TechTalk With Solomon
8.55K subscribers
116 photos
11 videos
1 file
295 links
This is the official channel for Solomon Kassa’s TechTalk With Solomon. A channel created under “techtalkwithsolomon” is not official.
Download Telegram
በ2020 African Code Challenge (AfriCAN Code) ላይ ተወዳድራ ካሸነፈችው ብሩህ የ10 ዓመት ታዳጊዋ ሶሊያና ግዛው ጋር ያደረኩትን ቆይታ እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ! ላመለጣችሁ ሙሉ ጭውውቱ እነሆ!

https://www.youtube.com/watch?v=GBmI0gZ4KTM
የአገራት በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ልዕለ ኃያልነት ሩጫ | The Race to AI Superpower: አርብ መጋቢት 3 ከምሽቱ 2:30 ቆይታ በኢቢኤስ
በልዕለ ኃያላን አገራት መካከል የሚደረገው ፉክክር በሚሊቴሪ፣ በጠፈር ምርምር፣ በኒኩሊየር ኃይል፣ በስለላ እና ሌሎችም ጉዳዮች የነበረና ያለ ጉዳይ ነው። በዚህ የዲጂታል አብዮት ደግሞ አዲስ ፉክክር ብቅ ብሏል፤ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዙሪያ የዓለም ቁንጮ መሆን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ላይ በሁለት ክፍል የማቀብርብላችሁ የመጀመሪያ ክፍል ፕሮግራም በመጪው አርብ መጋቢት 3 ከምሽቱ 2:30 ቆይታ በኢቢኤስ እንዳያመልጣችሁ! https://youtu.be/tz_FjbFl6iA
በልዕለ ኃያላን አገራት መካከል የሚደረገው ፉክክር በሚሊቴሪ፣ በጠፈር ምርምር፣ በኒኩሊየር ኃይል፣ በስለላ እና ሌሎችም ጉዳዮች የነበረና ያለ ጉዳይ ነው። በዚህ የዲጂታል አብዮት ደግሞ አዲስ ፉክክር ብቅ ብሏል፤ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዙሪያ የዓለም ቁንጮ መሆን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ላይ በሁለት ክፍል የማቀብርብላችሁን የዛሬውን የመጀመሪያ ክፍል ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ እነሆ!
https://youtu.be/gyY_1mkorAg
TechTalk With Solomon S19 Ep4 [Part2]: የቻይና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ መራቀቅ እና ስጋቱ - The Race to AI Superpower
ቻይና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ በመታገዝ የሰዎችን የህይወት ዘይቤ የሚቆጣጠርና Social Score System የሚባል አሰራር ቻይናውያን እንደሚሰጣቸው የደረጃ ምደባ ልክ ምን ያህል ልጅ መውለድ እንደሚፈቀድላቸው፣ ምን አይነት ጥሩ ስራ ማግኝት እንደሚችሉ፣ በነጻነት ወደውጪ ሃገር መጓዝ እንደሚችሉ፣ ከምን አይነት የፍቅር አጋር ጋር መቆራኘት እንደሚችሉ እና ሌሎችንም ውሳኔዎች ማስተላልፈ ጀምራለች። ጥቅሙና መዘዙ ምን ይሆን?
በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ላይ በሁለት ክፍል ያቀረብኩላችሁን የዛሬውን የሁለተኛ ክፍል ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ እነሆ!
https://youtu.be/Io3QHSZuFPE
በሆላንድ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ የድሮን ተመራማሪ ዶ/ር አበጀ የኔሁን ጋር ያደረኩትን ቆይታ እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ እነሆ! Dr. Abeje is a nominee for the 2021 Best Engineer of the year award in Holland. The award is an initiative by the price to recognize those who distinguishes themselves in their work in the areas of expertise, innovation, entrepreneurship and social impact.

https://youtu.be/okcwo8HuzsY
የምናውቀው አይነት የአውሮፕላን የመብረር እና የማረፍ ሂደት ከ1800 ሜትር እስከ 2400 ሜትር ርዝመት ያለው መንደርደሪያ ያስፈልገዋል። ታዲያ የጦር አውሮፕላኖች የፊዚክስ ህግን የሚጥስ በሚመስል አሰራር 100 ወይንም 150 ሜትር በማይበልጥ አጭር መንደርደሪያ ካላቸው የጦር መርከቦች ላይ እንዴት ይበራሉ እንዴትስ በዚህ አጭር ማረፊያ ላይ ከፍጥነታቸው ቀዝቅዘው መቆም ይችላሉ? በዚህ ጉዳይ ያቀረብኩትን የዛሬውን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ላመለጣችሁ ሙሉ ዝግጅቱ እነሆ!

https://youtu.be/YkM0uMFRzic
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተፈጥሮ በአየር ላይ የተከማቸ ዳመናን ወደዝናብ ቀይሮ ማዝነብን በተመለከተ በሳይንሳዊ አጠራሩ ክላውድ ሲዲንግ ስለሚባለው አሰራር ያቀረብኩትን የዛሬውን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። በተለይም ኢትዮጵያ በዚህ ሂደት ውስጥ እየተሳተፈች መሆኗ ከተገለጸ በኋላ በርካቶች መልዕክት ልካችሁልኝ በጉዳዩ ላይ ሳይንሳዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ማብራሪያ እንድሰጥ ጠይቃችሁኛል። ፕሮግራሙ በቴሌቪዥን ያመለጣችሁ ሙሉ ዝግጅቱ እነሆ!

https://www.youtube.com/watch?v=2hjipWEGvqg
Suez Canal አስገራሚ ከሆኑ የሰው ልጅ የኢንጂነሪንግ ክህሎቶች አንዱ ነው። ከዚሁ የሰውሰራሽ የመርከቦች መተላለፊያ ጋር በተያያዘ አንድ ግዙፍ የንግድ መርከብ የጎንዮሽ ተቀርቅሮ ሰሞኑን አንድ የዜና መስህብ ሆኖ ነበር። ኢላን መስክ የማርስ ጉዞ ህልሙን ለማሳካት የማያደርገው ነገር የለም ሰሞኑንም ወደማርስ ለመሄድ የሚያግዝን ሮኬት በተደጋጋሚ እየሞከረ ይገኛል።

ስለነዚህ ጉዳዮች ያዘጋጀሁት ፕሮግራም አርብ ሚያዚያ 8 ከምሽቱ 2:30 በኢቢኤስ እንዳያመልጣችሁ!

https://m.youtube.com/watch?fbclid=IwAR3pFMvbEh4zFw_nzeBEMzq7CivuEQHTKFfW_PG4Y5qw16KJ5Ip6aneH8xc&v=fZgHwbcuHrw&feature=youtu.be
Suez Canal አስገራሚ ከሆኑ የሰው ልጅ የኢንጂነሪንግ ክህሎቶች አንዱ ነው። ከዚሁ የሰውሰራሽ የመርከቦች መተላለፊያ ጋር በተያያዘ አንድ ግዙፍ የንግድ መርከብ የጎንዮሽ ተቀርቅሮ ሰሞኑን አንድ የዜና መስህብ ሆኖ ነበር። ኢላን መስክ የማርስ ጉዞ ህልሙን ለማሳካት የማያደርገው ነገር የለም ሰሞኑንም ወደማርስ ለመሄድ የሚያግዝን ሮኬት በተደጋጋሚ እየሞከረ ይገኛል። ስለነዚህ ጉዳዮች ያዘጋጀሁትን የዛሬውን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ ሙሉ ዝግጅቱ እነሆ!
https://www.youtube.com/watch?v=RCmYcnwHXjM
ነዳጅ አስገራሚ የየተፈጥሮ ስጦታ ነው ይህ ወሳኝ የዘመናችን የሃብት እና የሃይል ምንጭ እንዴት ይፈጠራል፣ እንዴት ይገኛል፣ ከጥልቅ መሬትና የውቅያኖስ ምርድ ስር እንዴት ይወጣል? ስለነዚህ ጉዳይ ያዘጋጀሁትን የዛሬውን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ! የዛሬው ፕሮግራም ላመለጣችሁ፣ ሙሉ ዝግጅቱ እነሆ!

https://youtu.be/AI51pk4WOXI
828 ሜትር ቈመት ስላለው ባለ 160 ፎቁ የዓለማችን ረጅም ህንጻ በአሸዋ ላይ እንዴት እንደገነባ ያቀረብኩትን የዛሬውን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ከዛሬው ፕሮግራም በጣም የገረማችሁ ነገር ምንድነው? ፕሮግራሙ በቴሌዢዥን ላመለጣችሁ ሙሉ ፕሮግራሙ እነሆ!

https://youtu.be/0wiULmyi8o8
የቴክኖሎጂ ፈጠራ ለኢትዮጵያ የዲጂታል የወደፊት ጉዞ ያለውን ፋይዳ በተመለከተ ከዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር ያደረኩትን ጭውውት እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ ሙሉ ጭውውቱ እነሆ
https://youtu.be/uGhkMXj8uAc
ከተመልካቾች በደረሰኝ በርካታ ጥያቄ መሰረት ስለተለያዩ አይነት ድሮኖች በተለይም ስለሚሊቴሪ ድሮን አሰራር ያቀረብኩት የዛሬውን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ ሙሉ ዝግጅቱ እነሆ!

https://youtu.be/2S6_gnAoo3U
በዛሬ የምዕራፍ 19 መዝጊያ ዝግጅት ፕሮግራም ላይ ስለ እስራኤሉ የሮኬት ጥቃት መከላከያ አይረን ዶም፣ በራሪ ሰው፣ የመሬት ውስጥ እርሻ፣ ተንሳፋፊ ከተማ፣ የአየር ላይ ዋና፣ በካርበን ሞኖክሳይድ ፈንታ ኦክስጅን እና ውሃ የሚያስወጣው መኪና፣ እና የድሮን የምሽት ትዕይንት ያስቃኘኋችሁን ፕሮግራም እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ! ፕሮግራሙ ላመለጣችሁ፣ ሙሉ ዝግጅቱ እነሆ!
https://youtu.be/XhLMn5Xfczk
TechTalk With Solomon - አዲስ ምዕራፍ 20 | New Season 20 - ቆይታ ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምራት ጋር በቅርብ ቀን
https://youtu.be/Sq31q7ZB4Ro