THIQAH
9.38K subscribers
5.12K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 21 ንጹሐን በግፍ ተገደሉ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (HRW) በጎማ ከተማ የ11 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን አስታውቋል።

ድርጅቱ ግድያውን የፈጸመው በሩዋንዳ የሚደገፈው አማፂው የኤም 23 ቡድን ነው ብሏል።
#africannews

@ThiqahEth
😭124
በቱርክ ተከሰተ በተባለ መሬት መንቀጥቀጥ ከ70 በላይ ሰዎች ተጎዱ።

በቱርክ በሬክተር ስኬል 5.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተሰምቷል።

ድንገት በተከሰተው አደጋ ከ70 በላይ የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውንም የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አደጋው የተከሰተው በሀገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ በምትገኘው የማርማሪስ ክልል መሆኑ ተገልጿል። 
#dailyausaf

@ThiqahEth
😢142🕊2
"አስቀያሚ ነው" - ኤለን መስክ

"አስተያየቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ውሳኔ አይቀይረውም" - ዋይትሐውስ

ቢሊየነሩ መስክና ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጀመሪያ ትችት አዘል ሀሳብ ተለዋወጡ።

በቅርቡ ከመንግስታዊ ሀላፊነት የተነሱት መስክ ትራምፕ በተለያዩ ሀገራት ላይ የሚያሳልፉትን የታሪፍ ውሳኔ "አስቀያሚ" ሲሉ ወቅሰዋል።

ቢሊየነሩ የቴስላ ባለቤት ታሪፉ "የአሜሪካን ኢኮኖሚ ይበልጥ ያዳክመዋል" ብለዋል።

ከመስክ ለቀረበው ወቀሳ ምላሽ የሰጡት የዋይትሐውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት "ፕሬዝዳንት ትራምፕ መስክ ምን ለማለት እንደፈለገ ይገባቸዋል" ብለዋል።

"አስተያየቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ውሳኔ አይቀይረውም" ሲሉም አክለዋል።  
#outlookus

@ThiqahEth
10🤔4👏3😢2
THIQAH
Photo
#Update

ሊ ጃይ ምዩንግ አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በትናንትናው እለት ምርጫ ባካሄደችው ሴዑል የሊበራል ፓርቲው ሊቀመንበር ምዩንግ ማሸነፍ ችለዋል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት በወታደራዊ አስተዳደር (martial law) ምክንያት የመልካም አስተዳደር ስርዓት መሸርሸር ታይቶባታል ለተባለችው ደቡብ ኮሪያ ድሞክራሲን ያሰፍናሉ የሚል ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
#asiaone

@ThiqahEth
11👏4🕊3
በፓኪስታን ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ።

በፓኪስታን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ከአደጋው ለማምለጥ የሞከሩ ሰዎች እስርቤቱን ሰብረው መውጣታቸው ተገልጿል።

በካራቺ ከተማ በተከሰተው አደጋ በድምሩ 216 እስረኞች አምልጠው የነበረ ሲሆን 78 ቱን መመለስ መቻሉን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

እስረኞች ለማምለጥ ሲሞክሩ በነበረ የተኩስ ልውውጥ አንድ ታራሚ ሲሞት ሶስት ሶስት ፖሊሶች ቆስለዋል ተብሏል።
#thenation

@ThiqahEth
👏65😢2🕊2
የአሜሪካ ደህንነት ቢሮ (FBI)፣ "የግብርና ሽብርተኝነት" ፈጽመዋል ያላቸውን ሁለት ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አዋለ።

ቢሮው ቻይናውያኑ ዜጎች ወደ አሜሪካ በሽታ አስተላላፊ ፈንገስ በማስገባታቸው እንደተያዙ አስታውቋል።

የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ በበኩሉ፣ ተህዋሱ በግብርና ምርቶች ላይ በሽታ የሚያመጣ እና ምርትን የሚጎዳ መሆኑን አጣርቶ እንደደረሰበት አስታውቋል።

ፍትህ ቢሮው በሽታ አምጭው ተህዋስ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኢኮኖሚያዊ ውድመት ያስከትላል ብሏል።
#telegraphindia

@ThiqahEth
🤔169🕊4
"የኑክሌር ምርት የብሄራዊ ክብር ጉዳይ ነው" -  ኢራን

የኢራን መሪ አያቶላህ ኮሚኒ በኑክሌር ጉዳይ አሜሪካ ያቀረበችውን እቅድ ውድቅ አደረጉ።

ለአምስት ዙር በቀጠለው የሁለቱ ሀገራት ውይይት ዋሽንግተን ኢራን የዩራኒየም ምርቷን እንድታቆም ጠይቃለች።

ይህን ተከትሎ ኮሚኒ በሰጡት አስተያየት ከአሜሪካ በኩል የቀረበው እቅድ "100% ተቃራኒ ነው" ብለዋል።

በኦማን አሸማጋይነት የተደረጉት ውይይቶች ያለስምምነት መጠናቀቃቸው ተገልጿል።
#foxnews

@ThiqahEth
25👏5🤔3🕊2
"እቅዱ አሜሪካ እያደረገች ያለውን የሰላም ጥረት ከግምት ያላስገባ ነው" - ድሮቲ ሺያ

"ያቀረባችሁት ወደ ሰላም የሚወስደንን ሳይሆን ለሽብርተኝነት እድል የሚሰጥ እቅድ ነው"  - እስራኤል

የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረበው እቅድ በአሜሪካ ውድቅ ተደረገ።

ምክርቤቱ ያቀረበው "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ ዘላቂ የተኩስ አቁም" እቅድ ከአሜሪካ ውጭ 14ቱ ሀገራት የድጋፍ ድምጽ ሰጥተውበታል።

በተመድ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ ድሮቲ ሺያ፣ "እቅዱ አሜሪካ እያደረገች ያለውን የሰላም ጥረት ከግምት ያላስገባ ነው" ሲሉ ተችተዋል።

የእንግሊዝ ቋሚ መልዕክተኛ ባርባራ ውድዋርድ በበኩላቸው የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ የሚያደርገውን ወታደራዊ መስፋፋት ተቃውመዋል።

የእስራኤል መልዕክተኛ ዳኒ ዳኖን "ያቀረባችሁት ወደ ሰላም የሚወስደንን ሳይሆን ለሽብርተኝነት እድል የሚሰጥ እቅድ ነው" ሲሉ ነቅፈዋል። 
#asiaone

@ThiqahEth
9😡9🤔6👏4😱1🙏1
የትራምፕ አስተዳደር በ12 ሀገራት ላይ ሙሉ በሙሉ በ7 ሀገራት ላይ ደግሞ ከፊል እገዳ ጣለ።

ትራምፕ "የውጭ ሽብርተኞችን" ለመከላከል የውጭ ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በሚል የወጣው አዋጅ ላይ ፈርመዋል።

በዚሁ መሠረት ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ማይናማር እና ሄይቲ ሙሉ ለሙሉ እገዳ የተጣለባቸው ናቸው። 

ከፊል እገዳ የተጣለባቸው ደግሞ ቡርንዲ፣ ሴራሊዮን፣ ቶጎ፣ ኩባ፣ ሌኦስ፣ ቱርኪሚስታን  እና ቬንዙዌላ ናቸው።
#timeslive

@ThiqahEth
👏103🕊2😢1
"የዩክሬኑ መሪ ሰላም ይፈልጋል ብየ አላስብም" - ፑቲን

"ውይይት አድርገናል፣ ግን ወደ ሰላም የሚያመራ አይደለም" - ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ፑቲንና የአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ሰዓት በላይ የቆየ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ሁለቱም ወገኖች ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን በቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቿ ላይ ላደረሰችው ጥቃት ሩሲያ እርምጃ እንደምትወስድ ለትራምፕ አሳውቀዋቸዋል።

"የዩክሬኑ መሪ ሰላም ይፈልጋል ብየ አላስብም" ያሉት ፑቲን፣ ትላልቅ መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን ተናግረዋል።

ትራምፕ በበኩላቸው፣ ከፑቲን ጋር መወያየታቸውን ገልጸው፣ "ዩክሬን ስላደረሰችው ጉዳት ተወያይተናል፣ ግን ወደ ሰላም የሚያመራ አልነበረም" ብለዋል።

ትራምፕ፣ "ፑቲን በቅርቡ ለተፈጸመው ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ በጥብቅ ነግሮኛል" ሲሉ ገልጸዋል።

ኪቭ እሁድ'ለት ከ100 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የሩሲያ አየር ሀይል ላይ ጥቃት አድርሳለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱ ሀገራት በጥቃቱ ማግስት ባሳለፍነው ሰኞ በቱርክ ውይይት አድርገዋል። 
#thejapantimes

@ThiqahEth
14😢7
THIQAH
Photo
ዶናልድ ትራምፕ የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ቪዛ እገዳ መመሪያን በፊርማቸው አጸደቁ።

መመሪያው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሁንም በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ቪዛ እንዲያግድ ስልጣን የሚሰጥ ነው ተብሏል።

የትራምፕ አስተዳደር በቅርቡ ለሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ሲሰጥ የነበረውን 450 ሚሊዮን ዶላር በጀት አቋርጧል።

እርምጃውን ያወገዘው ዩኒቨርስቲውም የትራምፕን አስተዳደር በፍርድ ቤት እንደሚከስ አስታውቋል።

አሜሪካ በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ለተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ ከአንድ ሳምንት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ አሳስቦ ነበር። 
#telegraphindia

@ThiqahEth
😢12🤔32🕊2
ሳዑዲ አረቢያ ያለፍቃድ የሄዱ 269,678 የሃጂ ተጓዦችን ወደ መካ እንዳይገቡ አገደች።

ከታገዱት መካከል "23,000 የሚሆኑት የሳዑዲ ዜጎች ናቸው" ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ሳዑዲ 400 የሀጂ ጉዞ አዘጋጅ ካምፓኒዎችን ፍቃድ ሰርዛለች።

በዘንድሮው የሀጂ ጉዞ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ተጓዦች መሳተፋቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በዚህ አመታዊ ሃይማኖታዊ በዓል ወቅት በየአመቱ ህጋዊ ያልሆኑ ተጓዦች ወ ደሳዑዲ እንደሚገቡ ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። 
#thenewarab

@ThiqahEth
😢106💔1😡1