ተድባበ ጽዮን
94 subscribers
82 photos
53 videos
20 files
84 links
የግራኝ እመቤት ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም (ተድባበ ጽዮን) ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ982ዓ.ዓ የተመሰረተች ሲሆን ለበርካታ ዘመናት መስዋእተ ኦሪት የተሰዋባት ከ፬ቱ ጥንታዊ መናብርተ ጽዮን አንዷ ገዳም ናት።
Download Telegram
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ዘጰላድዮስ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ የትኞቹን አስደናቂ ገዳማት እንሳለማለን?
* የጉዟችን መነሻ ኅዳር 15
* መመለሻ ኅዳር 27
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 11000 ብር

በጉዟችን የምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ደብረ ሐተታ አቡነ ጽሕማ፣
👉 አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣
👉 አክሱም ደብረ ኖሕ ቅዱስ ያሬድ፣
👉 ተአምረኛው አቡነ መዝገበ ሥላሴ፣
👉 ጥንታዊቷ ፋፄ ቅድስት ማርያም፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 መካነ ሰማእታት አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ማይ ወይኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ ወአቡነ አሞኒ፣
👉 ተአምረኛዋ እንዳ ማርያም ደሓን (በገመድ ታስረው የሚወረወሩበት ጸበል)፣
👉 ዕዳጋ ዓርቢ አቡነ አረጋዊ፣
👉 ታሪካዊው ጎሕ ሥላሴ፣
👉 አላማጣ ኢየሱስ፣
👉 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉 ሸዋሮቢት አቡነ አረጋዊ (ሙቅ ጸበል)፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣
👉 ተአምረኛዋ ሽብሻቦ ማርያም ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ እና ሌሎችም...
★ ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

• የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ (ለመመዝገብ)፦
👉🏾 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 36

👉🏾 ቀጨኔ መድኃኔዓለም ማርሶሊ ዲጂታል ስቱዲዮ
Forwarded from ሞዐ ተዋህዶ - Moa Tewahido (አንተነህ ውብሸት)
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ እንደ ተጨማሪ ጥቃት ሊወሰድ የሚችል ነው።

በአርሲ የሚፈጸመው የኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግድያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በየዕለቱ ግድያዎች ይፈጸማሉ። ዛሬን ጨምሮ ኦርቶዶክሳዉያን እየተገደሉ ናቸው። አንድም ተከላካይም የለም። ባለፈው ሰሞን ኦርቶዶክሳዉያኑን ለማስጠለል የሞከሩ ሁለት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንደተገደሉ ሰምተናል። የእነርሱ ሞት በእጂጉ የሚያሳዝነው ስለሌሎች ብለው በመገደላቸው ነው። እስልምናን በመከተላቸው ምክንያት ግን አልተገደሉም። ዓላማውም ሌሎች እስላሞች እዚህ ተግባር ውስጥ እንዳይገኙ ለማስጠንቀቅ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ከዚህ በቀር በሐረር የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መገደላቸውንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም ስለሁኔታው መግለጫ ማውጣቷን አይተናል፤ ሰምተናል። በአርሲ ግን በየዕለቱ በተከታታይ እየተገድሉ ያሉት ኦርቶዶክሳዉያን ብቻ ናቸው።

ሁኔታዎች እንዲህ ባሉበት ሁኔታ ነው እንግዲህ ዛሬ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን መግለጫን የሰማነው። እንደ እውነቱ ከሆነ መግለጫውን በማስተዋል ካየነው እንደ ጥቃት የሚቆጠር ነው። ለእኔ እንደዚያ ነው ያየሁት ። ሌላው ቀርቶ ስለመቼው እና ስለየትኛው ግድያ እንደሆነ ሳይነግረን አንድ ሰው ከሁሉም ሃይማኖቶች እንደሆነ ገልጸውልናል ብሎ መናገሩ አሳዛኝ እና አስገራሚ ቢሆንም እኔን ያስገረመኝ ግን ይህ ብቻ አይደለም።

ዋናው ያሳሰበው የሰዎች ሞት አይመስልም። በጣም ያሳሰበው የሚመስለው የኦርቶዶክሳዉያን መባሉ ይመስላል፤ ከአቀራረቡ፤ ከጽሑፉ ። ከዚያም ያልታወቁ ሲባሉ የከረሙትን ገዳዮች ወደ ማሳወቅ ሲመጣ ደግሞ እንዲሁ የጠየቅኋቸው ሰዎች ነገሩኝ ብሎ የሌለ ነገር ማቅረብ ትዝብት ላይ የሚጥል ነው። ዛሬ ባያሳፍር ነገ ያሳፍራል። እንኳን የሟች ቤተሰብ ይቅርና ገዳዮችም የሚገረሙ ይመስለኛል። ሁኔታውን ላየው ደግሞ አውቆም ይሁን ሳያውቁ ገዳይን የመደበቅ ተግባር ይመስላል። ይህ ሒደት የብዙዎችን ግምት እውነት እንድል አስገድዶኛልም።

እስከሚገባኝ ድረስ ከየትኛውም ተቋም የሚጠበቀው የሟቿች የሃይማኖትና የብሔር ስብጥርን የማወቅ ጉዳይ አይደለም። ዋናው አንገብጋቢ ጉዳይ ተጨማሪ ንጹሐን እንዳይሞቱ የመከላከል ጉዳይ፣ መንግሥትን የማሳሰብ ጉዳይ ነው። ዋናውን ጉዳይ ትቶ የማኅበራዊ ሚዲያ ተሟጋቹን በሟቾች ስብጥር ላይ ጊዜያቸውን ለመውሰድ ወይም አትኩሮታቸውን ለማስቀየስ የሚደረገው ጥረት ከገዳዮች ያስቆጥር ካልሆነ የሚፈይደው ነገር የለም። ከሞቱትም ይልቅ እንገደላለን ብለው በፍርሃት ቆፈን ተይዘው በጭንቀት ችንካር ተቸንክረው በመሰደድ፣ በለቅሶ እና በሐዘን ውስጥ ላሉትም አንዳች ተስፋ አይፈነጥቅም። መግለጫውን እንደ ተጨማሪ ጥቃት የሚቆጠር ነው ያልኩት ለዚህ ነው። ስለሞቱት ማንነት እንጂ ስላሉት መጠበቅና መዳን ምንም ቁብ የማይሰጥ እንዲያውም ሁኔታውን ሊያባብስ የሚችል ስለሆነ ማለት ነው።

አሁንም መቼም ማንም ሊስተው የማይገባው ጉዳይ ግን መንግሥትን የተመለከው ጉዳይ ነው። መንግሥት ማስቆም ቢፈልግ ማስቆም ይችላል፤ ፈጽሞ ማስቆም ቢያቅተው እንኳ የሌለ ያህል በሚያስችል መጠን እጅግ አድርጎ ሊቀንሰው ይችል ነበር። ለምን ይችላል? ገና ሥልጣን እንደ ተረከበ በዘመነ አብዲ ኢሌ በኦሮሙኛ ተነጋራዎች ላይ የተፈጠረውን ችግር እንዴት እንዳስቆመው ማስታወስ ይቻላል። ገና ባልተደላደለበት በዚያ ጊዜ የቻለውን ነገር አሁን አይችልም ብዬ ላስብ አልችልም። ከዚያም በኋላ ቢሆን እንዲህ ዓይነት አካላትን ማስቆም ፈልጎ ያልቻለበትን ሁኔታ አላስታውስም። እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት ይቅርና ሌሎች ደካማ የሚባሉት መንግሥታት እንኳ እንዲህ ያለውን ድርጊት ማስቆም ፈልገው ያልቻሉበት አጋጣሚ ብዙ ሰምቼ አላውቅም። ፈጸሞ እንዳይከሰት ማድረግ ቢያቅታቸው ተከታትለው ማጥፋትና ማስቆም የሁሉም መንግሥታት ተግባርና የተለመደ ግዴታ ነውና።

አሁን በአርሲ እየሆነ ያለው ግን ፈጽሞ የሚያስገርም ነገር ነው። ሰዎች በየቀኑ ይገደላሉ። ጩኸቱ በጣም በርከት ያለ ጊዜ ከፍተኛ ንቀት የተመላበት፤ ለተቃርኖ እና ለማስረጃ የማይጨነቅ መልስ ይሰጣሉ፤ ። ልክ እንደምንሰማቸው “ተመጣጣኝ እርምጃ ተወስዷል”፣ “ከእኛም መሥዋዕትነት እየተከፈለ ነው” ዓይነት የፌዝና የስላቅ፣ ለሰሚዎቹ ሟቾቹን ከመግደል ያልተናነሰ፤ ለሕግም ለሞራልም ዴንታ የሌለው መግለጫ ይሰጣል። ለሕግ ዴንታ የሌለው ያልኩት አንድ የሕግ አካል መሠረታዊ ግዴታው አጥፊዎቹን ይዞ ለሕግ ማቅረብ ነው እንጂ ተመጣጣኝ እርምጃ ወስዶ እንኮ ቢሆን መውሰድ የሚያስችል የሕግ ድጋፍ እንዳለው አላውቅም። የአካባቢው አስተዳደር ግን አንድም ጊዜ ይህን አድርጎ አሳይቶ አያውቅም። እንዲያውም የቀሩትንና ሕግ አለ ብለው መረጃ የሰጡትን የቀሩትን የሟች ቤተሰቦች ድጋሚ ተጠቂ ያደርጋቸዋል እንጂ። ዛሬም ከአካባቢው ሰዎች የተሰማው መረጃ ይህን የመሰለ ነው። ይህ ሁሉ በእውነት የሚያሳዝንና የሚያስገርም ነው።

✍️ መምህር ብርሃኑ አድማስ
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ይሩማሊስ ዘዋልድባ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዳ ማርያም ደሓን - መቐለ
⛪️ በአክሱም ጽዮን ጉዟችን ከምንሳለማቸው ከ30 በላይ ቅዱሳት መካናት አንዷ ናት
👉 መነሻ ኅዳር 15 መመለሻ ኅዳር 27
👉 የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 11000 ብር

ለበለጠ መረጃ፦
📱 0901070707 / 0911289877
👉 አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
👉 አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መኮሬታ የገዳማት ትሩፋት
👉🏾 ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት መጻሕፍት
👉🏾 ንዋያተ ቅዱሳት
👉🏾 ከገዳማት የመጡ ነጠላዎችና ወይባዎች
👉🏾 የእጅና የአንገት መስቀሎች
👉🏾 ለቤተክርስቲያንና ለጸሎት ቤት የሚሆኑ ሽቶዎች
👉🏾 ከግብጽ የመጡ የአገልጋይ አይከኖች
👉🏾 የግሪክ ዕጣንና ከርቤ
👉🏾 የሰም ጧፍ፣ ንጹሕ ዕጣንና ፍሬ ያለው ዘቢብ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበናል

📱 ይደውሉ ይዘዙን፦ 0901070707
አድራሻ መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር
Forwarded from ቅዱሳት መካናት (ይሩማሊስ ዘዋልድባ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለአስተርእዮ ማርያም ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ከእኛ ጋር ይጓዙ!
* መነሻ ጥር 18
* መመለሻ ጥር 23
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 6500 ብር

👉🏾 በጉዟችን ላይ ሐይቅ ቅ/እስጢፋኖስ፣ ሳር አምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት፣ ሽብሻቦ ማርያምና ሌሎችንም ገዳማት እንሳለማለን
👉 የጉዞ ምዝገባ እያጠናቀቅን ነው

አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
☎️ 0901070707
📱 0911289877

👉🏼 አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር
ከግብፅ የመጡ የሚጠቀለሉ በጣም ሚያምሩ ሥዕለ አድኅኖዎች
ጥቂት ፍሬ ብቻ አሉን
👉 ትልቁ 70cm * 154cm
👉 ትንሿ 37cm * 97cm
👉🏾 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር
👉🏾 ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707
ለቤተክርስቲያን የሚሰጥ የምንጣፍ ሽቶ
👉 በጣም ደስ የሚል መዓዛ ያለው
👉 ባለ 1 ሊትር
👉 በሚገርም ቅናሽ
👉🏾 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር
👉🏾 ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ዘጰላድዮስ)
በፍፁም የማይቀርበት 9ኛው ዙር የንግሥ ጉዞ ወደ አስደናቂዎቹ ገዳማት ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ እና ማኅበረ ሥላሴ በአክሱም ጽዮን ልዩ ዙር
→ መነሻ የካቲት 20 መመለሻ መጋቢት 4
→ የጉዞ ዋጋ ማረፊያን ጨምሮ 14000 ብር
* ለበለጠ መረጃ፦ 0911289877 / 0901070707

★ ይህ ልዩ የጉዞ መርሐ ግብር፦
→ እምነቱ በቅዱሳን መላእክት ከገነት የሚመጣበት ድንቅ ቦታ፤
→ በከባዱ መከራ ዘመን ክርስቲያኖች የሚጠለሉበት የዘመናችን ሐመረ ኖኅ፤
→ በርካታ ኅቡዓን አበው የከተሙበትና ፈቃደ እግዚአብሔር ለሆነላቸው ሁሉ እየተገለጡ የሚባርኩበት መካነ ግኁሣን፤
→ ዘመንዎና ሕይወትዎ ብሩክ ይሆን ዘንድ ሰው ሆነው እንደ መላእክት ከሚኖሩ ከእውነተኞቹ መናኒያንን በርከክ ብለው ቡራኬ ተቀብለው የሚመለሱበት የበረከት ምድር፤
→ ትምህርት ለማይገባው ሁሉ በኃይለ እግዚአብሔር በቅዱስ ያሬድ ቃልኪዳን አእምሮውን ለብዎውን ባርኮ አስተዋይና ጠቢብ የሚያደርግ ፈዋሽ ጠበሉን ተጠምቀውና ጠጥተው የሚመለሱበት፤
→ ጃንደረባው ባኮስ፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድና ሌሎች በርካታ ቅዱሳን በተሰወሩበት ደብረ ሐዊ ገዳም የቃልኪዳናቸውን በረከት የሚያፍሱበት፤
→ ለብዙ ዘመናት ወንበር ተክለው ጉባዔ ዘርግተው ምሥጢር እያደላደሉ በርካታ ሊቃውንተ ቤተከርስቲያንን ከሚያፈሩ መምህራነ ጉባዔያት ጋር ተገናኝተው ለጥያቄዎቻችሁ ሁሉ መልስ የምታገኙበት፤
→ በጸሎት ተጋድሏቸው ከተጠቀሙ ንዑዳን ክቡራን አበው ጸሎትና ቡራኬ የምትቀበሉበት፤
→ እጅግ በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን የምንሳለምበት እና ታሪካዊ ቦታዎችን የምንጎበኝበት የ15 ቀናት ልዩ ጉዞ ነው።

❖ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ይህንን ቅዱስ ቦታ ለመሳለም የምትሹ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ! ለበለጠ መረጃ፦
👉 0901070707 / 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

❖ በዚህ ታሪካዊ የንግሥ ጉዟችን የምንሳለማቸው ጥንታዊ ገዳማትና የምንጎበኛቸው መካነ ቅርሶች፦
👉🏿 ራስደጀን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ፣
👉🏿 መንታበር ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ አረጋዊ፣
👉🏿 ላይ ጣና - ጥጉና ቅ.ኪዳነ ምሕረት፣
👉🏿 ወርቅ አበባ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፣
👉🏿 ደባርቅ መድኃኔዓለም፣
👉🏿 አይከል አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣
👉🏿 ጥንታዊው ማኅበረ ሥላሴ፣
👉🏿 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉🏿 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉🏿 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉🏿 ደብረ ሐተታ አቡነ ጽሕማ፣
👉🏿 ደብረ የሐ አቡነ አፍፄ፣
👉🏿 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉🏿 ጻድቋ ቅ.ዕድና ተጋድሎ ያረገችባት ቅ.ኪዳነ ምሕረት፣
👉🏿 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉🏿 ጎሕ ቅ.ሥላሴ፣
👉🏿 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉🏿 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉🏿 ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም፣
👉🏿 ማይኪራሕ ቅዱስ ያሬድ፣
👉🏿 አክሱም ኢየሱስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ አባ ሊባኖስ፣...
👉🏿 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉🏿 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉🏿 ማይወይኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣
👉🏿 ሰቋር ዋልድባ ኪዳነ ምሕረት ወመድኃኔዓለም፣
👉🏿 ዓዲ አርቃይ አስጋዲት ቅ.ማርያም፣
👉🏿 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉🏿 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ ወአባ አሞኒ፣
👉🏿 አስደናቂው አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣
👉🏿 መቐለ ደብረ ሰላም ቅ.ሚካኤል፣
👉🏿 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉🏿 ታሪካዊው ደሴ መድኃኔዓለም፣
👉🏿 ታሪካዊው ደብረ ብርሃን ሥላሴና ሌሎችም...
👉🏿 ከ1450 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው ራስ ደጀን ሆጨው ቤተ ጉባዔ [ቅዱስ ያሬድ ወንበር ተክሎ ጉባዔ ዘርግቶ ለ40 ዓመታት ያስተማረበትና እነ ቅዱስ ባኮስ የተሰወሩበት የስውሩ መቅደስ ጉልላት]፣
👉🏿 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበትና ለተገባው በየጊዜው የሚገለጥበት ደብረ ሐዊ ቅ/ያሬድ ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ የዋሻ ገዳም፣
👉🏿 ራሱ ቅ/ያሬድ በኪደተ እግሩ ከልሎ የገደመውና በቅዱሱ ሐይቅ በጣና ስም የሚጠራው መካነ ኅቡዓን ጣና ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም፣
👉🏿 ጃንደረባው ባኮስ የተሰወረበትን ደብረ ራስ ደጀን፣
👉🏿 ትምህርት ለማይገባው ሁሉ በቃልኪዳኑ አምነው ቢጠጡት አእምሮን የሚከፍት ጥበብና ማስተዋልን የሚያድል ተአምረኛ ጠበሉን ይጠመቃሉ፤ ይጠጣሉም።
👉🏿 ተአምረኛው ባለልብስ ጠበል የሚገኝበት ጥንታዊው መካነ ኅቡዓን ጨነቅ መድኃኔዓለም ገዳም፣
👉🏿 ታሪካዊዎቹ የጎንደር አድባራት (በተለይ በአቡነ ዓምደ ሥላሴ የተመሠረቱት፦ ጥንታዊው ደብረ ብርሃን ቅ/ሥላሴ፣ መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም፣ አጣጣሚ ቅ/ሚካኤል፣ ርእሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ፣ ፊት ቅ/ሚካኤል፣ ታሪካዊቷ ግምጃቤት ማርያም፣ እንዲሁም ታሪካዊቷ የእቴጌ ምንትዋብ ደብር ቅ/ቁስቋም፣ ተአምረኛዋ በዓታ ለማርያም፣ ቅ/ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል፣ አደባባይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ፊት በር አደባባይ ቅ/ጊዮርጊስ፣ ታሪካዊው ጎንደር ቅ/ዮሐንስ መጥምቅ፣... ወዘተ እንሳለማለን፤ በጎንደር ፋሲለደስ ጊቢ የሚገኙትን ታሪካዊዎቹን አብያተ መንግሥታት እንጎበኛለን

❖ ማሳሰቢያ፦ ጊዜያችንን በአግባቡ ከተጠቀምን በሕይወታችሁ የማትረሷቸውና ግሩም በረከት የምታገኙባቸው ሌሎች ገዳማትም ሰርፕራይዝ ይኖራሉ።
→ መነሻ የካቲት 20 መመለሻ መጋቢት 4
→ የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 14000 ብር

👉 በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ ጉዞ መሳተፍ ያልቻላችሁ ወገኖቻችን መክፈል የማይችሉ ወንድምና እህቶቻችንን በማገዝ ከበረከቱ ተሳተፉ።

✞❖✞ በማኅበራችን የጉዞ መርሐ ግብራት መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረውን ይጓዙ!!!
▶️ የመሄድ አሳብ ካሎትና ከወሰኑ ቀድመው  ይመዝገቡ!
👉 0911289877 / 0901070707
⛪️ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

• በአካል ለመመዝገብ፦
👉🏾 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር «መኮሬታ የገዳማት ትሩፋት»
👉🏾 ቀጨኔ መድኃኔዓለም ማርሶሊ ዲጂታል ስቱዲዮ

. በባንክ / በቴሌብር / ከፍሎ ለመመዝገብ
👉🏾 አንተነህ ውብሸት
☞ CBE 1000355477448
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ 0042939910101
☞ አማራ 9900001752271
☞ አዋሽ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707 / 0911289877

በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
👉🏿 @waldiba
@negeretewahido
የማኅበራችንን አካውንት Copy Link, Share, Repost, በማድረግ አግዙን!
👇👇👇👇👇👇👇

https://www.tiktok.com/@zegedamat
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ይሩማሊስ ዘዋልድባ)
አቡነ ፍሬ ካህን ዘገዳመ ሃይዳ
👉🏽 በመተትና በዓይነጥላ የታሰረ ሰው የጻድቁን ገድል ቢያነብና ሲነበብ ቢሰማ ከእስራቱ ይፈታል። መጽሐፈ ገድላቸው ተተርጉሞ በግእዝና በአማርኛ ታትሞ ለምእመናን በመጠነኛ ዋጋ እያከፋፈልን ነው።

👉🏾 አቡነ ፍሬካህን አባታቸው ንዋየ ማርያም ዘላስታ፣ እናታቸው ደግም ይዐቢ ክብራ ለማርያም ዘአበርገለ ናቸው። የተወለዱት ጥቅምት 3 ቀን 1351 ዓ.ም ሲሆን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና ምሁረ መጻሕፍት፤ የቅዱሳንን ዜና ሕይወት አጥንተው ያደጉ ጻድቅ ናቸው።

👉🏾 ጻድቁ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለቅመው ከትግራይና ጎንደር አውራጃዎች በአህዮቻቸው ጭነው በደብረ ሃይዳ ገዳም ለመነኑ የአቡነ ቶማስ ልጆች ያመጡ ነበር። በእሳት ሰረገላና በደመና ተጭነው የሚሄዱ ከ1000 የሚበልጡ በተጋድሎ ጽሙዳን ባሕታዊያንና ተኀራሚ መነኮሳት በገዳሙ መንነውበት ነበር።

👉🏾 አበው ዘገዳመ ዋሊ ቅድስቲቷን የዋልድባ ምድር «በአህያ አታስረግጥብን» ቢሏቸው በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት አህዮቹን ባርከው እፍ ቢሉባቸው ለእያንዳንዳቸው 2 ክንፍ አውጥተው በረሩ፤ ለራሳቸውም 6 ክንፍ ተሰጥቷቸው በተከዜ አድርገው ገዳመ ሃይዳ ገብተዋል።

👉🏾 ጻድቁ የአክስታቸውን ልጅ አቡነ እስጢፋኖስን አስከትለው በመጀመሪያ ከላስታ ተነስተው አበርገለን ባርከው በተንቤን አምበራ (ደብረ ጸለይ) እና በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ ምውት አስነስተው የሲኦልን መከራና ስቃይ እንዲመሰክሩ አድርገዋል። በቦታው ላይ ፈዋሽ ጸበል አፍልቀው በሰውና በእንስሳት ላይ ገቢረ ተአምራት ይሰራል።

👉🏽 ጻድቁ ደደቢት አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ደብረ ሃይዳ ገዳም ሄደው መንነው በመንፈስ አባታቸው በሥጋ አጎታቸው በሆኑት በአቡነ ቶማስ እጅም መነኮሱ። ጻድቁ ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆኑ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ይታወቃሉ።

👉🏾 አቡነ ቶማስ ካረፉ በኋላ አቡነ ፍሬ ካህን ገዳማቸውን ተረክበው በጽድቅ መንገድ መነኮሳቱን አስተዳድረዋል። አቡነ ፍሬ ካህን በአህዮቻቸው ከኢየሩሳሌም አፈር አምጥተው ገዳመ ሃይዳን በበረከት ሞልተዋታል።

👉🏽 አባታችን የቆላ ተንቤኑ ደብረ ጸለይ እና ከሽረ እንዳ ሥላሴ (ሽሬ) ከተማ 46 ኪ.ሜ ርቀት ላይ «ኮር ተክሊ» የምትባል አነስተኛ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የአቡነ ቶማስ ገዳም (ደብረ ሃይዳ) የተጋድሎ ቦታዎቻቸው ናቸው።

👉🏽 ወደዚህ ገዳም ውስጥ ሥጋና ቅቤ ተበልቶም ሆነ ተይዞ መውጣት ፈጽሞ አይቻልም። አልታየሁም ተብሎ በድብቅ ሥጋ ተይዞ ቢገባ ሥጋው ይተላል። ሥጋና ቅቤ የበላ ሰውም ዕለቱን በድፍረት ወደ ገዳሙ ቢገባ ሆዱ በኃይል ይነፋል በዚህም ይታወቅበታል። ከብቶችም ቢሆኑ ወደ ገዳሙ አይወጡም፣ ማንም ሳይመልሳቸው ራሳቸው ይመለሳሉ።

👉🏽 የአቡነ ፍሬ ካህን በዓለ ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ነው። በየዓመቱ በበዓለ ዕረፍታቸው ዋዜማ የተለየ መዓዛ ያላቸው ነፍሳት ድንገት መጥተው ቤተክርስቲያኑን ለ40 ቀናት አጥነው ታኅሣሥ 12 እንዴት እንደሄዱ ሳይታወቅ ይጠፋሉ።

የአቡነ ፍሬ ካህን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)
በመምህር ብንያም

"አነ ጽጌ ገዳም ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቄላት ወከመ ጽጌ ደንጎላት በማእከለ አስዋክ-እኔ የምድረ በዳ አበባ ነኝ በቆላ ውስጥ ያለ በሾህ መካከል የበቀለ የሱፍ አበባ ነኝ።" (መኃ.፪፥፩) ብሎ ነቢዩ ሰሎሞን እንደተናገረ ግንቦት አንድ ቀን በምድረ በዳ በአድባረ ሊባኖስ የበቀለችውን አማናዊት ንጽሕት የሱፍ፣ የጽጌረዳ አበባ የሆነችውን በመዓዛዋ ጣዕም የዓለምን የኀጢአትን ሽታ ያስወገደችውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት እናከብራለን፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በመዝሙሩ ፮፥፲ ላይ “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሐይ” (ይህቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፣ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሐይም የጠራች፣ ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) በማለት እንደ ፀሐይ የሞቀ፣ እንደ ጨረቃ የደመቀ፣ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጐበኘላት የእውነት ፀሐይ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ፤ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት ፩ በተወለደች ጊዜ ፊቷ በእጅጉ ያበራ ነበር፤ መዓዛዋም ከሽቱ ሁሉ ይበልጥ ነበር፡፡ የእመቤታችን ዜና ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ በብዙ ሕብረ አምሳል እና ትንቢት ሲነገርላት የመጣች ምልዕተ ምሥጢር ናት እንጂ፡፡
ይኸውም ልደቷ በሦስት ክፍል ተነግሮላታል፡፡
👉🏾 በልበ ሥላሴ

"እግዝእትነ ማርያም ነበረት እምቅድመ ዓለም በኅሊና አምላክ-እመቤታችን ዓለም ሳይፈጠር አስቀድማ በአምላከ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር" ተብሎ ተነግሮላታል። እግዚአብሔር ይህን ዓለም ሳይፈጥረው ግብሩን ያውቀው ነበር እና የሚድንበትንም ከፍጥረት አስቀድሞ በኅሊናው ያውቅ ነበር። እንዲህ ሲባል ግን ማወቅ እና ማሠራት ይለያያል። አወቀው ማለት አዳምን ክፉ አሠራው ማለት ግን አይደለም፡፡ ስንኳን እመቤታችንን ስለእኛ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር፦ "ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ መረጠን።" (ኤፌ.፩፥፬) ብሎ ተናግሯል፡፡ "እስመ እግዚእ ኀረያ-ጌታ መርጧታልና" እንድትመረጥ ሁና ብትገኝ ተመረጠች ብሎ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምም ተናግሮላታል፡፡

👉🏾 በሥነ ፍጥረት ተነግሮታል፦

እመቤታችን በበርካታ ሥነ ፍጥረት ምሳሌ ተመስላለች።
ከረቂቁ እስከ ግዙፉ ዓለም ድረስ ፡፡
ግብር እምግብር (ከተፈጠረ ነገር የተገኙ) ከተፈጠሩ ፍጥረታት በሰዓት እስከ ሚቆጠሩ ዕለታት ድረስ ፡፡
ከባሕር እስከ የብስ፣ ከየብስ እስከ ባሕር ድረስ፡፡
ከዓለመ መላእክት እስከ ዓለመ ሰብእ ድረስ፡፡
ለዚህ ነው ሊቁ አባ ሕርያቆስ፦
"በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ-በምን እና በምን እንመስልሻለን?" በማለት የተናገረው።

👉🏾 በሕገ ልቡና እና በሕገ መጻሕፍት ተነግሮላታል።

ይህም በብዙ ኅብረ አምሳል እና በብዙ ኅብረ ትንቢት የተነገረው ነው።
ኅብረ ትንቢት እንደሚከተለው ነው፦
"በአንተና በሴቲቱ በዘርህ እና በዘሯ መካከል ጠላትነትን አደርጋለው።" (ዘፍ.፫፥፲፭)
"ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ" (ዘፍ.፱፥፲፫)
"እግዚአብሔርም በሴም ድንኳን ይደር።" (ዘፍ.፱፥፳፯)
"በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች።" (ኢሳ.፯፥፲፬)
"ከእሴይ በትር ትወጣለች" …(ኢሳ.፲፩፥፩) ወዘተ በማለት ትንቢት ተናግረዋል።
በተለይም በጠቢቡ ሰሎሞን “ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስዩ” (መኃ ፬፥፰ ) ብሎ በአድባረ ሊባኖስ እንደምትወልድ በሚደንቅ ትንቢት ተናግሯል።

በብዙ ኅብረ አምሳል ደግሞ እንደሚከተለው ሲሆን
👉 በአምሳለ ሰዋስው (መሰላል) ለያዕቆብ (ዘፍ.፳፯፥፲፯)
👉 በአምሳለ ሐመልማል ለሙሴ (ዘጸ .፫፥፫)
👉 "በአምሳለ መሶበ ወርቅ፤ በአምሳለ ተቅዋመ ወርቅ፤ በአምሳለ ማዕጠንተ ወርቅ፤ በአምሳለ ታቦት" ለሙሴ፡፡

በጠቅላለው በኦሪት ውስጥ የተመሰሉ ምሳሌዎች ለእመቤታችን አምሳል ናቸው፡፡
በዘመነ መሳፍንት እና በዘመነ ነገሥትም በብዙ ተመስላለች።
👉🏻 "በአምሳለ ጸምር ለጌዴወን" (መሳ.፮፴፭)
👉🏻 "በአምሳለ መሶብ ለኤልያስ" (፩.ነገ.፲፱፥፮)
👉🏻 "በአምሳለ ንግሥት ለዳዊት"(መዝ.፵፬፥፱)
👉🏻 "በአምሳለ መርዓት ‹ሙሽራ›ለሰሎሞን (መኃ፬፥፰)
👉🏻 "በአምሳለ ፈጣን ደመና ለኢሳይያስ" (ኢሳ.፲፱፥፩) ወዘተ በመሳሰሉ ምሳሌያት እየተመሰለች እየተነገረች ዘመነ አበውን በምሥጢር እያለፈች አበውን በተስፋ እያጽናናች የመጣች እርሷ ናት፡፡

"ይእቲኬ መድኃኒት እንተ ኀሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት-ነቢያት የሿት እና የፈለጓት መድኃኒት ይህች ናት።" (፩.ጴጥ.፩፥፲) ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደነገረን፡፡ ራሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር ለአባታችን ለአዳም የሰጠው ዘለዓለማዊ ተስፋ የሚፈጸመው በእርሷ በኩል ነው።"ተስፋ ሕይወት ተሠርዐ-የሕይወት ተስፋ ተሠራልን።" ቅዱስ ያሬድ የሕይወት ተስፋም በድንግል ማርያም ተፈጽሟል።
"ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል-የአበው ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ።"እንዲል ደራሲው ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም።

ስለሆነም ቀን ሲደርስ አንባ ይፈርስ እንዲሉ፦
አማናዊ ቃል ኪዳን ሊጻፍባት አማናዊት ብራና ፤
አማናዊ ካህን ሊያገለግልባት አማናዊት መቅደስ፤
አማናዊ ፀሐየ-ጽድቅ ክርስቶስ ለሚወጣባት አማናዊት ሰማይ፤
አማናዊ ስንዴ ሊበቅልባት አማናዊት ምድር።

ግንቦት አንድ ቀን ከቅድስት ሐናና ከቅዱስ ኢያቄም በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ በሊባኖስ ተራራ ተወለደች፡፡ ባሕርየ ሰብእን የፈጠረ ባሕርይዋን ሊዋሐድ ንጽሕት እናቱን ፈጠረ። ፅንሰቷ በዘር በሩካቤ ቢሆንም ባሕርይዋ ሳያድፍ ጥንተ በደል ሳይደርስባት ተወለደች። "እምጽቡር ጽሩየ ገብራ-ንጽሕት አድርጎ ሠራት።" “ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን ከድንግልናዋ አልተለወጠችም።” (ሃይ.፶፫፥፳፪) ብሎ ሊቁ ቅዱስ ቴዎዶጦስ እንደተናገረ ፡፡አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም፦"ዐቀባ መንፈስ ቅዱስ እምከርሠ እማ-መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ማሕፀን ጀምሮ ጠበቃት።" (መ.ምሥ.፳፥፲)
ቀዳማዊት ሔዋን ያጣችውን ንጽሕና እመቤታችን ግን ሳይጎድልባት ይዛ ተወለደች፡፡

ስለዚህም ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፦ ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል-የንጽሕናችን የቅድስናችን መሠረትስ በማርያም ድንግል ተደረገልን" አለ፡፡
አምላካችን ከበረከተ ልደቷ ያሳትፈን!አሜን። ይቆየን
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ዘጰላድዮስ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የንግሥ ጉዞ ወደ ጻድቃኔ ማርያም
❖ እንባችሁ የሚታበስባት፣ ጸሎታችሁ የሚሰማባት፣ ጥያቄያችሁ የሚሰማባት ድንቅ ገዳም ናት
👉🏾 መነሻ ቀን ግንቦት 20
👉🏾 መመለሻ ቀን ግንቦት 21
👉🏾 የጉዞ ዋጋ ምሳን ጨምሮ 2200 ብር

❖ ወደ ምድራዊው ገነት እመጓ ቅ.ዑራኤል
ከጻድቃኔ ማርያም በዓለ ንግሥ ጋር
* መነሻ፦ ግንቦት 20 ከጠዋቱ
→ 10:30 አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣
→ 11:00 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ
→ 11:30 ጣፎ አደባባይ
* መመለሻ ግንቦት 23 (ለ4 ቀናት)
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 5000 ብር

✞❖✞ የቀሩን ወንበሮች ጥቂት ብቻ ናቸው፤ ይደውሉልና አብረውን ይጓዙ! አስቀድመው ድርሣነ ዑራኤልንና እመጓ መጽሐፍን ቢያነቡ ጥሩ ነው

ቢቀሩ የሚቆጩባቸው ሌሎች ጉዞዎቻችን፦
1) ሚጣቅ አማኑኤል
👉🏾 ግንቦት 28 እሑድ ደርሶመልስ
👉🏾 የጉዞ ዋጋ ምሳን ጨምሮ 2000 ብር

2) ተአምረኛው በርሚል ቅዱስ ጊዮርጊስ ጸበል
👉🏾 መነሻ ቀን ግንቦት 29
👉🏾 መመለሻ ቀን ሰኔ 10
👉🏾 የጉዞ ዋጋ ማረፊያን ጨምሮ 30000 ብር

ለጉዞው የሚያስፈልጉት፦
👉🏻 ለሙቀት የሚሆን ስስ ልብስ፣
👉🏻 ለወንዶች ቁምጣ፣
👉🏻 ለሴቶች ቢጃማ፣
👉🏻 ነጠላ ጫማ፣
👉🏻 ምንጣፍ፣
👉🏻 ቀለል ያለ ስልክ እንድትይዙ
👉🏻 ቀድመው ይመዝገቡ!
👉🏻 ሼር በማድረግ የዓለም ሕዝብ ይድንበት ዘንድ አድርሱ

ለምዝገባ (ትኬት ለመቁረጥ)፦
👉🏾 መኮሬታ የገዳማት ትሩፋት
👉🏽 አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር

ለበለጠ መረጃ፦
☞ 0901070707
☞ 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ዘጰላድዮስ)
መንፈሳዊ የንግሥ ጉዞ ወደ ስዕለት ሰሚው ቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
* መነሻ፦ ሐምሌ 17 ጠዋት 10፡30
* መመለሻ፦ ሐምሌ 20
* የጉዞ ዋጋ፦
👉🏾 ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 5000
👉🏾 ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 6500
* ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877
* ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

★ ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጋራ ሙለታ የሚገኘው፦

#ጥንታዊው_ቁሉቢ_ቅዱስ_ገብርኤል

→ ዘወትር ብዙ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸምበት መካነ መንክራት፤
→ በቅዱስ ገብርኤል ምልጃ ተማምነው በመድኃኔዓለም ቸርነት አምነው የለመኑት በጎ መሻት ሁሉ ፈጥኖ የሚፈጽምበት የብዙዎች መካነ ጸሎት፤
→ ጥንታዊውን ተአምረኛ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በ፱ኛው መ/ክ/ዘ ከዝዋይ ወደ ቦታው ይዘው የመጡትና በቦታው ላይ ለብዙ ጊዜ ተጋድሎ ያደረጉት የታላቁ ጸሎተኛ አባት የአባ ሌዊ ዘገዳመ ሲሐትና የሌሎችም ቅዱሳን የቃልኪዳን በረከት የሚገኝበት መካነ ቅዱሳን፤
→ በርካታ ስውራን ዘወትር የሚጸልዩበት መካነ ግኁሣን፤
→ ከጥንት ነገሥታትና ሹማምንት ጀምሮ በርካቶች በቦታው ላይ የተሳሉት ስዕታቸው እየሰመረላቸው "እሰይ ስዕለቴ ሰመረ!" እያሉ መባቸውን በደስታ የሚያገቡለት ስዕለት ሰሚ ነው።

★ እግዚአብሔር በልብ የመከረውን፣ በቃል ያስነገረውን እርሱ በወደደና በፈቀደ ጊዜ ያከናውናልና የእርስዎም ከእኛ ጋር ተጉዘው ስእለትዎ ሰምሮ እንዲመለሱ እንሻለን። "ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው" (መዝ ፻፲፰፥ ፻፳፮) እንዲል።

★ የጉዞ ምዝገባ ልናጠናቅቅ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ከማኅበራችን ጋር ለመጓዝ አስቀድመው እንዲመዘገቡ እናሳስባለን።
#ኑ_አብረን_እንጓዝ!!!

★ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የነዚህን ቅዱሳት መካናት የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

👉 "ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!
Forwarded from ዋልድባ ገዳም (ዘጰላድዮስ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የንግሥ ጉዞ ምዝገባ እንደቀጠለ ነው
* መነሻ መስከረም 15 እና 17
* መመለሻ መስከረም 24
* ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 11000 & 12000 ብር

👉🏾 በጉዟችን ላይ ፅጋጃ አቡነ አኖሬዎስ፣ ሐይቅ ቅ/እስጢፋኖስ፣ ሳር አምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት፣ ሽብሻቦ ማርያምና ሌሎችንም ገዳማት እንሳለማለን

አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
☎️ 0901070707
📱 0911289877

👉🏼 አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር