The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#እግዚአብሔርን_አመስግኑ
#አብረን_ለማመስገንም_እንዘጋጅ
#ወጣት_አብረሃም_በሰላም_ወደ_ሀገሩ_ተመልሷል

ከጥቂት ወራት በፊት ሁለቱም ኩላሊቱ ተግባራቸውን መለገስ የተሳናቸውን እንዲሁም በዚሁ ምክንያት በተያያዥ በሽታ ማለትም በሳምንት ሁለት ግዜ ብቻ ዲያሊስስ በማድረጉ . . . በርካታ ችግሮች በአንድ ላይ የተጋፈጠ ወጣትን ታሪክ ሰምተን ብዙዎቻችን አዘነን እንደነበር ይታወሳል።

ወጣት አብርሃም ጌታቸው ወደ እስክሪን ከቀረበ በኋላ የእናንተም ቅጽበታዊ ምላሽ በፍጥነት ከተጠየቀው ገንዘብ በላይ እንዲያገኝ አግዞት ወደ ቱርክ ለቀዶ ህክምና ከሁለት ወንድሞቹ ጋር እንደሄደ የሚታወስ ነው!

በዛም ያለው ቆይታቸው ብዙ ፈተና ቢበዛውም ከቤተክርስትያን ጀምሮ በእናንተንም ጥብቅ ጸሎት ያሉትን ችግሮች ሁሉ አቅም ያሳጣ የእግዚአብሄር ደግነትና ምህርት ፈጥኖለት በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ጥገናውን አድርጎ አሁን እሱም እንዲሁም ኩላሊቱን የሰጠው ወንድሙ ጌድዮን ጌታቸውም በጥሩ ጤንነት በሰላም ወደ ሀገራቸው በዛሬው እለት ገብተዋል።

የክርስቲያን ዜና ከ ቤታችን ቴሌቪዥን ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት በኢትዮጵያ አየር ማረፊያ ተገኝተን ከወዳጅ ቤተሰቦቹ ጋር መልካም አቀባበልን አድርገንለታል።

እሱም ለቅዱሳን አጭር መልዕክት በቪዲዮ ያስተላለፈ ሲሆን እሱን በዝርዝር በቪዲዮ ዜና ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።

በቅርብ ቀን ደግሞ በቤታችን ቲቪ ሙሉ ቃለ መጠይቁን በተለይም በቱርክ የነበረውን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ተወዳጅ ቆይታ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#አዲስ #ዜና

የካናዳ ፍርድ #ቤት አብያተ ክርስቲያናት ላይ የኮቪድ ወቅት እግድን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።

#ፍርድ ቤቱ የካናዳ #ሁለት ግዛቶች #ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ በበረታበት ወቅት በአካል መሰብሰብን አግዶ በነበረበት ወቅት በመሰብሰባቸው ምክንያት ነው ጉዳዩን አልመለከተውም ያለው።

በወቅቱ አብያተ ክርስቲያናቱ በካናዳ #መንግስት የተወሰነውን በአካል ተገናኝቶ የማምለክ እገዳን ተላልፈው ሲሰበሰቡ ነበር ተብሏል።

ዘ ቸርች ኦፍ ጋድስ የተሰኘችው ቤተ ክርስቲያኗ ይሄንንም በመተላልፏ 240ሺህ ዶላር ቅጣት በግዛቷ ፍርድ ቤት ተጥሎባታል።

በኦንታሪዮ የምትገኘው የቸርች ኦፍ ጋድ መሪዎች በበኩላቸው ይሄ የፍርድ ቤት ውሳኔ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋ ነው ብለውታል።
በሃገሪቱ የፍትህና ነጻነት ታሪክም አሳዛኝ #ቀን ነው ብለውታል።

ሬስቶራንቶችና ስፖርት ቤቶች፣ መክፈት በተፈቀደበት #ጊዜ #ቤተክርስቲያን እንዲዘጋና አቤቱታን አላስተናግድም ማለታቸው የእምነትን ነጻነት የሚጋፋ ነው ብለውታል።

እኛ ሰውን ሰምተን ሳይሆን #እግዚአብሔርን ነው የምንታዘዘው በማለት በወቅቱ በሮቻቸውን ሳይዘጉ የአምልኮ መርሃ ግብሮቻቸውን ሲያካሂዱ እንደነበረ ገልጸዋል።
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#RegisterNow

ዘመናችን፦ 👉ከቅድስና ይልቅ ኃጢአት #ክብር የመሰለበት
👉 የዚህች #ዓለም ወጥመዶች በየጓዳችን ዘልቀው የገቡበት
👉ከኑሮ ውጥረት የተነሳ ተረጋግቶ ከልጆች #ጋር #ጊዜ ለማሳለፍ የከበደበት
👉ልጆችን መግራት ኋላቀርነት በሆነበት
👉የትምህርቱ ዓለም ጮክ ብሎ " #እግዚአብሔር የለም" በሚልበት በዚህች ዓለም ልጆችን #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደግሞም በሰውም ፊት የላቁ አድርጎ ማሳደግ እንዴት ይቻላል?

አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን/ በመደወል #ይመዝገቡ

https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk

📱0911136520/0988343523
⌚️መጋቢት 7 ፣ ከጠዋቱ 2:30-10:30

ቦታው :- የምርጦቹ 7000 #ቤተክርስቲያን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Please 🙏WATCH me
& #Register

#እግዚአብሔር የለም" በሚልበት በዚህች ዓለም ልጆችን

#እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደግሞም በሰውም ፊት የላቁ አድርጎ ማሳደግ እንዴት ይቻላል?

#ሁሉም ሊሰሙት #እና ሊማሩበት የሚገባ ...

የቀረን ጥቂት #ቦታ ነው #ብቻ በመሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

#ማሳሰቢያ ያለምዝገባ መግባት አይቻልም!!!

ልጆቻችንን የሚጠብቅልን የለም ብላችሁ አትስጉ #ልጆች እየተጫዉቱ የሚጠበቁበት #እኛ በቂ ቦታ አዘጋጅተናል።

#Register #Register #ይመዝገቡ #ይመዝገቡ #ይመዝገቡ

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ /ይደውሉ
https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk
0911136520/0988353423
#ዘማሪ ቴዎድሮስ ታደሰ (ቴዲ) #ፓስተር ተደርጎ ተሾመ።

ዘማሪ ቴዲ በአሁኑ ሰዓት "አንድ ምዕራፍ" በሚል የዝማሬ ኮንሰርት እያከናወነ ሲሆን በኮንሰርቱ ላይ በመጋቢነት ሲሾም የቀረውን ጊዜ በተሰጠው ጸጋ #እግዚአብሔርን እና የእግዚአብሔን ሕዝብ በታማኝነት እና በቅንነት በተሰጠው ጸጋ ልክ ለማገልገል ቃል ገብቷል።

ቃል የማስገባቱን ስነ-ስረዓት የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ አስፈጽመዋል።