ከእርስ በርስ ጦርነት ሸሽተው የተሰደዱ ሱዳናውያን በሊቢያ በረሃ እየሞቱ ነው።
ከቻድ ተነስተው ወደ ሊቢያ ሲጓዙ ከነበሩ 34 ሱዳናውያን ውስጥ ሰባቱ በሊቢያ በረሃ ሙተው መገኘታቸውን የኩፍላ አምቡላንስና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።
22 ሰዎችን ከአደጋ ማትረፍ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፣ አምስቱ ህፃናት ናቸው ተብሏል።
አምስት ስደተኞች እስካሁን ድረስ አልተገኙም ያለው ኩፍላ፣ ካሁን በፊት 260 ሱዳናውያን ህይወት መታደጉን ገልጿል።
787,000 ስደተኞች በሊቢያ እንደሚገኙ አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IMO) መረጃ ያመላክታል።#africannews
@ThiqahEth

😢27👍4🔥2❤1😭1
THIQAH
Photo
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል። አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአውሮፓ ላይ የጣሉትን የ50% ታሪፍ ለወር አራዘሙ።
ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ሰኔ ላይ ይተገበራል ያሉት ውሳኔ ወደ ሐምሌ እንዲዛወር መወሰናቸውን ገልጸዋል።
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል" ያሉት ትራምፕ "አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" ሲሉ የተራዘመበትን ምክንያት አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከአውሮፓ በሚገቡ ምሬቶች ላይ የጣሉት ቀረጥ ባለፈው ሳምንት ከ30% ወደ 50% ከፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።#irishexaminer

😁8👍2❤1🔥1😱1
"33,764 አቅማቸው ያልደረሱ ሴቶች አርግዘዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 3,368 ተማሪዎች በመሆናቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል" - የዝምባብዌ ትምህርት ሚኒስትር
በተለይ በትምህርት ቤት ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የልጃገረዶች እርግዝና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የዝምባብዌ ትምህርት ሚኒስትር ድዔታ አንጀሊን ጋታ ገልጸዋል።
በፈረንጆች 2024 ብቻ 33,764 አቅማቸው ያልደረሱ ሴቶች ማርገዛቸውን የተናገሩት ጋታ፣ ከእነዚህ ውስጥ 3,368 ተማሪዎች በመሆናቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በ2023 ደግሞ 4,000 ተማሪዎች በእርግዝና ምክንያት ከትምህርት ገበታ መገለላቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም ይህን ያለ እድሜ ጋብቻ ችግር ለመቅረፍ የማሰልጠኛ መፅሐፍት መዘጋጀቱንና በድምፅ የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ስርጭት መጀመሩን አብራርተዋል።
ዝምባዋብዌ ያለእድሜ ጋብቻን ለመከላከል 40,000 መምህራንን ማሰልጠን መጀመሯም ተገልጿል። #bulawayo24news

👍15😁8😱2🥰1🤔1😭1😡1
"ዩክሬን የሩሲያን ሲቪልና ማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ኢላማ አድርጋለች፤ በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃዎች ናቸው" - ዲሚትሪ ፔስኮቭ
የሩሲያና ዩክሬን ንግግርን ለማስቀጠል አሁንም መግባባት ላይ እንዳልተደረሰ፣ ለቀጣዩ ዙር መዘጋጀት እንደሚገባ ክሬምሊን ገለጸ።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ምን አሉ?
"ዩክሬን የሩሲያን ሲቪልና ማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ኢላማ አድርጋለች፤ በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃዎች ናቸው።
የዩክሬን የድርድር ሂደት መጀመሩ ስኬት ነው፤ ሩሲያ ሂደቱን ስላመቻቹ ለትራምፕ እና ለዩናይትድ ስቴትስ ምስጋና ታቀርባለች፡፡
በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ውጤታማ የሁለትዮሽ ግንኙነትን እንደገና የመገንባት ሂደት እየተጀመረ ነው።
የንግድ ተወካዮች በዛሬው እለት ከፑቲን ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ስለ ሥራቸው እና የልማት እቅዶች ይወያያሉ።
ፑቲን ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊዳን ጋር ዛሬ ይገናኛሉ። የፊዳን ጉብኝት በሩሲያ እና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት ትኩረቱን ያደርጋል" ማለታቸውን #ስፑትኒክ ዘግቧል።

👍8❤2🥰1
THIQAH
#Amhara #Gojam "ስምንት ሹፌርና ረዳቶች ታግተዋል" - የሹፌሮች አንደበት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም በ17/09/2017 ዓ/ም ከ ዱርቤቴ ወተት አባይ (ቢኮሎ አባይ) መካከል ድብካን ጊዮርጊስ የሚባል ልዩ ቦታ ከቀኑ 8 ሰዓት 30 ገደማ 3 ኦባማ 1 ካሦኒ ሾፌርና ረዳት/በድምሩ 8 ረዳትና ሹፌር ታግተው መወሰዳቸውን የሹፌሮች አንደበት ገልጿል። በምዕራብ ጎጃም ከ3 ቀና በፊት፣ ፍኖተ ሰላም…
#አማራክልል #እገታ
“በ10 ቀናት ብቻ በአማራ ክልል 31 ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል” - ማኀበሩ
ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር፣ “በ10 ቀናት ብቻ በአማራ ክልል 31 ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል” ሲል ነግሮናል።
"ገንዘብ ከፍለው የሚወጡ አሉ፤ ነገር ግን ማስፈራሪያ ስለሚደርስባቸው ከወጡ በኋላ የገጠማቸውን የመናገር ድፍረት አይኖራቸውም። ምንክንያቱም ተመልሰው በዚያው መንገድ ነው የሚያሽከረክሩት። የሕግ ከለላ የላቸውም" ብሏል።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቢኮሎና ዱርቤቴ መካከል ባለ ቦታ ግንቦት 17/2017 ዓ/ም አራት ሹፌሮችና አራት ረዳቶች መታገታቸውን ገልጾ፣ “በየቦታው ያለው ነገር ከባድ ነው። ከቀን ቀን እየከፋ፣ እገታ ባልተለመደባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተስፋፋ ነው” ብሏል።
በደብረ ብርሃን መንገድ፣ እንጅባራ፣ ቻግኒ በቅርቡ እገታ መፈጸሙን ጠቅሶ፣ “ደቡብ ጎንደር ከጋይንት እስከ ወረታ መገንጠያ ከባድ መንገድ ሆኗል፤ ለየት ባለ መልኩ እገታ ይፈጸምበታል” ነው ያለው።
ማኀበሩ፣ “ድሮ 24 ሰዓት ይነዳባቸው በነበሩ መንገዶች አሁን ሙሉ ለሙሉ ቆሟል። በቀን ለ10 ሰዓታት ነው የሚነዳው። በዚህ ሳቢያ የግድያ ጥቃቱ ቀንሷል። እገታው ግን በጣሞ ተጧጡፏል” ሲልም ገልጿል።
@EyobTikuye @ThiqhEth

😢11👍5😁2❤1🙏1
"የህልውና ጉዳይ ስለሆነ እስራኤል አማራጭ የላትም ጦርነቱን ትቀጥላለች" - አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ
በኢትዮጵያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የእስራኤልን 58ኛ አመት የነፃነት ቀን ዛሬ አክብሯል።
ይህም "የእየሩሳሌም ቀን" ተብሎ ይጠራል። የእየሩሳሌም ቀን ማለት፣ እስራዔላዊያን በአረብ፣ እንግሊዝ፣ ኦቶማን ቱርክ አስተዳደር ስር ከቆየ ከ2000 ዓመታት በኋላ የኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራን ተረክበው ማስተዳደር የጀመሩበት ቀን ነው።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ፣ ከቲቃህ ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት በቆይታ ምን አሉ?
"እስራኤል ከአንድ አመት ተኩል በላይ በጦርነት ነው ያለችው። ይሄን ጦርነት ፈልጋው አይደለም የገባችው፣ ተደፍራ፣ ዜጓቿ ታርደው ነው።
በአሸባሪው ሀማስ ጥቃት ደርሶባት፣ የታፈኑ ዜጎቿን ለማስመለስ ነው። በእስራኤል ላይ በሰባት አቅጣጫ ነው ጦርነት የተከፈተው።
እነዚህ ሁሉ በኢራን አስተባባሪነት ነው የተከፈቱት። ስለዚህ እስራኤል የህልውና ጉዳይ ስለሆነ አማራጭ የላትም መከላከል አለባት" ብለዋል።
(ተጨማሪ አለን)
@EyobTikuye @ThiqahEth

😡87❤17👍14🤔2😢2🙏2🥰1
THIQAH
"የህልውና ጉዳይ ስለሆነ እስራኤል አማራጭ የላትም ጦርነቱን ትቀጥላለች" - አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ በኢትዮጵያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የእስራኤልን 58ኛ አመት የነፃነት ቀን ዛሬ አክብሯል። ይህም "የእየሩሳሌም ቀን" ተብሎ ይጠራል። የእየሩሳሌም ቀን ማለት፣ እስራዔላዊያን በአረብ፣ እንግሊዝ፣ ኦቶማን ቱርክ አስተዳደር ስር ከቆየ ከ2000 ዓመታት በኋላ የኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራን ተረክበው ማስተዳደር…
"'እስራኤል የዘር ጭፍጨፋ ታደርጋለች፣ የጦር ወንጀል ትሰራለች' የሚለው ውንጀላ ወደ ጥይት ተቀይሮ እነሆ ዋሽንግተን ላይ ሁለት ዲፕሎማቶች እንደተገደሉ እናውቃለን" - አምባሳደሩ
ከቲቃህ ኢትዮጵናያ ጋር ቆይታ የነበራቸው በኢትዮጵያ የእስራኤም ኤምባሲ አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ አክለው ምን አሉ?
"ሀማስ እስኪደመሰስ ድረስ እስራኤል" ጦርነቱን እንደምትቀጥል አስረግጠው ተናግረዋል።
ምን አሉ? "ሌሎች ሀገራት በእስራኤል ላይ የሚያቀርቡት ትችት በእውነቱ ፀብ አጫሪው ቡድን የያዛቸውን ልቀቁ በማለት ፈንታ እስራኤልን ለምን ተከላከልሽ ብለው ይወነጅላሉ።
ይሄ እውነት የጎደለው ነው፤ ኢ-ኢፍትሀዊ ስለሆነ፣ ሀማስ እስኪደመሰስ ድረስ እስራኤል ምንጊዜም ደህንነቷን ለማስጠበቅ ጦርነቱን ትቀጥላለች።
ሌላው እጅግ በጣም የሚያሳዝነው እስራኤልን በሀሰት የሚወነጅሉ፣ 'እስራኤል የዘር ጭፍጨፋ ታደርጋለች፣ የጦር ወንጀል ትሰራለች' የሚለው ውንጀላ ወደ ጥይት ተቀይሮ እነሆ ዋሽንግተን ላይም ሁለት ድፕሎማቶች እንደተገደሉ እናውቃለን።
ይሄ በሀሰት የሚደረገው ቅስቀሳና ለእስራኤል መጥፎ ስም የሚሰጡ አካላት ውጤት ነው። ስለዚህ እስራኤል ምንጊዜም ቢሆን ህልውናዋን ለማስቀጠል ጦርነቱን ትቀጥላለች ማለት ነው" ብለዋል።
@ByThiqahReporter @ThiqahEth

😡63👍22❤3🥰1😱1😢1
#Ethiopia #Gambella
ስድስት ሰዎች በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች መገደላቸው ጋምቤላ ክልል ገለጸ።
የደቡብ ሱዳን መርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በመግባት ባደረሱት ጥቃት ንጹሐን መገደላቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነግሮናል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ጊሎ፣ ከትላንት ወዲያ ጠዋት ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ 4 ወንዶችና ሁለት ሴቶች መገደላቸውን ገልጸዋል።
ኃላፊው፣ “ታጣቂዎቹ ከብት መዝረፍ፣ ህፃናት መውሰድ የለመደባቸው ትሬንድ ነው። ትላንት ባሱ የተመታበት ቦታ ብዙ ጊዜ የወረዳው ከፍተኛ አካላት ትኩረት የሚያደርበት ነው። ግን የትላንቱ ክስተት በአጋጣሚ ከባድ ነበር” ብለዋል።
ቢሮው ከወር በፊት በሰጠን ቃል፣ “ በተለይ በዚህ ወርና እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ ታጣቂዎቹ የሚፈታተኑንበት ወቅት ነው። ኩሬዎች ስለሚደርቁ ለእነርሱ መምጣት አመቺ ይሆናል። አሁን ትንሽ፣ ትንሽ ምልክቶችን እያየን ነው። እየመጡ ነው" ብሎ ነበር።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ተነስተው የጋምቤላ ክልልን ድንበር ጥሰው በመግባት ልጆችን፣ ከብቶችን ሰርቀው በመውሰድ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ይታወቃል። Read More፡ https://t.me/tikvahethiopia/97152
@ThiqahEth @TikvahEthiopia

👍10😭3
ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ከወርቅ ገበያ 2.57 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ።
በእነዚህ አስር ወራት ውስጥ 29,396 ኪሎግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ መቅረቡን የማዕድን ሚኒስቴር አመላክቷል።
በሚኒስቴሩ መረጃ መሰረት ከትግራይ ክልል 12,210 ኪግ፣ ከኦሮሚያ ክልል 6910 ኪግ፣ ከጋምቤላ ክልል 4590 ኪግ እንድሁም ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 3689 ኪግ ወርቅ ገቢ ተደርጓል። #sputnikafrica

❤14👍5🥰2🤔2😡2😱1👌1
21 የግሪክ የባሕር ጠባቂዎች የስደተኞች መርከብ ላይ አደጋ በማድረስ ወንጀል ተከሰሱ።
ከተከሳሾቹ መካከል አራቱ ባለስልጣናት መሆናቸው ተገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ የተከሰሱት በ2023 የ650 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የጀልባ አደጋ እጃቸው አለበት በሚል ነው ተብሏል።
በተጨማሪም 750 ስደተኞችን ከሊቢያ ወደ ጣልያን ለማስገባት ጉቦ ተቀብለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። #upi

👍15❤5😁2😡2🤔1👌1
"ፑቲን ከእሳት ጋር እየተጫወተ ነው" - ፕሬዝዳንት ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ፑቲንን "ከመጥፎ ነገር እየጠበኩት ነው" አሉ። ፑቲን ከእሳት ጋር እየተጫወተ ነው"ም ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም "ፑቲን ያላወቀው ነገር ቢኖር፣ እኔ ባልኖር በሩሲያ ላይ በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮች ይፈጠሩ ነበር" ብለዋል።
ይሁን እንጂ "መጥፎ" ያሏቸውን ነገሮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ትራምፕ የሩሲያ መንግስት በዩክሬን የሚፈጸመው ጥቃቶችን ማስቆም አለመቻሉንም ተችተዋል። #rawstory

😁42👍6🤔3🥰2❤1
የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ላይ "ወረራ" ሲፈጽሙ በንጹሐን ላይ ሞትና መቁሰል አጋጠመ።
በወረራ በያዙት ዌስት ባንክ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም በወሰዱት የኃይል እርምጃ አንድ ፍልስጤማዊ ህይወቱ ሲያልፍ 30 የሚደርሱት ቆስለዋል።
የራማላህ፣ ናቡልስ፣ ቤተልሔም እና ጄኒን ከተሞች ውድመት ደርሶባቸዋል ተብሏል። #aljazeera

😡26👍6🔥3🤔2❤1🥰1😢1