Telebirr
278 subscribers
59 photos
2 files
10 links
Download Telegram
Forwarded from telebirr
በዌስተርን ዩኒየን ከባህርማዶ የተላከልዎትን ሃዋላ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ይቀበሉ!
የተላከልዎትን ሃዋላ በቀጥታ ወደቴሌብር አካውንትዎ ሲያዘዋውሩ ደግሞ 5 በመቶውን በስጦታ እናበረክትልዎታለን።

ቴሌብር - ፈጣን፣ ቀላል፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
Forwarded from telebirr
ኩባንያችን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለጉዳዮች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ለሚያገኟቸው የአገልግሎት ክፍያዎች ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ በሆነው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር በመጠቀም ለመፈጸም የሚያስችል አሰራር በዛሬው ዕለት ተግባራዊ አደረገ!
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለጉዳዮች በድረ ገጽ www.etrade.gov.et ላይ ለሚያገኟቸው የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ስያሜ እንዲሁም ተያያዥ አገልግሎቶች በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሆነው አገልግሎት በማግኘት እና ክፍያቸውን በቴሌብር በመፈጸም ውጣውረዳቸውን ማስቀረት እና ውድ ጊዜያቸውን መቆጠብ እንዲችሉ ያደርጋል፡፡
ይህ አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ በሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ 4.8 ሚሊየን ብር የአገልግሎት ክፍያ ለ38 ሺህ አገልግሎቶች ተፈጽሞበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ bit.ly/3TQz7xW
#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
Forwarded from telebirr
Forwarded from telebirr
ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በድረ-ገፅ www.etrade.gov.et ለሚያገኟቸው የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ስያሜ እንዲሁም ተያያዥ አገልግሎቶች ክፍያዎን በቀላሉ በቴሌብር ይፈጽሙ!

#ቴሌብር ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ
Forwarded from telebirr
የቴሌብር መላ ብድርዎን ለመክፈል ቀላል መንገዶችን እናጋራችሁ
በቴሌብር መተግበሪያ፡ የፋይናንስ አገልግሎትን መርጠው - ቴሌብር መላ ገፅ ላይ የእኔ ቴሌብር መላ የሚለውን በመምረጥ ሂደቶቹን ይከተሉ
ወይም
*127# በመደወል: (1) ፋይናንሺያል አገልግሎት ላይ ቴሌብር መላ - ቀጥሎም ብድር ለመክፈል የሚለውን መርጠው ሂደቶቹን ይከተሉ

#የፋይናንስ_አገልግሎት_ለሁሉም
ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት
Forwarded from telebirr
ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ የደንበኞቹን የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ የሚያዘምን እና የሚያሳልጥ፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ የመረጃ ክምችት እና አጠቃቀም እንዲሁም ተዛማች የክላውድ አገልግሎት ፍላጎት የሚያሟላ የቴሌ ክላውድ አገልግሎትን ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስጀምሯል።

የቴሌክላውድ ኮምፒዩቲንግ አገልግሎቶች በሶስት አማራጮች የቀረበ ሲሆን Infrastructure as a Service (IaaS) መረጃዎቻቸውን ማስቀመጥ፣ መቀመር የሚያስችል የክላውድ መሰረተ ልማት፣ Platform as a Service (PaaS)- የሶፍትዌር አልሚዎች ካሉበት ሆነው ላበለፀጓቸው ሶፍትዌሮች የተሟላ የዳታቤዝ ማኔጅመንት ሲስተም (MySQL DB) የሚያገኙበት እና Software as a Service (SaaS)- በውጭ ምንዛሪ የላይሰንስ ክፍያ ሳይከፍሉ ሶፍትዌሮችን ከቴሌክላውድ በተመጣጣኝ ክፍያ በብር ማግኘት የሚችሉበት አገልግሎቶች ናቸው።

ቴሌክላውድ አገልግሎትን በድረ-ገጻችን https://telecloud.ethiotelecom.et ማግኘት የሚቻል ሲሆን ክፍያውንም ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነው ቴሌብር ካሉበት በመክፈል ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ፡ bit.ly/3Wa7eCI
#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ