THIQAH
9.78K subscribers
4.55K photos
50 videos
1 file
38 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
40 ስደተኞች በቱኒዚያ ድንበር ህይወታቸው አልፎ ተገኙ።

70 ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በመገልበጧ ነው አደጋው የደረሰው ተብሏል።

ቀሪዎቹ 30 ስደተኞች በህይወት መትረፋቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ስደተኞቹ በህገወጥ መንገድ አውሮፓ ለመግባት ሲጓዙ ነበር ተብሏል።

የአውሮፓ ህብረት "ህገወጥ ስደትን ለመቆጣጠር" በሚል በ2023 ለሞሮኮ 127 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ተመላክቷል። #anadoluagency

@ThiqahEth
🕊53👏2🙏2😢1
#Ethiopia

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው ለተለያዩ አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶች ምደባ አከናውኗል።

በዚህ መሠረት፦
ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ የኢሉባቡር ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮምያ ብሔረሰብ ዞን ኬሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣

ብፁዕ አቡነ ቶማስ  የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣

ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና የሆሮጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ በሁለተኛ ቀን የጉባኤው ውሎው ወስኗል።
#ተሚማ

@ThiqahETH
11🙏5🤔1
ቤልጂየም ምን አለች?

ቤልጅየም የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ድጋፍ አደርጋለሁ ማለቱን ተቃወመች።

ህብረቱ እንዳይንቀሳቀሱ የታገደው 182 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመተው የሩሲያ ንብረት ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት ጥቅም ላይ እንዲውል ወስኗል።

የቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር ባርት ዌቨር ግን፣ "መፍትሄ መፈለግ ይሻላል ወይስ ዛሬም ለዩክሬን  ድጋፍ ማድረግ?" ሲሉ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ይህ ነገር የከፋ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ አለብን" ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በብራሰልስ የሁለት ቀናት ስብሰባ እያካሄዱ ይገኛሉ። #helsinkitimes

@ThiqahETH
12👏6😢3🙏3🕊1
በሱዳን በድሮን ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገደሉ።

ጥቃቱን የፈጸሙት የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች  መሆናቸውን የሱዳን ጦር አስታውቋል።

ጦሩ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው በካርቱም አየርመንገድ አጠገብ መሆኑም ገልጿል። #trtworld

@ThiqahETH
🕊43🤔3👏2😱1
"ከእስራኤል ጋር ያለንን ሁሉንም ግንኙነት እናቋርጣለን" - ትራምፕ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ዌስት ባንክን እንዳትቆጣጠር አስጠነቀቁ።

"እስራኤል ዌስት ባንክን ከያዘች ወሳኝ አጋሯን አሜሪካን ታጣለች" ብለዋል ትራምፕ።

ፕሬዚደንቱ "ከእስራኤል ጋር ያለንን ሁሉንም ግንኙነት እናቋርጣለን" ሲሉ ተደምጠዋል።

"ያ ፈጽሞ አይሆንም ለአረብ መሪዎች ነግሪያቸዋለሁ" ነው ያሉት።

ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው "አትጨነቁ እስራኤል ከዌስት ባንክ ጋር በተያያዘ ምንም አታደርግም" በማለት ገልጸዋል።
#thenewarab

@ThiqhETH
27😡7🕊4🤔3🙏3👏2
አሜሪካ በኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ላይ ማዕቀብ ጣለች።

ማዕቀቡ "የአደንዛዥ እፅ ምርትን አስፋፍቷል እና ፀረ ናሮቲክ እርምጃዎችን አደናቅፈዋል" በሚል እንደሆነ ተገልጿል።

የአሜሪካ ገንዘብ ቢሮ ሀላፊ ስኮት ባሰንት በአሜሪካ የሚገኘው የፕሬዝዳንት ፔትሮ ገንዘብ እንዳይቀሰቀስ አግደዋል ተብሏል።

አሜሪካ ከፕሬዝዳንቱ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሉዊስ ፈርናንዶ ላይም ማዕቀብ ጥላለች። #shafaaqnews

@ThiqhETH
😡109😱2👏1🤔1
በደቡብ ሱዳን 9.3 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ።

አብዛኞቹ እርዳታ ፈላጊዎች በጎርፍ፣ በፖለቲካ እና በምጣኔ ሀብት ውድቀት የተጎዱ መሆናቸውን ተመድ አስታውቋል።

በደቡብ ሱዳን የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ አኒታ ጌቦ "በተለይ ስድስት ግዛቶች የተለየ ችግር አለባቸው" ብለዋል።

ጌቦ "በቅርቡ በተከሰተው ጎርፍ ብቻ 960,000 ህዝብ በጎርፍ ተጎድቷል" ሲሉ ተናግረዋል።

"በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ችግሩን አባብሶታል" ብለዋል።

ኃላፊዋ አክለውም በተያዘው አመት ሶስት ሚሊየን ሰዎች እርዳታ ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል። #aa

@ThiqahETH
💔7😢5🕊21
"ትራምፕ ጦርነት እየፈበረኩ ነው" - ቬንዙዌላ

የቬኔዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በጦርነት ቀስቃሽነት ወነጀሉ።

ማዱሮ "ሀገራችንን ለግጭት እየገፋፉ ነው" ሲሉ ወንጅለዋል።

"ትራምፕ ጦርነት እየፈበረኩ ነው። ጦርነት አንፈልግም ይሉናል ግን ወንጀለኛ አድርገው እየሳሉን ነው" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ መከላከያ ቢሮ ፔንታጎን ትልቁ የጦር አውሮፕላን ወደላቲን አሜሪካ መጓጓዙን ማስታወቁን ተከትሎ ነው። #time

@ThiqahETH
10🕊5🤔2😱1
አይቮሪኮስት ብሄራዊ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።

የወቅቱን ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራን ጨምሮ አምስት እጩዎች በምርጫው እየተወዳደሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ከእጩዎቹ መካከል የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ጂን ሉዊስ እና በኦታራ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመን የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አሁዋዶን ሜሎ ይገኙበታል ተብሏል።

ሀገሪቱ ካላት 30 ሚሊየን ህዝብ 37% የሚሆነው በድህነት ወለል እንደሚገኝ ተመላክቷል። #france24

@ThiqahETH
7👏3🕊2😱1
ፖርቹጋል ለውጭ ሀገር ዜጎች የስራ ቪዛ አገደች።

ደቡብ አውሮፓዊቷ ሀገር ይህን ውሳኔ ያሳለፈችው አዲስ የወጣው የስደተኞች መቆጣጠር አንቀጽ 61/2025 መሰረት እንደሆነ ተገልጿል።

አዲሱ ህግ የውጭ ሀገር ዜጎችን ካሁን በኋላ ለስራ ፍለጋ ወደ ፖርቹጋል እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ ይከለክላል ተብሏል።

በሀገሪቱ የቱሪዝምና ኮንስትራክሽን ዘርፎች በውጭ ሀገር ባለሙያዎች እንደሚሰሩ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በዚሁ መሰረት አዋጁ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ካሁን በፊት የተያዙ የስራ ቪዛ አመልካች ቀጠሮዎች እንደተሰረዙ ተገልጿል። #shengennews

@ThiqahEth
5😢5🤔2😱2
ካትሪን ኮሎኒ የአየርላንድ ብሄራዊ ምርጫን አሸነፉ።

የ68 አመቷ ኮሎኒ ረቡዕ የተካሄደውን ምርጫ 55.7 በመቶ ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቷ የጋላዋይ ከተማ ከንቲባ ሁነው አገልግለዋል። #bbc

@ThiqahETH
10😱4
ሁለት የአሜሪካ ጦር ጀቶች ተከሰከሱ።

ሁለቱ የጦር ጄቶች በደቡብ ቻይና በግዳጅ ላይ በነበሩበት ወቅት አደጋው መድረሱን በፓስፊክ የአሜሪካ ጦር ቢሮ አስታውቋል።

በሁለቱም ጀቶች አምስት የበረራ አባላት የነበሩ ሲሆን፣ ሁሉም በጥሩ ደህንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። #forcesnews

@ThiqahETH
13👏3😢2
ዩናይትድ ኪንግደም ለዩክሬን 5000 ሚሳዔል እንደምትሰጥ ኬር ስታርመር ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር ድጋፉ በቀጣዩ የበጋ ወቅት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ስታርመር ሀገራቸው ለዩክሬን የምታደርገው ድጋፍ ዘላቂ መሆኑን አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሮዝኔፍት እና ሉኮይል የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን አድንቀዋል ተብሏል። #indiatoday

@ThiqahETH
4😡4👏3😢2😱1
የጅቡቲ ፓርላማ የፕሬዝዳንታዊ እጩ የእድሜ ገደብን አነሳ።

ይሄ ውሳኔ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ለስድስተኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ መወዳደር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

የ77 አመቱ ጉሌህ በቀጣይ አመት 2026 የምርጫ ዘመን እጩ ሆነው ይቀርባሉ ተብሏል።

የሀገሪቱ ህግ እድሚያቸው ከ75 በላይ የሆኑ ፖለቲከኞች ለመሪነት እጩ መሆን እንደማይችሉ ይደነግጋል።

ህጉ የጸደቀው ከ15 አመት በፊት በ2010 ሲሆን፣ ሀሳቡን ያመጡት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ጉሌህ ናቸው።

ጉሌህ ከፈረንጆች 1999 ጀምሮ ላለፉት 26 አመታት ጅቡቲን በፕሬዝዳንትነት እያስተዳደሩ ይገኛሉ። #aljazeera

@ThiqahEth
🤔15😡4😱3👏21
#Ethiopia

"በቻናሉ የሚተላለፉ መልዕክቶች የፌዴሬሽኑ አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን" - ፌዴሬሽኑ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዩቲዩብ ቻናል ለጊዜው ከቁጥጥራችን ውጪ መሆኑን አስታውቋል።

ቁጥጥሩን ለማስመለስ ጥረት እያደረግን መሆኑን ገልጾ፣ "በቻናሉ የሚተላለፉ መልዕክቶችም የፌዴሬሽኑ አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን" ብሏል።
#EFF

@ThiqahETH
🤔51