ ሆስፒታል በማረፉ ንፁሃን ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል። ሆስፒታሉ ባለ 300 አልጋ ሲሆን፣ በሁሉም አልጋዎች ህሙማን እንደሚገኙበት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተናግረዋል።…
"የሞቱት ንጹሐን አይደሉም፣ የአሸባሪው ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው" - መንግስት

የማይናማር መንግስት "ከ30 በላይ ንጹሐን" የቀጠፈውን ጥቃት አስተባብሏል።

የወቅቱ የማይናማር መንግስት በራኪን ግዛት በሚገኘው ሆስፒታል ላይ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጦ፣ ነገር ግን "ጥቃቱ ንጹሐን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ አልነበረም" ብሏል።

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ጁንታ "የሞቱት ንጹሐን አይደሉም፣ የአሸባሪው ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው" ሲል የደረሰበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ "የራኪን ግዛት ከ2024 ጀምሮ በአርካን አማፂ ኃይሎች (AA) ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው፣ ሆስፒታሉን የሚገለገሉበትም የታጠቁ ሀይሎች ናቸው" ነው ያለው።

ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ በተፈጸመው የአየር ላይ ጥቃት 33 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ፣ 76 መቁሰላቸውና 27 የሚሆኑት በጽኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኙ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። #anadoluagency

@ThiqahETH
8💔2🤔1🕊1
ቤላሩስ ለ123 የፖለቲካ እስረኞች ምህረት አደረገች።

መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው አሜሪካ ቤላሩስ ወደ ውጭ በምትልከው የማዳበሪያ ምርት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተከትሎ ነው።

በይቅርታ ከወጡት መካከል በ2020 የተደረገውን ፀረ መንግስት ተቃውሞ የመራችው ማሪያ ኮላስኒኮቫ እና የሰላም ኖቤል ተሸላሚው አሌስ ቢያሊያትስኪ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

አሜሪካ የፕሬዝዳንት ሉካሽንኮ መንግስት በ2021 ያካሄው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ አይደለም በሚል የቤላሩስ መንግስት ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

ፕሬዚዳንት ሉካሽንኮ በዩክሬን ጦርነት ሀገራቸው ለሩሲያ እንደምትወግን በግልጽ ድጋፍ ማሳየታቸው ተገልጿል። #radiofreeeurope #skynews

@ThiqahETH
11👏2🙏2🤔1😭1
"የበቀል እርምጃ እንወስዳለን" - ዶናልድ ትራምፕ

በሶሪያ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው ተነግሯል።

አይኤስአይኤስ (ISIS) በማዕከላዊ ሶሪያ ባደረሰው ጥቃት ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች እና አስተርጓሚ የነበረ የሀገሪቱ ዜጋ ሲገደሉ ሌሎች ሶስት ወታደሮች ተጎድለዋል።

ጥቃቱን ያደረሰው የቡድኑ አባል የነበረ ግለሰብ ፓልምይራ ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በፈጸመው ጥቃት ነው። 

ስለክስተቱ አስተያየታቸውን የሰጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ጥቃት የደረሰበት አደገኛ ቦታ በሶሪያ መንግስት ስር አይደለም" ብለዋል።

"የሶርያ ፕሬዚዳንት አልሻራም ሀዘኑን ገልጿል" ያሉ ሲሆን "በወታደሮቻችን ላይ ለተፈፀመው ጥቃት የበቀል እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉም አክለዋል። #euronews

@ThiqahETH
8👏3🤔2😱1😢1