THIQAH
9.39K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
#DebubEthiolpia #Gamozone

“በእኛ አካባቢ ብቻ ሰሞኑን ስድስት ሰዎች ተገድለዋል። ትላንት ብቻ ከ50 በላይ ቤቶች ናቸው ከነሙሉ እቃቸው  የተቃጠሉት” - ነዋሪዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ያሉ ነዋሪዎች ግድያና የቤት፣ ንብረት ቃጠሎ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ነዋሪዎቹና የምክር ቤት አባል ነግረውናል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ነዋሪ፣ "ሰሞኑን አንድ ሰው ተገድሎ ሬሳው ተነስቷል፤ ዱራ ላይም ሁለት ሴቶች ተገድለዋል፤ ሬሳቸውን ለማንሳት ግን አይፈቅዱልንም። ያለፈው እሁድም ድቀሳ አካባቢ ሦስት ሰዎች ገድለዋል” ብለዋል።

“ሰሞኑን ብቻ ከ50 በላይ ቤቶች ናቸው ከሙሉ እቃቸው የተቃጠሉት” ብለው፣ ይህንን የሚያደርጉት “የጸጥታ አካላት” እንደሆኑ ገልጸው፣ “ዱራ፣ ማሃይላ ቦላ፣ ካውለ ዘንሳ፣ ሀውሻ፣ ጎንዳ፣ ጉሮ፣ ጉቡዤ፣ ካይበኛ፣ ኦይባለ፣ ሳራሬ፣ ጋባ፣ ሳይታ" ቦታዎች ላይ ጥቃቱ መፈጸሙንም አስረድተዋል።

ሌላኛው ቤታቸው የተቃጠለባቸው አርሶ አደር፣ “በአንድ ቀን ብቻ ከ50 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል” ብለው፣ “ልብስ፣ 20 ኩንታል ጤፍ፣ 30 ኩንታል በቆሎ፣ 25 ኩንታል ማሽላ፣ የቡናና የእንሰት ተክል በአድማ በታኝ ኃይሎች ተቃጥለዋል” ነው ያሉት።

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ፣ "ዛሬ አራት ሰዎች በአድማ በታኝ ተወስደዋል። ነዋሪው ማሳው ላይ እየታደነ እየተገደለ ነው። ወዴት እንሂድ?" ብለው፣ ይህ ጥቃት የደረሰባቸው፣ "ለምን ኢዜማን መረጣችሁ?" በሚልና በወረዳነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘት መሆኑን አስረድተዋል።

(አንድ የምክር ቤት አባል በጉዳዩ የሰጡንን ንግግርና ማሳሰቢያ በቀጣይ ይጠብቁ)

@EyobTikuye  @ThuiqahEth
🤔9👍32🥰1😱1
THIQAH
Photo
#DebubEthiopia #GamoZone

“በዘይሴ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ በደሎች እጅግ በጣም ሰፊ ናቸው። አንዱ ህዝቡን አሳዶ በጦር መሳሪያ መግደል ነው” - የፓርላማ አባል

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘይሴ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ አብርሃም አሞሸ፣ "በዘይሴ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ በደሎች እጅግ በጣም ሰፊ ናቸው። አንዱ ህዝቡን አሳዶ በጦር መሳሪያ መግደል ነው" አሉ።

"ከዛ ባለፈ አሁን የነዋሪዎቹን ቤቶቻቸውን እያቃጠሉባቸው ነው" ያሉት የምክር ቤት አባሉ፣ "በተለይ ከግንቦት 3/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ህዝቡ መፈናቀል ላይ ነው" ብለዋል።

"የጋሞ ዞን መደበኛ ፓሊስ፣ በኢመደበኛ አደረጃጀት በጋሞ በተደራጁ በቀድሞ የጦር ተመላሽ አባላት፣ በሚሊሻዎች በአጠቃላይ የዘይሴን ህዝብ ከገዛ ከዘይሴ ምድር ላይ አጥፍቶ ምድሩን የመውረስ ነው ስትራቴጂ ቀይሰው እየሰሩ ያሉት” ነው ያሉት።

ችግሩ ከምርጫ ጀምሮ በየወቅቱ እየተከሰተ የቆዬና ያለ እንደሆነ፣ ከዚህ ቀደም በፓርላማ ተገኝተው ደጋግመው ትኩረት እንዲሰጥ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጭምር ቢያሳስቡም መፍትሄ እንዳልተሰጠ ተወካዩ ገልጸዋል።

መፍትሄውን በተመለከተም፣ ጥቃት እየተፈጸመበት ባለው ቦታ ገለልተኛ የሆኑት ፌደራል ፓሊስና መከላከያ ሠራዊት በአስቸኳይ እንዲመደቡ አሳስበዋል።

@EyobTikuye @ThiqahEth
👍6🔥2😱2🥰1
THIQAH
#DebubEthiopia #GamoZone “በዘይሴ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ በደሎች እጅግ በጣም ሰፊ ናቸው። አንዱ ህዝቡን አሳዶ በጦር መሳሪያ መግደል ነው” - የፓርላማ አባል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘይሴ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ አብርሃም አሞሸ፣ "በዘይሴ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ በደሎች እጅግ በጣም ሰፊ ናቸው። አንዱ ህዝቡን አሳዶ በጦር መሳሪያ መግደል ነው" አሉ። "ከዛ ባለፈ አሁን…
"እስካሁን ከ25 ሰዎች በላይ ተገድለዋል" - አቶ አብርሃም አሞሸ

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ "የጸጥታ አካላት፤ በነዋሪዎች የሚያደርሱት ጥቃት" ትኩረት እንዲሰጠው በተወካዮች ምክር ቤት የዘይሴ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ አብርሃም አሞሸ አሳስበዋል።

"ይህንን የልዩ ዞን ጥያቄ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ዙር ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ አቅርቤያለሁ ይህ አሁን የተጀመረ ሳይሆን ከምርጫ ማግስት ጀምሮ እየተደረገ ያለ ድርጊት ነው" ብለዋል።

ይሁን እንጂ መፍትሄ ባለመገኘቱ፣ "እስካሁን 25 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። በየጊዜው ጥያቄዎችን እያነሳን እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎችና ያላግባብ የሚደረጉ እስሮችን ራሳቸው እየፈጸሙ በሕዝቡ ላይና በኢዜማ ፓርቲ እንደተፈጸመ የሚያሳስቡትን ጉዳይ ስናገር ኖሬያለሁ" ነው ያሉት።

"ለሰላም ሚኒስትርም ድረስ ጥያቄ አቅርቤያለሁ፣ አሁንም ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እያቀረብኩ ነው" ብለዋል።


@EyobTikuye   @ThiqahEth
👍6🔥2🥰1😭1
THIQAH
#EthiopianHealthProfessionals “በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለው የፈደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ  ዝምታ መርጧል እንጂ የስራ ማቆም አድማ አልከለከለም” - የጤና ባለሙያዎች ሕግ ክፍል የሥራ ማቆም አድማ እያደረጉ ያሉ ባለሙያዎች የሕግ ክፍል ዛሬ የፌደራል ፓሊስ 47 ባለሙያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተንተርሶ በሰጠው አስተያየት፣ " ፓሊስ የሕግ…
#EthiopianHealthProfessionals

"ሁሉም የጤና ተቋማት ላይ ሙሉ አገልግሎት እየተሰጠ ነው" - ጤና ሚኒስቴር

"በተለያዩ ክልሎች በተለይ በትግራይ ክልል በሁሉም ጤና ተቋማት በሚባል ደረጃ ሥራ ቆሟል" - ጤና ባለሙያዎች

ብሔራዊ ቴሌቪዥን በዘገባው ምን አለ?

"ባለፉት ቀናት አልፎ፣ አልፎ በአንዳንድ የሥራ ክፍሎች የነበሩ የሥራ መስተጓጎሎች አሁን በመላ ሀገሪቱ በሙሉ ወደ ሥራ መገባቱን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ከሰሞኑ የተፈጠረውን ክስተት መነሻ በማድረግ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው የሚኖሩ ችግሮችን ለመፍታት ሰፊ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ተናግረዋል።

የህክምና ባልሞያዎች ያሏቸውን ጥያቄዎች ሁሉ ሥራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ መጠየቅ እንዲችሉ ማድረግ ሊለመድ የሚገባ ነው ያሉት ዴዔታው መንግስትም ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል።

በሥራ ያሉትን ባለሞያዎች አመስግነናል ህብረተሰቡም በብዛት ወደ ህክምና ተቋማት መሄዱን ተመልክተናል። እንዲህ አይነት ክስተቶች በሴክተራችን በድጋሜ እንዳይመጣ በቀጣይነት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል" ብሏል።

የጤና ባለሙያዎች ደግሞ፣ "በተለያዩ ክልሎች በተለይ በትግራይ ክልል በሁሉም ጤና ተቋማት በሚባል ደረጃ ሥራ ቆሟል" ብለውናል።

@ThiqahEth
😁14👍62🔥1😡1
#Ethiopia #FnoteSelam

"የካሶኒና ኦባማ ሹፌሮች፣ በድምሩ 2 ታግተው ተወስደዋል" - የሹፌሮች አንደበት

"በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ዛሬ  (15/09/2017 ዓ/ም) ከፍኖተ ሰላም ከተማ በ3 ኪሎ ሜትር እርቀት ከሆዳንሽ ፍኖተ ሰላም መሀል 10 ሰዓት 30 ላይ ካሶኒና ኦባማ ሹፌሮች፣ በድምሩ 2 ታግተው ተወስደዋል። 

በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የአሽከርካሪዎች፣ ረዳቶችና ተሳፋሪዎች እገታ በዝምታ መታየቱ፣ መንግስትም አጋችን ቴክኖሎጅ ተጠቅሞ አሳዶ ለመቅጣት ባለመንቀሳቀሱ፣ አሽከርካሪውም በሙያ አጋሩ የሚደርስን ግፍ አውግዞ መብቱን ለማስከበር ፍትህን ለመጠየቅ ባለመነሳቱ ምክንያት እገታ እንዳይቆም አድማሱን አስፍቶ በየቦታው ብዙዎች እገታን እንደ ክፍት የስራ መስክ ቆጥረው እንዳሻቸው እንዲሆኑ በርን ከፍቷል" ብሏል የሹፌሮችን ውሎ የሚከታተለው የሹፌሮች አንደበት።

@ThiqahEth
👍8🤔2😢21
ትራምፕ በአውሮፓ ገበያ ላይ የ50% ታሪፍ እንደሚጥሉ አስታወቁ።

ካሁን በፊት ጥለውት ከነበረው 30% ወደ 50% ከፍ ለማድረግ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

አዲሱ የታሪፍ ውሳኔ ከመጪው ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
#kyivpost

@ThiqahEth
😁12🤔7🥰4👍3
ሁቲ በእስራኤል አየር መንገድ ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ሦስት ጥቃቶችን ፈጸመ።

ቡድኑ ሀይፐርሶኒክ ሚሳዔልን በመጠቀም የቤንጉሪን አየር መንገድን ኢላማ ማድረጉን አስታውቋል።

የሁቲ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ፣ "የአየር መንገዱን ሥራ አስተጓጉለናል፤ ግባችንን በሚገባ አሳክተናል" ብሏል።

ስለአየር መንገዱ ጥቃት ከእስራኤል በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።  
#anadoluagency

@ThiqahEth
👍29🤔5🥰3😁2😱21🔥1
"በዓለም አቀፍ ደረጃ 500,000 ሰዎች የፊስቱላ ተጠቂ ናቸው" - ተመድ

በተመድ የስነተዋልዶ ጤና ዳይሬክተር ሲማ ባሁስ፣ "ዝምተኛ ገዳይ" ሲሉ የጠሩት የፊስቱላ በሽታ በአሁኑ ወቅት ትልቅ የጤና ስጋት ሆኗል ብለዋል።

"በዓለም አቀፍ ደረጃ 500,000 ሰዎች የፊስቱላ ተጠቂ ናቸው" ነው ያሉት።

ባሁስ ከ2003 እስከ 2024 ባሉት 21 አመታት 150,000 ለሚሆኑ ሴቶች የፊስቱላ ህክምና መደረጉን ተናግረዋል። 
#peoplesgazette

@ThiqahEth
😭8👍3🥰21😁1
ሩሲያ እና ዩክሬን ለሁለተኛ ጊዜ የእስረኞች ልውውጥ አደረጉ።

ዛሬ ብቻ 307 የሩሲያ ወታደሮች ከዩክሬን ተለቀው ወደ ሀገራቸው ገብተዋል ተብሏል።

ነገር ግን ሩሲያ በዛሬው እለት በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት 15 ሰዎች መጎዳታቸውን የኪቭ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
#radiofreeeurope

@ThiqahEth
😁12👍5😡2🔥1
"ከአሜሪካ ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ተከፍቶብናል" - የአውሮፓ ህብረት ንግድ ኮሚሽን

የአውሮፓ ህብረት የንግድ ኮሚሽን"አውሮፓን ለማዳን አራት ሳምንታት አሉን" ሲል ገለጸ።

የህብረቱ የንግድ ኮሚሽነር ማሮስ ሰቭኮቪች "ከአሜሪካ ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ተከፍቶብናል" ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ በአውሮፓ ገበያ ላይ 50% ቀረጥ መጨመሯን ያስታወቁት ሰቭኮቪች "አውሮፓን የምናድንበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገናኛለን"ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር የጣለው ታሪፍ "ምክንያታዊ እና ግልጽነት የጎደለው ነው" ሲሉ ተችተዋል።
#independent

@ThiqahEth
👍12🔥3🥰1🤔1
THIQAH
Photo
ሩሲያ እና ዩክሬን 1, 000 እስረኞችን ለመልቀቅ ያደረጉት ስምምነት ተጠናቀቀ።

በዛሬው እለት 303 የዩክሬን ወታደሮች ከሩሲያ እስር ቤት ተለቀው ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።

ሰሞኑን በመጀመሪያው ዙር 390፣ ትላንት ደግሞ 307 እስረኞችን ተለዋውጠዋል።

በጦርነት ውስጥ የሚገኙት ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርቡ በቱርክ ባደረጉት ስብሰባ 1000 እስረኞችን ለመለዋወጥ ተስማምተው ነበር።
#kyivpost

ሁለቱ ሀገራት ከሳምንት በፊት አድርገውት የነበረው እስረኞችን የመለዋወጥ ስምምነት፥
https://t.me/thiqahEth/3200

@ThiqahEth
👍9🤔21🔥1