ባንክ መክፈት ሚፈልጉ የአረብ ሀገር ልጆች
2.8K subscribers
75 photos
21 videos
3 files
173 links
አዲስ በስማች ባንክ አካውንት እንዲከፈትላቹ ምትፈልጉ ልጆች እዚህ ግሩፕ ተቀላቀሉ
Download Telegram
ጊዜው ግንቦት ሀያ ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሶስት ዓ.ም ነው፤ያሁኑ ባለ አስደንጋጭ ተስጥኦ ባለቤት ድምፃዊ ማርኮናል ከ አባቱ አቶ አለማየሁ መኮንን ዘር እና ከ ውድ እናቱ ወ/ሮ ደብሪቱ በቀለ ማህፀን ተፈርቶ ይህቺን ውብ ሀገር ሳሪስ አካባቢ ልዩ ስሙ ቀይ አፈር ከሚባል ስፍራ በ ድምፀ መረዋ ለቅሶ ተቀላቀላት፡፡ያኔ ግን የማራኪውን ድምቡሽቡሽ ጨቅላ ለቅሶ እንጂ የዛሬውን ተስረቅራቂ ድምፅ ባለፀጋ እና የሙዚቃ ፈርጥ የሚሆን ባለ ተስፋ ፍሬ እንደሆነ ማንም ልብ አላለም ነበር፡፡እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ህፃን ከ ቄስ ትምህርት ቤት የተጀመረው የ ቀለም ትምህርት ሂወቱ እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ እንደ ሰኔ ዘጠኝ፣ አብዮት ፋና እና ላፍቶ ትምህርት ቤት በመቀያየር ተገፋ፤በመቀጠልም ለወላጅ እናቱ ታላቅ ፍቅር ያለው ታዳጊው የ እናቱን ድካም ለመጋራት አፍላ ወጣትነቱን ችላ ብሎ ስራ በመጀመር ቤተሰቡን እገዛ ከ ስምንት እስከ አስረኛ ክፍል ፍሬ-ህይወት ትምህርት ቤት ውስጥ በማታ መርሀ ግብር መማሩን ቀጠለ፡፡በነዚህም ጊዜ የ ሙዚቃ፣የክበባት የባህል ውዝዋዜ እና ዘመናዊ ዳንስ አሰልጣኝ በመሆን ህይወቱንና የጥበብ ስሜቱንም ማስታገስ ጀመረ፡፡በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማኀበር የ ባህል ቡድኑ መሪና ውዝዋዜ አስተማሪ በመሆን በ ስኬታማነት አሳለፈ፡፡አስተማሪዎቹ በ ትምህርት ቤት ውስጥ በሙዚቃው ላይ ያለውን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በማጤን ታላቅ ሞራል ስንቅ ይሆኑት ጀመር፡፡በ ትምህርት ሲሰላችም ለታማሪዎቹ ፈጣን የ ፈጠራ ግጥም እና ዜማ ድርሰቶችን በማዘጋጀት በ ሸጋ ድምፁ ያዜምላቸውና ያዝናናቸው ነበር፡፡በዚህም ከ ትምህርቱ ይልቅ የ ኪነ-ጥበብ ስራዎቹ ላይ ሙሉ ትኩረት አድርጎ በመስራት እራሱን እና ቤተሰቡን በ አፍላ ወጣትነቱ መደጎም ጀመረ፡፡ለ ተከታታይ ሰባት አመታትም አነስተኛ ክለቦችን ጨምሮ ሀቫና፣ፈንዲሻ፣አይከን እና መሰል ትላልቅ ክለቦች ውስጥ በዲጀነት በማገልገል ራሱን ለ ሙዚቃ ይበልጥ ቅርብ አደረገ፡፡እንግዲህ አርቲስ ማርኮናል በዚህ ጊዜ ነበር በ አጋጣሚ ከ አሁኑ የ ሙዚቃ ስራዎቹ ፕሮዲውሰር እና ማናጀር እንዲሁም የልብ ወዳጁ የ ማይከራህ ስቱዲዮስ ባለቤት አርኪቴክት እና አርቲስት ልዑል ቫለንቲኖ ጋር ፒያሳ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት፡፡በ ማርኮናል ድምፅ የተገረመው ልዑል ቫለንቲኖ አብሮት የሆነ ቀን የ ሙዚቃ አልበም መስራት እንደሚፈልግ ቀልድ በሚመስል ስሜት ነግሮት ተለየው፡፡እንደተባለውም ሳይቀር ቃል እምነት ሆኖ ሊሰምር ከ አንድ አመት በኋላ ዳግም ተገናኙ፤ያኔ ግን በ ቆራጥነት ስራውን ፕሮዲውስ ለማደረግ በመስማማት እርምጃቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡አዲስ እና የተለየ የሙዚቃ ስራ አቅም ያላቸውን ባለሙያዎች ለወራት ካፈላለጉ በኃላ አሃዱ ከሚባሉ ሶስተ ወጣት ዲጄ ፕሮዲውሰሮች ጋር ተገናኘተው ሙሉ አልበም ለመስራት ውል አሰሩ፡፡ከ አንድ አመት በላይ ሙሉ ጊዜ፣እውቀት፣ጥበብ እና በጀት በመመደብ በታላቅ ቅንጅት ያሁኑ ህሊና የተሰኘ ድንቅ አልበም ተሰራ፡፡ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን በ ማራኪና በሳል የ ልዑል ቫለንቲኖ የ ግጥም ድርሰት የዳሰሰው አልበሙ በ ዜማ፣በሙዚቃ መሳሪያ፣በድምፅ፣እና በ ዘረፈ ብዙ ተያያዥ ዘረፎች ብዙ ባለሞያተኞች በ ቅንጅት ተሳትፈውበታል፡፡ተጨማሪ ሁለት ስራ ከ አይ ኤም ቲ ሪከርድስ እና ከ ሙዚቀኛ ኤርሚያስ ዘውዱ ጋር በመስራት የ አልበሙን አስራ ሶሰት ትራኮች በ ማጠናቀቅ ለ ሚክሲንግ እና ማሰተሪን ከ ታዋቂው የ ኢስት አፍሪካን ሪኮርዲንግ ስቱዲዮ ባለቤት አርቲስት ኬኒ አለን ጋር በመደራደር ስራዎች አለም አቀፋዊ ደረጃቸውን ጠብቀው ተሰናዱ፡፡ከዚህም በኃላ ማይከራህ ስቱዲዮስ የ ግራፊክስ ዲዛይን ስራውን ከ ጉዱ ካሳ ግራፊክስ፣የ ፎቶ ስራውን ከ አንጀሎ ፒክቸርስ እንዲሁም የ ዲጂታል ዲስትርቢውሽኑን እና ለ አለም አቀፍ አድማጭ ተመልካቹ የማቅረብ ሀላፊነቱን በ አጭር ጊዜ ውስጥ ተሰማርቶ ለ አርቲስቱ ጥቅም መጠበቅ ዘብ ከቆመው ሎሚ ቲብ ጋር ትልቅ የ ውል ስምነነት በ ጣይቱ ሆቴል በመፈራረም ወደ ስራ ገብተዋል፡፡አልበሙን በ ሲዲ ጨምሮ በ ዩቲዩብ፣በ አይቱንስ፣በ አማዞን፣በ ስፖትስፋይ እና መሰል አለም አቀፍ የ ዲጂታል መገበያያ ድህረ-ገፆች ላይ በ ቅርብ ቀን ውስጥ ያገኙታል፡፡አርቲስት ማርኮናል ታላቅ ፍቅር እና አክብሮት ላለው ለ ኢትዮጵያ የ ሙዚቃ አድማጭ ተመልካች ስለ አልበሙ እንዲህ ይላል...‹‹...ዝም......አንደበቴን በ አልበሜ ውስጥ ያገኙታልና!!!›› ከአልበሙ ውጪ የሆነውን ቡፌ ደላጋር ነጠላ ዜማን ነገ ከሎሚ ቲዩብ ወደርሶ ይደርሳል ።
ሙዚቃ ያለም ቋንቋነው ይህ አባባል ልክ መሆኑን ለማረጋገጥ እራሳችንን ብናዳምጥ ቋንቋው ሳይገባን ከልብ የወደድናቸው ሙዚቃዎች አሉ ሀገራችንንም ባለብዙ ባህል እና ቋንቋ የሚነገርባት ሀገር መሆኗ እርግጥነው ይህንን ማለት ለምን አስፈለገህ ብላችሁ ብጠይቁኝ በቀላሉ ከዚህ በፊት በስራቸው ነጠላ ዜማዎች ሁላችንንም ብስራው እንድንወደው ብሎም ቋንቋውን የማይናገሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምፅ ያደነቅነው ውዝወዝ ያልንበት ስራዎቹ ህያው ምስክር ናቸው ድምጻዊ ዳዊት ነጋ "ብንፀለይ" በሚለው አዲስ ነጠላ ዜማው በቅርቡ ብቅ ይላል የሙዚቃው ክሊፕ በምስል እና በቅንብር ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራሲሆን በውስጡ ብዙ ሰርፕራይዝ የሚያደርጉ ነገሮችም ተካተዋል በቅርቡ ይጠብቁ በቸር ያቆየን