THIQAH
9.39K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
ተመድ 20% በጀቱን ሊቀንስ ነው ተባለ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአሜሪካ የሚያገኘው ድጋፍ መቀነሱን ተከትሎ አንዳንድ እቅዶቹን ለመሰረዝ ተገዷል ተብሏል።

የ2025 በጀቱ 3.72 ቢሊዮን ዶላር የነበረው ተመድ በ2026 የዚህን በጀት 80% ብቻ እንደሚጠቀም ተገልጿል። 
#sputnikafrica

@ThiqahEth
6😭4🙏2
ትራምፕ 500,000 ስደተኞችን እንዲያባርሩ ከፍተኛው ፍርድቤት ወሰነ።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድቤት የአራት ሀገራት ማለትም ኩባ፣ ሀይቲ፣ ኒካራጉዋና ቬንዙዌላ ስደተኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ መብትን አንስቷል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የነበራቸው 350,000 የቬኔዙዌላ ስደተኞችን ከሀገር እንዲያስወጡ ፍቃዱን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ከሀገር የሚያስወጣቸው ስደተኞች ብዛት አንድ ሚሊዮን ደርሷል ተብሏል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሬዚዳንቱን የስደተኞች በኃይል ማስወጣት እርምጃ የሰብዓዊ መብት አያያዝን ይጣረሳል በሚል ሲቃወም ቆይቷል።
#france24

@ThiqahEth
😢157😡2
THIQAH
#አማራክልል #እገታ “በ10 ቀናት ብቻ በአማራ ክልል 31 ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል” - ማኀበሩ ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር፣ “በ10 ቀናት ብቻ በአማራ ክልል 31 ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል” ሲል ነግሮናል። "ገንዘብ ከፍለው የሚወጡ አሉ፤ ነገር ግን ማስፈራሪያ ስለሚደርስባቸው ከወጡ በኋላ የገጠማቸውን የመናገር ድፍረት አይኖራቸውም። ምንክንያቱም ተመልሰው በዚያው መንገድ ነው የሚያሽከረክሩት።…
#Ethiopia #Dirivers

"በ27 ቀናት 53 ሾፌር እና ረዳቶች ታግተዋል" - የሹፌሮች አንደበት

የሹፌሮች አንደበት፣ "ከ25/08/2017 እስከ 21/09/2017 ዓም 53 ሹፌር እና ረዳቶች በ 27 ቀን ውስጥ በዘራፊዎች ታፍነው ታግተው ተወስደው መከራ አይተው እንልፍ አጠው በሀሩር ቀልጠው ያጠራቀሙትን ጥሪት እየከፈሉ ተለቀዋል" ብሏል።

አክሎ፣ "እውነታው ይሄ ነው" ሲል አስታውቋል።

የኢትዮጵናያ ፌደራል ፓሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሰሞኑን ለፋና፣ "ሰው ወደፈለገበት ቦታ መንቀሳቀስ የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል" ማለታቸውን የጠቀሰው የሺፌሮች አንደበት፣ ለዚህም አስተያየት ሰጥቷል።

"ተው እንጂ ችግራችንን ባትፈቱ፣ በደላችን ባትመለከቱ፣ መታገታችን ባይሰማችሁ መዘረፋችን ባይገዳችሁ፣ ሞታችን ምንም ባይመስላችሁ እንኳ መሬት ላይ ያለን ሀቅ ክዳችሁ 'እገታን አስቀረን' ማለታችሁ የሚያሳፍርም የሚያሸማቅቅም ነው" ብሏል።

"እንዴት በየመንገዱ እየደረሰብን ያለን በደል ዝርፊያ እገታ መገደል እንደቀረ አድርጋችሁ ትናገራላችሁ? የትኛው ሹፌር ያገተ አጋች ነው የጠፋው? ማን ጠይቆት ማን ተከታትሎ ይዞት ነው እገታውስ የሚቆም?" ሲልም ጠይቋል።
(ፌደራል ፓሊስ በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ከተሰጠን የምናቀርብ ይሆናል)

@ThiqahEth
😭164🤔3😱2
"አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" - ናይጄሪያ

ናይጄሪያ በጎርፍ አደጋ የሞቱ፣"እስካሁን 115 አስክሬኖች አንስተናል" አለች።

በማክዋ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።

የናይጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ አስተዳደር (SEMA) ቃል አቀባይ ኢብራሂም ሁሴን "አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" ሲሉ ተናግረዋል።

በባለፈው አመት በተከሰተ ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ከ1200 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
#aljazeera

@ThiqahEth
😢155😭5🕊2
ዩክሬን በ11 የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎቿን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች።

ዜጎቹ እንዲለቁ ማሳሰቢያ የተሰጠባቸው ሁሉም ቀበሌዎች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ውሳኔው ሩሲያ በነዋሪዎቹ ላይ የምታደርሰው የቦምብ ጥቃት ባለመቋረጡ የተላለፈ መሆኑ ተገልጿል።
#france24

@ThiqahEth
😢11🤔43🕊3😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪዲዮ፦ ግብፅ በበረዶ አዘል ከባድ ዝናብና ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች።

እስክንድርያ ከተማ በበረዶ ስትጥለቀለቅ፣ በአውሎ ነፋስ ስትታመስ ተስተውላለች።

@ThiqahEth
16💔8😭2😢1
THIQAH
Photo
#Update

የሟቾች ቁጥር 151 ደርሷል።

በናይጄሪያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን የሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር (SEMA) አስታውቋል።

ጎርፉ 380 ኪሎሜትር መሸፋኑን የገለፀው አስተዳደሩ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማፈላለግ ስራው ቀጥሏል ብሏል።

በዚህ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ከ3000 የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ መልኩ 500 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
#associatedpress #pbsnews #telegraphindia

@ThiqahEth
😢177😭4🤔1😱1
በጃፓን በሬክተር ስኬል 6.1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

አደጋው የተከሰተው በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ግዛት በምትገኘው ኩሺሮ ከተማ መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) አስታውቋል።

እስካሁን በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተመዘገበ ጉዳት የለም ተብሏል።

የጃፓን ባለስልጣናት የመሬት መንቀጥቀጡን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያም ሆነ ማስጠንቀቂያ አልተሰጠም።
#yenisafaq

@ThiqahEth
💔95😭3🕊2
ዩክሬን 40 የሩሲያ ጦር ጄቶችን መትታ ጣለች።

ዩክሬን ጥቃቱን በሩሲያ ግዛት ገብታ እንደፈፀመችው አንድ የሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ተናግረዋል።

ኪቭ ይህን እርምጃ ለመውሰድ 18 ወራት እንደፈጀባት አመራሩ አብራርተዋል።

ዩክሬን ጥቃቱን እንደፈፀመች ያረጋገጠው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፣ በኢርኩትስክ ክልል ዘልቃ መግባቷን አስታውቋል።

ሩሲያ እና ዩክሬን በነገው እለት በቱርክ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። 
#thewashingtontimes   #dailyausaf

@ThiqahEth
👏10😢63🤔3😱3💔2🕊1
"ከ30 በላይ እርዳታ ፈላጊዎች በእስራኤል ተገድለዋል" - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር

"የደረሰ ጉዳት የለም፣የእርዳታ ስርጭቱ በሰላም ተጠናቋል" - የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን

የእስራኤል ጦር በራፋህ የእርዳታ ጣቢያ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ንፁሃን ላይ ጥቃት ማድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 170 የሚደርሱት መጎዳታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን (GHF) በበኩሉ ደረሰ የተባለውን ጉዳት "በእርዳታ ወቅት ሰዎች በስነስርዓቱ ተከፋፍለው ሂደዋል" በማለት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ማስተባበያ ሰጥቷል።

የእስራኤል ጦርም በተመሳሳይ "በንፁሃን ላይ የተቃጣ እርምጃ የለም" ሲል የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

አንድ የአይን እማኝ ግን "የእስራኤል ወታደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ እርዳታ ጠባቂዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር" በማለት ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ሆስፒታል ላይ በፈፀመችው ጥቃት 54 ሰዎች መገደላቸውንና የኩላሊት መታጠቢያ ማሽንን ሙሉ በሙሉ ማውደሟን ተመድ አስታውቋል።
#cnn #aljazeera

@ThiqahEth
😢21😡43🙏3🕊2😱1