THIQAH
9.38K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
"የዩክሬኑ መሪ ሰላም ይፈልጋል ብየ አላስብም" - ፑቲን

"ውይይት አድርገናል፣ ግን ወደ ሰላም የሚያመራ አይደለም" - ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ፑቲንና የአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ሰዓት በላይ የቆየ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ሁለቱም ወገኖች ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን በቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቿ ላይ ላደረሰችው ጥቃት ሩሲያ እርምጃ እንደምትወስድ ለትራምፕ አሳውቀዋቸዋል።

"የዩክሬኑ መሪ ሰላም ይፈልጋል ብየ አላስብም" ያሉት ፑቲን፣ ትላልቅ መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን ተናግረዋል።

ትራምፕ በበኩላቸው፣ ከፑቲን ጋር መወያየታቸውን ገልጸው፣ "ዩክሬን ስላደረሰችው ጉዳት ተወያይተናል፣ ግን ወደ ሰላም የሚያመራ አልነበረም" ብለዋል።

ትራምፕ፣ "ፑቲን በቅርቡ ለተፈጸመው ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ በጥብቅ ነግሮኛል" ሲሉ ገልጸዋል።

ኪቭ እሁድ'ለት ከ100 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የሩሲያ አየር ሀይል ላይ ጥቃት አድርሳለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱ ሀገራት በጥቃቱ ማግስት ባሳለፍነው ሰኞ በቱርክ ውይይት አድርገዋል። 
#thejapantimes

@ThiqahEth
14😢7
THIQAH
Photo
ዶናልድ ትራምፕ የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ቪዛ እገዳ መመሪያን በፊርማቸው አጸደቁ።

መመሪያው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሁንም በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ቪዛ እንዲያግድ ስልጣን የሚሰጥ ነው ተብሏል።

የትራምፕ አስተዳደር በቅርቡ ለሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ሲሰጥ የነበረውን 450 ሚሊዮን ዶላር በጀት አቋርጧል።

እርምጃውን ያወገዘው ዩኒቨርስቲውም የትራምፕን አስተዳደር በፍርድ ቤት እንደሚከስ አስታውቋል።

አሜሪካ በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ለተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ ከአንድ ሳምንት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ አሳስቦ ነበር። 
#telegraphindia

@ThiqahEth
😢12🤔32🕊2
ሳዑዲ አረቢያ ያለፍቃድ የሄዱ 269,678 የሃጂ ተጓዦችን ወደ መካ እንዳይገቡ አገደች።

ከታገዱት መካከል "23,000 የሚሆኑት የሳዑዲ ዜጎች ናቸው" ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ሳዑዲ 400 የሀጂ ጉዞ አዘጋጅ ካምፓኒዎችን ፍቃድ ሰርዛለች።

በዘንድሮው የሀጂ ጉዞ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ተጓዦች መሳተፋቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በዚህ አመታዊ ሃይማኖታዊ በዓል ወቅት በየአመቱ ህጋዊ ያልሆኑ ተጓዦች ወ ደሳዑዲ እንደሚገቡ ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። 
#thenewarab

@ThiqahEth
😢106💔1😡1
"በአየርላንድ ያለፍቃድ ለሚኖሩ ሁሉ ግልጽ መልዕክት ነው" - ጂም ኦካላጋን

አየርላንድ 25 የናይጄሪያውያ ዜጎችን ወደሀገራቸው መለሰች።

የአየርላንድ የፍትህ ሚኒስትር ጂም ኦካላጋን "አየርላንድ የምታስተናግደው ህግን መሰረት ያደረገ ፍልሰት ብቻ ነው" ብለዋል።

አየርላንድ 2025 ከገባ በኋላ "ህጋዊ አይደሉም" ያለቻቸውን 106 ናይጄሪያውያንን ወደሀገራቸው መልሳለች።

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት ውስጥ 5 ህፃናት፣ 21 ወንዶችና 9 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። 
#breakingnewsie

@ThiqahEth
7😢3🕊1😡1
THIQAH
የትራምፕ አስተዳደር በ12 ሀገራት ላይ ሙሉ በሙሉ በ7 ሀገራት ላይ ደግሞ ከፊል እገዳ ጣለ። ትራምፕ "የውጭ ሽብርተኞችን" ለመከላከል የውጭ ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በሚል የወጣው አዋጅ ላይ ፈርመዋል። በዚሁ መሠረት ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ማይናማር እና ሄይቲ ሙሉ ለሙሉ እገዳ የተጣለባቸው ናቸው።  ከፊል እገዳ…
"የአሜሪካ ውሳኔ ያሳስበኛል" - የአፍሪካ ህብረት

የአፍሪካ ህብረት የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ያሳለፈውን የጉዞ እግድ ውሳኔ ተቃውሞታል።

ህብረቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ "ሚዛናዊ አካሄድና ገንቢ ውይይት" እንዲደረግ ጠይቋል።

መመሪያው በአፍሪካና በአሜሪካ መካከል ያለውን የግለሰቦች ግንኙነት እና የንግድ ልውውጥ ይጎዳል ብሏል።

የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካን ሉዓላዊ መብት እና የዜጎችን ደህንነት እንደሚያከብር በመግለጫው ጠቅሷል። 
#yen

@ThiqahEth
🙏154🕊4👏2😭2😡1
"ሂዝቦላ ከመሰረተ ልማቶች ቀጥሎ የመሸገው እናንተ ውስጥ ነው"  - እስራኤል

እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አቪቻይ አድራየ በሀዳት፣ ሀረት ኸሪክ እና ቡርጂ አልባራን የሚገኙ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

"ሂዝቦላ ከመሰረተ ልማቶች ቀጥሎ የመሸገው እናንተ ውስጥ ነው" ብለዋል ቃል አቀባዩ።

በእስራኤልና ሊባኖስ መካከል ባሳለፍነው ህዳር ወር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ላለፉት ሰባት ወራት አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ የእስራኤል ጦር ከሂዝቦላህ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል። 
#aljazeera

@ThiqahEth
12😡6
ቻድ ለአሜሪካ ዜጎች የቪዛ አገልግሎት አገደች።

እርምጃው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰባት የአፍሪካ ሀገራት ላይ ላሳለፉት ውሳኔ የአፀፋ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ማህማት እንድሪስ "ቻድ የምትሰጠው ቢሊዮን ዶላርም ሆነ እቅድ የላትም፣ ነገር ግን የራሷ ክብርና ኩራት ያላት ሀገር ናት" ሲሉ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዱላሂ ሳብሬ በበኩላቸው፣ በውሳኔው መገረማቸውን ገልጸው፣ በተለይ ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ መሆኑ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።
#nzherald

@ThiqahEth
👏576🤔3😢2
እንኳን 1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።

ቲቃህ ኢትዮጵያ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ የእምነቱ ተከታዮችን በዓል ለምትጋሩ ወዳጆች በሙሉ መልካም በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ ይመኛል።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!

@ThiqhEth
22👏2🙏1🕊1
"ከኤለን መስክ ጋር የተፈፀሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን እንሰርዛለን" - ዶናልድ ትራምፕ

"ትራምፕ ያለ እኔ እገዛ ምርጫ አያሸንፍም ነበር" - ኤለን መስክ

የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ በ150 ቢሊዮን ዶላር ቀንሷል።

ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ፕሬዝዳንቱና ባለሀብቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የገቡበት ውዝግብ የቴስላን ኩባንያ ለኪሳራ ዳርጓል።

የዓለም ቁጥር አንድ ባለሀብቱ መስክ ፕሬዝዳንት ትራምፕን "ያለ እኔ ድጋፍ ምርጫ ማሸነፍ አይችሉም ነበር" ብሏቸዋል።

"የትራምፕ አስተዳደር በታሪፍ ጭማሪ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የአሜሪካን ኢኮኖሚ እየጎዳ መጥቷል" በማለትም ተችቷል።

ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ ለኤለን መስክ ድጎማ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

"በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭዎችን ለመቆጠብ ከኤለን መስክ ጋር የተፈጸሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን መሰረዝ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

በትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ትልቅ ድጋፍ ያደረገው መስክ በፕሬዚዳንቱ አስተዳደር ሹመት እስከማገኘት ደርሷል።  
#timeslive #theirishtimes

@ThiqahEth
22👏10🕊2😭2🤔1
ሩሲያ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 4 ዩክሬናውያን ሲገደሉ 53 ቆሰሉ።

የኪቭ ከተማ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የዘለቀው የሩሲያ ጥቃት በዋናነት የኢንደስትሪ ማዕከላትን ኢላማ ያደረገ ነው ብለዋል።

ሞስኮ በእነዚህ ሁለት ቀናት ከ500 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ኪቭ ማስወንጨፏን ከንቲባው ገልጸዋል።
#upi

@ThiqahEth
👏154🕊4😭3😱2
"ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ አይደለም" - አሜሪካ

"ማዕቀቡ በግፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው" - የአውሮፓ ህብረት

አሜሪካ "ገለልተኛ ተቋም አይደለም" ባለችው በአለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አራት ዳኞች ላይ ማዕቀብ ጣለች።

ዳኞቹ በአሜሪካ የሚገኝ ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል።

የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ፣"ማዕቀቡ በግፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው" ሲል ማዕቀቡን ተችቷል።

ህብረቱ "የዳኝነት ባለሙያዎቹ ያለጫና በነፃነት መስራት ይኖርባቸዋል" ሲል የአሜሪካን ውሳኔ ተቃውሟል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ላይ ያወጣውን የእስር ማዘዣ ተቃውመዋል።  
#france24

@ThiqahEth
😢138👏6🤔3🙏1