"አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" - ናይጄሪያ
ናይጄሪያ በጎርፍ አደጋ የሞቱ፣"እስካሁን 115 አስክሬኖች አንስተናል" አለች።
በማክዋ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።
የናይጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ አስተዳደር (SEMA) ቃል አቀባይ ኢብራሂም ሁሴን "አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" ሲሉ ተናግረዋል።
በባለፈው አመት በተከሰተ ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ከ1200 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። #aljazeera
@ThiqahEth

😢15❤5😭5🕊2
ዩክሬን በ11 የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎቿን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች።
ዜጎቹ እንዲለቁ ማሳሰቢያ የተሰጠባቸው ሁሉም ቀበሌዎች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
ውሳኔው ሩሲያ በነዋሪዎቹ ላይ የምታደርሰው የቦምብ ጥቃት ባለመቋረጡ የተላለፈ መሆኑ ተገልጿል። #france24

😢11🤔4❤3🕊3😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪዲዮ፦ ግብፅ በበረዶ አዘል ከባድ ዝናብና ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች።
እስክንድርያ ከተማ በበረዶ ስትጥለቀለቅ፣ በአውሎ ነፋስ ስትታመስ ተስተውላለች።
@ThiqahEth
እስክንድርያ ከተማ በበረዶ ስትጥለቀለቅ፣ በአውሎ ነፋስ ስትታመስ ተስተውላለች።
@ThiqahEth
❤16💔8😭2😢1
THIQAH
Photo
#Update
የሟቾች ቁጥር 151 ደርሷል።
በናይጄሪያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን የሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር (SEMA) አስታውቋል።
ጎርፉ 380 ኪሎሜትር መሸፋኑን የገለፀው አስተዳደሩ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማፈላለግ ስራው ቀጥሏል ብሏል።
በዚህ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ከ3000 የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ 500 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል። #associatedpress #pbsnews #telegraphindia

😢17❤7😭4🤔1😱1
በጃፓን በሬክተር ስኬል 6.1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።
አደጋው የተከሰተው በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ግዛት በምትገኘው ኩሺሮ ከተማ መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) አስታውቋል።
እስካሁን በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተመዘገበ ጉዳት የለም ተብሏል።
የጃፓን ባለስልጣናት የመሬት መንቀጥቀጡን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያም ሆነ ማስጠንቀቂያ አልተሰጠም። #yenisafaq

💔9❤5😭3🕊2
ዩክሬን 40 የሩሲያ ጦር ጄቶችን መትታ ጣለች።
ዩክሬን ጥቃቱን በሩሲያ ግዛት ገብታ እንደፈፀመችው አንድ የሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ተናግረዋል።
ኪቭ ይህን እርምጃ ለመውሰድ 18 ወራት እንደፈጀባት አመራሩ አብራርተዋል።
ዩክሬን ጥቃቱን እንደፈፀመች ያረጋገጠው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፣ በኢርኩትስክ ክልል ዘልቃ መግባቷን አስታውቋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን በነገው እለት በቱርክ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። #thewashingtontimes #dailyausaf

👏10😢6❤3🤔3😱3💔2🕊1
"ከ30 በላይ እርዳታ ፈላጊዎች በእስራኤል ተገድለዋል" - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
"የደረሰ ጉዳት የለም፣የእርዳታ ስርጭቱ በሰላም ተጠናቋል" - የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን
የእስራኤል ጦር በራፋህ የእርዳታ ጣቢያ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ንፁሃን ላይ ጥቃት ማድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 170 የሚደርሱት መጎዳታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን (GHF) በበኩሉ ደረሰ የተባለውን ጉዳት "በእርዳታ ወቅት ሰዎች በስነስርዓቱ ተከፋፍለው ሂደዋል" በማለት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ማስተባበያ ሰጥቷል።
የእስራኤል ጦርም በተመሳሳይ "በንፁሃን ላይ የተቃጣ እርምጃ የለም" ሲል የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።
አንድ የአይን እማኝ ግን "የእስራኤል ወታደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ እርዳታ ጠባቂዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር" በማለት ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ሆስፒታል ላይ በፈፀመችው ጥቃት 54 ሰዎች መገደላቸውንና የኩላሊት መታጠቢያ ማሽንን ሙሉ በሙሉ ማውደሟን ተመድ አስታውቋል።#cnn #aljazeera

😢21😡4❤3🙏3🕊2😱1
ካሮል ናውሮኪ የፖላንድን ብሄራዊ ምርጫ አሸነፉ።
"የፖለቲካ ልምድ የላቸውም" የሚባሉት "ቀኝ ዘመሙ" የታሪክ ባለሙያ ናውሮኪ አዲሱ የፖላንድ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
የ42 አመቱ ናውሮኪ 50.89% ድምፅ በማግኘት ነው ምርጫውን ማሸነፍ የቻሉት። #indiatoday

🕊4❤3🙏2😱1
#Update
በናይጄሪያው ጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ200 እንዳሻበቀ፣ 500 ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ፣ የሟቾች ብዛት 700 እንደሚደርስ ተነገረ።
በናይጄሪያዋ ሞካዋ ከተማ በጎርፍ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ እንደሆነ፣ ቁጥሩ እስከ 700 እንደሚደርስ ቢቢሲ ዘግቧል።
ዘገባው፣ “እስካሁን 500 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሕይወት የሚገኝ ሰው ከዚህ በኋላ አይኖርም በሚል እምነት የነፍስ አድን ጥረቱ ተቋርጧል” ብሏል።
በአካባቢው ተላላፊ በሽታ እንዳይዛመት በጎርፉ የተቀበሩ ግለሰቦችን ቆፍሮ በማውጣት ተገቢው የቀብር ሥነ ሥርዓት ማከናወን በቅርቡ እንደሚጀመር የሞካዋ አካባቢ አስተዳዳሪ ሙሐመዱ አሊዩ ተናግረዋል።
ባለቤቱ እና ጨቅላ ልጁ በጎርፍ የተወሰዱበት አዳሙ ዩሱፍ የተባለው ግለሰብ "ቤተሰቤን ጎርፍ ሲወስድ ምንም ማድረግ ሳልችል ቆሜ ተመልክቻለሁ። እኔም መዋኘት በመቻሌ ነው የተረፍኩት" ሲል ገልጿል።
እ.አ.አ በ2022 በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ600 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ዘገባው ጠቅሷል። #BBC

😭16❤2🤔1😱1😢1