THIQAH
9.39K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
#Ethiopia #FnoteSelam

"የካሶኒና ኦባማ ሹፌሮች፣ በድምሩ 2 ታግተው ተወስደዋል" - የሹፌሮች አንደበት

"በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ዛሬ  (15/09/2017 ዓ/ም) ከፍኖተ ሰላም ከተማ በ3 ኪሎ ሜትር እርቀት ከሆዳንሽ ፍኖተ ሰላም መሀል 10 ሰዓት 30 ላይ ካሶኒና ኦባማ ሹፌሮች፣ በድምሩ 2 ታግተው ተወስደዋል። 

በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የአሽከርካሪዎች፣ ረዳቶችና ተሳፋሪዎች እገታ በዝምታ መታየቱ፣ መንግስትም አጋችን ቴክኖሎጅ ተጠቅሞ አሳዶ ለመቅጣት ባለመንቀሳቀሱ፣ አሽከርካሪውም በሙያ አጋሩ የሚደርስን ግፍ አውግዞ መብቱን ለማስከበር ፍትህን ለመጠየቅ ባለመነሳቱ ምክንያት እገታ እንዳይቆም አድማሱን አስፍቶ በየቦታው ብዙዎች እገታን እንደ ክፍት የስራ መስክ ቆጥረው እንዳሻቸው እንዲሆኑ በርን ከፍቷል" ብሏል የሹፌሮችን ውሎ የሚከታተለው የሹፌሮች አንደበት።

@ThiqahEth
👍8🤔2😢21
ትራምፕ በአውሮፓ ገበያ ላይ የ50% ታሪፍ እንደሚጥሉ አስታወቁ።

ካሁን በፊት ጥለውት ከነበረው 30% ወደ 50% ከፍ ለማድረግ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

አዲሱ የታሪፍ ውሳኔ ከመጪው ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
#kyivpost

@ThiqahEth
😁12🤔7🥰4👍3
ሁቲ በእስራኤል አየር መንገድ ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ሦስት ጥቃቶችን ፈጸመ።

ቡድኑ ሀይፐርሶኒክ ሚሳዔልን በመጠቀም የቤንጉሪን አየር መንገድን ኢላማ ማድረጉን አስታውቋል።

የሁቲ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ፣ "የአየር መንገዱን ሥራ አስተጓጉለናል፤ ግባችንን በሚገባ አሳክተናል" ብሏል።

ስለአየር መንገዱ ጥቃት ከእስራኤል በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።  
#anadoluagency

@ThiqahEth
👍29🤔5🥰3😁2😱21🔥1
"በዓለም አቀፍ ደረጃ 500,000 ሰዎች የፊስቱላ ተጠቂ ናቸው" - ተመድ

በተመድ የስነተዋልዶ ጤና ዳይሬክተር ሲማ ባሁስ፣ "ዝምተኛ ገዳይ" ሲሉ የጠሩት የፊስቱላ በሽታ በአሁኑ ወቅት ትልቅ የጤና ስጋት ሆኗል ብለዋል።

"በዓለም አቀፍ ደረጃ 500,000 ሰዎች የፊስቱላ ተጠቂ ናቸው" ነው ያሉት።

ባሁስ ከ2003 እስከ 2024 ባሉት 21 አመታት 150,000 ለሚሆኑ ሴቶች የፊስቱላ ህክምና መደረጉን ተናግረዋል። 
#peoplesgazette

@ThiqahEth
😭8👍3🥰21😁1
ሩሲያ እና ዩክሬን ለሁለተኛ ጊዜ የእስረኞች ልውውጥ አደረጉ።

ዛሬ ብቻ 307 የሩሲያ ወታደሮች ከዩክሬን ተለቀው ወደ ሀገራቸው ገብተዋል ተብሏል።

ነገር ግን ሩሲያ በዛሬው እለት በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት 15 ሰዎች መጎዳታቸውን የኪቭ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
#radiofreeeurope

@ThiqahEth
😁12👍5😡2🔥1
"ከአሜሪካ ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ተከፍቶብናል" - የአውሮፓ ህብረት ንግድ ኮሚሽን

የአውሮፓ ህብረት የንግድ ኮሚሽን"አውሮፓን ለማዳን አራት ሳምንታት አሉን" ሲል ገለጸ።

የህብረቱ የንግድ ኮሚሽነር ማሮስ ሰቭኮቪች "ከአሜሪካ ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ተከፍቶብናል" ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ በአውሮፓ ገበያ ላይ 50% ቀረጥ መጨመሯን ያስታወቁት ሰቭኮቪች "አውሮፓን የምናድንበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገናኛለን"ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር የጣለው ታሪፍ "ምክንያታዊ እና ግልጽነት የጎደለው ነው" ሲሉ ተችተዋል።
#independent

@ThiqahEth
👍12🔥3🥰1🤔1
THIQAH
Photo
ሩሲያ እና ዩክሬን 1, 000 እስረኞችን ለመልቀቅ ያደረጉት ስምምነት ተጠናቀቀ።

በዛሬው እለት 303 የዩክሬን ወታደሮች ከሩሲያ እስር ቤት ተለቀው ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።

ሰሞኑን በመጀመሪያው ዙር 390፣ ትላንት ደግሞ 307 እስረኞችን ተለዋውጠዋል።

በጦርነት ውስጥ የሚገኙት ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርቡ በቱርክ ባደረጉት ስብሰባ 1000 እስረኞችን ለመለዋወጥ ተስማምተው ነበር።
#kyivpost

ሁለቱ ሀገራት ከሳምንት በፊት አድርገውት የነበረው እስረኞችን የመለዋወጥ ስምምነት፥
https://t.me/thiqahEth/3200

@ThiqahEth
👍9🤔21🔥1
#Ethiopia #የዝንጀሮፈንጣጣ

“የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ በሕመማሙ መያዛቸው ከተጠረጠሩ ታማሚዎች በወሰደው ናሙና በMpox ቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቱን አረጋግጧል” - ኢንስቲትዩቱና ሚኒስቴሩ

በኢትዮጵያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ/Mpox የተያዘ ሰው መገኘቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ጤና ሚኒስቴር የጋራ መግለጫቸው ዛሬ አስታውቀዋል።

በቫይረሱ የተጠቃው የ21 ቀን እድሜ ህፃን ሲሆን እናቱም ለቫይረሱ መጋለጣቸው በምርመራ መረጋገጡ ተነግሯል።

(የጋራ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)


@ThiqahEth
😱5😢3👍1😁1😭1
THIQAH
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪዲዮ፦ ከእስር የተፈቱ የሩሲያ ወታደሮች ባንዲራቸውን በማውለብለብ ታሪክና ባህላቸውን ማክበራቸው ተሰማ።

ከእስር የተፈቱ የሩሲያ ወታደሮች የሩሲያ፣ የሶቪየት ኅብረት እና የሩሲያ ግዛት ባንዲራዎችን በመያዝ በሀገራቸው ታላቅ ታሪክ እንደሚኮሩ አሳይተዋል።
#Sputnik

@ThiqahEth
👍217🥰4😁2😢1
እስራኤል በዛሬው ዕለት በፈጸመችው ጥቃት 23 ሰዎች ተገደሉ።

ከሟቾቹ ውስጥ ጋዜጠኞችና የእርዳታ ጊዜ ሰራተኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ጥቃቱ በካሃን የኑስ፣ በጃባሊያ እና ኑስራት ከተሞች ነው የተፈጸመው።
#theindependent

@ThiqahEth
😢35👍6😭4🔥3😡2🥰1😱1