Ethio Entrance
2.38K subscribers
42 photos
3 videos
45 files
36 links
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇
ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም
 
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇
https://student.ethernet.edu.et/
 
የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።
 
👍1
ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገቡና ለፈተና ለተመረጡ ተማሪዎች ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና መስጠቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ለፈተና ተመርጣችሁ በተለያየ ምክንያት ፈተና ያልተፈተናችሁ ተማሪዎች፣ ሰኞ ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፈተና መስጫ ማዕከል በመገኘት መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በድጋሜ መፈተን የማይቻል መሆኑ ተገልጿል።
❤1👍1
#OdaBultumUniversity

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ትምህርት መስከረም 11/2019 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፤ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ (ፍሬሽማን) ተማሪዎች ምደባ በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ሲደረግ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል፡፡
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች (2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ) የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑን አሳውቋል።

ምዝገባ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ እንደሚከናወን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ማንኛውም ተማሪ ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ እንዳለበት ገልጿል።
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በሀትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ አዲስ ገቢ መደበኛ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተከታተላችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
መልካም አዲስ ዓመት ! 🎉🇪🇹

አዲሱ ዓመት 2019 ዓ/ም የሰላም ዜና የምንሰማበት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ድምፅ የሚሰማበት፤ የሀዘን እንባ በደስታ እንባ የሚተካበት፣ ቤተሰቦች በሰላም የሚገናኙበት፣ ወጣቶች በተስፋ ወደ ግባቸው የሚመለከቱበት ዓመት ይሁንልን።

ግጭት ቦታውን ለሰላም፣ ፍርሃት ለተስፋ፣ ችግር ለመፍትሔ የሚለቅበት፤ የኑሮ ጫና የሚቀልበት፣ ሠርቶ መለወጥ የሚቻልበት፣ በሀገራችን መኖር ኩራት የሚሆንበት ዓመት ይሁንልን።


መልካም አዲስ ዓ
መት!
🥰1
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%)

2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)

በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ

1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%)

4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም
Remedial student!

Disqualified የተደረገባችሁ ተስተካክሏል ገብታችሁ check አድርጉ
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ተለቋል ገብታችሁ እዩ።

Here is the link https://student.ethernet.edu.et/view-placement
" ቅሬታ አለን ይታይልን " ያሉት የሪሚዲያል ተማሪዎች

በ2018 ዓ.ም. የሪሚዲያል (Remedial) ፕሮግራምን በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመድበው የተማሩ ተማሪዎች፣ በቅርቡ የተለቀቀው የማጠናቀቂያ ፈተና ውጤታቸው በእነሱ ጥረትና ትጋት ልክ ያልሆነ እና እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን በመግለጽ ውጤታቸው እንዲጣራ ለትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ቅሬታ አቀረቡ።

ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎቹ በጋራ በላኩት መልዕክት በፈተናው ሂደትና በውጤት አሰጣጡ ላይ መሠረታዊ ችግሮች እንዳጋጠሟቸው ጠቅሰዋል።

1. በጆግራፊና ፊዚክስ የታየው ዝቅተኛ ውጤት

በማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በጆግራፊ (Geography)፣ በተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች ደግሞ በፊዚክስ (Physics) ትምህርቶች ያገኙት ውጤት በብዙ ተማሪዎች ላይ በተመሳሳይ መልኩ እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ መጥቷል ብለዋል።

ይህም ከፍተኛ ጥረት ያደረጉና በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ ተማሪዎችንም ያካተተ በመሆኑ፣ በውጤት አሰጣጡ ወይም በእርማት ሂደቱ ላይ ስህተት ሊኖር ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳደረባቸው ገልጸዋል።

2. የኢንተርኔት መቆራረጥ

ተማሪዎቹ ፈተናውን በሚወስዱበት ወቅት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የኢንተርኔት ኮኔክሽን መቆራረጥና መዘጋት እንዳጋጠመ ጠቅሰዋል።

እንደ ተማሪዎቹ ገለጻ፣ ይህ ችግር ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ ለመሥራትና በተመደበለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

3. ፈተናው በሦስት ዙሮች መሰጠቱ

ፈተናው በሦስት የተለያዩ ዙሮች ወይም "Seasons" መሰጠቱን ተማሪዎቹ ጠቅሰው፣ በዙሮቹ መካከል የውጤት መደባለቅ ወይም "Data mismatch" ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል ጠርጥረዋል።

በመሆኑም የፈተና ውጤቶቹ ከተማሪዎች መረጃ ጋር በድጋሚ እንዲጣራ ጠይቀዋል።

4. " Disqualified " ከተባሉ በኋላ የታየው ውጤት

ተማሪዎቹ አብዛኛዎቹ በመጀመሪያ " Disqualified " ተብለው እንደነበር ገልጸው፣ በኋላ ውጤታቸው ተስተካክሎ ሲመጣ ግን እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ይህም በእርማት ሂደቱ ወይም በፈተናው ሲስተም ላይ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል ያሳያል የሚል ስጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም አንዳንድ ተማሪዎች " Disqualified " ተብለው እንደነበር በድጋሚ እንዲታይ ጠይቀዋል።

ተማሪዎቹ በሌሊትና በቀን በመማር ያደረጉት ጥረት በውጤታቸው እንዳልተንጸባረቀ በመግለጽ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ቅሬታ እንዲመለከት ጠይቀዋል።

በተለይም በፊዚክስና ጆግራፊ የታዩ ዝቅተኛ ውጤቶች ከ100 በላይ እንዳይቀየሩ በማስቀመጥ፣ የፈተና አሰጣጥ ሲስተም፣ የሦስቱ ዙሮች መረጃ እና የእርማት ሂደቱ በጥብቅ እንዲጣራ ጠይቀዋል።

እንዲሁም በፈተናው ውስጥ ትክክለኛ ጥያቄ ያልሆኑ ጥያቄዎች ካሉ ታሳቢ ተደርገው ውጤታቸው እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ የልፋታቸው ፍሬ እንዲሰጣቸውና ቅሬታቸው እንዲደመጥ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahuniversity
PEN: Write; RUBBER: ____
Anonymous Quiz
13%
A. Eliminate
30%
B. Remove
43%
C. Erase
13%
D. Sweep
❤1👍1
📝 I make my bed every morning.

🈯️ ጠዋት ጠዋት አልጋዬን አስተካከላለሁ።

I wash the dishes after dinner.

🈯️ ከእራት በኋላ ሳህኖቹን እጠባለሁ።

I sweep the floor every day.

🈯️ ወለሉን በየቀኑ እጠርጋለሁ።

I do the laundry on weekends.

🈯️ ?????
❤2😁2🥰1
SLOW ENGLISH Vs FAST ENGLISH

- I don't know. = Dunno.

- I am going to Leave. = I'm gonna leave.

- what are you doing? = whatcha doing?

- Do you want to come? = Wannacome?

- Have fun. = Enjoy !

- I think so. = I guess so.
🎉1
#MoE
 
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ላይ በመግባትና የፋይዳ ቁጥራችሁን በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
በተመሳሳይ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/view-placement ላይ በመግባት መመልከት እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል መርሐግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ
https://student.ethernet.edu.et/view-placement በመግባት መመልከት እንደምትችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
 
በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በ https://student.ethernet.edu.et/complaints አማካኝነት ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
 
ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia