በብራዚል 64 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገደሉ።
ፖሊስ በዋና ከተማዋ ሪዮ ዴጄናሮ የአደገኛ እፅ አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ ልዩ ኦፕሬሽን መጀመሩን ተከትሎ አመፅ ተቀስቅሷል ተብሏል።
በዚህም ቢያንስ 64 ሰዎች ተገድለዋል ነው የተባለው።
ዘመቻው በሄሊኮፕተሮች እና በወታደራዊ ፓትሮል ተሽከርካሪዎች የታገዘ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ ዘመቻ 81 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጸው ፖሊስ፣ ግማሽ ቶን አደገኛ እፅ መያዙን አስታውቋል።
የሰብዓዊ መብት ተቋማት ለደረሰው ግድያ ገለልተኛ ምርመራ እንድደረግ ጠይቀዋል ተብሏል። #euronews
@ThiqahEth

❤19👏3😢2
"ከ104 ከሟቾች ውስጥ 46 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው" - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተጣሰ በኋላ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 104 ፍልስጤማውያን ተገደሉ።
ከሟቾቹ ውስጥ 46 የሚሆኑት ህፃናት መሆናቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የሰላም ስምምነቱ ተጥሷል ቢሉም፣ በአሁኑ ወቅት ስምምነቱ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው "ምንም ነገር ስምምነቱን አይቀይረውም" ብለዋል። #aljazeera
@ThiqahETH

😭21❤7💔6👏2🤔1😢1😡1
THIQAH
Photo
በብራዚል በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉት ሟቾች ቁጥር 132 ደረሰ።
በዋና ከተማዋ ሪዮ ድጄናሮ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ በተጀመረው ኦፕሬሽን የሟቾች ቁጥር 132 ደርሷል።
የተተጎጂዎች ቁጥር በውል አይታወቅም ተብሏል።
የሪዮ ከተማ ከንቲባ ቪክቶር ሳንቶስ "ዘመቻው የሚጠበቅ ነው ግን ፈልገነው አይደለም" ብለዋል።
ከንቲባው አክለው፣ "ከአለማቀፍ ስብሰባው ጋር አይገናኝም፣ የተመድ ኮፕ30 ቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል" ብለዋል።
የከተማዋ ፖሊስ በበኩሉ የዘመቻው እቅድ ከሁለት ወር በፊት እንደተጀመረ ገልፆ፣ 2500 ኦፊሰሮች ተሰማርተዋል ብሏል።
በዚህ ኦፕሬሽን ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።#sundaytimes

❤12🤔4😢2
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የኑክሌር ሙከራ ማድረግ እንደምትጀምር ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሶስት አስርት አመታት በፊት አቁማው የነበረውን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ በቅርቡ ትጀምራለች ብለዋል።
የኑክሌር ሙከራ የሚደረገው ከሩሲያ እና ቻይና ጋር እኩል ቦታ ላይ እንደምንገኝ ለማሳየት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት ከቻይናው አቻቸው ዥ ጂ ፒንግ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ነው ተብሏል።
አሜሪካ የኑክሌር ሙከራ ያደረገችው በ1992 በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ የስልጣን ዘመን ነበር። #forbes

❤6😱1🕊1
177 ሺሕ ሱዳናውያን ከኤልፋሽር ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ።
ከተማዋ በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ቁጥጥር ስር መዋሏን ተከትሎ የጅምላ ግድያ ይፈፀማል በሚል ስጋት ነው የወጡት ተብሏል።
ቡድኑ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ 2,000 ሰዎች መገደላቸውን ተመድ ገልጿል።
ባለፉት ሶስት ቀናት 36,000 ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን 1000 የሚሆኑት ወደ ታዊላ ከተማ ተሰደዋል ነው የተባለው።
ተመድ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የዘር ማጥፋት ወንጀልና ጭፍጨፋ እየፈፀመ እንደሆነ በተደጋጋሚ አስታውቋል።
በሄመቲ የሚመራው አር ኤስ ኤፍ ንፁሃንን በአንድ ቦታ አሰባስቦ የመረሸን፣ ቤት ለቤት እየዞረ የመግደል እና ፆታዊ ጥቃት ወንጀል ፈፅሟል ተብሏል። #trtworld

😢9💔6❤3🕊2👏1🤔1😭1
THIQAH
በጃማይካ ከባድ አውሎ ነፋስ ተከስቷል። የጃማይካ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሪው ሆልስ ዜጎች ወደውጭ እንዳይወጡና በቤታቸው እንዲቆዩ አስጠንቅቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኃይለኛ ንፋስ፣ ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል" ብለዋል። "ሜሊሳ" የተሰኘው አውሎ ነፋስ መላው ካሪቢያን ደሴትን እና አካባቢውን መምታቱ ተገልጿል። አውዳሚ ነው የተባለው ይህ አውሎ ነፋስ በሰዓት 282 ኪሎሜትር…
በካሪቢያን በተከሰተው አውሎንፋስ የሟቾች ቁጥር 50 ደረሰ።
ከሟቾች ባሻገር፣ ከ16 ሺሕ በላይ ሰዎች የሚኖሩባቸው ከ1000 በላይ ሴቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
"ሜሊሳ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የአውሎንፋስ አደጋ አድማሱን አስፍቶ ከጃማይካ ወደ ኩባ መሸጋገሩ ተገልጿል።
በተለይ በጃማይካ የመገናኛ አውታሮች ተቋርጠዋል፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ቁሟል ተብሏል።
የጃማይካ መንግስት 735 ሺሕ ዜጎችን አደጋ ከተጋረጠባቸው ሶስት ከተሞች ማስወጣታቸውን አስታውቀዋል።
ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል። #nzherald

😢3❤2🙏2🕊2
ሩሲያ 700 ድሮንና ሚሳዔል ወደ ዩክሬን አስወነጨፈች።
በዚህ ከባድ የአየር ላይ ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
ጥቃቱ የሀይል መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ በመሆኑ ውድመት አስከትሏለል ተብሏል። #nzherald

❤4🕊4🤔1
በታንዛኒያ ምርጫ ሲጀመር ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።
አመጹ መባባሱን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል ተብሏል።
በተቃውሞው እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸው እና መጎዳታቸው ተገልጿል።
የፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ መንግስት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን አስሯል ቀሪዎቹንም ከምርጫ አግዷቸዋል ተብሏል።
አመጸኞቹ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሳይሳተፉ የሚደረግ ምርጫ ፍትሃዊ ባለመሆኑ መደረግ የለበትም በሚል ነው አመፁን የጀመሩት ተብሏል። #news24

🤔3❤2👏1🕊1😭1
THIQAH
አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለሁለት ቀን ወይም 48 ሰዓት ይቆያል ተብሏል። ለጦርነቱ መጀመር ሁለቱም ሀገራት አንዱ አንዱን ተጠያቂ አድርገዋል ተብሏል። ለሶስት ቀን በቆየው ጦርነት 12 ንጹሐሃን መሞታቸውንና ከ100 በላይ መቁሰላቸውን የታሊባን መንግስት አስታውቋል። የፓኪስታን ጦር በበኩሉ፣ 11 አባላቱ እንደተገደሉበት ገልጿል። #cbsnews …
ፓኪስታን እና አፍጋኒስታን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም ተስማሙ።
ሁለቱ ሀገራት በቱርክ አሸማጋይነት በኢስታንቡል ውይይት አካሂደዋል።
ሀገራቱ በድንበር አካባቢ የጋራ ቁጥጥር ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የኢስታንቡሉ ውይይት ለሰባት ቀናት መዝለቁን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ባለስልጣናት በቀጣይ ህዳር ወር ላይ ዳግም ተገናኝተው ስለተኩስ አቁም ስምምነቱ ይገመግማሉ ተብሏል። #samma

❤7🕊2
ሁሴን አሊ ምዊኒ የዛንዚባር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።
ምዊኒ ለሁለተኛ ጊዜ ሀገሪቱን መምራት የሚያስችላቸውን ድምፅ ማግኘታቸውን የዛንዚባር ምርጫ ኮሚሽን (ZEC) አስታውቋል።
ገዥው ቻማ ቻ ማፒንዲ (CCM) ፓርቲ ሀገሪቱ ነፃ ከወጣችበት ከ1964 ጀምሮ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ይገኛል። #bbc

🤔7❤5👏4😡3
"በመላ ሀገሪቱ ከ700 እስከ 800 ሰዎች ተገድለዋል" - የታንዛኒያ ተቃዋሚ ፓርቲ
በታንዛኒያ በተቀሰቀሰው አመፅ ቢያንስ የ700 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
የሀገሪቱ ዜጎች ረቡዕ መካሄድ የጀመረውን ምርጫ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል ተብሏል።
የቻደማ ተቃዋሚ ፓርቲ ቃል አቀባይ ጆን ኪቶካ "በመላ ሀገሪቱ ከ700 እስከ 800 ሰዎች ተገድለዋል" ብለዋል።
"በዳሬሰላም ብቻ 350 ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች ጥቃት ህይወታቸው አልፏል" ያሉት ኪቶካ "የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ መብለጡ አይቀርም" ሲሉ ተናግረዋል።
"ብዙ ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች መረጃ ለመስጠት ፈርተው እየደበቁ ነው" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ለተፈጠረው አለመረጋጋት የፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉን መንግስት ተጠያቂ አድርገዋል። #france24 #ajiancefrancepress
@ThiqhETH

😢6❤5🤔3👏1
"በታንዛኒያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው" - የአውሮፓ ሀገራት
ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኖርዌይና ካናዳ ምርጫን ስበብ አድርጎ የተቀሰቀሰው የታንዛኒያ አመጽ መፍትሄ እንዲበጅለት ጠየቁ።
ሀገራቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ "ምርጫ ባስከተለው አመጽ ከፍተኛ የሞትና የጉዳት መጠን መኖሩን ሪፖርቶች ደርሰውናል" ሲሉ ገልጸዋል።
"በታንዛኒያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው" ያሉት ሀገራቱ፣ "ባለስልጣናት የመናገር እና የመሰብሰብ መብትን ማክበር አለባቸው" ብለዋል።
አክለው፣ "ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተቃዋሚዎች፣ የመብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመው አፈሳና እስር በጣም አሳሳቢ ሁኗል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። #gov.uk

❤4🤔2🕊1
THIQAH
"በመላ ሀገሪቱ ከ700 እስከ 800 ሰዎች ተገድለዋል" - የታንዛኒያ ተቃዋሚ ፓርቲ በታንዛኒያ በተቀሰቀሰው አመፅ ቢያንስ የ700 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ። የሀገሪቱ ዜጎች ረቡዕ መካሄድ የጀመረውን ምርጫ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል ተብሏል። የቻደማ ተቃዋሚ ፓርቲ ቃል አቀባይ ጆን ኪቶካ "በመላ ሀገሪቱ ከ700 እስከ 800 ሰዎች ተገድለዋል" ብለዋል። "በዳሬሰላም ብቻ 350 ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች…
ሳሚያ ሱሁሉ 98% ድምፅ በማግኘት የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
ታንዛኒያ ባካሄደችው ምርጫ 32 ሚሊዮን ዜጎች መሳተፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሳውቋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በሀገራዊ ምርጫው እንዳይሳተፉ ማገዳቸው ህዝባዊ ተቃውሞ አስከትሏል።
በታንዛኒያ በምርጫ ውዝግብ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ700 በላይ ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል።
በ2021 ወደስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንቷ ለተጨማሪ አምስት አመት በሀላፊነት መቆየት የሚያስችላትን ድምፅ ማግኘቷን ኮሚሽኑ አረጋግጧል። #bbc

❤12🤔12💔4😡3😱1🕊1