THIQAH
9.38K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
በሎስ አንጀለስ ከ150 በላይ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞችን ፍሰት ለመቆጣጠር 2000 ብሄራዊ ዘብ ወደ ሎስ አንጀለስ ልከዋል።

ድርጊቱን የተቃወሙ ስደተኞች ወደ ስፍራው ከተላኩት ፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ተቃዋሚዎቹ የፌዴራል ኢሚግሬሽን ባለስልጣናትን ስም እየጠሩ ትችት ያዘለ መልዕክት ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል።

ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተገልጿል።
#cnn

@ThiqahEth
👏1912😱4😢2
"እኛን ማጥቃት የሚፈልግ፣ ሩሲያም ትሁን ሌላ መዘዙ አስከፊ ነው" - ማርክ ሩቴ

የኔቶን በጀት በ400% ማሳደግ ይገባል ተባለ።

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (NATO) "እየጨመሩ መጥተዋል" ያላቸውን ስጋቶች ለመቀነስ የአየር እና የሚሳዔል አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ዋና ፀሐፊው ማርክ ሩቴ ተናግረዋል።

ሩቴ በለንደን ቻታም ሀውስ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ስጋቶች በተለየ መልኩ ከሩሲያ እና ቻይና እንደሚመነጩ ተናግረዋል።

ዋና ፀሐፊው፣ "ኔቶ በአንድ አመት የሚያመርተውን የመሳሪያ አቅም ሩሲያ በሶስት ወር እያመረተችው ነው" ሲሉ በንፅፅር አስረድተዋል።

ነገር ግን "እኛን ማጥቃት የሚፈልግ፣ ሩሲያም ትሁን ሌላ መዘዙ አስከፊ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። 
#anadoluagency

@ThiqahEth
14🤔3🕊3😢1🙏1😡1
THIQAH
Video
"በወታደራዊ ስምሪቱ ዙሪያ የግዛቲቱ አመራሮች እውቅና የላቸውም " - ካሊፎርኒያ

የካሊፎርኒያ ገዥ ትራምፕ ወታደሮችን ወደ ሎስአንጀለስ መላካቸውን ተቃወሙ።

የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሶም "ወታደሮቹ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ሳይሟላ ነው የመጡት ምግብ፣ መጠጥ እና መጠለያ የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

"ወታደሮቹ ወለል ላይ ነው የሚተኙት" ያሉት ኒውሶም "ይህ ደግሞ ክብር ነክ እርምጃ ነው" በማለት ውሳኔውን ተቃውመዋል።

በወታደራዊ ስምሪቱ ዙሪያ የግዛቲቱ አመራሮች እውቅና የላቸውም ብለዋል።


ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞችን ፍሰት ለመቆጣጠር በሚል 2000 ብሄራዊ ዘብ ወደ ሎስ አንጀለስ ላኩ መባላቸው ይታወሳል።

በዚህም ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ሲወስድ ተስተውሏል
#indiatoday

@ThiqahEth
17😢1🕊1
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ።

ጋዜጠኛ ተስፋለም እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን "ኢትዮጵያን ኢንሳይደር" አሳውቋል።

(ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)
#EthiopianInsider

@ThiqahEth
😭94👏1🙏1🕊1
በኦስትሪያ ትምህርት ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከሟቾች በተጨማሪ 30 ሰዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የግራዝ ከተማ ከንቲባ ኤልኬ ካህር ተናግረዋል።

ጥቃቱ የተከፈተው በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ሲሆን፣ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ ወዲያውኑ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።
#upi

@ThiqahEth
😢52💔2😭1
THIQAH
የእስራኤል ጦር ግሬቴ ተንበርግን የያዘችውን መርከብ አገደ። መርከቧ ወደ ጋዛ ለመግባት 200 ኪሎሜትር ሲቀራት እንድትቆም መደረጓ ተገልጿል። መርከቧ ከተንበርግ በተጨማሪ ሌሎች 12 የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ይዛለች ተብሏል። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ግሬታ ተንበርግን እና የሰብዓዊ እርዳታ የጫነችው መርከብ ወደ ጋዛ እንዳትገባ ለእስራኤል ጦር ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ ማለታቸው…
#Update

የመብት ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ ከእስራኤል መውጣቷ ተገለጸ።

የአካባቢ ጥበቃ አክቲቪስት ተንበርግ ወደ ስዊድን እንድትመለስ ማድረጉን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ግሬታ ተንበርግ ከሌሎች 3 ሰዎች ጋር በመሆን ወደቤንጉሪን አየርመንገድ መሸኘታቸውን አስታውቋል።

አንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባልና ሌሎች 8 የሚደርሱት ደግሞ የመመለሻ ፎርሙን (Deportation paperwork) ለመሙላት ፍላጎት አላሳዩም ብሏል።

አክቲቪስት ተንበርግ ከሌሎች 11 የመብት ተሟጋቾች ጋር በመሆን የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ጋዛ በሚገቡበት ወቅት በእስራኤል ጦር ተይዘው ነበር። 
#foxnews

@ThiqahEth
12👏1🙏1
እንግሊዝ በፍልስጤማውያን ላይ "ግጭት በማስነሳት" ኬዝ በሁለት የእስራኤል ሚኒስትሮች ማዕቀብ ጣለች።

ማዕቀብ የተጣለባቸው የፍልስጤምን የሀገርነት እውቅና ፈፅሞ የማይቀበሉ ናቸው የተባሉትን የእስራኤል ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤንግቪር እና የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች ናቸው።

በዚህም የእንግሊዝ መንግስት "በዌስት ባንክ በሚገኙ ፍልስጤማውያን ላይ ግጭት በማስነሳት" ኬዝ ማዕቀቡ እንደተጣለባቸው ገልጿል።

ማዕቀቡ ወደ እንግሊዝ እንዳይገቡ ከማድረግ በተጨማሪ በእንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል።

በሚኒስትሮቹ ላይ ከእንግሊዝ በተጨማሪ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድ እና ኖርዌይ ማዕቀብ የጣሉ ሀገራት ናቸው። 
#skynews

@ThiqahEth
46😡6👏5
THIQAH
"በወታደራዊ ስምሪቱ ዙሪያ የግዛቲቱ አመራሮች እውቅና የላቸውም " - ካሊፎርኒያ የካሊፎርኒያ ገዥ ትራምፕ ወታደሮችን ወደ ሎስአንጀለስ መላካቸውን ተቃወሙ። የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሶም "ወታደሮቹ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ሳይሟላ ነው የመጡት ምግብ፣ መጠጥ እና መጠለያ የለም" ሲሉ ተናግረዋል። "ወታደሮቹ ወለል ላይ ነው የሚተኙት" ያሉት ኒውሶም "ይህ ደግሞ ክብር ነክ እርምጃ ነው" በማለት ውሳኔውን ተቃውመዋል።…
"በካሊፎርኒያ ያስተዋልነው በሰላምና ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ጥቃትን ነው" - ትራምፕ

የትራምፕ ውሳኔ "ስልጣንን ያለ አግባብ የመጠቀምና የፀብ አጫሪነት ድርጊት ነው" - ካሊፎርኒያ

ትራምፕ የአሜሪካ ጦር የተመሰረተበትን ቀን ለማክበር በሰሜን ካሮላይና ይገኛሉ።

ፕሬዚደንቱ ባደረጉት ንግግር፣ "ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው" በሚል ተቃውሞ ያስከተለባቸውን በሎስአንጀለስ ያደረጉት ወታደራዊ ስምሪት ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።

"የዚህ ትውልድ ጀግና ወታደሮች በወራሪዎች እና በሦስተኛ ወገን ህግ አልባዎች ደማቸውን አያፈሱም" ብለዋል።

"በካሊፎርኒያ ያስተዋልነው በሰላምና ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ጥቃትን ነው፣ አመጸኞች የውጭ ባንድራን ሲያውለበልቡ ነው" ብለው፣ "መንግስት ሎስአንጀለስን ነፃ ያወጣል" በማለት ተናግረዋል።

ወታደሮቹ የተሰማሩት የፌዴራል ንብረት እና ዜጎችን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ዴሞክራቱ የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ የትራምፕን ውሳኔ "ስልጣንን ያለ አግባብ የመጠቀምና የፀብ አጫሪነት ድርጊት ነው" በማለት አውግዞታል።
#asiaone

@ThiqahEth
7🙏6🤔2
#Tigray

"ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፣ አንወጣም" - የፕሬዝዳንቱን ጽ/ቤት ጥሰው የገቡ ተፈናቃዮች

ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱ ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው መግባታቸውን ዲደብልዩ ዘግቧል።

በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱት በትግራዩ ጦርነት ከምዕራብ ትግራይና ሌሎች የኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ መንግስት ወደ ቀያችን እንዲመልስን ብንጠይቅም ምላሽ አጥተናል ሲሉ በምሬት ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ፣ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት ከፅሕፈት ቤቱ በራፍ ቆመው ምላሽ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ እንደቆዩ፣ ረፋዱ ላይም የክልሉን ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ግቢ ጥሰው እንደገቡ ተመልክቷል።

"ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፥ ከዚህ አንወጣም" ማለታቸውን
#DW ዘግቧል።

@ThiqahEth
👏216😭6🕊3😱1
THIQAH
"ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" - ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለዲሞክራቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዳያደርግ አስጠነቀቁ። "ለድሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ሲሉ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንቱ ይገጥመዋል ስላሉት አደጋ በዝርዝር አልተናገሩም። #nbcnews #aa @ThiqahEth
"በትራምፕ ጉዳይ የፃፍኳቸው አንዳንድ አስተያየቶች ይጸጽቱኛል" - ኤለን መስክ

ቢሊየነሩ መስክ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ትራምፕን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰፈርኳቸው ፅሑፎች "በጣም የተጋነኑ ነበሩ" አሉ።

"በትራምፕ ጉዳይ የፃፍኳቸው አንዳንድ አስተያየቶች ይጸጽቱኛል" ያሉት መስክ፣ ለጸጸት የዳረጋቸው የትኛው አስተያየት እንደሆነ በግልጽ ባይናገሩም የተወሰኑትን አጥፍቷቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው፣ ከኤለን መስክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት "ያበቃ ጉዳይ ነው" ቢሉም "የተለየ ችግር የለብኝም" ብለዋል።

ትራምፕና መስክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እርስበርስ አወዛጋቢ አስተያየቶችን ተለዋውጠው ነበር።
#timeslive

ከመንግስታዊ ኃላፊነት የተነሱት መስክ ትራምፕ በተለያዩ ሀገራት ላይ የሚያሳልፉትን የታሪፍ ውሳኔ "አስቀያሚ ነው። የአሜሪካን ኢኮኖሚ ይበልጥ ያዳክመዋል" በሚል፤ የዋይትሐውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት፣ "አስተያየቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ውሳኔ አይቀይረውም"በሚል የመጀመሪያ ትችት ተወራውረው ነበር።

እንዲሁም ትራምፕ፣ "ከኤለን መስክ ጋር የተፈጸሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን እንሰርዛለን" ሲሉ፣ መስክ ደግሞ "ትራምፕ ያለ እኔ እገዛ ምርጫ አያሸንፍም ነበር" በመባባል ተቃቅረው ነበር።

ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ሁለቱ አካላት ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው፣ የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ በ150 ቢሊዮን ዶላር መቀነሱም ከሳምንት በፊት ተዘግቦ ነበር።

በኋላም ትራምፕ መስክን፣ "ለዲሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ብለው ነበር።

@ThiqahEth
16🕊3😭3🤔2😱1
የኬንያ ባንኮች ብድር የማይመልሱ ግለሰቦች መበራከታቸውን ተከትሎ ለኪሳራ መጋለጣቸው ተገለጸ።

የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ (CBK) 10% የነበረውን የወለድ መጠን ከጥር 2025 ጀምሮ ወደ 9.5 ዝቅ አድርጓል።

በሀገሪቱ የሚገኙ የንግድ ባንኮች የሚያቀርቡትን ብድር በ15.4% ቀንሰዋል ተብሏል።
#tukonews

@ThiqahEth
11🤔2😱2😢2