THIQAH
9.62K subscribers
4.68K photos
51 videos
1 file
38 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
አሜሪካ ፕሬዚዳንት ማዱሮን በቁጥጥር ስር ላዋለ 50 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ቃል ገባች።

የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ በቬኔዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል ተብሏል።

እ.ኤ.አ በ2020 ማዱሮ ላይ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር ክስ የከፈተችባቸው አሜሪካ፣ ፕሬዚደንቱ ያሸነፉባቸውን ያለፉትን ሁለት ዙር ምርጫዎች እውቅና እንደማትሰጥ ገልፃለች። #bbc #france24

@ThiqahEth
😡234👏4🤔3😭2😱1🕊1
ሩሲያ ለቻይና ነዳጅ በርካሽ ዋጋ መሸጥ ጀምራለች ተባለ።

ሩሲያ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ የነዳጅ ሀብት ሽያጭ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮባታል ተብሏል።

ሞስኮ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የአለም አቀፍ ንግድ እንቅስቃሴዋ ገደብ ተጥሎበታል።

ቻይና የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ብትሆንም፣ አሁን ግን በርካሽ ዋጋ የመሸመት እድል ማግኘቷ ተገልጿል።

ከጦርነቱ መጀመር በኋላ ህንድ የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት ከፍተኛ ጠቀሜታን አግኝታለች ተብሏል።

ነገር ግን አሜሪካ ህንድ ነዳጅ ከሩሲያ መግዛት እንድታቆም ያሳሰበች ሲሆን ካልሆነ ግን ማዕቀብ እንደምትጥል አስጠንቅቃለች።

አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ማዕቀብ ሩሲያን ማዕቀብ ቢጥሉባትም ነዳጇን በህንድ በኩል እየገዙ ሲጠቀሙ መቆየታቸው ተገልጿል። #oilprice

@ThiqahEth
10👏2🤔2
ቤኑ 176 ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለጸች።

የቤኑ ብሄራዊ ፖሊስ በክህደት፣ እገታ፣ ዘረፋና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ተሳታፊ ሆነዋል ያላቸውን ዜጎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

እነዚህ ፖሊሶች ባሳለፍነው ሀምሌ ወር የተከሰቱ መሆናቸውን የቤኑ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኢፌኒ እነማሪ ተናግረዋል። #dailytrust

@ThiqahEth
🤔64😱1
አሜሪካ ለዝምባቡዌ ዜጎች ቪዛ መስጠት አቆመች።

በሀራሬ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ እግዱ የተጣለው በብሄራዊ እና የህዝብ ደህንነት ምክንያት መሆኑን ገልጿል።

ውሳኔው የተላለፈው በቀጥታ ከዋሽንግተን ነው ብሏል። #africannews

@ThiqahEth
😡64🤔3😱1🕊1
"ከፍተኛ የሞት መጠን ከተመዘገበባቸው መካከል ይህ ጥቃት አንዱ ነው" - ተመድ

"የሽብር ወንጀል እየተፈጸመ የሚደረግ የሰላም ስምምነት የለም" - የዲአር ኮንጎ መንግስት


በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 319 ንጹሃን በኤም 23 አማፂ ቡድን ተገደሉ።

በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው የM 23 አማፂ ቡድን በሰሜን ኪቩ ግዛት የንጹሃን ጭፍጨፋ መፈጸሙ ተገልጿል።

"አመፂ ቡድኑ ገደላቸው" ከተባሉ ንጹሃን መካከል 48 ሴቶች እና 19 ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል።

የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ "ተጎጂዎችን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ደርሶናል" ብለዋል።

ተርክ፣ "ከፍተኛ የሞት መጠን ከተሰዘገበባቸው ጥቃቶች መካከል ይህ አንዱ ነው" ሲሉ የድርጊቱን ዘግናኝነት አብራርተዋል።

"በንጹሃን ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች መቆም አለባቸው" ያሉት ኮሚሽነሩ "ጥቃት አድራሾች ተጠያቂ እንዲሆኑ" ጠይቀዋል። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግስት በበኩሉ የደረሰውን ጥቃት አውግዟል።

የመንግስት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ "የሽብር ወንጀል እየተፈጸመ የሚደረግ የሰላም ስምምነት የለም" ሲሉም አስታውቀዋል። ቃል አቀባዩ "የተደረጉ ስምምነቶች በግዴለሽነት ተጥሰዋል" ሲሉ ቡድኑን ወንጅለዋል።

የሀገሪቱ መንግስት እና አማፂ ቡድኑ ጦርነቱን ለማቆምና ዘላቂ ስምምነት ለመፈፀም ባሳለፍነው ሰኔ ወር የመጀመሪያ ስምምነታቸውን በዋሽንግተን ተፈራርመዋል። #aljazeera #anadoluagency  #abcnews

@ThiqahEth
😭76🤔2👏1
"35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል" - አሜሪካ

"ዛሬ ሰላምን መስርተናል" - አዘርባጃን

"ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ጉልህ ስራ ተሰርቷል" - አርሜኒያ

አርሜኒያና አዘርባጃን በአሜሪካ አማካኝነት የሰላም ስምምነት ፈጸሙ።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለአስርት አመታት የዘለቀውን ግጭት ያስቆማል የተባለ ስምምነት በዋሽንግተን ፈጽመዋል ተብሏል።

የአዘርባጃን ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሌቭ ከአርሜኒያው አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽኒያን ጋር በዶናልድ ትራምፕ አሸማጋይነት ውይይቱ መካሄዱ ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን "ረጅም ጊዜ የወሰደ ታሪካዊ ስምምነት ነው" ብለውታል።

አዘርባጃንና አርሜኒያ ከ1980ዎቹ ጀምሮ በአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛትጦርነት ውስጥ እንደነበሩ ያስታወሱት ትራምፕ ግጭቱን "እስከወዲያኛው ይወገዳል" በማለት ተናግረዋል።

ትራምፕ፣ "35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል" ያሉ ሲሆን፣ "የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት አሊቭ ደግሞ "ዛሬ ሰላምን መስርተናል" ብለዋል።

የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሺኒያን በበኩላቸው፣ "ለሁለቱ ጉልህ ሀገራት ግንኙነት ስራ ተሰርቷል" በማለት ገልጸዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ሀገራት የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የንግድ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲጀመሩ እና ለተፈፃሚነቱ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። #bbc

@ThiqahEth
27🕊9🙏3🤔1
"አሜሪካ ፍልስጤምን ሀገር የማድረግ እቅድ የላትም፣ እዚያ አቅም ያለው መንግስት የለም" - ጄይ ጂ ቫንስ

የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ቫንስ ሀገራቸው ፍልስጤም ሀገር እንድትሆን ፍላጎት የላትም አሉ።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ "እዚያ አቅም ያለው መንግስት የለም" በማለት ገልጸዋል።

ቫንስ ይህን ያሉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉባት ባለችው እንግሊዝ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ላሚ ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።

እስራኤል በጋዛ የምትፈጸመውን ግፍ እንድታቆም አሜሪካ ጫና ማድረግ እንዳለባት አሳስበዋል ተብሏል።

እንግሊዝ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ በሁለት ሀገርነት መፍትሄ መርህ ፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገር እንድትሆን ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። #indiatoday

@ThiqahEth
😡2515😱1🙏1🕊1
"ከኛ ተፃራሪ የሚሆን ውሳኔን አንቀበልም" - ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ትራምፕ እና ፑቲን በአካል ሊገናኙ ነው መባሉን ተከትሎ በግል የፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዘለንስኪ በዚህ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ልጥፋቸው በውይይቱ እሳቸውም እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ "ኪቭ ያልተካተተችበት የትኛውም ስብሰባ ውጤት አይኖረውም" ብለዋል።

አክለውም፣ "ከኛ ተፃራሪ የሚሆን ውሳኔን አንቀበልም" በማለት ፑቲንና ትራምፕ ብቻ የሚያካሂዱትን ውይይት ነቅፈውታል።

የሁለትዮሽ ንግግሩ የሚያመጣውን ውጤት "የሞተ መፍትሄ" በማለት ገና ከወዲሁ ተቃውመውታል።

"ዩክሬናውያን መሬታቸውን ለወራሪዎች አይሰጡም" ያሉት ዘለንስኪ ሀገራቸው ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። #telegraph

@ThiqahEth
14😡3🤔2😱2😭1
"ከጋዛ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ዘር ማጥፋትን እንቃወማለን፣ የፍልስጤምን ድርጊት እንደግፋለን" - ሰልፈኞች

የለንደን ፖሊስ ከ460 በላይ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

የፍልስጤም ተሟጋቾች እስራዔል በፍልስጤውያን ላይ የምትፈጽመውን ግፍ ለመቃወም በፓርላማ አዳራሽ ፊት ለፊት መሰባሰባቸው ተገልጿል።

ተቃዋሚዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር መንግስት እስራኤል ላይ ማዕቀብ መጣልን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በሰልፉ ወቅት "ከጋዛ ላይ እጃችሁን አንሱ"
ዘር ማጥፋትን እንቃወማለን፣ የፍልስጤምን ድርጊት እንደግፋለን" በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል።  

ይህንን ተከትሎ የከተማዋ ፖሊስ ከ460 በላይ የሰልፉ ታዳሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ዩናይትድ ኪንግደም እንደ "የሽብር ተግባር" በመቁጠር በሀገሯ የሚደረጉ የፍልስጤም መብት ተሟጋቾችን እንቅስቃሴ አግዳለች ተብሏል። #reuters

@ThiqahEth
41😡3🕊2👏1🤔1
THIQAH
"ከኛ ተፃራሪ የሚሆን ውሳኔን አንቀበልም" - ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ትራምፕ እና ፑቲን በአካል ሊገናኙ ነው መባሉን ተከትሎ በግል የፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ዘለንስኪ በዚህ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ልጥፋቸው በውይይቱ እሳቸውም እንዲሳተፉ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ "ኪቭ ያልተካተተችበት የትኛውም ስብሰባ ውጤት አይኖረውም" ብለዋል። አክለውም፣ "ከኛ…
"ዩክሬንን ለመቀራመት የሚደረግ ውይይት አዋጭ አይደለም" - የዩክሬን አጋር የአውሮፓ ሀገራት

6 የአውሮፓ ሀገራት የትራምፕንና የፑቲንን የተናጠል ውይይት ተቃወሙ።

ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፊንላንድ እንዲሁም ፖላንድና እንግሊዝ በመሪዎቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ "የሀገር ሉዓላዊነት የሚባለው ጉዳይ ሊከበር ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።

የዩክሬን አጋር የተባሉት እነዚህ የአውሮፓ ሀገራት "ዩክሬንን ለመቀራመት የሚደረግ ውይይት አዋጭ አይደለም" ብለዋል።

ሀገራቱ "በውይይቱ ዩክሬን መሳተፍ ይኖርባታል"  በማለት ጠይቀዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው፣ "የዩክሬን ሰላም ያለዩክሬን ተሳትፎ አይወሰንም" ብለዋል።

"ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች የዩክሬንን እና የአውሮፓን ደህንነት መጠበቅ አለባቸው" ሲሉም ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ "ኪቭ ያልተካተተችበት የትኛውም ስብሰባ ውጤት አይኖረውም" በማለት የሁለቱን መሪዎች ስብሰባ ተቃውመዋል። #politico

@ThiqahEth
17👏4🤔1😢1
"የሱዳንን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር ሲቪል መር አስተዳደር እንዲመሰረት እንፈልጋለን" - አቡዳቢ

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሱዳን የርስበርስ ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቀረበች።

አቡዳቢ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፃለች።

መግለጫው "ሰላምን መረጋጋትን እና የነገን ተስፋ መፈለግ ይገባል" ብሏል። "የተኩስ አቁም እንዲደረስ፣ ንጹሃን እንዲጠበቁ እና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀናል" ሲል ገልጿል።

መግለጫው አክሎም፣ "የሱዳንን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር ሲቪል መር አስተዳደር እንድመሠረት እንፈልጋለን" ነው የሚለው።

ኤምሬትስ ከሱዳን የሚቀርብባትን ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ የመስጠት ውንጀላ "ሆን ተብሎ የተሰራ ፕሮፓጋንዳ" ስትል አጣጥላዋለች። #khaleejtimes

@ThiqahEth
10🕊5🤔4👏1🙏1
"በሽፋ ሆስፒታል አንድ ጋዜጠኛዬ በእስራኤል ጥቃት ተገድሎብኛል" - አልጀዚራ

"ጋዜጠኛ ሳይሆን የሃማስ የህዋስ መሪ ነበር" - እስራኤል

የ28 አመቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ አናስ አል ሻሪፍ በምስራቅ ጋዛ በስራ ላይ እያለ መገደሉን አልጀዚራ አስታውቋል።

ጣቢያው ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ "በሽፋ ሆስፒታል አንድ ጋዜጠኛዬ በእስራኤል ጥቃት ተገድሎብኛል" ብሎ፣ "ጥቃቱ በጋዛ የሚካሄደውን ህገወጥ ወረራ በተመለከተ ድምፅ የሚሆኑትን ለማስቆም የተደረገ ሙከራ ነው" በማለት ተቃውሟል።

የእስራኤል ጦር በበኩሉ ሟቹ "ከሀማስ አመራሮች ጋር ቅርብ ግንኙነት ነበረው" በማለት ወንጅሏል።

ጦሩ ባወጣው የማስተባበያ መግለጫ "ጋዜጠኛ ሳይሆን የሃማስ የህዋስ መሪ ነበር" ብሏል።

"በእስራኤል ንጹሃን ላይ በተፈጸሙ የሮኬት ጥቃቶች ላይ እጁ አለበት" ሲል ወቅሷል። ለዚህም የደህንነት እና የሰነድ ማስረጃዎች እንዳሉት ገልጿል።

@ThiqahEth
9😭4😢1