THIQAH
9.38K subscribers
5.11K photos
56 videos
1 file
40 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
#Ethiopia

ፎቶ፦ ባለፉት አመታት በታጠቁ አካላት ከተገደሉ 250 በላይ ሹፌሮች መካከል ማኀበሩ 90 የሚሆኑትን አጋርቶናል።

ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር ባለፉት ዓመታት ከ250 በላይ ሹፌሮች ለሥራ በወጡበት በታጠቁ አካላት እንደተገደሉ በየወቅቱ ከሚያስባስባቸው መረጃዎች እንደተረዳ ገልጿል።

በታጣቂዎች ከተገደሉት ሹፌሮች መካከል አብዛኛዎቹ ቤተሰብ አስተዳዳሪና ወላጆች ሲሆኑ፣ 90 የሚሆኑ ሟቾችን ፎቶም አጋርቶናል።

ማኀበሩ በተደጋጋሚ እንደሚገልጸው፣ በተለያዩ አካባቢዎች በታጠቂዎች የሚፈጸም ጥቃት መቆም አልቻለም። ጩኸቱ ቢበዛም የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ መፍትሄ አልሰጡም።

@ThiqahEth
😭62👍6😡4
የኢትዮጵያዊያኑ ተማጽኖ!

“ብዛታችን 247 ኢትዮጵያውያን ስንሆን ህይወታችን በጣም አስጊ ሁኔታ ላይ ነው” - ኢትዮጵያዊያን በታይላንድ

ከማንናማር ከእገታ ወጥተው ታይላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፤ “ብዛታችን 247 ኢትዮጵያውያን ስንሆን ህይወታችን በጣም አስጊ ሁኔታ ላይ ነው። እዚህ ወጥተን ወደ ሀገራችን መመለስ ለኛ ዳግም መወለድ ነው” ሲሉ ተማጸኑ።

ዝርዝሩን ከአፍታ በኋላ ይጠብቁ!

@ThiqahEth
😢12👍3😱1
THIQAH
የኢትዮጵያዊያኑ ተማጽኖ! “ብዛታችን 247 ኢትዮጵያውያን ስንሆን ህይወታችን በጣም አስጊ ሁኔታ ላይ ነው” - ኢትዮጵያዊያን በታይላንድ ከማንናማር ከእገታ ወጥተው ታይላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፤ “ብዛታችን 247 ኢትዮጵያውያን ስንሆን ህይወታችን በጣም አስጊ ሁኔታ ላይ ነው። እዚህ ወጥተን ወደ ሀገራችን መመለስ ለኛ ዳግም መወለድ ነው” ሲሉ ተማጸኑ። ዝርዝሩን ከአፍታ በኋላ ይጠብቁ! @ThiqahEth
“እዚህ ያለው ህይወት ጣረ ሞት ነው” - ለሥራ የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን

ለሥራ ወደ ታይላንድ የተሰደዱ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ጭምር ኢትዮጵያዊያን፣ ውላቸው ታጥፎ በማይናማር ታግተው ቆይተው የወጡትም ቢሆኑ መንግስት ትኩረት ባለመስጠቱ የድረሱልን ጥሪ ለፈፉ።

ኢትዮጵያዊያኑ፦

“ይሄንን መልዕክት የምንጽፍላቹ ማይናማር ታይላንድ ድንበር ከDKBA ወታደር ካምብ ነው።

እዚህ የገጠመንና ያለው ህይወት ጣረ ሞት ነው። መገረፈ፣ መደበደበ፣ መነበርከክ፣ ጨለማ ክፍል መታሰር፣ መሰቀልና የኤሌተሪክ ሾክ እንዲሁም ከአንድ ድርጅት ወደ ሌላ መሸጥ ነው።

ከእገታ የወጣነው በፈጣሪ ተዐምር ነው፤ ወጥተን አሁን ያለንበት የወታደር ካምብ ከገባን አንድ ወር ሊሆነን ነው። 

ከድርጅቱ (ከማይናማር) 5 ኪሎ ሜትር ርቀት እንገኛለን።  

ብዛታችን 247 ኢትዮጰዉያን ስንሆን ህይወታችን በጣም አሰጊ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ረሃብ አለ፤ በጣም እያደከመን ነው፤ በቂ የመጠጥ ውሃ እያገኘን አይደለም፤ እየታመምን ነው። በጣም ፈታኝ የሆነብን ነገር እኛ ውስጥ የተለየ አላማ ያላቸው የሚረቤሹ አሉ።

እዚህ ወጥተን ወደ ሀገራችን መመለስ ለኛ ዳግም መወለድ ማለት ነው። እባካችሁ የኢትዮጰያ ህዝብና መንግስት ከዚህ ስቃይ ታደጉን፤ ድረሱልን” ሲሉ ተማጽነዋል።

@ThiqahEth
😢23👍41
ጀነራሉና በርካታ ሰዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሄሊኮፕተር ላይ በተፈጸመ ጥቃት ተገደሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄሊኮፕተር ደቡብ ሱዳን ላይ በተፈጸባት ጥቃት የሱዳን ጦር ጄኔራልን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

ጥቃቱ የደረሰው፣ ሄሊኮፕተሯ ግጭት በተፋፋመበት የላይኛው ናይል ተፋሰስ ግዛት የአገሪቱን ጦር አባላት ልታስወጣ በምትሞክርበት ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል።

በዚህም አንድ የሄሊኮፕተሯ ሠራተኛ፣ ጄኔራሉና፣ በርካታ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች መገደላቸውን በደቡብ ሱዳን የመንግስታቱ ድርጅት አስታውቋል።

ተፈጸመ የተባለው ጥቃት በጦር ወንጀለኛነት ሊፈረጅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ከወዲሁ ገልጿል።

@ThiqahEth
😭14👍43
የደቡብ ኮሪያ  ፕሬዝዳንት ከእስር መለቀቃቸው ተሰማ።

የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ይግባኝ ላለመጠየቅ በመወሰኑ ዛሬ ከእስር ተለቀዋል፡፡

ዮን በእ.አ.አ ታህሳስ 3 ቀን ባሳለፉትና ለአጭር ጊዜ በቆየው የማርሻል ህግ ምክንያት ከስራቸው እንደታገዱ የሚቆዩ ሲሆን፣ በአመፅ የቀረበባቸው ክስም እንዳለ ይቆያል ተብሏል፡፡

የወንጀል ጉዳዩ በስልጣን ላይ በሚኖራቸው ቆይታ ዙርያ ከሚታየው የፍርድ ሂደት የተለየ ሲሆን፣ በህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ወደ ሥራ ይመለሱ፣ ከስልጣናቸው ይነሱ በሚለው ጉዳይ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
 
@ThiqahEth
6👍2
THIQAH
ሶሪያ! በሶሪያ በተቀሰቀሰ ግጭት 70 የሚደርሱ ሰዎች ተገደሉ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በሶሪያ ጦርና በቀድሞው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ታማኞች መካከል ነው ተብሏል፡፡ በሽርን በኃይል በማስወገድ ስልጣን የተቆጣጠረው የሀያት ታህሪር አልሻም መንግስት የቀድሞው ፕሬዜዳንት ወደተወለዱበት የአለዋይት ማህበረሰብ ከፍተኛ ኃይል ያለው ጦር ማሰማራቱ ተዘግቧል፡፡ የሽር አላሳድ መንግስት በኃይል ከተወገደ በኋላ…
ሶሪያ!

በሶሪያ የሟቾች ቁጥር 600 ደረሰ።

በሶሪያ የሽግግር መንግስት እና በአሳድ ታማኝ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ጦርነት ዛሬም ቀጥሏል።

ሁሉም ሟቾች የቀድሞው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የዘር ሀረግ የሚመዘዝበት የአልዋይቲ አናሳ ማህበረሰብ አባል መሆናቸው ተገልጿል።

በጦርነቱ ከፍተኛ የቤትና ንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ ነው ተብሏል። #burnabynow

@ThiqahEth
😱16😢11👍2
"ሁለት ስደተኞች ሙተዋል፤ 186ቱ እስካሁን ድረስ አልተገኙም"  - IOM

ዓለማቀፍ ስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ስደተኞችን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 4 ጀልባዎች መገልበጣቸውን አስታውቋል።

ድርጅቱ ስደተኞቹ 57 ሴቶችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጿል።

IOM ባለፈው የፈረንጆች አመት 2024 ውስጥ 558 ስደተኞች ከምስራቅ አፍሪካ ተነስተው ጅቡቲና የመንን ለማቋረጥ ሲሞክሩ ህይወታቸው ማለፉን አመላክቷል።  
#thedailytribunenewsofbahrain #vaticannews

ThiqahEth
😢21👍42
THIQAH
ሶሪያ! በሶሪያ የሟቾች ቁጥር 600 ደረሰ። በሶሪያ የሽግግር መንግስት እና በአሳድ ታማኝ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ጦርነት ዛሬም ቀጥሏል። ሁሉም ሟቾች የቀድሞው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የዘር ሀረግ የሚመዘዝበት የአልዋይቲ አናሳ ማህበረሰብ አባል መሆናቸው ተገልጿል። በጦርነቱ ከፍተኛ የቤትና ንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ ነው ተብሏል። #burnabynow @ThiqahEth
#Update

ሶሪያ!

"የሟቾች ቁጥር ከ1000 በልጧል" -  ስይሪያን ኦብዘርቫቶሪ

በሶሪያ በተፈጠረው ግጭት የሟቾች ቁጥር ከ70 ወደ 600 ከፍ ማለቱ ትላንት መዘገቡ ይታወሳል።

የስይሪያን ኦብዘርቫቶሪ የዛሬ መረጃ እንደሚያስረዳው ደግሞ የሟቾች ቁጥር ከ400 በላይ አሻቅቧል።

በሶሪያ ከቀናት በፊት የጀመረው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉን መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገው ስይሪያን ኦብዘርቫቶሪ አስታውቋል።

እስካሁን ድረስ 745 ንጹሃን ሰዎች፣ 148 የአሳድ ታማኝ ወታደሮችና 125 የሽግግር መንግሥቱ ወታደሮች ህይወታቸው ማለፉን ተቋሙ ገልጿል።

"ታጣቂዎች በግጭቱ ወቅት ቤቶችን አቃጥለዋል፣ ተሽከርካሪዎችን ሰርቀዋል" ተብሏል። #outlookindia

@ThiqahEth
😢21👍91😱1
የአሜሪካ ጤና ቢሮ ስራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለሚለቁ ሰራተኞች 25,000 ዶላር እሰጣለሁ አለ።

በጤናና ሰብዓዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት የሚሰሩ ከ80,000 የሚልቁ የፌዴራል ሰራተኞች ስራቸውን ከለቀቁ የካሳ ክፍያው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

የቢሮው ውሳኔ የፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ "ወጭ መቀነስ" እርምጃ አካል ነው ተብሏል።

ሰራተኞቹ እስከመጪው ሳምንት አርብ ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁ ተነግሯቸዋል ነው የተባለው።

ይህ እርምጃ በአሜሪካ የጤናው ዘርፍ ላይ የሰው ኃይልና የበጀት እጥረት ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋት አስከትሏል።
#theeconomictimes

@ThiqahEth
👍13🤔7😁1
ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ሊፈፅም ነበር የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት (USSS) አንድ አጥፍቶ ጠፊ ወጣት በዋሽንግተን ከተማ ሲንቀሳቀስ ተይዟል ሲል አስታውቋል።

አገልግሎቱ፣ ጥቃቱን ሊፈፅም የነበረው ግለሰብ የህንድ ዜግነት እንዳለውና በቅርቡ ወደ አሜሪካ መግባቱን ገልጿል።

ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቷል ተብሏል። 
#theweek

@ThiqahEth
👍20😁9🔥71🤔1
THIQAH
Photo
#Update

32 ኢትዮጵያዊያን ከታይላንድ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በማይናማር ታግተው ከቆዩ በኋላ ከሳምንታት በፊት ወደ ታይላንድ ተሻግረው ከነበሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 32ቱ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።

32 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መድረሳቸውን ከተመላሾቹ አረጋግጠናል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ 32 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውን አስታውቋል።

ተመላሾቹ እንደሚሉት ከሆነ፤ የታይላንድ መንግስት አልቀበላችሁም ያላቸው ወደ 300 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ካምፕ ገና አልወጡም።

ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩት መካከል ደግሞ ወደ 5 ልጆች ተመልሰው ተወስደዋል።

ወደ 29 የሚሆኑ ኢትዮጵውያን ደግሞ ማይናማር ውስጥ "ዋልዋይ" የሚባል ቦታ የከፋ ግፍ እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ።

ታይላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያኑ በበኩላቸው፣ "ሌሎች በርካቶች በሌሎች ካምፓች ስቃይ እየደረሰባቸው ነው" ብለዋል።

@ThiqahEth
👍153👌1