THIQAH
9.38K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
ትራምፕ 60 ቢሊዮን ዶላር በማገዳቸው ከ150 ሺሕ በላይ የሄይቲ ዜጎች በኤችአይቪ ተጠቂ መሆናቸው ተሰማ።

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) በጀት መቋረጥን ተከትሎ በሄይቲ የኤችአይቪ መድኃኒት እጥረት አጋጥሟታል።

ትራምፕ አሜሪካ ለውጭ እርዳታ ከምትመድበው በጀት 90% የሚሆነውን የዩኤስኤይድ ድጎማ በማቋረጣቸው ለአለማቀፍ እርዳታ ሊለቀቅ የነበረ 60 ቢሊዮን ዶላር አግደዋል።

ይህን ተከትሎ የእረዳታው መቋረጥ ጫና ከፈጠረባቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሄይቲ በአሁኑ ወቅት ከ150,000 በላይ የሚሆኑት ዜጎቿ የበሽታው ተጠቂ መሆናቸው ተገልጿል።

ካረቢያኗ ሄይቲ ከ2023 ወዲህ "በወሮበላ" ቡድኖች እየታመሰች ትገኛለች። 
#africannews

@ThiqahEth
👍10🤔92🥰1😁1😭1
5000 ቶን የምትመዝነው የጦር መርከብ በመስጠሟ ሦስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ጉዳዩን "የወንጀል ድርጊት ነው" ሲሉ የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ጆንግ ኡን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ቺፍ ሜካኒኩ፣ የግንባታ ወርክ ሾፕ ኃላፊ እና የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ናቸው። 

ሰሜን ኮሪያ የባህር ላይ ጦር መርከብ መስጠሟን ተከትሎ ጥፋተኛ ያለቻቸውን ሦስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አውላለች።

የጦር መርከቧ ፕሬዚደንት ኪም ጆንግ ኡን በተገኙበት ስራ ለመጀመር በሂደት ላይ በነበረችበት ወቅት ነው አደጋው የገጠማት ተብሏል።

5000 ቶን የምትመዝነው የጦር መርከብ በገጠማት አደጋ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
#dailymirror #thestandard

@ThiqahEth
😁20👍11😭2🥰1😱1
#Amhara #Gojam

"ስምንት ሹፌርና ረዳቶች ታግተዋል" - የሹፌሮች አንደበት

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም በ17/09/2017 ዓ/ም ከ ዱርቤቴ ወተት አባይ (ቢኮሎ አባይ) መካከል ድብካን ጊዮርጊስ የሚባል ልዩ ቦታ ከቀኑ 8 ሰዓት 30 ገደማ 3 ኦባማ 1 ካሦኒ ሾፌርና ረዳት/በድምሩ 8 ረዳትና ሹፌር  ታግተው መወሰዳቸውን የሹፌሮች አንደበት ገልጿል።

በምዕራብ ጎጃም ከ3 ቀና በፊት፣ ፍኖተ ሰላም አካባቢ ከ5 ቀን በፊት ከእንጅባራ ቻግኒ መንገድ እገታ መፈጸሙን አስታውሶ፣  "አሽከርካሪዎች ጥንቃቄን አድርጉ" ሲል አሳስቧል።

@ThiqahEth
👍3😱2🔥1🥰1
"አሜሪካም ፈጣን የታሪፍ መፍትሄን ትፈልጋለች። ማጋነን አይገባም፣ ከአሜሪካ ጋር የጋራ መፍትሔ እንፈልጋለን" - ጀርመን

የጀርመን ምክትል መራሄ መንግስት እና የገንዘብ ሚኒስትር ላርስ ክሊንግቤል አሜሪካ እና አውሮፓ በታሪፍ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል።

"ማጋነን አይገባም፣ ከአሜሪካ ጋር የጋራ መፍትሄ እንፈልጋለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ "አሜሪካም ፈጣን የታሪፍ መፍትሄን ትፈልጋለች" ሲሉ ገልጸዋል።

ጀርመን 183 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ አሜሪካ በመላክ ከአውሮፓ ተቀዳሚ ሀገር ናት።

የትራምፕ መንግስት በአውሮፓ ምርቶች ላይ 50% ታሪፍ መጣላቸውን አስታውቀዋል።
#reuters

@ThiqahEth
😁9👍5🤔2😱2🥰1
#Ethiopia

“ፓሊሲዎቹ ድሃን ከድህነት ማውጣት አልቻሉም፤ ድህነትን ለመቀነስ ያመጡት ውጤትም ከዜሮ ያንሳል”- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን 

የኢትዮጵያ መንግስት ለ22 ዓመታት ድህነትን ለመቀነስ ያወጣቸው ፓሊሲዎች ውጤት ከዜሮ እንደሚያንስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ጥናት አመለከተ።

አሶሴሽኑ እ.ኤ.አ ከ2001 እስከ 2023 ያለውን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አፈጻጸምን የተመለከተ ጥናት ሰሞኑን ይፋ ማድረጉን ሪፓርተር አስነብቧል።
 
ኢትዮጵያ እያደጉ ካሉ አገሮች አንዷ የነበረች ቢሆንም፣ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ማሽቆልቆሉን ጥናቱ መለየቱን ተገልጿል።

ግጭቶች፦
₀የ10 አመታት የልማት እቅድ በአግባቡ እንዳይተገበር፣
₀ኢኮሚኖሚ እንዳይረጋጋ፣
₀ድህነት እንዲጨምር፣ 
₀ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ፣
₀ሥራ አጥነት እንዲጨምር ማድረጋቸው በጥናቱ ተለይቷል።

ግብርና ለሀገራዊ ጠቅላላ ምርት ያለው አስተዋጽኦ በተለይ እ.ኤ.አ በ2024 እና 2025 አንድ ሦስተኛ ድርሻ እንዳለው፣ ይሁን እንጂ የመቀነስ ምጣኔ አሁንም እንደሚቀረው ዘገባው ጠቅሷል።

"ሆኖም የሀገሪቱ 32.4 በመቶ ኢኮኖሚ ለሚያስገኘው የግብርና ዘርፍ የብድር መጠን አነስተኛ በመሆኑ በተለይ እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ መጠኑ እየቀነሰ ከ3 በመቶ ማነሱ ተጠቅሷል" ተብሏል።
#Reporter

@ThiqahEth
😢20👍16🔥1🥰1😡1
ከእርስ በርስ ጦርነት ሸሽተው የተሰደዱ ሱዳናውያን በሊቢያ በረሃ እየሞቱ ነው።

ከቻድ ተነስተው ወደ ሊቢያ ሲጓዙ ከነበሩ 34 ሱዳናውያን ውስጥ ሰባቱ በሊቢያ በረሃ ሙተው መገኘታቸውን የኩፍላ አምቡላንስና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።

22 ሰዎችን ከአደጋ ማትረፍ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፣ አምስቱ ህፃናት ናቸው ተብሏል።

አምስት ስደተኞች እስካሁን ድረስ አልተገኙም ያለው ኩፍላ፣ ካሁን በፊት 260 ሱዳናውያን ህይወት መታደጉን ገልጿል።

787,000 ስደተኞች በሊቢያ እንደሚገኙ አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IMO) መረጃ ያመላክታል።
#africannews

@ThiqahEth
😢27👍4🔥21😭1
THIQAH
Photo
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል። አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" - ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአውሮፓ ላይ የጣሉትን የ50% ታሪፍ ለወር አራዘሙ።

ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ሰኔ ላይ ይተገበራል ያሉት ውሳኔ ወደ ሐምሌ እንዲዛወር መወሰናቸውን ገልጸዋል።

"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል" ያሉት ትራምፕ "አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" ሲሉ የተራዘመበትን ምክንያት አብራርተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከአውሮፓ በሚገቡ ምሬቶች ላይ የጣሉት ቀረጥ ባለፈው ሳምንት ከ30% ወደ 50% ከፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።
#irishexaminer

@ThiqahEth
😁8👍21🔥1😱1
"33,764 አቅማቸው ያልደረሱ ሴቶች አርግዘዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 3,368 ተማሪዎች በመሆናቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል" - የዝምባብዌ ትምህርት ሚኒስትር

በተለይ በትምህርት ቤት ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የልጃገረዶች እርግዝና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የዝምባብዌ ትምህርት ሚኒስትር ድዔታ አንጀሊን ጋታ ገልጸዋል።

በፈረንጆች 2024 ብቻ 33,764 አቅማቸው ያልደረሱ ሴቶች ማርገዛቸውን የተናገሩት ጋታ፣ ከእነዚህ ውስጥ 3,368 ተማሪዎች በመሆናቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል ብለዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በ2023 ደግሞ 4,000 ተማሪዎች በእርግዝና ምክንያት ከትምህርት ገበታ መገለላቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም ይህን ያለ እድሜ ጋብቻ ችግር ለመቅረፍ የማሰልጠኛ መፅሐፍት መዘጋጀቱንና በድምፅ የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ስርጭት መጀመሩን አብራርተዋል።

ዝምባዋብዌ ያለእድሜ ጋብቻን ለመከላከል 40,000 መምህራንን ማሰልጠን መጀመሯም ተገልጿል።
#bulawayo24news

@ThiqahEth
👍15😁8😱2🥰1🤔1😭1😡1
"ዩክሬን የሩሲያን ሲቪልና ማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ኢላማ አድርጋለች፤ በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃዎች ናቸው" - ዲሚትሪ ፔስኮቭ

የሩሲያና ዩክሬን ንግግርን ለማስቀጠል አሁንም መግባባት ላይ እንዳልተደረሰ፣ ለቀጣዩ ዙር መዘጋጀት እንደሚገባ ክሬምሊን ገለጸ።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ምን አሉ?

"ዩክሬን የሩሲያን ሲቪልና ማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ኢላማ አድርጋለች፤ በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃዎች ናቸው።

የዩክሬን የድርድር ሂደት መጀመሩ ስኬት ነው፤ ሩሲያ ሂደቱን ስላመቻቹ ለትራምፕ እና ለዩናይትድ ስቴትስ ምስጋና ታቀርባለች፡፡

በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ውጤታማ የሁለትዮሽ ግንኙነትን እንደገና የመገንባት ሂደት እየተጀመረ ነው።

የንግድ ተወካዮች በዛሬው እለት ከፑቲን ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ስለ ሥራቸው እና የልማት እቅዶች ይወያያሉ።

ፑቲን ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊዳን ጋር ዛሬ ይገናኛሉ። የፊዳን ጉብኝት በሩሲያ እና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት ትኩረቱን ያደርጋል" ማለታቸውን
#ስፑትኒክ ዘግቧል።

@ThiqahEth
👍82🥰1
THIQAH
#Amhara #Gojam "ስምንት ሹፌርና ረዳቶች ታግተዋል" - የሹፌሮች አንደበት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም በ17/09/2017 ዓ/ም ከ ዱርቤቴ ወተት አባይ (ቢኮሎ አባይ) መካከል ድብካን ጊዮርጊስ የሚባል ልዩ ቦታ ከቀኑ 8 ሰዓት 30 ገደማ 3 ኦባማ 1 ካሦኒ ሾፌርና ረዳት/በድምሩ 8 ረዳትና ሹፌር  ታግተው መወሰዳቸውን የሹፌሮች አንደበት ገልጿል። በምዕራብ ጎጃም ከ3 ቀና በፊት፣ ፍኖተ ሰላም…
#አማራክልል #እገታ

“በ10 ቀናት ብቻ በአማራ ክልል 31 ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል” - ማኀበሩ

ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር፣ “በ10 ቀናት ብቻ በአማራ ክልል 31 ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል” ሲል ነግሮናል።

"ገንዘብ ከፍለው የሚወጡ አሉ፤ ነገር ግን ማስፈራሪያ ስለሚደርስባቸው ከወጡ በኋላ የገጠማቸውን የመናገር ድፍረት አይኖራቸውም። ምንክንያቱም ተመልሰው በዚያው መንገድ ነው የሚያሽከረክሩት። የሕግ ከለላ የላቸውም" ብሏል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን ቢኮሎና ዱርቤቴ መካከል ባለ ቦታ ግንቦት 17/2017 ዓ/ም አራት ሹፌሮችና አራት ረዳቶች መታገታቸውን ገልጾ፣ “በየቦታው ያለው ነገር ከባድ ነው። ከቀን ቀን እየከፋ፣ እገታ ባልተለመደባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተስፋፋ ነው” ብሏል።

በደብረ ብርሃን መንገድ፣ እንጅባራ፣ ቻግኒ በቅርቡ እገታ መፈጸሙን ጠቅሶ፣ “ደቡብ ጎንደር ከጋይንት እስከ ወረታ መገንጠያ ከባድ መንገድ ሆኗል፤ ለየት ባለ መልኩ እገታ ይፈጸምበታል” ነው ያለው።

ማኀበሩ፣ “ድሮ 24 ሰዓት ይነዳባቸው በነበሩ መንገዶች አሁን ሙሉ ለሙሉ ቆሟል። በቀን ለ10 ሰዓታት ነው የሚነዳው። በዚህ ሳቢያ የግድያ ጥቃቱ ቀንሷል። እገታው ግን በጣሞ ተጧጡፏል” ሲልም ገልጿል።

@EyobTikuye  @ThiqhEth
😢11👍5😁21🙏1
"የህልውና ጉዳይ ስለሆነ እስራኤል አማራጭ የላትም ጦርነቱን ትቀጥላለች" - አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ

በኢትዮጵያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የእስራኤልን 58ኛ አመት የነፃነት ቀን ዛሬ አክብሯል።

ይህም "የእየሩሳሌም ቀን" ተብሎ ይጠራል። የእየሩሳሌም ቀን ማለት፣ እስራዔላዊያን በአረብ፣ እንግሊዝ፣ ኦቶማን ቱርክ አስተዳደር ስር ከቆየ ከ2000 ዓመታት በኋላ የኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራን ተረክበው ማስተዳደር የጀመሩበት ቀን ነው።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ፣ ከቲቃህ ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት በቆይታ ምን አሉ?

"እስራኤል ከአንድ አመት ተኩል በላይ በጦርነት ነው ያለችው። ይሄን ጦርነት ፈልጋው አይደለም የገባችው፣ ተደፍራ፣ ዜጓቿ ታርደው ነው።

በአሸባሪው ሀማስ ጥቃት ደርሶባት፣ የታፈኑ ዜጎቿን ለማስመለስ ነው። በእስራኤል ላይ በሰባት አቅጣጫ ነው ጦርነት የተከፈተው።

እነዚህ ሁሉ በኢራን አስተባባሪነት ነው የተከፈቱት። ስለዚህ እስራኤል የህልውና ጉዳይ ስለሆነ አማራጭ የላትም መከላከል አለባት" ብለዋል።

(ተጨማሪ አለን)

@EyobTikuye @ThiqahEth
😡8717👍14🤔2😢2🙏2🥰1
THIQAH
"የህልውና ጉዳይ ስለሆነ እስራኤል አማራጭ የላትም ጦርነቱን ትቀጥላለች" - አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ በኢትዮጵያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የእስራኤልን 58ኛ አመት የነፃነት ቀን ዛሬ አክብሯል። ይህም "የእየሩሳሌም ቀን" ተብሎ ይጠራል። የእየሩሳሌም ቀን ማለት፣ እስራዔላዊያን በአረብ፣ እንግሊዝ፣ ኦቶማን ቱርክ አስተዳደር ስር ከቆየ ከ2000 ዓመታት በኋላ የኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራን ተረክበው ማስተዳደር…
"'እስራኤል የዘር ጭፍጨፋ ታደርጋለች፣ የጦር ወንጀል ትሰራለች' የሚለው ውንጀላ ወደ ጥይት ተቀይሮ እነሆ ዋሽንግተን ላይ ሁለት ዲፕሎማቶች እንደተገደሉ እናውቃለን" - አምባሳደሩ

ከቲቃህ ኢትዮጵናያ ጋር ቆይታ የነበራቸው በኢትዮጵያ የእስራኤም ኤምባሲ አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ አክለው ምን አሉ?

"ሀማስ እስኪደመሰስ ድረስ እስራኤል" ጦርነቱን እንደምትቀጥል አስረግጠው ተናግረዋል።

ምን አሉ? "ሌሎች ሀገራት በእስራኤል ላይ የሚያቀርቡት ትችት በእውነቱ ፀብ አጫሪው ቡድን የያዛቸውን ልቀቁ በማለት ፈንታ እስራኤልን ለምን ተከላከልሽ ብለው ይወነጅላሉ።

ይሄ እውነት የጎደለው ነው፤ ኢ-ኢፍትሀዊ ስለሆነ፣ ሀማስ እስኪደመሰስ ድረስ እስራኤል ምንጊዜም ደህንነቷን ለማስጠበቅ ጦርነቱን ትቀጥላለች።

ሌላው እጅግ በጣም የሚያሳዝነው እስራኤልን በሀሰት የሚወነጅሉ፣ 'እስራኤል የዘር ጭፍጨፋ ታደርጋለች፣ የጦር ወንጀል ትሰራለች' የሚለው ውንጀላ ወደ ጥይት ተቀይሮ እነሆ ዋሽንግተን ላይም ሁለት ድፕሎማቶች እንደተገደሉ እናውቃለን።

ይሄ በሀሰት የሚደረገው ቅስቀሳና ለእስራኤል መጥፎ ስም የሚሰጡ አካላት ውጤት ነው። ስለዚህ እስራኤል ምንጊዜም ቢሆን ህልውናዋን ለማስቀጠል ጦርነቱን ትቀጥላለች ማለት ነው" ብለዋል።

@ByThiqahReporter @ThiqahEth
😡63👍223🥰1😱1😢1
#Ethiopia #Gambella

ስድስት ሰዎች በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች መገደላቸው ጋምቤላ ክልል ገለጸ።

የደቡብ ሱዳን መርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በመግባት ባደረሱት ጥቃት ንጹሐን መገደላቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነግሮናል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ጊሎ፣ ከትላንት ወዲያ ጠዋት ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ 4 ወንዶችና ሁለት ሴቶች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊው፣ “ታጣቂዎቹ ከብት መዝረፍ፣ ህፃናት መውሰድ የለመደባቸው ትሬንድ ነው። ትላንት ባሱ የተመታበት ቦታ ብዙ ጊዜ የወረዳው ከፍተኛ አካላት ትኩረት የሚያደርበት ነው። ግን የትላንቱ ክስተት በአጋጣሚ ከባድ ነበር” ብለዋል።

ቢሮው ከወር በፊት በሰጠን ቃል፣ “ በተለይ በዚህ ወርና እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ ታጣቂዎቹ የሚፈታተኑንበት ወቅት ነው። ኩሬዎች ስለሚደርቁ ለእነርሱ መምጣት አመቺ ይሆናል። አሁን ትንሽ፣ ትንሽ ምልክቶችን እያየን ነው። እየመጡ ነው" ብሎ ነበር።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ተነስተው የጋምቤላ ክልልን ድንበር ጥሰው በመግባት ልጆችን፣ ከብቶችን ሰርቀው በመውሰድ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ይታወቃል። Read More፡
https://t.me/tikvahethiopia/97152

@ThiqahEth @TikvahEthiopia
👍10😭3