✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
51.6K subscribers
1.65K photos
300 videos
1.88K files
4.86K links
"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ"
መዝ 118 (119) ፥ 71
ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ
http://t.me/OrthodoxTewahedo12
ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ
ለአስተያየት 📥@Tewahedo12_bot
Download Telegram
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ሥርዓተ ጸሎት ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ  ካህናት እያዜሙ እየሰገዱ እኛም እየተቀበልን እያዜምን የምንሰግድበትን ሥርዓት ለማውቅ እና ለመፈፀም ከስር ያንብቡ
      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

❖ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡

❖ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን  እስከ ይዌድስዋ  ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡

❖ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና  በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና  ሰዓቱ የተመደበውን አቡነ ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ  ይመራሉ፡፡

❖ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፤ በመቀጠል

📌 ትእዛዝ

❖ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ)

❖ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም "

❖ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም"

❖ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም "

❖ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት"

📌 ትእዛዝ

❖ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ።

❖ ይህን የላይኛውን ጸሎት እያመላለሱ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር 12 ጊዜ ይበሉ

❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለሕማሙ  ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

📌 ትእዛዝ

❖ ይህ ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል፡፡

❖ በመጨረሻም የሚከተለውን ሦስት ጊዜ እያመላለሱ ይበሉ፡፡

❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም"

❖ ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" እየተባለ ይሰገዳል፡፡

📌 ትእዛዝ

❖ ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቡ የሚከተሉትን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉ፤

"ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤  ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡

📌 ትእዛዝ

❖ ቀጥሎም ሕዝቡ በሁለት ክፍል ሆነው የሚከተለውን ጸሎት ሁለት ጊዜ በመከታተል አንድጊዜ በማስተዛዘል ይበሉት፡፡

ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

አብኖዲ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን

ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን ፤

ታዖስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ማስያስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ኢየሱስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ክርስቶስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

አማኑኤል ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ትስቡጣ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን

📌 ትእዛዝ

❖ ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን አርባ አንድ ጊዜ ይባላል፡፡

❖ ይኸውም በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እየተባለ ይሰገዳል፡፡

📌 በመጨረሻ ጊዜ

❖ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)

❖ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)

❖ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ  እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡ /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
#እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 🧲  https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
🧲  http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
2🔥1
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ሕማማት ሰሞን ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ ቋንቋዎች ትርጉም
       ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

❖ በግብረ ሕማማት (በሕማማት ሰሞን) ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ

➊ የዕብራይስጥ(hebrew)
➋ የቅብጥ (ግብጽ) (coptic)
➌ የግሪክ (ጽርዕ) (greek) ቃላት ይገኛሉ፡፡

📌 የእነዚህ ቃላት ትርጉም በጥቂቱ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡

#ኪርያላይሶን

❖ ቃሉ የግሪክ(ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነዉ፡፡
❖ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ፤ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፤ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፤ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን

❖ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን "መሐረነ / ማረን" ማለት ነዉ፡፡

# አብኖዲ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "አብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ ፡፡

#ታኦስ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ጌታ / አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "ታኦስ ናይናን" ሲልም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

#ማስያስ

❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "መሲሕ" ማለት ነዉ።
❖ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

#ትስቡጣ

❖ "ዴስፓታ" ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ደግ ገዢ" ማለት ነዉ፡፡

#ሙዳሱጣ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ነበልባላዊ" ማለት ነዉ፡፡

#መዓግያ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "እሳታዊ" ማለት ነዉ፡፡

#አንቲፋሲልያሱ

❖ ቃሉ "በመንግስትከ / በመንግስትህ" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚኦ በዉስጠ መንግስትከ / አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በዉስጠ መንግስትከ / ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚአ ኲሉ መንግስትከ / የሁሉ የላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

#ኤልማስ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "አምላኪየ / አምላኬ" ማለት ነዉ፡፡

#አህያ ሸራህያ

❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "ያለና የሚኖር" ማለት ነዉ፡፡

❖ እነዚህ ከላይ ያሉና ሌሎች ቃላት ከሌሎች ቋንቋዎች በቀጥታ የተወሰዱ ናቸዉ፡፡

መልካም የሰሙነ ሕማማት ወቅት ይሁንልን

ስብሐት ለከ፤
ሰጊድ ለአቡከ፤
ዕበይ ለመንፈስከ፤
ወምህረተ ፈኑ ለሕዝብከ፤
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡    

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽዐነ በፍሥሐ ወበሰላም

ሙሉዉን ያነበበ ብቻ አሜን ይበል እንዲሁ #ሼር ያድርግ

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
#እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 🧲  https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
🧲  http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
3
✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ 📌
በሰሞነ ሕማማት ከሚፀለዩት መካከል ለማንበብ ጊዜ ለሌላችሁ በድምጽ እነሆ

ድርሳነ ማሕየዊ ሰኞ https://t.me/Tewahedo12/18697
ድርሳነ ማሕየዊ ማክሰኞ https://t.me/Tewahedo12/18724
ድርሳነ ማሕየዊ ዕረቡ https://t.me/Tewahedo12/18748
ድርሳነ ማሕየዊ ሐሙስ https://t.me/Tewahedo12/18780
ድርሳነ ማሕየዊ አርብ https://t.me/Tewahedo12/18815
ድርሳነ ማሕየዊ ቅዳሜ https://t.me/Tewahedo12/18850
2
➯ በዓመት ለተወሰኑ ቀናት ከእያንዳንዱ የአገሪቱ ዜጋ ጋር የሚገናኝና ጥያቄዎቻቸውን በግለሰብ ደረጃ የሚመልስ መንግሥት ቢገኝ ምን ያህል ሊወደድ እንደሚችል አስቡት?  ሕዝቡም በዚህ ደረጃ ቅርብ ሆኖ የሚጨነቅለትና ጥያቄዎቹን የሚሰማለት ደግ ንጉሥ በማግኘቱ ይህን ባሰበ ቁጥር አንዳች የደስታና የኩራት ስሜት ሰውነቱን ውርር ሳያደርገው አይቀርም።

➯ ሰማይና ምድርን የፈጠረው፣ ዓለሙን የሚመግብና የሚያስተዳድረው ታላቁ ንጉሥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንድንገናኝና ጥያቄዎቻችንን እንድናቀርብ በዓመት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ሰጠን? ምድራውያን ነገሥታት ቢገዙ የሚታየውን ዓለም ያውም ደግሞ በተራራ እና በወንዝ ተቆራርሶ፣ በግዛት ታጥሮ የተሰጣቸውን ኩርማን መሬትና በዚያ የሚኖሩትን ሕዝብ ነው፤ እንዲህም ሆኖ ግን ሥራ ስለሚበዛባቸው ከጊዜያቸው አጣበው በዓመት አንድ ወይም ሁለት ቀን እያንዳንዱን ዜጋ ቢያገኙ እጅግ ታላቅ ጀብዱ ሆኖ ይነገርላቸዋል።

➯ በእውነት እንደ እግዚአብሔር ያለ "ሥራ ብዙ" ማን ነው? መድኃኒታችን በወንጌል "አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ" እንዳለ እርሱ እኮ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ሲያስተዳድር ዕረፍት አያውቅም፤ ድካምም የለበትም፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ጋር ለመገናኘት ግን የወር ወይም የቀናት ቀጠሮ አይሰጠንም።
📖ዮሐ 5፥17

➯ ዛሬስ አይታሰብም ባይሆን ነገ ሞክሩ ብሎ አይመልሰንም፤ ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ለመቀበል እጆቹ ዘወትር የተዘረጉ ናቸው "ትናንት አላናገርኩህም? ዛሬ ምን ቀረህ?" ብሎ አያሳቅቅም፤ አይሰለችም፤ በዚህ ቀንና በዚህ ሰዓት ብቻ እገኛለሁ አይልም፤ ብንችል ሳናቋርጥ አብረነው ብንሆንና ብናነጋግረው ደስ ይለዋል፤ በእርሱም ዘንድ የተቆለፈ በር የለም፤ እንደውም ወደ ልባችን እልፍኝ እስክናስገባው ከውጭ ሆኖ እኛን ደጅ ይጠናል ያንኳኳል፤ ክፈቱልኝ ይላል፤ ሲከፈትለትም ምስኪኑን ቤት አይቶ አይጸየፍም። የልባችንን እልፍኝ ያሰናዳዋል፤ ለእራትም አብሮን ይቀመጣል።
📖1ኛ ተሰ 5፥17
📖ራእይ 3፥20

➯ ታዲያ እንዲህ ያለ ቸር ጌታ እያለን እንዴት ዝም ይባላል? እንግዲህስ ከተኛንበት የስንፍና አልጋ እንነሣ፤ ንጉሡን እናነጋግረው፤ ወደ እርሱ ስላቀረበን እናመስግነው፣ የልባችንንም ኃዘን እንንገረው።

➯ ተንሥኡ ለጸሎት!
"በማታና በጥዋት በቀትርም እናገራለሁ...ቃሌንም ይሰማኛል"
📖መዝ 55፥17

📌 ምንጨ
✍️ዲያቆን አቤል ካሳሁን
1
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
           የአንድ ሰው ውሎና አመሻሽ
        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

➯ ይህ እስካሁን ምንጩን ያላገኘሁት አንድ ወንድሜ የላከልኝ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ የቆየ የአንድ ሰው ገጠመኝ ነው።

➯ አንድ ወንድም ስልኩን ድምፅ አልባ ማድረግ ረስቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ስብከት ይማራል፤ በዚህ መካከል ስልኩ ይጮኃል፤ ሰባኪው ስብከቱን አቁሞ በዓይኖቹ ተቆጣው፤ ከስብከቱ በኋላ ምእመናን ስብከቱን በመረበሹ ወቀሱት፤ አንዳንዶቹም እያዩት ራሳቸውን በትዝብት ነቀነቁ፤ ከሚስቱ ጋር ወደ ቤታቸው ሲሔዱም ሚስቱ ስለ ቸልተኝነቱ ምክር መሥጠትዋን ቀጠለች፤ እፍረት መሸማቀቅና ውርደት ዘልቆ እንደተሰማው በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፤  ከዚያች ሰንበት በኋላ እግሩን ወደ ቤተ ክርስቲያን አንሥቶ አያውቅም፤ ውስጡ የተረበሸው ይህ ሰው ያንኑ ምሽት ወደ መጠጥ ቤት አመራ አእምሮው እንደታወከ ነበር።

➯ ቁጭ ባለበት ድንገት የሚጠጣበት ጠርሙስ ወድቆ ተሰበረና መጠጡም በዙሪያ ተረጨ፤ ፍንጣሪው የነካቸው ሰዎች ወደ እሱ መጠጋት ጀመሩ፤ ሊጮኹበትና በጥፊ ሊሉት እንደሆነ ታውቆት ቀድሞ ዓይኖቹን ጨፈነ፤ ሰዎቹ ግን በተሰበረው ጠርሙስ ስብርባሪ ተጎድቶ እንደሆነ ተጨንቀው ጠየቁት፤ አስተናጋጁ መጥቶ የፈሰሰበትን እንዲያደርቅ ማበሻ ሰጠው፤ የጽዳት ሠራተኛዋ መሬቱን ወለወለች፤ የቤቱ ባለቤት "አይዞህ ያጋጥማል? ዕቃ የማይሰብር ማን አለና?" አለችውና ሌላ መጠጥ አስመጣችለት፤ ከዚያች ቀን ጀምሮ ከዚያ መጠጥ ቤት ቀርቶ አያውቅም።

➯ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስልክን ክፍት ማድረግና ሥርዓተ አምልኮ መረበሽ መቅደስ ውስጥ ጫማ አድርጎ የመግባት ያህል ስኅተት ነው፤ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ኤምባሲ እንኩዋን ስልክህን ውጪ አስቀምጠህ ትገባለህ፤ ሰውዬው ላጠፋው ጥፋት ግን በፍቅር የሚያናግረው ሰው በማጣቱ ከነ ስልኩ ሊጠፋ ወሰነ::

➯ ቤተክርስቲያን የድኅነት ሥፍራ ናት፤ መጠጥ ቤት ደግሞ የጥፋት ጎዳና ነው፤ በዚህ ሰው ታሪክ ውስጥ ግን በድኅነት ሥፍራ ካሉ ሰዎች ይልቅ በጥፋት ሥፍራ ያሉ ሰዎች ለሰውዬው ስኅተት የተሻለ ፍቅር አሳዩ፤ አንዳንዴ የአንዳንድ ምእመናን ጠባይ ነፍሳትን ወደ ሲኦል ይሰድዳል፤ አንዳችን የአንዳችን ጠባቂ መሆን እንችላለን ዓለምን ለመፈወስ የሚቻለንን እናድርግ፤ ነፍሳትን ከማዳን ነፍሳትን ማጥፋት በጣም ቀላል ነው::

➯ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነበረ፤ እሱ የማንንም ቅስም በክፉ ቃል አልሰበረም፤ እኛ ግን ሰው ላይ ስንጨክን መጠን የለንም፤ በዚህ ምክንያት እንደ ኒቼ ያሉ ሰዎች "ብቸኛው ክርስቲያን መስቀል ላይ የሞተው ነው" ብለው እስኪ ዘብቱብን ደርሰዋል።

➯ መጽሐፍ ግን ሰው ሲሳሳት ስናይ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲህ ሲል ይናገራል
✍️"ወንድሞች ሆይ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፤ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት"
📖ገላ 6፥1

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
#እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

📌 ምንጭ
✍️ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሐምሌ 26 2014 ዓ.ም

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
 🧲  https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
🧲  http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
መዝሙረ ዳዊት.pdf
6.3 MB
📘 መዝሙረ ዳዊት PDF

📚 #በውስጡ የያዛቸው #የጸሎት አይነቶች

❖ የዳዊት መዝሙራት በጠቅላላው መቶ ሃምሳ እና የነቢያት ጸሎት በቤተክርስትያን በሰባቱ ዕለታት ተከፋፍለው ይጸለያሉ ፤ እነርሱም

የሰኞ ከመዝሙር 1 – 30 (ፍካሬ፥ አድኅነኒ ፥ አምላኪየ) ፤
የማክሰኞ ከመዝሙር 31 – 60 (ብፁዓን ፥ ከመያፈቅር ፥ ለምንት ይዜኃር ) ፤
የረቡዕ ከመዝሙር 61 – 80 (አኮኑ ፥ እግዚኦ ኩነኔከ)፤
የኀሙስ ከመዝሙር 81 -110 (እግዚአብሔር ቆመ ፥ ይኄይስ ፥ ስምዐኒ) ፤
የዐርብ ከመዝሙር 111 – 130 ( ብፁዕ ብእሲ ፥ ተፈሣሕኩ)፡
የቀዳሚት ከመዝሙር 131 – 150 (ተዘከሮ ፥ ቃልየ) እና
የእሑድ የነቢያት ጸሎት እና መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን ናቸው።


───────────
Channel
 Ⓡ @Tewahedo12

Group
@OrtodoxTewahedo12
 ───────────
መልክአ ሕማማት ዘ፯ቱ .pdf
511.4 KB
📘 መልክአ_ሕማማት፤ (የ፯ቱ ጊዜያት ጸሎት)

📚 #በውስጡ ያሉ የጸሎት #አይነቶችና ሰዓት

ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/
ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/
ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/

የ፯ቱ ጊዜያት

፩. መንፈቀ ሌሊት (ሌሊት 6 ሰዐት)
፪. ነግህ (ማለዳ፥ ጧት)
፫. ሠለስት (ጠዋት ሦስት ሰዐት)
፬. ቀትር (6 ሰዐት)
፭. ተስዓት (ዘጠኝ ሰዐት)
፮. ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዐት)
፯. ንዋም (የመኝታ ሰዐት)፤

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

@Tewahedo12

@OrtodoxTewahedo12
መልክአ ማሕየዊ.pdf
2.2 MB
📚 መልክአ ማሕየዊ

Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

              
@Tewahedo12

      
@OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ሰይፈ ሥላሴ ወሰይፈ መለኮት.pdf
48.8 MB
📚 ሰይፈ ሥላሴ
📘 ሰይፈ ሥላሴ ዘዘወትር
📗 ሰይፈ ሥላሴ ዘሰነይ
📙 ሰይፈ ሥላሴ ዘሠሉስ
📕 ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ
📔 ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ
📓 ሰይፈ ሥላሴ ዘአርብ
📒 ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት
📖 ሰይፈ ሥላሴ ዘሰንበተ ክርስቲያን
📚 ሰይፈ መለኮት
📚 መልክአ ሥላሴ

Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

              
@Tewahedo12

      
@OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ግብረ ሕማማት.pdf
60.4 MB
📚 መጽሐፍ ግብረ ሕማማት


Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

              
@Tewahedo12

      
@OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ድርሳነ ማሕየዊ.pdf
111.1 MB
📚 ድርሳነ ማሕየዊ
📚 መልክአ ማሕየዊ

Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

              
@Tewahedo12

      
@OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
3
📌 ዐቢይ ጦም ሊጠናቀቅ ሲል የተሰጠ  ምዕዳን

❖ እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፤ ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡

❖ የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡

❖ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡

❖ ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፤ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡ 

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
    አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ
      እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ
         በፍስሓ ወበሰላም"

📌 ምንጭ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚 አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148
3
❖ መልካም ምግባር ሰዎች እንዲያዩልን ብለን አናድርግ ብንጾምም፣ ብንመጸውትም፣ ብንጸልይም፣ ሌላም በጎ ምግባር ብናደርግ የተገለጠውንም የተሰወረውንም ሁሉ ለሚያውቅ እግዚአብሔር ብለን የማናደርገው ከሆነ ከሰዎች አንዳች ጥቅም አያስገኝልንም፤ እንዲህ በማድረጋችን ሰዎች ቢያመሰግኑን እየጎዱን እንደሆነ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፤ እንዲህ ከሆነ ታድያ ለምንድነው ሰዎች እንዲጎዱን ምቹ ሁኔታዎችን የምንፈጥርላቸው? ትክክለኛ ማንነታችን የሚያውቀው፣ የዘለዓለምንም ሹመት ሽልማታችንን የሚሰጠን እግዚአብሔር አይደለምን? ታድያ ለምንድነው ጥቅም ከማይሰጠን ይልቁንም ከሚጎዳን አካል ውዳሴን የምንጠብቀው? ስለዚህ በቃላችንም፣ በግብራችንም፣ በሐሳባችንም እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ ልናሰኝ አይገባንም እላችኋለሁ፡፡

📌 ምንጭ
✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
1
#ጸሎተ_ሐሙስ_ወሕጽበተ_እግር_

"ሐዋርያቲሁ ከበበ፥
እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ፤
ኮኖሙ አበ ወእመ፤
ወመሐሮሙ ጥበበ"

👉ሐዋርያቱን ሾመ፤
የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፤
አባትና እናት ኾናቸው፤
ጥበብንም አስተማራቸው፡፡

📚ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፣ በድጓ

Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

               @Tewahedo12

       @OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
2