የሁለቱ ብፁዓን አባቶች የሽኝት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመከናወን ላይ ነው።
ገብርኄር ማለት መልካም ቸር ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ መታመንን፥ ታማኝ አገልጋይነትን፥ የመታመንን ዋጋ፥
የአለመታመንን ቅጣት ያመለከተበት ምሳሌያዊ ታሪክ እንደሚከተለው ቀርቧል
"ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥.....እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። "ማቴ 25:14-30
ይህ ታሪክ ምን አስተማረን? ራሳችንን አሳየን? ምንድነው የተቀበልነው ? ምን ያህል አተረፍንበት ? የጸጋ ስጦታችንን እናውቃለን? ድርሻችንን ተወጥተናል ? የኛ መክሊት ለሌሎች ምን ጠቀመ? በሌሎችስ መክሊት ምን ተጠቀምን ?በመክሊታችን ሰጭውን አከበርንበት ? እግዚአብሔር እንደ አቅማችን ማትረፊያ መክሊት ሰጥቶናል፡፡የሰጠንን መቅበር አንችልም፡፡በተሾምንበት ነገር ታማኝ መሆን አለብን፡፡የተቀበልን ነን የተቀበለ ደግሞ ይሰጣል የተቀበለ ሰጪውን ያከብራል የተቀበለ እንዳልተቀበለ አይኩራራም፡፡የተሰጠንን ሳንሰጥ ከሄድን እንጠየቃለን፡፡በተሰጠን መክሊት ራሳችንን እና ዓለምን ለእግዚአብሔር ክብር ማትረፍ አለብን፡፡ድርሻችንን መወጣት አለብን፡፡በአቅማችን ከሠራን በተሰጠን ከታመንን እግዚአብሔር በዚህ ደስ ይለዋል፡፡እግዚአብሔር አለመታመንን ይጠላል፡፡በተሰጠን ታምነን ማትረፍ አለብን፡፡ከምድር የጠፋ ትልቁ ሀብት ታማኝነት ነው፡፡ሰው እንኳን ሰውን ራሱን የሚያታልልበት ለራሱ እንኳ መታመን ያልቻለበት ሁኔታ አለ፡፡እግዚአብሔር ሳይሰጥ አልጠየቀም ለጋስነቱን እያመሰገንን በተሰጠን ልክ ታምነን መሥራት አለብን፡፡በተሰጠን በተሾምንበት በጥቂቱ ከታመንን እግዚአብሔር በብዙ ይሾመናል፡፡

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ የሽኝት ሥነ ሥርዓት በፎቶ
#የሁለቱ_ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት #ሥርዓተ_ቀብር_ተፈጸመ
የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሌሎች እምነት ተቋማት መሪዎች እንዲሁም
ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጽሟል።
ምንጭ:-ተ.ሚ.ማ