THIQAH
9.39K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
"ከ30 በላይ እርዳታ ፈላጊዎች በእስራኤል ተገድለዋል" - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር

"የደረሰ ጉዳት የለም፣የእርዳታ ስርጭቱ በሰላም ተጠናቋል" - የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን

የእስራኤል ጦር በራፋህ የእርዳታ ጣቢያ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ንፁሃን ላይ ጥቃት ማድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 170 የሚደርሱት መጎዳታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን (GHF) በበኩሉ ደረሰ የተባለውን ጉዳት "በእርዳታ ወቅት ሰዎች በስነስርዓቱ ተከፋፍለው ሂደዋል" በማለት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ማስተባበያ ሰጥቷል።

የእስራኤል ጦርም በተመሳሳይ "በንፁሃን ላይ የተቃጣ እርምጃ የለም" ሲል የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

አንድ የአይን እማኝ ግን "የእስራኤል ወታደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ እርዳታ ጠባቂዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር" በማለት ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ሆስፒታል ላይ በፈፀመችው ጥቃት 54 ሰዎች መገደላቸውንና የኩላሊት መታጠቢያ ማሽንን ሙሉ በሙሉ ማውደሟን ተመድ አስታውቋል።
#cnn #aljazeera

@ThiqahEth
😢21😡43🙏3🕊2😱1
ካሮል ናውሮኪ የፖላንድን ብሄራዊ ምርጫ አሸነፉ።

"የፖለቲካ ልምድ የላቸውም" የሚባሉት "ቀኝ ዘመሙ" የታሪክ ባለሙያ ናውሮኪ አዲሱ የፖላንድ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

የ42 አመቱ ናውሮኪ 50.89% ድምፅ በማግኘት ነው ምርጫውን ማሸነፍ የቻሉት።
#indiatoday

@ThiqahEth
🕊43🙏2😱1
#Update

በናይጄሪያው ጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ200 እንዳሻበቀ፣ 500 ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ፣ የሟቾች ብዛት 700 እንደሚደርስ ተነገረ።

በናይጄሪያዋ ሞካዋ ከተማ በጎርፍ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ እንደሆነ፣ ቁጥሩ እስከ 700 እንደሚደርስ ቢቢሲ ዘግቧል።

ዘገባው፣ “እስካሁን 500 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሕይወት የሚገኝ ሰው ከዚህ በኋላ አይኖርም በሚል እምነት የነፍስ አድን ጥረቱ ተቋርጧል” ብሏል።

በአካባቢው ተላላፊ በሽታ እንዳይዛመት በጎርፉ የተቀበሩ ግለሰቦችን ቆፍሮ በማውጣት ተገቢው የቀብር ሥነ ሥርዓት ማከናወን በቅርቡ እንደሚጀመር የሞካዋ አካባቢ አስተዳዳሪ ሙሐመዱ አሊዩ ተናግረዋል።

ባለቤቱ እና ጨቅላ ልጁ በጎርፍ የተወሰዱበት አዳሙ ዩሱፍ የተባለው ግለሰብ "ቤተሰቤን ጎርፍ ሲወስድ ምንም ማድረግ ሳልችል ቆሜ ተመልክቻለሁ። እኔም መዋኘት በመቻሌ ነው የተረፍኩት" ሲል ገልጿል።

እ.አ.አ በ2022 በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ600 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
#BBC

@ThiqahEth
😭162🤔1😱1😢1
በኤትና ተራራ እሳተ ገሞራ ተከሰተ።

በሰሜን ጣልያን የሲሲሊ ግዛት በሚገኘው በዚህ ተራራ ዛሬ ድንገተኛ የእሳተ ገሞራ መፈንዳቱን የጣልያን ብሄራዊ ጃዖፊዚክስ ኢኒስቲትዩት(NIG) ገልጿል።

በእሳተ ገሞራው ውሃ እና ሰልፈር ዳይ ኦክሳይድ የተሸከሙ ከፍተኛ ብናኝ እና ጋዝ ወደ ሰማይ ሲወጣ ታይቷል ብሏል።

በስፍራው የነበሩ ቱሪስቶች ከአካባቢው በሩጫ ሲያመልጡ መመልከታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

የኤትና ተራራ በተደጋጋሚ ለእሳተ ገሞራ ተጋላጭ ከሆኑ የአውሮፓ ተራራዎች ውስጥ ቀዳሚው መሆኑን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል።
#mailonline #theherald

@ThiqahEth
😱117🕊2🤔1😢1
THIQAH
ሩሲያ እና ዩክሬን ተጨማሪ እስረኞችን ለመልቀቅ ተስማምተዋል። የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ዛሬ በቱርክ ሁለተኛውን ዙር ውይይት አካሂደዋል። #SputnikAfrica (ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን) @ThiqahEth
ሩሲያና ዩክሬን ከ300 የሚበልጡ የታገቱ ህፃናትን ለመልቀቅና በሌሎች ጉዳዮች ተስማሙ።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ስብሰባው በመሪዎች ደረጃ ንግግር የሚጀመርበት ሁኔታ እንድፈጠር ያለመ ነው ብለዋል።

የሰብዓዊ እርዳታ እንድዳረስና የእስረኞች ልውውጥ እንድደረግ አሳስበዋል።

ቱርክ ግጭቱን ለመፍታት የትኛውንም አስፈላጊ ነገር ለማድረግ ዝግጁ ናት ያሉት ፊዳን፣ ዘላቂ የተኩስ አቁም ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይገባል ብለዋል።

የሁለቱ ሀገራት ልዑካን ከአንድ ሰዓት በላይ በዝግ ከተወያዩ በኋላ በምን ተስማሙ?

-ግዛታቸውን አልፎ የሚገኘውን ጦራቸውን ለማስወጣት፣
-የሚቀርቡ የውጭ ወታደራዊ ድጋፎችን ለማቆም፣
-የሦስተኛ ወገን ጦር እንዳይሳተፍ ለማድረግ ሁለቱም ሀገራት ተስማምተዋል።

እንጂሁም፦ በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ለማንሳት (ከጦርነቱ መጀመር በኋላ በአውሮፓ ሀገራት የተጣለባት)፣

የተጎዱና የቆሰሉ ወታደሮችን ለመለዋወጥ: ይህን ለማድረግ እንዲያስችል በተወሰኑ ግንባሮች የ2/3 ቀን ተኩስ አቁም ለማወጅ፣

ከ300 የሚበልጡ የታገቱ ህፃናትን ለመልቀቅ (በቅርቡ ሩሲያ 101 ዩክሬን 20 ህፃናትን ለቀዋል) ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
#sputniknews

@ThiqahEth
🕊185🤔3😢2😭1
"በሰብዓዊ መብት ጥሰት" ምክንያት የጠ/ሚ አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንግሊዝ ጉብኝት ውድቅ ተደረገ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኬር ስታርመር የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን የጉብኝት ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል ተብሏል።

"በሰብዓዊ መብት ጥሰት" ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) በእንግሊዝ ሊያደርጉት ያሰቡትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ውድቅ መደረጉ ነው የተገለጸው።

የሜትሮፖሊታን ፖሊስ የአባይን የጉዞ ደህንነት ሽፋን አልሰጥም ማለቱም ተሰምቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር ውሳኔ እንግሊዝ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዳሳሰባት ማሳያ ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በቅርቡ በአውሮፓ ሀገራት ባደረጉት ጉዞ በፈረንሳይ፣ ሮም እና ጣልያን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
#thehabesha

@ThiqahEth
92👏56😡6🤔2😱1
ደቡብ ኮሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እያካሄደች ትገኛለች።

ላለፉት ስድስት ወራት በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የቆየችው ደቡብ ኮሪያ በዛሬው እለት ሀገራዊ ምርጫ በማካሄድ ላይ ናት።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮዔል በህዳር ወር ባወጁት የወታደራዊ አስተዳደር (martial law) ምክንያት ከስልጣናቸው መነሳታቸው ይታወቃል። 
#cnn

@ThiqahEth
🤔2🕊2
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 21 ንጹሐን በግፍ ተገደሉ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (HRW) በጎማ ከተማ የ11 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን አስታውቋል።

ድርጅቱ ግድያውን የፈጸመው በሩዋንዳ የሚደገፈው አማፂው የኤም 23 ቡድን ነው ብሏል።
#africannews

@ThiqahEth
😭124