🫡 ለ ሰብስክራይበሮቻችን አንኩዋን ደና መጣችሁ አያልን!
🔬የዚ ቻናል ዋና አላማ
🧬 ስለ በሽታ አመጣጦች አና ምልክቶች ግንዛቤ መስጠት::
🧬የበሽታ መከላከያ ዘዴዎችን ግንዛቤ መስጠት::
🧬ስለ መድሃኒት አጠቃቀም አና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ማሳወቅ::
🧬ስለ ፅዳት አጠባበቅ አና ቀላል የፅዳት ዘዴዎችን ማስተማር::
🔬የዚ ቻናል ዋና አላማ
🧬 ስለ በሽታ አመጣጦች አና ምልክቶች ግንዛቤ መስጠት::
🧬የበሽታ መከላከያ ዘዴዎችን ግንዛቤ መስጠት::
🧬ስለ መድሃኒት አጠቃቀም አና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ማሳወቅ::
🧬ስለ ፅዳት አጠባበቅ አና ቀላል የፅዳት ዘዴዎችን ማስተማር::
👍9❤1
🫵 ስለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ያውቃሉ?
📍የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ባክቴሪያ ወደ ሽንት ቧንቧ ገብቶ በሚራባበት ጊዜ ነው።
📍የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ኩላሊትን፣ የሽንት ፊኛን እና የላይኛውን እና የታችኛውን የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦዎች የሚያጠቃ የኢንፌክሽን አይነት ነው።
📍ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚሆኑ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
💉የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን አንዳንድ ጊዜ ምልክት ላያሳይ ቢችልም በአብዛኛው
💧 በመጠን አነስተኛ ግን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት
💧ደመናማ የመሰለ የሽንት ቀለም
💧 የሽንት መልክ መቀየር
💧ከሽንት ጋር የደም ምልክት መታየት
💧ሽንት በመሽኛ ጊዜ የማቃጠል ስሜት
💧ያልተለመደ ጠንከር ያለ የሽንት ሽታ
💧ማህፀን አካባቢ የሚሰማ የመጫን ሕመም (ለሴቶች) ወይም ወንዶች ብልታቸው አካባቢ እና የሽንት ፊኛ አካባቢ የሚሰማ ሕመም
📍የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን መከላከያ መንገዶች
💦 በቂ ውኃ መጠጣት÷ ውኃ መጠጣት ሽንትን ይበርዛል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንድንሸና በማድረግ ባክቴሪያው ኢንፌክሽን ሳያመጣ ከሽንት ቧንቧ እንዲወርድ ያደርጋል።
💦መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ ቡሀላ ከፊት ወደ ሁዋላ የአስተጣጠብ ዘዴን መከተል::
💦ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሽንት ቧንቧ አካባቢን ማጽዳት እንዲሁም ውኃ በመጠጣት ባክቴሪያው እንዲወገድ ማድረግ
💦 የወሊድ መከላከያ መንገዶችን መቀየር ካስፈለገ ሐኪም ማማከር በተለይ ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሕመም ካለ፡፡
💦በጊዜ ሐኪም ማማከር እና መድኃኒት ከታዘዘ በአግባቡ በመውሰድ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን መከላከል እንደሚቻል ከጥቁር አንበሳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
🫴 ሀሣብ አስተያየት እንዲሁም ጥያቄ ካሎት 👉@nu9191
🙏ጤናን ለሁሉም ተመኘን ቸር ሠንብቱልን

👍10❤3
የስኳር ህመም መከላከያ መንገዶች
የስኳር ህመምን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶችየአኗኗር ዘይቤዎ ላይ ለዉጥ ማድረግ የስኳር ህመምን ይከላካል
በጣም የተለመደዉና በብዛት ያለዉ የስኳር ህመም አይነት 2ኛ አይነቱ (type 2 diabetes) ሲሆን ህመሙ እንዳይይዝዎ መከላከሉ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡
💪 ስለሆነም የሚከተሉትን መንገዶች ይተግብሩዋቸዉ፡፡
1.ተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ🏃♀🏃
• ክብደትዎን ለመቀነስ
• የደም የስኳር መጠን ለመቀነስና
• የስኳር ህምተኛ ከሆኑና ኢንሱሊን እየወሰዱ ከሆነ የሰዉነትዎ ሴሎች ላይ እንሱሊኑ በደንብ እንዲሰራ ያነቃቃቸዋል፡፡
2. የፈይበር/ቃጫነት/ ይዘት ምግቦችን አዘዉትሮ/በብዛት መመገብ🥦🌽🫘🥜
• የሰዉነትዎን የስኳር ቁጥጥር በማሻሻል ለስኳር ህመም ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ ይረዳል
• ለልብ ህመም ተጋላጭነትዎን ይቀንሳል
• የሰዉነት ክብደትዎን ለመቀነስ የሚያግዝዎት ሲሆን የፋይበር ምንጭ ከሆኑ ምግቦች ዉስጥ አትክልትና ፍራፍሬ፣ጥራጥሬ፣አተርና ባቄላ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
3. ክብደትዎን መቀነስ🏋
4. የካርቦሃይድሬት መቀነስ🚫🍰🍞
🤔 የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚያስፈልግዎ መቼ ነዉ?
እንደ አሜሪካን የስኳር ህመምተኞች ማህበር አንድ ሰዉ የስኳር ምርመራ ማድረግ ያለበት
• እድሜዉ ከ45 አመታትና ከዚያን በላይ ከሆነና ክብደቱ ከመጠን በላይ ከሆነ
• እደሜዉ ከ45 አመታት ሆኖ ክብደቱ ከመጠን በላይ ሆኖ በተጨማሪ ለሁለተኛዉ የስኳር አይነት ተጋላጭነትን ሊጨምሩ የሚችሉ እንደ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤና በቤተሰብ የስኳር ችግር ያለበት ከሆነ
ምንጭ-hello doctor.com
🫴 ሀሣብ አስተያየት እንዲሁም ጥያቄ ካሎት 👉@nu9191
🙏ጤናን ለሁሉም ተመኘን ቸር ሠንብቱልን!!

ምንጭ-
🫴 ሀሣብ አስተያየት እንዲሁም ጥያቄ ካሎት 👉@
🙏ጤናን ለሁሉም ተመኘን ቸር ሠንብቱልን!!
👍7❤3
🧂የሚመገቡትን የጨዉ መጠን መመጠን/መቀነስ የሚገባበት ምክንያቶች🧂
🧂ጨዉ እንደሚታወቀዉ በደም ግፊት ጤንነት ላይ ችግር እንደሚፈጥር ነዉ ፡፡ ምንም እንኳ ሶዲየም ለሰዉነታችን ከሚያስፈልጉ አስፈላጊ ንጥረነገሮች ዉስጥ ቢመደብም ከመጠን በላይ ይህን ንጥረነገር መዉሰድ የደም ግፊትን እንደሚጨምር በጥናቶች ተረጋግጧል፡፡ ከመጠን ያለፈ ጨዉ (ሶዲያም) መመገብ የደም ግፊቱን እንኳ ባይጨምር በልብ፣ በደም ቧንቧ፣ በኩላሊትና በአእምሮ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡
ጨዉ በልብ፣ በደም ስሮች፣ በአእምሮና ኩላሊትዎ ላይ የሚኖረዉን ጫና/ጉዳት ለመቀነስ/ ለመከላከል
🍽 የቤት ምግብ መመገብ፡- በቤትዎ የተሰራን ምግብ ሲመገቡ ምን ያህል ጨዉ ምግብዎ ላይ እንደሚጨምሩ መቆጣጠር ስለሚችሉ የቤት ምግብ ለመመገብ ይሞክሩ፡፡
🥒አትክልት፣ ፍራፍሬና ሌሎች የምግብ ይዘታቸዉ ጥሩ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር የተመጣጠነ የምግብ ይዘት ስለሚኖራቸዉና በዉስጣቸዉ እንደፖታሲየም ያሉ ንጥረነገሮችን ስለሚኖራቸዉ ለደም ቧንቧ ጤንነት መልካም ነገሮች ናቸዉ፡፡

👍6
የእርግዝና ወቅት አመጋገብ🤰
🥬ፎሌትና እና ፎሊክ አሲድ -ከወሊድ ጋር ተያያዥ የሆነዉን ተፈጥሮያዊ ጉድለቶችንይከላከላል፡፡ፎሌት የቫይታሚን ቢ አይነት ሲሆን በህብለ ሰረሰር ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ተፈጥሮያዊ ክፍተት ለመከላከል ይረዳል፡፡
ምንጮች፡- የበለፀጉ የጥራጥሬ ዘሮች ጥሩ የፎሌትና የፎሊክ አሲድ ምንጮች ናቸዉ፡፡ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎ፣የደረቁ ባቄላና አተር በተፈጥሮ ጥሩ የፎሌት ምንጮች ናቸው፡፡
🥛ካልሲየም- ለአጥንት ጥንካሬ
እርስዎም ሆኑ ፅንሱ ለአጥንትና ለጥርስ ጥንካሬ ካልሲየም ያስፈልጋችኃል፡፡
ምንጮች፡- ወተትና የወተት ተዋፅኦዎች ጥሩ የካልሲየም ምንጮች ናቸዉ፡፡ ሌሎች ምንጮች የአበባ ጎመን፣ብዙዎቹ የፍራፍሬ ጅዉስ እና ጥራጥሬዎች
🥗 ቫይታሚን ዲ፡- ለአጥንት ጥንካሬ መጎልበትቫይታሚን ዲ የልጅዎን አጥንትና ጥርስ ለመገንባት ይጠቅማል፡፡
ምንጮች፡- ዓሳ፣ የበለፀጉ ወተቶችና የብርቱካን ጂዉስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
🫘ፕሮቲን፡- እድገትን ለማፋጠን
በእርግዝናዎ ወቅት ፕሮቲን ለፅንሱ እድገት ከሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡
ምንጮች፡- ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ ዓሳና እቁላል ጥሩ የፕሮቲን ምንጮች ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም ፕሮቲንን ከባቄላ፣ ኦቾሎኒ ከአዝርእትና አኩሪአተር ዉጤቶች ይገኛሉ፡፡
🍗የብረት ማዕድን፡- በብረት ማዕድን እጥረት ምክንያት የሚመጣዉን የደም ማነስ ለመከላከል ሰዉነታችን የብረት ማዕድንን ሄሞግሎቢንን ለመስራት ይጠቀምበታል፡፡ ሄሞግሎቢን ደግሞ ኦክሲጅንን ወደ ሰዉነታችን ተሸክሞ ለማድረስ ያገለግላል፡፡
ምንጮች፡- ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋና ዓሳ ጥሩ ምንጮች ናቸዉ፡፡ በብረት ማእድን የበለፀጉ ምግቦች እንዲሁም ባቄላና አትክልቶች ተጨማሪ የብረት ማዕድን ምንጮች ናቸው።

👍8❤1
ሄፓታይትስ ቢ (Hepatitis B)
👉 ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ጉበትን ከሚያጠቁ አምስቱ የሄታይትስ ቫይረሶች አንዱ ሲሆን እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በአለማችን እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ የተጠቁ ናቸዉ፡፡ በየዓመቱም 600,000 ሰዎች በሄፓታይትስ ቢ ምክንያት ለህልፈተ ሞት ይዳረጋሉ፡፡ሄፓታይትስ ቢ በጉበት ላይ ጉዳት የሚያመጣ ሲሆን በዚህ ቫይረስ የተያዙ የተወሰኑ ሰዎች ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከሰዉነታቸዉ ዉስጥ ማጥፋት ስለማይችሉ ቫይረሱ ለረጅም ጊዜ በጉበታቸዉ ዉስጥ በመቆየት (chronic hepatitis B) በጉበት ላይ ጉዳት እነዲደርስ ያደርጋል፡፡
👉ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ እና ኤችአይቪ ቫይረስ የመተላለፊያ መነገዶቻቸዉ ተመሳሳይ ቢሆንም ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ከኤችአይቪ አንፃር ሲታይ ከ50 እስከ 100 ጊዜ እጅግ ተላላፊ ነዉ፡፡
የሄፓታይትስ ቢ የህመም ምልክቶች
በሄፓታይትስ ቢ እንፌክሽን ምክንያት የሚታዩ ምልክቶች የሚታዩት ኢንፌክሽኑ ከተከሰተ ከ3 ወራት በኃላ ሲሆን ምልክቶቹ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ከነዚህ ምልክቶች ዉስጥ ጥቂቶቹ፡-
🦠የሆድ ህመም
🦠 ጠቆር ያለ የዉሃ ሽንት
🦠 የሰዉነት ትኩሳት
🦠 የመገጣጣሚያ ላይ ህመም
🦠 የምግብ ፍላጎት መቀነስ
🦠ማቅለሽለሽና ማስታወክ
🦠የድካም ስሜት
🦠የቆዳና የአይን ነጩ ክፍል ቢጫ መሆን ናቸዉ፡፡
ነገር ግን በሄፓታይትስ ቢ የተያዙ ህፃናትና የተወሰኑ አዋቂዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አያሳዩም፡፡
ለሄታይትስ ቢ ቫይረስ እንፌክሽን የሚያጋልጡ ነገሮች
📌ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ
📌ያለ ጥንቃቄ ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ከተያዘ/ች ሰዉ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ
📌እንደ ጨብጥና ከርክር ባሉ የአባለዘር በሽታዎች ተይዘሁ ከሆነ
📌 መርፌ፣የጥርስ ብሩሾችንና ሌሎች ነገሮችን በጋራ የሚጠቀሙ ከሆነ
📌ለሄፓታትስ ቢ ሊያጋልጦት የሚችል ስራዎች፡-የጤና ባለሙያዎች፣የእሳት አደጋ ሰራተኞች
📌 ዲያሊስስ(የኩላሊት ዕጥበት) የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
የሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች
🦠ልቅ በሆነ የግብረስጋ ግንኙነት
🦠ከእናት ወደ ልጅ
🦠በደምና ደም ንኪኪ(ጤንነቱን ያልጠበቀ የሌላ ሰዉ ደም በመዉሰድ፣ጤንነቱን ያልጠበቀ መርፌ መወጋት፣አደንዛዥ ዕፅ ለሚጠቀሙ መርፌ በጋራ መጠቀም)
🦠 ሄፓታይትስ ቢ ከተያዘ ሰዉ ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት መኖር (intimate contact)
የሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ መከላከያ መንገዶች
🧬የሄፓታይትስ ቢ ክትባት መዉሰድ
🧬ጥንቃቄ ያለዉ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ
🧬ማንኛዉንም ደም የነካቸዉን ነገሮች በጋራ ያለመጠቀም(መርፌ፣ምላጭ፣የጥርስ መቦረሻ፣የፂም መላጫ)
🧬እናቶች በእርግዝና ወቅት ለሄፓታይትስ ቢ ምርመራ ማድረግ
🧬ደም ለሌላ ሰዉ ከመሰጠቱ በፊት ለሄፓታይትስ ቢ መመርመር
ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ እና ክትባቱ (HBV vaccine)
ሄፓታይትስ ቢ ቫየረስን ለመከላከል ከሚረዱ ነገሮች ዉስጥ አንዱ የሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ክትባትን መከተብ ሲሆን ማንኛዉም ሰዉ ከላይ በተገለፀዉ መሰረት ተጋላጭነት ካለዉ ተመርምሮ በሄፓታይትስ ቢ ያልተያዘ መሆኑ ከተረጋገጠ የሄፓታትስ ቢ ቫይረስን ለመከላከል ክትባት መዉሰድ የሚችል ሲሆን ክትባቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲሰራ ሶስት ጊዜ መከተብ ያስፈልጋል፡፡ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ቫክሲንን ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ ከ95% በላይ የሚሆኑ ህፃናትና አዋቂዎች በሽታዉን የሚከላከሉ አንቲቦዲዎችን(Antibodies) የሚያዘጋጁ ሲሆን ክትባቱ ቢያነስ ለ 20 ዓመታትና ምናልበትም እስከ እድሜ ልክ በሽታዉን ሊከላከል ይችላል፡፡
የሄታይትስ ቢ እንፌክሽን ያላቸዉ ሰዎች የህክምና ክትትል ማድረግና ሊደረጉ የሚገባቸዉን ጥንቃቄዎች መዉሰድ ያስፈልጋቸዋል፡፡

👍9👏2
የቶንሲል ህመም/ Tonsillitis
የቶንሲል ህመም/ቶንሲል በቶንሲል መቆጥቆጥ ምክንያት የሚከሰት ነዉ፡፡
የቶንሲል ህመም ምልክቶች
የቶንሲል ህመም በብዛት የሚያጠቃዉ ህፃናትን ሲሆን የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡
🤒የቶንሲል መቅላትና እብጠት
🤒የቶንሲል መከርከር
🤒 ምግብ በሚዉጡበት ወቅት ህመም መኖር/ መዋጥ መቸገር
🤒 ትኩሳት
🤒በአንገት ላይ ያበጡና ህመም ያላቸዉ ዕጢዎች መከሰት
🤒የድምፅ መቀየር
🤒መጥፎ የአፍ ሽታ
🤒የሆድ ህመም( በተለይ በእድሜያቸዉ ትናንሽ ህፃናት ላይ)
🤒የአንገት ህመም/መጠንከር
🤒የራስ ምታት
በጣም ጨቅላ በሆኑ ህፃናትና የህመማቸዉን ሁኔታ መግለፅ በማይችሉ ህፃናት ላይ
😮💨 ሲዉጡ ህመም ስላላቸዉ የምራቅ/ለሃጭ መዝረከርክ
😮💨ምግብ መመገብ እምቢ ማለትና
😮💨 ያልተለመደ ድካም የህመሙ ምልክቶች ናቸዉ፡፡
የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
📌 በ24 ሰዓታት ዉስጥ ለዉጥ የሌለዉ የቶንሲል ህመም ካጋጠመዎ
📌 ምግብ ሲዉጡ ህመም ካለዎና
📌የድካም/የመዝለፍልፍ ስሜቶች ከፍ ያለ ከሆኑ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
የቶንሲል ህክምና
1.የቶንሲል ህመሙ የተከሰተዉ በቫይረስ መሆኑ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያዎ ምንም ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒት ስለማያዝልዎ ህመሙ እንዲድን የቤት ዉስጥ ህክምና ማከናወን የህክምናዉ ዋናዉ አካል ነዉ፡፡ የቶንሲል ህመም በ10 ቀናት ዉስጥ ሊሻሻል ይችላል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ የቤት ዉስጥ ህክምናዎች
👉 በቂ እረፍት ማግኘት፡- ብዙ ያለማዉራትና በቂ እንቅልፍ ማግኘት
👉ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ
👉ምቾትን ሊሰጡ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ፡- ትኩስ ፈሳሾች እንደ ሾርባ፣ ሻይ፣ የሞቀ ዉሃ በማር የጉሮሮ መከርከርን ሊያክሙ ይችላሉ፡፡
👉 ጨዉ ባለዉ ዉሃ አፍን መጉመጥመጥ
👉እንፋሎት መታጠን ደረቅ አየር ጉሮሮ ላይ የሚያመጣዉን መከንከን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
👉ሊቆጠቁጡ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ፡- ጉሮሮን ሊከረክሩ ከሚችሉ እንደ የሲጋራ ጭስና የቤት ማጽጃ ኬሚካሎች እራስን መጠበቅ
👉ህመምና ትኩሳት ካለ ማስታገሻ መዉሰድ፡- እንደ ፓራሲታሞላና አይቡ ፕሮፌን ያሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡፡
2. መድሃኒቶች
የቶንሲል ህመም የተከሰተዉ በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ከሆነ የግድ ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችን (አንቲባዮቲክሶችን) መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡ በህክምና ባለሙያዎ የታዘዘልዎትን መድሃኒት በአግባቡ ወስዶ መጨረስ የሚያስፈልግ ሲሆን በአግባቡ ካልተወሰደ ግን ባክቴሪያዉ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰራጭ፤ህፃናት ላይ ደግሞ የልብ ህመም እንዲከሰት መንስኤ መሆንና ቀጣይነት ያለዉ የቶንሲል ህመም (ክሮኒክ ቶንሲላይትስ) እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
የቶንሲል ህመምን መከላከል
ቶንሲልን ሊያመጡ የሚችሉ ጀርሞች (ባክቴሪያና ቫይረስ) ከሰዉ ወደ ሰዉ ተላላፊ ናቸዉ፡፡ ስለሆነም የቶንሲል ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ዉስጥ ዋነኛዉ የግል ንፅህናን መጠበቅ ነዉ፡፡
📍ምግብ ከመመገባችሁ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጃችሁን በደንብ መታጠብ
📍የመጠጫና መመገቢያ እቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም ይመከራል፡፡ልጆች የቶንሲል ህመም ካላቸዉ ኢንፌክሽኑን ወደሌሎች እንዳያዛምቱ
📍ልጅዎ ታሞ ከሆነ ለተወሰነ ቀናት እቤት እንዲቆይ ማድረግ
📍ልጅዎ መቼ ት/ት ቤት መሄድ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር
📍ልጅዎ በሚስልበትና በሚያስነጥስበት ወቅት አፍና አፍንጫዉን በሶፍት ወይም በክርኑ የዉስጠኛዉ ክፍል እንዲሸፍን ማስተማርና
📍ልጅዎ ካሳለዉ ወይም ካስነጠሰዉ በኃላ እጁን/እጇን እንዲታጠቡ ማስተማር ናቸዉ፡፡

👍4👏3❤2👌2🤩1
የሳምባ ምች/Pneumonia
የሳምባ ምች በአንዱ ወይም በሁለቱም ሳምባ ላይ የአየር ከረጢቶች ላይ ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ የሳምባ ምች ከመጠነኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ሲሆን በህፃናት፣ እድሜያቸዉ ከ65 ዓመታት በላይ ለሆኑ አዛዉንቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ በተዳከመባቸዉ ሰዎች ላይ እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሊያመጣ ይችላል፡፡
የህመሙ ምልክቶች
የህመሙ ምልክቶች:- የህመሙ ምልክቶች ህመሙን እንዳመጣዉ የጀርም አይነት፣ የታማሚዉ እድሜና አጠቃላይ የጤንነት ሁኔታ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡ መጠነኛ የሳምባ ምች ያላቸዉ ሰዎች የህመም ምልክቶቻቸዉ ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም ህመሙ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡
የህመም ምልክቶቹ የሚከተሉትንም ሊያጠቃልል ይችላል፡-
• ትኩሳት፣ማላብና ብርድ ብርድ ማለት
• ሳል
• በሚያስሉበትና በሚተነፍሱበት ወቅት የደረት ላይ ህመም
• የትንፋሽ ማጠር
• ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣ተቅማጥ ናቸዉ፡፡
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
👉የአተነፋፈስ ችግር
👉የደረት ላይ ህመም
👉የማይቀንስና ከ39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት
👉የማያቋርጥ ሳል በተለይ መግል የመሰለ አክታ ከገጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
የሳምባ ምች ማንኛዉንም ሰዉ ሊያጠቃ ይችላል፡፡ነገር ግን በጣም ተጋላጭነትን ከሚጨምሩት ዉስጥ
• ከ2 አመትና ከዚያ በታች የሆኑ ህፃናት
• ከ65 አመትና በላይ የሆኑ አዛዉንቶች
ሌሎች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ
• የበሽታ መከላከል አቅምዎ የተዳከመ ከሆነ፡- የኤች አይቪ ኤድስ፣ የአካል ንቅለ-ተከላ የተደረገላቸዉና የካንሰር ህክምና መድሃኒቶችን እየወሰዱ ያሉ
• ለረጅም ጊዜ የቆየ ህመም ካለ፡- እንደ አስምና የልብ ህመም ያሉ ህመሞች ካሉ
• ሲጋራ ማጨስ፡- ማጨስ በተፈጥሮ የሳምባ ምችን ከባክቴሪያና ቫይረስ ሊከላከሉ የሚችሉ የበሽታ መከላከያን ስለሚቀንስ
• ሆስፒታል መተኛት፡- ሆስፒታል የተኙ ህሙማን በተለይ የመተንፈሻ ማሽን ላይ የተደረጉ ከሆነ
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡-
የሳምባ ምች ህክምና ከሚያጠቃልላቸዉ ነገሮች ዉስጥ እንፌክሽኑን ማዳንና ሊያመጣ የሚችለዉን ጉዳት መከላከል ናቸዉ፡፡ ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ
• መድሃኒቶች/አንቲባዮቲክስ፡- በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የሳምባ ምች አንቲባዮቲክስ ሊሰጥ ይችላል፡፡
• የትኩሳት መቀነሻ
• የሳል መድሃኒት፡- እረፍት ለማድረግ እንዲችሉ የሳል መቀነሻ መድሃኒት ሊሰጥዎ ይችላል፡፡
እንዴት መከላከል ይቻላል?
• ህፃናት እንዲከተቡ ማድረግ
• የግል ፅህናዎን በአግባቡ መጠበቅ፡- አንዳንዴ የሳምባ ምች ከሚያመጡ የመተንፈሻ ላይ እንፌክሽኖች እራስን ለመጠበቅ እጅዎን በመደበኛ ሁኔታ መታጠብ አሊያም አልኮሆል ያላቸዉ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘሮችን መጠቀም
• ያለማጨስ፡- ማጨስ በተፈጥሮ የመተንፈሻ አካላትን ከእንፌክሽንን ሊከላከል የሚችለዉን አቅም ስለሚቀንስ ከማጨስ መቆጠብ
• የሰዉነትዎን የበሽታ መከላከል አቅም ማጎልበት፡- ጤናማ አመጋገብ፣መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና በቂ እንቅልፍ ማግኘት የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅምዎን ለማጎልበት/ማጠንከር ይረዳል፡፡

👍6❤1
#ለጥንቃቄ
የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት ባህሪ ስላለው በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አሳስቧል።
ቢሮው ምን አለ ?
- በከተማው በተለይ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በብዙ ሰዎች ላይ ጉንፋን መሰል በሽታ ተከስቷል።
- ይህ ወቅታዊና በየዓመቱ ከቅዝቃዜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን፤ በወረርሽኝ መልክ የሚገለጽ አይደለም።
- የተከሰተውን የቫይረስ አይነት ለመለየት ከትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እንዲሁም ከፍተኛ መተላለፊያ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከሚገኙ ከ178 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ምርመራ ተደርጓል። በዚህም 17 በመቶ በላይ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ እና 3 በመቶ የሚሆነው ከኮቪድ-19 ቫይረስ ጋር የተገናኘ መሆኑ ተረጋግጧል።
- ይህ ህመም በተለይም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ ከመቶ ሰዎች መካከል ሃያ የሚሆኑት ላይ ይስተዋላል።
ምልክቶቹ ፦
° ከፍተኛ ራስ ምታት፣
° ሳል፣
° ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
° ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
° ጡንቻ አካባቢ ህመም፣
° የድካም እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸው።
- ምልክቶቹ ሲታዩ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ እራስን ከከባድ ህመም መከላከል ያስፈልጋል።
- በበሽታው የተያዙ ሰዎች አፋቸውን እና አፍንጫቸውን ሳይሸፍኑ ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ እንዲሁም ቫይረሱ ያረፈባቸውን ነገሮች ከነኩ በኋላ አፍን፣ አፍንጫ ወይም ዓይንን መንካት ቫይረሱ እንዲሰራጭ የሚያደርጉ መንገዶች ናቸው።
የመከለከያ መንገዶች ምንድናቸው ?
▫ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣
▫በሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን መክፈት፣
▫የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ
▫በንክኪ ወቅት እጅን በመታጠብ በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል።
* በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት ባህሪ ስላለው በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።
በበሽታው የተያዙ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ምንድነው ?
በበሽታው የተያዙ ሰዎች ህክምናው ከቤት የሚጀምር ሲሆን ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
☑ በቂ እረፍት መውሰድ፣
☑ ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች መጠቀም
☑ በአካባቢው በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር ማድረግ ከዚህ በተጨማሪ ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ማድረግ ይገባል።
#ማሳሰቢያ ፦ በሽታው ከአንድ ሳምንት በላይ የሚቆይ ከሆነ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የህክናምና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን አገልግሎትና የጤና ባለሙያዎች ምክረ ሃሳቦች ማግኘት ይገባል።
ምንጭ- @tikvahethiopia

👍7❤1
የሪህ በሽታ
ሪህ ከጥንት ግሪክ ታሪክ እኩል የሚታወቅ የመገጣጠሚያ በሽታ ነው ። የሚከሰተውም ሶዲየም ሞኖዩሬት የተባለው የፕሮቲን ምግብ ውጤት መገጣጠሚያ ላይ ሲጠራቀም ነው።
ምልክቶች፦
🤒 ድንገት ጀምሮ ከ8-12 ሰዓት በሚፈጅ ጊዜ እየተባባሰ የሚመጣ ሀይለኛ የእግር ወይም የእጅ መገጣጠሚያዎች ህመም
🤒እየተመላለሰ የሚመጣ የመገጣጠሚያ ህመም
🤒የመገጣጠሚያ ማበጥ፣መቅላትና ሙቀት መኖር
🤒ትኩሳት
ምርመራ፦
*የመገጣጠሚያ ፈሳሽ ምርመራ
*በደም የሪህ ምርመራ
*የ24 ስዓት የሽንት የሪህ ምርመራ
*የመገጣጠሚያ ራጅ
*የመገጣጠሚያ አልትራሳውንድ
*ባስ ካለም MRI እና CT scan ሊደረግ ይችላል
ሕክምና፦
ሕክምናውን በሶስት ዋና ዋና ደረጃዎች ማየት ይቻላል።
1ኛ፦ድንገት የጀመረውን ህመም ማከም፦ለዚህም የተለያዩ ማስታገሻዎችና ስቴሮድ የተባሉ መድኃኒቶች ሊታዘዙ ይችላል።
2ኛ፦የህመሙ ስሜት እንዳያገረሽ የሚሰጡ መድኃኒቶች
3ኛ፦ ከምንጩ የ ዪሪክ አሲድ ጠጣር የሚፈጥውን ነገር ለመቀነስ የሚደረጉ የመከላከያ ዘዴዎች፦
*መድኃኒት፡ አሎፑሪኖል፣ፌቡክሶስታት፣ፕሮቤንሲድ
*የፕሮቲን ምግብ መቀነስ
*አልኮል በተለይ ቢራ መተው
*ስኳር መቀነስ ጁስና ሶዳም መቀነስ
*ጨው መቀነስ
ካልታከሙት የሚያስከትለው ችግር
🦠የአይን ችግር ይህም ጠጣሩ ነገረ አይን ውስጥ ሊጠራቀም ስለሚችል ነው
🦠 የኩላሊት ጠጠር ፦ አንዱ የኩላሊት ጠጠር መንስኤ ሪህ ነው
🦠 የነርቭ በሽታ ናቸው::
ምንጭ- @health info

👍8❤7🤩1
አጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት(ኮሌራ)
ኮሌራ አጣዳፊ የሆነ የተቅማጥ ህመም/በሽታ የሚያመጣ ሲሆን በህመሙ የተያዘ ሰውን ተገቢውን ህክምና ካላገኘ በሰዓታት ውስጥ ለህልፈተ-ህይወት ሊዳርግ የሚችል የህመም አይነት ነዉ፡፡
ለኮሌራ መንስዔ የሆነዉ ቪብሮ ኮሌራ የሚባለው ባክቴሪያ ሲሆን በሽታዉ የሚመጣው በባክቴሪያው የተበከለ ውሃና ምግብ ስንመገብ ነው፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየአመቱ በአለማችን ከ1.3 ሚሊዮን እስከ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኮሌራ ህመም የሚያዙ ሲሆን ከዚህም ዉስጥ ከ21,000 እስከ 143,000 የሚደርሱ ሰዎችን ለህልፈተ-ህይወት ይዳርጋሉ፡፡ እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ እስከ 80 በመቶ የሚሆኑ የኮሌራ ህመምን በኦአርኤስ (ORS) ማከም ይቻላል፡፡
በባክቴሪያዉ ከተያዙት ውስጥ ብዙዎቹ የህመም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባክተሪያዉ ከ1 እስከ 10ቀናት ከሰገራቸዉ ጋር ሊወጣ ስለሚችል በቀላሉ ሌሎች ሰዎችን ሊበክል ይችላል፡፡
የህመሙ ምልክቶች
የህመም ምልክት ከታየ ብዙዎቹ ሰዎች ከመጠነኛ እስከ መካከለኛ የህመም ምልክቶች የሚታዩባቸዉ ሲሆን በጥቂቶች ህሙማን ላይ ግን ህመሙ ከፍተኛና አጣዳፊ የሆነ ጠቅማጥና ትውከት ያመጣል፡፡ ይህ የሰውነትን የፈሳሽ ምጣኔ በማዛባት ሰውነት ከፍተኛ የሆነ የፈሳሽ እጥረትና ድርቀት/dehydration/ እንዲከሰት ስለሚያደርግ ህክምና ካላገኘ ለህልፈተ-ህይወት ሊዳርግ ይችላል፡፡
አንድ ሰው በባክቴሪያው የተበከለ ውሃና ምግብ ከተመገበ በኃላ የበሽታዉን ምልክቶች ከ5 ሰዓታት እስከ 5 ቀናት ባሉ ጊዜያት ውስጥ ሊያሳይ/ሊታይበት ይችላል፡፡
መከላከያ መንገዶች
🔬 እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ፡-በተለይ ከመፀዳጃ ቤት መልስና ምግብ ከመመገብዎ ወይም ምግብ ለመስራት/ለማዘጋጀት ሲዘጋጁ
🔬 ንፅህናዉ ለጤና አስተማማኝ የሆነ ውሃ ብቻ መጠጣት፡- ፈልቶ የቀዘቀዘ፣ በውሃ ማከሚያ መድሃኒት የታከመ(የዉሃ አጋር) ወይም የታሸጉ ውሃዎችን መጠቀም፡፡
🔬በደንብ የበሰሉና ትኩስ የሆኑ ምግቦችን መመገብ፡- ከተቻለ በየመንገዱ እየተዘጋጁ የሚሸጡ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ(የሚመገቡም ከሆነ ደግሞ እርስዎ እያዩ የተዘጋጁና ትኩስ መሆናቸዉን ማረጋገጥ)፡፡
🔬አትክልትና ፍራፍሬ፡- ፍራፍሬዎችን እራስዎ ልጠዉ የሚመገቡዋቸዉ ቢሆኑ ይመከራሉ (ብርቱካን፣ሙዝ እና አቮካዶ)፡፡ ሊላጡ ከማይችሉ እንደ ሰላጣ፣ እንጆሪና ወይን/ግሬፕ/ ካሉት ቢቆጠቡ ይመከራል፡፡
🔬ፓስቸራይዝ ያልተደረገ ወተትና ከመጠቀምና በቀላሉ ሊበከሉ ከሚችሉ እንደ አይስ ከሬም ያሉ ነገሮችን ሲጠቀሙ ጥንቃቄ ማድረግዎን አይዘንጉ፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ኮሌራ በሰዓታት ውስጥ ለህልፈተ-ህይወት ሊዳርግ ስለሚችል አፈጣኝ የሆነ ህክምና ማድረግ ያስፈልገዋል፡፡
💊 በቂ ፈሳሽ መስጠት፡- አላማው በተቅማጥና በትውከት አማካይነት የወጣውን ፈሳሽና ኤሌክትሮላይት መተካት ሲሆን በፍጥነት ኦአርኤስ(ORS) መጀመር፡፡ ይህ በአንድ ሊተር ንፁህ ዉሃ ዉስጥ አንዱን የኦአርኤስ ዱቄት በመበጥበጥ ማዘጋጀትና መጠጣት ነው፡፡
💊 ጉሉኮስ መስጠት፡- ይህ በከፍተኛ ደረጃ ለታመሙ ህመሙማን የሚሰጥ ሲሆን ታካሚው በፍጥነት ወደጤና ድርጅት መሄድ/መውሰድ ያስፈልጋል፡፡
💊 ፀረ ባክቴሪያ(Antibiotics)፡- በከፍተኛ ደረጃ ለታመሙ ህሙማን ፀረባክቴሪያ መድሃኒት መስጠት የተቅማጡን መጠንና እርዝማኔ ለመቀነስ ይረዳል፡፡
💊የዚንክ እንክብል መስጠት
ምንጭ- @hello doctor

👍16❤8🤩3