እስራኤል በዛሬው ዕለት በፈጸመችው ጥቃት 23 ሰዎች ተገደሉ።
ከሟቾቹ ውስጥ ጋዜጠኞችና የእርዳታ ጊዜ ሰራተኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ጥቃቱ በካሃን የኑስ፣ በጃባሊያ እና ኑስራት ከተሞች ነው የተፈጸመው። #theindependent
@ThiqahEth

😢35👍6😭4🔥3😡2🥰1😱1
ተ.መ.ድ በደቡብ ሱዳን የሰላምና ፀጥታ ሁኔታው አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጸ።
በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ፣ የፖለቲካ ውጥረት ከጀመረበት ከባለፈው የካቲት ጀምሮ የሰብዓዊ እርዳታ መቀነሱን አስታውቀዋል።
በቅርቡ በደቡብ ሱዳን ወታደሮችና በሪክ ማቻር ታማኝ ጦር መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ቢያንስ 75 ሰዎች መሞታቸውንና 78 የሚደርሱት መቁሰላቸውን አብራርተዋል።
ባለፉት አራት ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን መፈናቀላቸውንም ገልጸዋል።#jursit

🔥4🤔2😭2❤1👍1😱1
ትራምፕ 60 ቢሊዮን ዶላር በማገዳቸው ከ150 ሺሕ በላይ የሄይቲ ዜጎች በኤችአይቪ ተጠቂ መሆናቸው ተሰማ።
የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) በጀት መቋረጥን ተከትሎ በሄይቲ የኤችአይቪ መድኃኒት እጥረት አጋጥሟታል።
ትራምፕ አሜሪካ ለውጭ እርዳታ ከምትመድበው በጀት 90% የሚሆነውን የዩኤስኤይድ ድጎማ በማቋረጣቸው ለአለማቀፍ እርዳታ ሊለቀቅ የነበረ 60 ቢሊዮን ዶላር አግደዋል።
ይህን ተከትሎ የእረዳታው መቋረጥ ጫና ከፈጠረባቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሄይቲ በአሁኑ ወቅት ከ150,000 በላይ የሚሆኑት ዜጎቿ የበሽታው ተጠቂ መሆናቸው ተገልጿል።
ካረቢያኗ ሄይቲ ከ2023 ወዲህ "በወሮበላ" ቡድኖች እየታመሰች ትገኛለች። #africannews

👍10🤔9❤2🥰1😁1😭1
5000 ቶን የምትመዝነው የጦር መርከብ በመስጠሟ ሦስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ጉዳዩን "የወንጀል ድርጊት ነው" ሲሉ የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ጆንግ ኡን ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ቺፍ ሜካኒኩ፣ የግንባታ ወርክ ሾፕ ኃላፊ እና የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ናቸው።
ሰሜን ኮሪያ የባህር ላይ ጦር መርከብ መስጠሟን ተከትሎ ጥፋተኛ ያለቻቸውን ሦስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አውላለች።
የጦር መርከቧ ፕሬዚደንት ኪም ጆንግ ኡን በተገኙበት ስራ ለመጀመር በሂደት ላይ በነበረችበት ወቅት ነው አደጋው የገጠማት ተብሏል።
5000 ቶን የምትመዝነው የጦር መርከብ በገጠማት አደጋ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
#dailymirror #thestandard

😁20👍11😭2🥰1😱1
#Amhara #Gojam
"ስምንት ሹፌርና ረዳቶች ታግተዋል" - የሹፌሮች አንደበት
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም በ17/09/2017 ዓ/ም ከ ዱርቤቴ ወተት አባይ (ቢኮሎ አባይ) መካከል ድብካን ጊዮርጊስ የሚባል ልዩ ቦታ ከቀኑ 8 ሰዓት 30 ገደማ 3 ኦባማ 1 ካሦኒ ሾፌርና ረዳት/በድምሩ 8 ረዳትና ሹፌር ታግተው መወሰዳቸውን የሹፌሮች አንደበት ገልጿል።
በምዕራብ ጎጃም ከ3 ቀና በፊት፣ ፍኖተ ሰላም አካባቢ ከ5 ቀን በፊት ከእንጅባራ ቻግኒ መንገድ እገታ መፈጸሙን አስታውሶ፣ "አሽከርካሪዎች ጥንቃቄን አድርጉ" ሲል አሳስቧል።

👍3😱2🔥1🥰1
"አሜሪካም ፈጣን የታሪፍ መፍትሄን ትፈልጋለች። ማጋነን አይገባም፣ ከአሜሪካ ጋር የጋራ መፍትሔ እንፈልጋለን" - ጀርመን
የጀርመን ምክትል መራሄ መንግስት እና የገንዘብ ሚኒስትር ላርስ ክሊንግቤል አሜሪካ እና አውሮፓ በታሪፍ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል።
"ማጋነን አይገባም፣ ከአሜሪካ ጋር የጋራ መፍትሄ እንፈልጋለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ "አሜሪካም ፈጣን የታሪፍ መፍትሄን ትፈልጋለች" ሲሉ ገልጸዋል።
ጀርመን 183 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ አሜሪካ በመላክ ከአውሮፓ ተቀዳሚ ሀገር ናት።
የትራምፕ መንግስት በአውሮፓ ምርቶች ላይ 50% ታሪፍ መጣላቸውን አስታውቀዋል። #reuters

😁9👍5🤔2😱2🥰1
#Ethiopia
“ፓሊሲዎቹ ድሃን ከድህነት ማውጣት አልቻሉም፤ ድህነትን ለመቀነስ ያመጡት ውጤትም ከዜሮ ያንሳል”- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን
የኢትዮጵያ መንግስት ለ22 ዓመታት ድህነትን ለመቀነስ ያወጣቸው ፓሊሲዎች ውጤት ከዜሮ እንደሚያንስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ጥናት አመለከተ።
አሶሴሽኑ እ.ኤ.አ ከ2001 እስከ 2023 ያለውን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አፈጻጸምን የተመለከተ ጥናት ሰሞኑን ይፋ ማድረጉን ሪፓርተር አስነብቧል።
ኢትዮጵያ እያደጉ ካሉ አገሮች አንዷ የነበረች ቢሆንም፣ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ማሽቆልቆሉን ጥናቱ መለየቱን ተገልጿል።
ግጭቶች፦
₀የ10 አመታት የልማት እቅድ በአግባቡ እንዳይተገበር፣
₀ኢኮሚኖሚ እንዳይረጋጋ፣
₀ድህነት እንዲጨምር፣
₀ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ፣
₀ሥራ አጥነት እንዲጨምር ማድረጋቸው በጥናቱ ተለይቷል።
ግብርና ለሀገራዊ ጠቅላላ ምርት ያለው አስተዋጽኦ በተለይ እ.ኤ.አ በ2024 እና 2025 አንድ ሦስተኛ ድርሻ እንዳለው፣ ይሁን እንጂ የመቀነስ ምጣኔ አሁንም እንደሚቀረው ዘገባው ጠቅሷል።
"ሆኖም የሀገሪቱ 32.4 በመቶ ኢኮኖሚ ለሚያስገኘው የግብርና ዘርፍ የብድር መጠን አነስተኛ በመሆኑ በተለይ እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ መጠኑ እየቀነሰ ከ3 በመቶ ማነሱ ተጠቅሷል" ተብሏል። #Reporter

😢20👍16🔥1🥰1😡1
ከእርስ በርስ ጦርነት ሸሽተው የተሰደዱ ሱዳናውያን በሊቢያ በረሃ እየሞቱ ነው።
ከቻድ ተነስተው ወደ ሊቢያ ሲጓዙ ከነበሩ 34 ሱዳናውያን ውስጥ ሰባቱ በሊቢያ በረሃ ሙተው መገኘታቸውን የኩፍላ አምቡላንስና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።
22 ሰዎችን ከአደጋ ማትረፍ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፣ አምስቱ ህፃናት ናቸው ተብሏል።
አምስት ስደተኞች እስካሁን ድረስ አልተገኙም ያለው ኩፍላ፣ ካሁን በፊት 260 ሱዳናውያን ህይወት መታደጉን ገልጿል።
787,000 ስደተኞች በሊቢያ እንደሚገኙ አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IMO) መረጃ ያመላክታል።#africannews

😢27👍4🔥2❤1😭1
THIQAH
Photo
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል። አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአውሮፓ ላይ የጣሉትን የ50% ታሪፍ ለወር አራዘሙ።
ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ሰኔ ላይ ይተገበራል ያሉት ውሳኔ ወደ ሐምሌ እንዲዛወር መወሰናቸውን ገልጸዋል።
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል" ያሉት ትራምፕ "አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" ሲሉ የተራዘመበትን ምክንያት አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከአውሮፓ በሚገቡ ምሬቶች ላይ የጣሉት ቀረጥ ባለፈው ሳምንት ከ30% ወደ 50% ከፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።#irishexaminer

😁8👍2❤1🔥1😱1
"33,764 አቅማቸው ያልደረሱ ሴቶች አርግዘዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 3,368 ተማሪዎች በመሆናቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል" - የዝምባብዌ ትምህርት ሚኒስትር
በተለይ በትምህርት ቤት ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የልጃገረዶች እርግዝና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የዝምባብዌ ትምህርት ሚኒስትር ድዔታ አንጀሊን ጋታ ገልጸዋል።
በፈረንጆች 2024 ብቻ 33,764 አቅማቸው ያልደረሱ ሴቶች ማርገዛቸውን የተናገሩት ጋታ፣ ከእነዚህ ውስጥ 3,368 ተማሪዎች በመሆናቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በ2023 ደግሞ 4,000 ተማሪዎች በእርግዝና ምክንያት ከትምህርት ገበታ መገለላቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም ይህን ያለ እድሜ ጋብቻ ችግር ለመቅረፍ የማሰልጠኛ መፅሐፍት መዘጋጀቱንና በድምፅ የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ስርጭት መጀመሩን አብራርተዋል።
ዝምባዋብዌ ያለእድሜ ጋብቻን ለመከላከል 40,000 መምህራንን ማሰልጠን መጀመሯም ተገልጿል። #bulawayo24news

👍15😁8😱2🥰1🤔1😭1😡1
"ዩክሬን የሩሲያን ሲቪልና ማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ኢላማ አድርጋለች፤ በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃዎች ናቸው" - ዲሚትሪ ፔስኮቭ
የሩሲያና ዩክሬን ንግግርን ለማስቀጠል አሁንም መግባባት ላይ እንዳልተደረሰ፣ ለቀጣዩ ዙር መዘጋጀት እንደሚገባ ክሬምሊን ገለጸ።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ምን አሉ?
"ዩክሬን የሩሲያን ሲቪልና ማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ኢላማ አድርጋለች፤ በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃዎች ናቸው።
የዩክሬን የድርድር ሂደት መጀመሩ ስኬት ነው፤ ሩሲያ ሂደቱን ስላመቻቹ ለትራምፕ እና ለዩናይትድ ስቴትስ ምስጋና ታቀርባለች፡፡
በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ውጤታማ የሁለትዮሽ ግንኙነትን እንደገና የመገንባት ሂደት እየተጀመረ ነው።
የንግድ ተወካዮች በዛሬው እለት ከፑቲን ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ስለ ሥራቸው እና የልማት እቅዶች ይወያያሉ።
ፑቲን ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊዳን ጋር ዛሬ ይገናኛሉ። የፊዳን ጉብኝት በሩሲያ እና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት ትኩረቱን ያደርጋል" ማለታቸውን #ስፑትኒክ ዘግቧል።

👍8❤2🥰1