ታዱ ኮምፒውተር እና ሞባይል ቴክኖሎጂ💻
109 subscribers
251 photos
6 videos
2 files
27 links
ሰላም ውድ የቻናሌ ተከታዮቸ ወቅታዊና ትምርታዊ ነክ መረጃዎችን አደርሳችኋለሁ share and like እና ሰብስክራይብ ማድረጋችሁን አትርሱ
Download Telegram
ስዊፍት/SWIFT ምንድነው?
ሰሞኑን አሜሪካ እና አጋር የአውሮፓ ሀገራት በዓለም የንግድ ታሪክ ከኢራን
በመቀጠል የተወሰኑ የሩሲያ ባንኮች የስዊፍት ስርአትን እንዳይጠቀሙ
አግደዋል። ጦርነቱ የማይቆም ከሆነም ሩሲያን ሙሉ በሙሉ ከስርአቱ
ለማስወጣት ዝተዋል።
ለመሆኑ ስዊፍት/SWIFT ምንድነው?
SWIFT የሚለው ቃል ምህጻረ-ቃል ሲሆን የሚወክለው Society of
Worldwide Interbank Financial Telecommunications የሚለውን
ነው። ይህ ስርአት በቤልጂየም ውስጥ እ.ኤ.አ. በ1973 የተመሠረተ ተቋም
ነው። የስዊፍት ስርአት ፋይናንስ ነክ መረጃዎች በፍጥነት፣ በአስተማማኝ ሁኔታ
እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በአለም ላይ በሚገኙ 200 ሀገራት ውስጥ ያሉ
11,000 ባንኮች እንዲላላኩ ያስችላል። ስዊፍት ባንኮችን ተክቶ ለደንበኞች
ገንዘብ የሚያስቀምጥ ተቋም አይደለም። ከእዚያ ይልቅ ባንኮች እርስ በእርስ
የሚያደርጉትን ፋይናንሺያል ትራንዛክሽኖችን የተመለከቱ ፋይናንስ ነክ ምስጢራዊ
መልእክቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ያቀባብላል። በአጭሩ የአለም አቀፍ ባንኮች
አስተማማኝ Gmail በመሆን ያገለግላል።
ለምሳሌ ያህል ባንኮች የመተማመኛ ሰነዶች/Letter of Credits ለመከፈት፣
የገንዘብ ዝውውር ትእዛዛትን ለማስተላለፍ፣ ገንዘባቸውን ካስቀመጡባቸው
ባንኮች ወደሌላ ባንክ እንዲዘዋወር ለማዘዝ፣ ለላኪዎች ክፍያ እንዲከፈል ገንዘብ
ያስቀመጡባቸውን ባንኮች /Correspondent Banks/ ለማዘዝ፣ ላኪዎች
ወደውጭ ሀገር ለላኳቸው ምርቶች ክፍያ ለመቀበል፣ ትልልቅ ኮርፖሬሽኖች
የከበሩ ማእድናትና የአክሲዮን ግዢዎችን ለመፈጸም የSWIFT ስርአትን
በመሣሪያነት ይጠቀማሉ።
የሩሲያ ባንኮች ከSWIFT ስርአቱ ተቆረጡ ማለት የሩሲያ የአለም አቀፍ ንግድ
ላይ ከፍተኛውን ጫና ይፈጥራል። ሩሲያ ከስዊፍት ስርአቱ ተገለለች ማለት
የሩሲያ ባንኮች ወደ ድንጋይ ዘመኑ የቴሌግራም እና የፋክስ ስርአት ለመመለስ
ይገደዳሉ። ሩሲያ SWIFTን የሚተካ ስርአት ብታበጅም የSWIFTን ያህል
ቅቡልነት ለማግኘት አመታትን መፍጀቱ አይቀሬ ይሆናል። አስከዛው ኢራን
ከSWIFT ስርአት የተሰረዘች ጊዜ የወጪ ንግዷ በ2/3 እንደቀነሰው ሁሉ የሩሲያ
የወጪ ንግድም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ አይቀሬ ይኾናል።
SWIFTን የሚቆጣጠሩት የG-10 ሀገራት ማእከላዊ ባንኮች ሲሆኑ እነዚህም
ሀገራት ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኢጣልያ፣ ኔዘርላንድ፣ ዩናይትድ
ኪንግደም፣ አሜሪካ፣ ስዊዘርላንድ እና ስዊዲን ናቸው። የእነዚህን ሀገራት
ማእከላዊ ባንኮች በበላይነት የሚመራው የቤልጅየሙ ማእከላዊ ባንክ ነዉ
@Tilahun Girma Ango
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ
እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን
አሳዩኝ።
# ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል
https://youtube.com/channel/UCxuKs2nEKmHaur3Z05MSvrg
የኮዲንግ ስሞችና ምስሎቻቸው