THIQAH
9.4K subscribers
5.09K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
"ለሩሲያ ተጨማሪ 6000 ወታደሮችን ለመላክ ፍላጎት አለን" - ሰሜን ኮሪያ

የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ለሩሲያ ተጨማሪ 6000 ወታደሮችን የመላክ ፍላጎት እንዳላት አስታውቀዋል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ያሳወቁት በፕዮንግያንግ ከሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ኃላፊ ሰርጌ ሾይጉ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።

ሰርጌ ሾይጉ በበኩላቸው በጦርነቱ ለተሳተፉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ክብር ለመስጠት እያሰበች እንደሆነ ገልጸዋል።

ወደ ሩሲያ ይላካሉ የተባሉት ወታደሮች በዩክሬን ኃይሎች የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያግዙ ናቸው ተብሏል።
#joins

@ThiqagEth
31😡2🙏1
"የኢራንን ሰማይ ተቆጣጥረነዋል" - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ካሁን በፊት በጦርነቱ ተሳትፎ እንደሌላት ሲገልጹ ቢቆዩም "አሁን ላይ የኢራንን ሰማይ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረነው እንገኛለን" ሲሉ ተናግረዋል።

"ከአሜሪካ ውጭ ይህን ማንም አያደርግም" ብለዋል ትራምፕ።

የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው፣ ትራምፕ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለማስቆም "ተጨማሪ እርምጃ" ሊወስዱ ይችላሉ ብለዋል።

ቫንስ የአሜሪካን ወታደራዊ ጣልቃገብነት በተመለከተ የሰጡት ሀሳብ የለም።
#hurriyetdailynews

@ThiqahEth
23😡7😭2🕊1
ኢራን የሳይበር ጥቃት እንደደረሰባት ባለስልጣናቱ ማረጋገጣቸው ተነገረ።

የእስራኤል ደጋፊ ናቸው የተባሉ የበይነመረብ ጠላፊዎች በኢራን የሰፓህ ባንክ ላይ የሳይበር ጥቃት ፈጽመዋል ተብሏል።

የሰፓህ ባንክ ለኢራን ብሄራዊ ዘብ እና ለኑክሌር ፕሮግራሞች ቀጥተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ባንክ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይበር ጥቃቱ የኤቲኤም አገልግሎቶች መቋሰጣቸው፣ የነዳጅ ማደያዎች ተስተጓጎላቸው፣ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው ተነግሯል። 

ጥቃቱ መፈጸሙን የኢራን ባለስልጣናትም አረጋግጠዋል።
#ynetnews

@ThiqahEth
22👏7😡1
"አያቶላሕ አሁን መግደል አንፈልግም" - ትራምፕ

"የአያቶላሕ መገደል ጦርነቱን አያባብሰውም" - ኔታንያሁ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ "አሜሪካ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የት እንደተደበቀ ታውቃለች፣ ግን አሁን መግደል አንፈልግም" አሉ።

"በቀላል ኢላማ ውስጥ ነው ያለው፣ ደህና ነው ፣ ግን ይዘን ማምጣት አንፈልግም" ነው ያሉት።

ፕሬዚዳንቱ "ነገር ግን ህፃናት በሚሳዔል እንዲያልቁ፣ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲሞቱ አንፈልግም" ሲሉም አክለዋል።  

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ሀገራቸው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ ላይ ግድያ የመፈጸም ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል።

"አያቶላሕ ቢገደሉ በቴላቪቭ እና በቴህራን መካከል ያለውን ጦርነት እያባባሰውምሟ እንዲያው ጦርነቱ ቶሎ ይቋጫል" በማለትም ተናግረዋል።

"ወደ ዝርዝር ጉዳዮች መግባት አልፈልግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ከፍተኛ የኑክሌር ሳይንቲስቶችን እንደገደልን ግን ላረጋግጥላችሁ እችላለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። 
#aa #gulftoday

@ThiqahEth
29😡14😱2
"አሜሪካና ምዕራባውያን ቀጠናዊ ቦታዎቻቸውን ኢራንን ለማጥቃት ከተጠቀሙበት ከአካባቢው እናጠፋቸዋለን" - የኢራን አብዮታዊ ዘብ

ኢራን በመካከላቸው ምስራቅ የሚገኙትን የአሜሪካን ወታደራዊ ሰፈሮች ልታጠቃ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

ቴህራን ፕሬዝዳንት ትራምፕ አያቶላህ ኮሚኒን በተመለከተ ያወጡትን ማስጠንቀቂያ አውግዛለች።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሌሊቱን ባወጣው መግለጫ፣ "አሜሪካና ምዕራባውያን ቀጠናዊ ቦታዎቻቸውን ኢራንን ለማጥቃት ከተጠቀሙበት ከአካባቢው እናጠፋቸዋለን" ብሏል።

"እንደዚህ አይነት ድርጊቶች ውጤታቸው ለሌሎች የአካባቢው ሀገራተት አስከፊ ነው" ሲል አስታውቋል። 
#khaamapress

@ThiqahEth
24🤔3🕊2😡1
"ወደፊት በመጥፎ መንገድ ካልሄደ፣ ቲክቶክ አሁን ላይ ጥሩ ቅርጽ ይዟል"  - የአሜሪካው ፕሬዚዳንት

ትራምፕ ለቲክቶክ ተጨማሪ 90 ቀናት ፈቀዱ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክ የተሰኘው የተንቀሳቃሽ ምስል መተግበሪያ "ብሔራዊ ደህንነት ስጋት" ነው በሚል የባይደን አስተዳደር ካገደው በኋላ በ24 ሰዓት ውስጥ በመሻር ወደ አገልግሎት መልሰውታል።

"ወደፊት በመጥፎ መንገድ ካልሄደ፣ ቲክቶክ አሁን ላይ ጥሩ ቅርጽ ይዟል" ሲሉ ተናግረዋል።

ባለቤትነቱ የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ የሆነው ይህ መተግበሪያ በአሜሪካ እንዲታገድ የተወሰነ ቢሆንም፣ ትራምፕ ግን የተወሰነ ድርሻውን ለአሜሪካ መሸጥ እንዳለበት አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንቱ የቲክቶክ መተግበሪያ እንዳይዘጋ ተመሳሳይ ውሳኔ ሲያሳልፉ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።
#nbcnews   #thekoreaherald

@ThiqahEth
9🙏8😱1😡1
የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት ለስድስተኛ ተከታታይ ቀናት ቀጥሏል።

ሁለቱም ሀገራት አንዱ በአንዱ ላይ ሚሳዔል አስወንጭፈዋል።

ሀገራቱ በጥቃታቸው ወታደራዊ ስፍራዎችን እና የኑክሌር ጣቢያዎችን ኢላማ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።
#gulftoday

@ThiqahEth
👏12
THIQAH
Photo
"የተኩስ አቁም ያደረግነው ያለአሜሪካ አሸማጋይነት ነው" - ህንድ

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከፓኪስታን ጋር የነበረው ግጭት እንዲቆም አሜሪካ ያደረገችው አስተዋጽኦ የለም ብለዋል።

"ህንድና ፓኪስታን ከአራት ቀናት ውጊያ በኋላ የተኩስ አቁም ያደረጉት በሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ አመራሮች ውይይት እንጅ በአሜሪካ አሸማጋይነት አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

ትራምፕ ባለፈው ወር የነበረው ግጭት "ሁለቱ የደቡብ እስያ የኑክሌር ታጣቂ ሀገሮች በአሜሪካ አደራዳሪነት ተኩስ አቁመዋል" ብለው ነበር።  

ምንም እንኳን ትራምፕ የሀገራቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ቢገልጹም ሞዲ ግን የሦስተኛ ወገኖች ተሳትፎ አልነበረም ብለዋል።
#asiaone

@ThiqahEth
49👏6😱3
THIQAH
"አሜሪካና ምዕራባውያን ቀጠናዊ ቦታዎቻቸውን ኢራንን ለማጥቃት ከተጠቀሙበት ከአካባቢው እናጠፋቸዋለን" - የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኢራን በመካከላቸው ምስራቅ የሚገኙትን የአሜሪካን ወታደራዊ ሰፈሮች ልታጠቃ እንደምትችል አስጠነቀቀች። ቴህራን ፕሬዝዳንት ትራምፕ አያቶላህ ኮሚኒን በተመለከተ ያወጡትን ማስጠንቀቂያ አውግዛለች። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሌሊቱን ባወጣው መግለጫ፣ "አሜሪካና ምዕራባውያን ቀጠናዊ ቦታዎቻቸውን…
"የአሜሪካ ጥቃት የማይጠገን ውጤት ያስከትላል። ኢራን እጇን አትሰጥም" - አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የኢራን እና የእስራኤል ጦርነት ከተጀመረ በኋላ የመጀመሪያ ንግግር አድርገዋል።

በብሔራዊ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈው ንግግራቸው፣ "ኢራን የአየር ክልሏ እየተጣሰ ዝምታን የምትመርጥበት ምክንያት የለም፣ ወታደራዊ ጣልቃገብነትንም በቸልታ አታልፈውም" ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ እጃቸውን እንዲሰጡ ባስተላለፉት መልዕክት ዙሪያ፣ "ሀገራችን በደማቸው ዋጋ የከፈሉ ሰማዕታትን አታረክስም፣ ኢራን እጇን አትሰጥም" ሲሉ ተደምጠዋል።

ለአሜሪካ ባስተላለፉት የማስጠንቀቂያ መልዕክት፣ "የአሜሪካ ጥቃት የማይጠገን ውጤት ያስከትላል" ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚኒ፣ "በግድ የሚደረግ ጦርነትንም ሆነ በግድ የሚመጣ ሰላም አንፈልግም" ብለዋል።
#outlookindia #telegraph

@ThiqahEth
46🕊7😡3👏2
"የአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ አካባቢውን ወደ አውዳሚ ጦርነት ይወስደዋል" - ሩሲያ

ሩሲያ በኢራንና እስራኤል ጦርነት አሜሪካ ከድርጊቷ እንድትቆጠብ አሳሰበች።

የሩሲያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰርጌ ሬያብኮቭ፣ "የአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ አካባቢውን ወደአውዳሚ ጦርነት ይወስደዋል" ብለዋል።

ሬያብኮቭ፣ "ሞስኮ ከሁለቱም ከእስራኤል እና ኢራን ጋር ውይይት እያደረገች ትገኛለች" ሲሉ ተናግረዋል። 
#yemennewsagency

@ThiqahEth
18👏8😱1😢1
THIQAH
"የህልውና ጉዳይ ስለሆነ እስራኤል አማራጭ የላትም ጦርነቱን ትቀጥላለች" - አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ በኢትዮጵያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የእስራኤልን 58ኛ አመት የነፃነት ቀን ዛሬ አክብሯል። ይህም "የእየሩሳሌም ቀን" ተብሎ ይጠራል። የእየሩሳሌም ቀን ማለት፣ እስራዔላዊያን በአረብ፣ እንግሊዝ፣ ኦቶማን ቱርክ አስተዳደር ስር ከቆየ ከ2000 ዓመታት በኋላ የኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራን ተረክበው ማስተዳደር…
"የእስራኤል ጥቃት በኢራን ሳትቀደም በፊት ቀድሞ የተሰነዘረ እንጂ ኢራንን ማጥፋትን ታሳቢ ያደረገ አይደለም" - በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር

"የጦርነቱ ዓላማ ኢራንን ማጥፋት ሳይሆን እስራኤልን ማዳን ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሤ (ዶ/ር) ትላንት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ?

በተደጋጋሚ "ኢራን የኒኩሊየርና የባለስቲክ ሚሳኤሎች ባለቤት ልትሆን አይገባም። እስራኤል ወደ አውዳሚ ጦርነቱ የገባቸው የህልውና አደጋ ስለተጋረጠባት ነው።

ጦርነቱ ከመፈንዳቱ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል 60 ቀናትን የፈጀ ድርድር ተካሂዷል። ኢራን በድርድሩ ወቅት ሳይቀር እስራኤልን የማጥፋት እቅዷን ለማሳካት እንቅስቃሴ ውስጥ ነበረች።

እስራኤል ራሷን ከመጥፋት ለመታደግ የገባችበት ጦርነት ፍትሃዊ ነው፤ የእስራኤል ጥቃት በኢራን ሳትቀደም ቀድሞ የተሰነዘረ እንጂ ኢራንን ማጥፋትን ታሳቢ ያደረገ አይደለም።

ኢራን እስራኤልን ብቻ ሳይሆን መላው አውሮፓን ሊያወድም የሚችል የኒኩሊየር መሳሪያ ዝግጅት ላይ ነበረች። ኢራን አላማዋ እስራሴልን ማጥፋት እንደሆነ በግልጽ እና በተደጋጋሚ አሳውቃለች። ይህም ከንግግር አልፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ የእስራኤል መንግስት ዜጎቹን ከጥፋት የማዳን ኃላፊነቱን ለመወጣት ወደዚህ ጦርነት ለመግባት ተገዷል" ብለዋል።

ኢራን እስራኤልን ማጥፋት የፈለገችበት ምክንያት ምንድን ነው?" የሚለውን ጥያቄ፤ “ኢራን የኒኩሊየር ባለቤት መሆን የፈለገችው እስራኤልን ለማጥፋት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የድንበር ግጭት የለንም፡፡ ከ2 ሺሕ ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ከሚገኝ ርቀት ተነስተው ከ10 ሚልዮን የሚበልጡ ዜጎችን ከታሪካዊ ቦታቸው ማጥፋት የፈለጉበት ምክንያት ግልጽ አይደለም” ሲሉ መልሰዋል።
#AhaduRadio

(ኢራን መግለጫ ከሰጠች የምናቀርብ ይሆናል)

@ThiqahEth
😡8550🕊4😭3😱2
"መጀመሪያ ሩሲያን አሸማግል ቭላድሚ፤ ለዚህኛው በኋላ ትጨነቃለህ ብየዋለሁ"  ዶናልድ ትራምፕ

ኢራን እና ሩሲያን ለማወያየት ፑቲን ያቀረቡትን ሀሳብ ትራምፕ በስልክ በነበራቸው ውይይት ተቀብለውት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ውድቅ አድርገውታል።

ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን ላቀረቡት የድርድር ጥያቄ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።

ትናንት አውርተን ነበር ያሉት ትራምፕ፣ "አንድ ነገር አድርግልኝ፣ መጀመሪያ ሩሲያን አሸማግል ቭላድሚር፣ ስለዚህኛው በኋላ ትጨነቃለህ ብየዋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ሩሲያ እና ኢራን ያላቸው ጥልቅ ወታደራዊ ትብብር የሩሲያን ገለልተኝነት ሁኔታ አጠራጣሪ አድርጎታል ተብሏል። 
#kyivindependent

@ThiqahEth
21😡1
ውድ እና የምናከብራችሁ ቤተሰቦቻችን አላስፈላጊ፣ ጸብ አጫሪ ንግግሮች እየተበራከቱ በመሆናቸው የአስተያየት መስጫውን ለጊዜው መዝጋታችንን በአክብሮት አሳወቅን።

@ThiqahEthFamily ይቅርታ🙏
👏113🙏7🕊4😡32😭1
"ጦርነቱ በእርግጠኝነት በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል" - ዞሃር ፓልቲ

ፐየቀድሞው የሞሳድ ዳይሬክተር"ጦርነቱ በቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል" ማለታቸው ተሰምቷል።

የቀድሞው የእስራኤል ኢንተሊጀንስ ሀላፊ ዞሃር ፓልቲ እስራዔል ኢራንን በተመለከተ ምን ልታደርግ እንደምትችል ቀድሞም የታወቀ ነገር ነው ብለዋል።

"ከጠረጴዛ የተሰወረ ምንም ነገር የለም" ያሉት ፓልቲ "ጦርነቱ በእርግጠኝነት በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል" ሲሉ ተናግረዋል። 
#skynews

ፓልቲ ምንን ተንተርሰው ለዚህ ንግግራቸው እርግጠኛ እንደሆኑ አልታወቀም።

@ThiqahEth
25😡5
THIQAH
"የአሜሪካ ጥቃት የማይጠገን ውጤት ያስከትላል። ኢራን እጇን አትሰጥም" - አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የኢራን እና የእስራኤል ጦርነት ከተጀመረ በኋላ የመጀመሪያ ንግግር አድርገዋል። በብሔራዊ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈው ንግግራቸው፣ "ኢራን የአየር ክልሏ እየተጣሰ ዝምታን የምትመርጥበት ምክንያት የለም፣ ወታደራዊ ጣልቃገብነትንም በቸልታ አታልፈውም" ብለዋል። ፕሬዝዳንት…
"ኢራን ስህተት ሰራች" - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ ለአያቶላህ ኮሚኒ አስተያየት ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኮሚኒ ከሰዓታት በፊት በብሄራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው "ኢራን እጅ አትሰጥም"  ካሉ በኋላ አሜሪካ በጦርነቱ ከተሳተፈች "የማይጠገን ውድመት ይደርሳል" ብለው ነበር።

ትራምፕ ለኮሚኒ ንግግር "መልካም እድል  ብያለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

"60 ቀን ነበራቸው ስህተት ሰርተዋል" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
#timesofindia

@ThiqahEth
33😡8😱4🕊1
ህንድ ዜጎቿን ከኢራን ማስወጣቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ አስታወቀ።

የህንድ መንግስት "ዘመቻ ሲንዱ" ሲል በጠራው ዘመቻ ከእስራኤል ጋር በጦርነት ላይ ከምትገኘው ኢራን ዜጎቹን አስወጥቷል።

እስካሁን 110 ህንዳውያን ከኢራን መውጣታቸውን የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጧል።
#dna

ዜጎቹ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተመለሱት እስራኤልና ኢራን እየተሰናዘሩት ባለው አውዳሚ ጦርነት ባደረባው ስጋት ነው።


@ThiqahEth
14😡3🕊2