Tesfish Hop (ኢትዮጵያዊነት ለዛ...)
929 subscribers
817 photos
30 videos
95 files
171 links
ይህ የናንተ፤ የኛ የሁላችንም ድምፅ ነዉ። በቻናላችን አዝናኝና አስተማሪ ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርቡበታል።
ሠላም አንድነትና በጎነትን እንሰብካለን።
የወጣቶች ድምፅ ...

ከፈለጉ ይቀላቀሉን።


ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት
@tesfahun27

@tesfa273

to subscribe
tube ገፃችንን ለመጎብኘት
https://youtu.be/9tTDeSzMgxk
Download Telegram
''ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ ህይወት የመቅጠፍ እድል አለዉ! የህክምና ባለሙያዎች'' በጥሞና ይነበብ?

እንደሚታወቀው ሰሞኑን ተወዳጁ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ተከትሎ ብዙዎችን አዝነናል ።

በተለይ ድምፃዊዉ ባለፉት ጥቂት ወራት Glow Ethio-Turkiye የተባለ ከህክምናው አካሄድ ዉጭ በሆነ መልኩ በ15 ቀናት እስከ 18 ኪሎግራም ክብደት እቀንሳለሁ የሚል አጉል ተስፋ የሚሰጥ ሌሎችንም ለአደጋ የሚዳርግ ማስታወቂያ ለመንገር መጠቀምያ አድርጎት "ወደዚህ ድርጅት ሄጄ የክብደት መቀነስ ህክምና በመከታተል ላይ ነኝ ብሎን በየጊዜው ያስመዘገበውን የክብደት ለውጥ(weight loss progress) እያሳየን በርታ በሉኝ እያለ ድርጅቱንም በ Social Media ላይ promote ሲያደርግ ሲያስተዋውቅ መታየቱ ግኑኝነት ይኖረዉ ይሆን ? ''የሚል ጥያቄዎች የሚጭር ቢሆንም ብዙዎች ትኩረት አልሰጡም፤ ይህም ማለት ተቋሙ ለሌሎችም ሞትና ተያያዥ የጤና ችግር እንዲዳርግ እንደመፍቀድ ነዉ።''

በመሆኑም ለክብደት መቀነስ ተጓዳኝ መድሃኒት ሳይጠቀሙ እንዴት ሊሆን ይችላል? ስለሚለው ከባለሙያዎች ያገኘነውን መረጃ ለማካፈል ወወድን፤ ከዛ በፊት ግን ይህን Glow Ethio-Turkiye የተባለውን ተቋም መሰል ይዘት ያለው በኢቢኤስ በኩል ቅዳሜ ከሰአት ላይ ለአንድ ዙር ብቻ ቀርቦ ተቋሙ ከሳይንሳዊ ህክምና አንፃር በአጭር ቀናት ከአምስት ኪሎ በላይ መቀነስ እንደማይቻል በመረዳት እንዲቆም ያደረገዉን ዉድድር ታሳቢ እያደረግን ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ ምን ችግር አለው?? ስለሚለው ባለሙያዎች የሰጡትን ማብራሪያ እንመልከት........


''ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ ምን ችግር አለው?? ለሚለው ጥያቄ አዎ ያዉም ለሞት የሚያደርስ የሚል ምላሽ እናገኛለን ።''

ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ በሰውነት ላይ የተለያዩ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል:- ከእነዚህም፦ በሐሞት ከረጢት ውስጥ ጠጠር (Gallstones) እንዲፈጠር ያደርጋል፣የጡንቻ መጠን መቀነስ ፣ ድካም፣ ማዞር ወይም ራስን መሳት፣ፀጉር መርገፍ ፣የሆድ ድርቀት (Constipation)፤ የንጥረ ምግብ እጥረት፣ የብረት (Iron) እጥረት ፣ የቫይታሚን B12 እጥረት ፣የፎሌት እጥረት ፣የቫይታሚን D እጥረት የፕሮቲን እጥረትና በሴቶች ላይ ደግሞ የወር አበባ መዛባት የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል ።

የኤሌክትሮላይት መዛባት ዝቅተኛ ፖታስየም (Hypokalemia) ዝቅተኛ ሶዲየም (Hyponatremia) ዝቅተኛ ማግኒዥየም (Hypomagnesemia) ባለሙያዎች የሚጠቅሷቸዉ ጉዳቶቹ ናቸዉ ።

የእነዚህ ኤሌክትሮላይት መዛባት ደሞ የጡንቻ መኮማተር፣ የልብ ምት መዛባት እና የነርቭ ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ይህ ከላይ የተጠቀሰው ተቋም በሰሜ ባላገሩ በኩል ሰርቶት የነበረዉና ከአርቲስቱ ሞት በኋላ በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ በማወቅ ከማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲነሳ ያደረገዉ የክብደት መቀነስ ሂደት እስከሞት ድረስ ሊያደርሱ የሚችሉ ከባድ ችግሮችንም ሊያመጣ ይችላል ።

ከእነሱም መካከል ፦ የልብ ምት መዛባት፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት፣የኩላሊት ጉዳት፣ ከባድ የንጥረ ምግብ እጥረት እና የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል።

በሳምንት 0.5–1 ኪ.ግ ያህል ክብደት መቀነስ ደህንነቱ የተጠበቀና ጤነኛ የምንለው ሲሆን ከዛ ያለፈ ግን ከላይ የዘረዘርናቸውን ችግሮች ሊያስከትል ስለሚችል ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ ካጋጠመዎ በአቅራቢያዎ የሚገኝን ሀኪም ያማክሩ ።

ሰሜን ድጋሜ ላይመለስ አጥተነዋል፤ ነገር ግን እንደዚህ ያሉ አካሄዶች ለሌሎች ሞት ምክንያት እንይሆን እንጂ ከተቋሙ ጋር የግል ችግር የለብኝም ፅሁፉም ታሳቢ የደረገዉ ድንግልና እንመልሳለን ዉፍረት እንቀንሳለን እንጨምራለን ምናምን የሚሉ ቢዝነስ ተኮር ተቋማት ያላቸዉን ጉዳት ለመጠቆም እንጂ ።

''በእርግጥ ወደዚህ አይነት ቦታ እንዲሄድ ያደረግነዉ እኛዉ በተክለ ሰዉነቱ እንዲሸማቀቅ ያደረግነው እንደሆነ በግል የማዉቀዉ ጉዳት ስላለ ነዉ የሆነ ጊዜ አንዱ ታዴ ምነዉ ብትወፍር በሚል ዉፍረት መጨመርያ መድሀኒት እንድገዛ መከረኝ እኔ እንደማልፈልግ ስነግረው አብሮኝ የነበረ ሌላ ወዳጃችን ወስዶት ዛሬ ለመንቀሳቀሴ የከበደዉ የከባድ የስኳር በሽተኛ ደም ግፊት በሽታዎች በወጣትነቱ ተጠቂ ሁኖ ስላየሁ ነዉ ።

Via:- ታዴ የማመይ ልጅ

@teafa273
@tesfa273
@tesfa273
👎1
በስልክ የተደረገ ቃለ ምልልስ ቁ 1
<unknown>
ኢትዮ ምክንያታዊ ወጣቶች በጎ ፈቃድ ማህበር እንዴት ተመሠረተ? ያለበት ሁኔታስ ምን ይመስላል? እና ቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ ከአሚኮ ጋር በስልክ የተደረገ ቃለ ምልልስ።

የድርጅታችን ከፍታ እየፈጠነ የመታወቅ እድማሱ እየሰፋና ወደ ለውጥ ማማ እየከነፈ ነው።

ኑ አብረን እንስራ...!

@tesfa273
@tesfa273
@tesfa273
👍21
ምክንያታዊነት የትክክለኛነት መንገድ ነው።
ስትደግፍም ሆነ ስትቃወም በምክንያት ይሁን...!!!
👍2
አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል እንድትሆን አማራጭ ሀሳብ ቀረበ!

​ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ባካሄደው ስብሰባ ተመካካሪዎች በቡድን ደረጃ ውይይታቸውን ቀጥለዋል።በኮሚሽኑ በቀረበው ሰነድ መሰረት የአዲስ አበባን ሕጋዊ አቋም በተመለከተ አራት ዋና ዋና አማራጮች ለውይይት ቀርበዋል፦

👉​ሲቲ ስቴት (ራስ ገዝ)

👉​የፌደራል አካል

👉​ራሷን የቻለች ክልል

👉​የኦሮሚያ አካል

​ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋ ወሰን፣ የሥራ ቋንቋ፣ የበጀት ድርሻ፣ የፖሊስና ፍርድ ቤት ጉዳዮች በንዑስ አጀንዳነት የተካተቱ ሲሆን፣ የከተማዋ በፌደሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ግን በሰነዱ አልተካተተም።

@tesfa273
@tesfa273
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ብቃት ያላቸው ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #ርዕሰ_መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

የመወዳዳሪያ መስፈርቶች

የትምህርት ዝግጅት፦ በትምህርት ቤት አመራርነት የ2ኛ ዲግሪ ወይም በትምህርት አይነቶች በመምህርነት ሙያ የ2ኛ ዲግሪ ያለው፡፡ ተጨማሪ የትምህርት አመራርነት ስልጠና የወሰደ።

አገልግሎት፦ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራርነት 5 ዓመትና በላይ ያገለገሉ፡፡

የምዘና ሒደት፦ የጽሁፍ ምዘና በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፤ ቃለመጠይቅ በአካል በመቅረብ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ክህሎት፦ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና መሰረታዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዕውቀትና ክህሎት ያለው/ያላት፡፡

የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት

ምደባ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በሚመድባችሁ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመስራት ፍላጎት ያላችሁ፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦ ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት

ይመዝገቡ 👇
https://sbs.moe.gov.et/directors

@tesfa273
@tesfa273
#Amhara

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ከሰኔ 3-5/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና 173,699 ተማሪዎች ውስደው ነበር።

ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ  የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot  ላይ መመልከት ይችላሉ።

ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው https://amhara.ministry.et/#/complaint ላይ በመግባት ቅሬታቸው ማቅረብ እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም

@tesfa273
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያዊነት

@tesfa273
@tesfa273
@tesfa273
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ብዙ ተማሪዎች ቅሬታ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። የፓዊ መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎችም ውጤቱ እኛን አይገልፅም እንደገና ይታይልን ሲሉ ተደምጠዋል።

@tesfa273
@tesfa273
@tesfa273
ሞገስ እባላለሁ።
ከአምስት አመት በፊት “ዊንታ” ከምትባል ቆንጆ ኤርትራዊት ልጅ ጋር ተገናኘውና ለትዳር ከጀልኳት።
ያንን የትዳር አላማ ለማሟላት የህክምና ሙያዬ በቂ ነው ብዬ አስቤ ጠየቅኳት። ነገር ግን ዊንታ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ነበራት።

በጥያቄ ታጣድፈኝ ጀመር፦

“በትርፍ ግዜ የምታሳልፋቸው ሆቢዎች አሉህ?”

-አይ

“ፊልሞችን ትመለከታለህ?”

-አይ

“ሌሎች ቦታዎች ጉዞ አድርገህ ታውቃለህ?”

-አይ

“አዝናኝ መፅሃፍት ታነባለህ?”

-አይ

“ተራራዎችን ወጥተ ታውቃለህ?”

-አይ

“ታድያ በትርፍ ጊዜህ ምንድነው የምታደርገው?”

-ትርፍ ጊዜ የለኝም በትምህርትና በስራ ነው የማሳልፈው።

ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ እንዲህ አለችኝ፦

“አየህ አንተ ተራ ሰው ነህ! ተራ ባትሆን ኖሮ አንተን ለማግባት ፍላጎት ይኖረኝ ነበር።”

እነዚያ ቃላት ጭንቅላቴን እንደ ነጎድጓድ መቱት።

19 አመታትን ብዙ የትምህርት ተቋማትንና የህክምና መጽሃፍቶችን ሳገላብጥ ኖሬ በመጨረሻም “ተራ” የሚባል ማዕረግ አገኘሁ!።

ወደ ቤት ተመለስኩ እና በዚያ ምሽት እንቅልፍ እንዳልተኛሁ አስታውሳለሁ።

በጠዋቱ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ትኬቴን ቆርጬ በፕሌን ተጓዝኩ። በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ነገሮችን ጎብኝቸና ተዝናንቸ ወደ አገር ቤት ተመለስኩ።
ስመለስ አዕምሮዬ ላይ የመጣው ቀጥታ ዊንታን ማግኘት ነበር።

ነገር ግን ይህ ሁኔታ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ገባኝ። ብዙ አዝናኝ መፅሃፍቶችን ማንበብ አለብኝ።

ቤት ውስጥ ራሴን አግልዬ በደርዘን የሚቆጠሩ የፍልስፍና፣ የልብ ወለድ እና የሶሺዮሎጂ መጽሃፎችን በማንበብ ግዜዬን አሳለፍኩኝ።

ከጨረስኩ በኋላ “ይህ በቂ አይደለም” አልኩና ለአንድ ወር ያህል የተለያዩ ሮማንቲክ፣ አድቬንቸርና ኮሜዲ ፊልሞች መርጬ አየሁ።

ስጨርስ “ይህ በቂ አይደለም” አልኩና ፈረስ ግልቢያ፣ ሙዚቃ መጫወትና ፎቶግራፍ ማንሳት በትንሽ በትንሹ ሰለጠንኩ እና ብዙ አስደናቂ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን እስከሚዋሃደኝ ድረስ ተለማመድኩ።

ስጨርስ ይህ በቂ አይደለም አልኩኝና ወደ ተራራ ጫፍ መውጣት እንዳለብኝ ወሰንኩኝ።

ከሁለት ሳምንት አድካሚ ጉዞ በኋላ ወደ ተራራው ጫፍ ደረስኩና እጆቼን ዘርግቼ ጭንቅላቴን ቀና አደረኩኝ።

ስለመለስ ይህ ሁሉ ሆቢ ለዊንታ ባል ለመሆን በቂ እንደሆነ ተሰማኝ፤ ነገር ግን በድንገት ወደ ዊንታ የመመለስ አምሮቴ እሬት እሬት አለኝ።

ምክንያቱም አሁን እኔ የብዙ ሆቢዎች ባለቤት ስለሆንኩ ዊንታ ተራ ሴት ሆነችብኝ።

አ መ ሰ ግ ና ለ ሁ ዊ ን ታ ዬ..🚶🏼🙏😌

#የፖስቱ_ጭብጥ፦ ስንንቅ እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ! ይልቁንም የምንፈልገውን መስፈርት የሚያሟላ ከጠፋ የተገኘውን ይዘን መስፈርቱን እንዲያሟላ ማገዝ ይሻላል ለማለት ነው።

©ሞገስ
ከሶሻል ሚዲያ የተገኜ

@tesfa273
@tesfa273
@tesfa273
4
🎉🌿 እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን ! 🌿🎉
አዲሱ ዓመት ለሁላችንም
የስኬት
😊 የደስታ
🙏 የጤና
🕊️ የሰላም
🌟 የበረከትና የተስፋ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።
በአዲሱ ዓመት የልባችን መልካም ምኞቶች ሁሉ እንዲሳኩ፣ ቤታችን በደስታ፣ በፍቅርና በሰላም እንዲሞላ ከልብ እመኛለሁ ።🙏🎊
በድጋሜ  መልካም አዲስ ዓመት! 🎊 🙏🌿❤️

@tesfa273
@tesfa273
@tesfa273
👍21