ታዱ ኮምፒውተር እና ሞባይል ቴክኖሎጂ💻
109 subscribers
251 photos
6 videos
2 files
27 links
ሰላም ውድ የቻናሌ ተከታዮቸ ወቅታዊና ትምርታዊ ነክ መረጃዎችን አደርሳችኋለሁ share and like እና ሰብስክራይብ ማድረጋችሁን አትርሱ
Download Telegram
#ላፕቶፕ #ኮምፒውተራችን_ ላይ_ Sleep, Hibernate,_ Shutdown_ ልዩነታቸው_ ምንድን ነው?

ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል።
ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች በዝርዝር እንመለከታለን::

“ስሊፕ”
በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ” የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።
ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።
ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ። በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ ማድረግ ተገቢ ነው።

“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር)
ይወስዳል።

“ሀይበርኔት”
ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው።
“ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥ ከ“ስሊፕ”
አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው። በሀይበርኔትም ሆነ
“ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው ሀይል ተመሳሳይ ነው።
ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።
መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?
በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ
ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።
ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።
ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን” ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ ይልቅ “ሀይበርኔት”ን
ይመርጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን” ማድረጉ ተመራጭ ነው።
ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው። ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል።
ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ። “ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል። በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።
የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ

https://youtube.com/channel/UCxuKs2nEKmHaur3Z05MSvrg

Telegram channel

t.me/taducom
👍1
#ከመተኛቶ_በፊት_ከስልክዎ_ጋር_ለረጅም_ሰዓት_ያሳልፋሉ?

እንግዲያውስ እንዲያቆሙ እንመክሮታለን፡፡
ከመኝታ በፊት ከስልክዎ ጋር ረጅም ሰዓትን ማሳለፍ 3 ከፍተኛ ጉዳትን በጤናዎ ላይ ያመጣል ይጠነቀቁ ዘንድ እንንገሮዎ
1. አይኖን ይጎዳል ስማርት ስልኮች ስክሪን (blue light) ናቸው፡፡ bluelight ማለት የተለያዩ
የብርሃን ቀለሞች ጥርቅም ሲሆን አይኖቻችን ውስጥ ሬቲና(retina) and Macular degeneration የሚባሉ የአይኖቻችንን ክፍል ይጎዱታል ይሄ ማለት የማየት አቅማችን ይቀንሳል ከፊት ለፊታችን ያለውን ማየት አንችልም ማለት ነው፡፡ በቀላሉ የ blue light ን ጉዳት ለማወቅ በየቀኑ ወደ ፀሃይ አተኩሮ ከማየት ጋር እኩል ነው ይሉታል እንደ ሳይንቲስቶቹ ጥናት ስለዚህም ስማርት ስልኮች ፤ ታብሌቶች ፤ ላፕቶፖች blue light ስላላቸው በተለይ ከመኝታ በፊት ለረጅም
ሰዓታትን መጠቀሞን ይተዉ፡፡

2. የእንቅልፍ ማጣት ቅድም በመጀመሪያው ላይ እንደገለፅነው ስልኮቻችን blue light አላቸው ብለናል ይሄው blue light በሰውነታችን ያለውን melatonin production የሚባለውን ሆርሞን ያዛባል melatonin production የተስተካከለ እንቅልፍ እንዲኖረን የሚያደርግ ነው ፤ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ማግኘት አንችችም ማለት ነው ይሄ ደግሞ ለብዙ የጤና ችግር ይዳርገናል

ለምሳሌ፡- ለልብ በሽታ ፤ ለማስታውስ ችግር ፤ ለጭንቀት፤ ክብደት መቀነስና የቆዳ ማርጀትን ያመጣል፡፡

3. ከፍተኛ የካንሰር ተጋላጭነት በምሽት የስልኮቻችንን መጠቀም ስናበዛ ለእንቅልፍ ችግር እንዳረጋለን ይሄ ደግሞ ለካንሰር ተጋላጭ ያደርገናል በተለይ ለጡት ካንሰር በወንድ መራቢያ አካል (prostate cancer) ካንሰር ያጋልጣል
melatonin የሚባለው ሆርሞን ስራውን ይዛባል፡፡ በነገራችን ላይ melatonin ካንሰርን ለመዋጋት
የሚረዳ ተፈጥሮ የሰጠችን ሆረሞን ነው፡፡
ይሄ ተጎዳ ማለት የሚጣውን አስቡት፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች የሚፈጠሩት በብዛት በመኝታ ሰዓታችን ስልኮችቻን ፤ ታብሌት ወይም

ኮምፒተራችን ስንጠቀም ነው፡፡
# እባክዎ ብዙዎችን ስለሚጠቅም ሼር በማድረግ ጓደኞቸዎም እንዲጠነቀቁ ያሳውቋቸው - -ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስዎ ፔጃችን
like ያድርጉ::

▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።

Youtube channel
here it is
https://youtube.com/channel/UCxuKs2nEKmHaur3Z05MSvrg
👍2
#ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ?
How to tell if your android phone is infected by virus or malware?

በተለይ ቁጥር 6. ጠቃሚ ምልክት ነው!
ለዛሬ ይዘንላቹህ የመጣነው ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ስልኮዎንስ ከቫይረስ እንዴት ነጻ ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ ትምህርት ነው መልካም ቆይታ

-ስለ ሞባይል እና ኮምፒውተር መረጃ - ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ?

1፡በስልኮዎ ውሰጥ ያሉ ፐሮግራሞቸ አልከፍትይላሉ
2፡በሚሞሪ ካርድዎ እና በስልክዎ ውስጥ ያሉ የራስዎ ፋይሎች ራሳቸውን ይቀይራሉ በተለይ ደግሞ በቫይረስ የተጠቃው ስልክዎ ከሆነ ፋይሎችን አልያ ሶፍትዌሮችን ለመክፈት ሲሞክሩ application not supported or file
dasn’t exist የሚል ሜሴጅ ሊመጣ ይችላል

3፡የስልክዎ የባትሪ ጉልበት በጣም እየደከመ ይመጣል ይሀ ምልክት ግን በኖርማልስልኮች ላይም ሊስተዋል ይችላል ያ የሚሆነው ደግሞ የሚጠቀሙትበባትሪ ኦርጅናል ባለመሆኑና በሌሎችም ችግሮች ሊሆን ይችላል ለምሳሌ
የስልክዎ ባትሪ ኮኔክተር ችግር ካለበት ባትሪዎን ቶሎ ቶሎ ይጨርስቦታል

4:ምናልባት ስልክ ደውለው እያናገሩ እያለ አልያ ደግሞ ገና እየደወሉ እያለ ስልክዎ ይቋረጣል :(ይህም ሌላ ምክነያትሊኖረው ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ ስክሪን ችግር ካለበትና ስልክዎ ባጋጣሚ የሚጠፋ ከሆነ፣የባትሪዎ ችግርም ሊሆን ይችላል

5: በስልክዎ ላይ በጫኑት አፕልኬሽን እየተጠቀሙ እያሉ ፕሮግራሙ በራሱ ጊዜ ሊዘጋቦ ይችላል

6: እንደ አጠቃላይ ልናየው የምንችለው ደግሞ የስልክዎ ነገራቶችን በፍጥነት የመከወን ብቃት እጅጉን ይቀንሳል ተሰላችተ እስከመወርወር ድረስ ሊያናድድዎም ይችላል ስለምለክቶቹ ይህን ያክል ካልን እንዴት መከላከል እንዳለብንና እንዴትስ ሁነቱ
ከተከሰተ በኋላ ማስወገድ እንደምንችል አንዳንድ ነገራቶችን እንጥቀስ

*ስለ ሞባይል እና ኮምፒውተር መረጃ *
1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው ስልክዎን ወዲያውኑ አጥፍተው ያብሩት/ ያስነሱት ይህን ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ይረዳወ ዘንድ ነው

2:የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ ለማጥፋት ይሞክሩ ይህ አልሆን ካለ

3:ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው app የሚለውን ጠቅ ሲያደርጉ ብዙ ፕሮግራሞች ይታያሉ ከነኛ መካከልእርስዎ የተጠራጠሩትን ያጥፉት select and then press uninstall

4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security የሚለውን ይምረጡ ከዚክ ጋ device adminstartore የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው ስልክዎን ሪስታርት ያድርጉት
ምናልባት ስልክዎ ቫይረስ ከሌለው ይህኛው አማራጭ በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉነ ፕሮግራሞችን ላያመጣይችላል

5.ስልኮን አጥፍተው የድምፅ መቀነሻው ይጫኑና እሲከበራ አይልቀቁ በዚህን ጊዜ ስልኮ ሴፍ ሞድ የሚል ፅሁፍ ያመጣልናል: ይህ የሚጠቅመን አልጠፋም ያሉ የቫይረስ አፕሊኬሽኖችን ከሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ በቀላሉ ለማጥፋት ነው::

ስልካችን በቫይረስ ከተጣቃ ምን ማደረግ አለብን?
1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው ስልክዎን ወዲያውኑ አጥፍተው ያብሩት/ ያስነሱት ይህን ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ይረዳወ ዘንድ ነው
2:የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ ለማጥፋት ይሞክሩ ይህ አልሆን ካለ
3:ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው app የሚለውን ስትጫኑ ሲያደርጉ ብዙ ፕሮግራሞች ይታያሉ ከነኛ መካከልእርስዎ
የተጠራጠሩትን ያጥፉት select and then press uninstall
4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security የሚለውን ይምረጡ ከዚክ ጋ
device adminstartore የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው ስልክዎን ሪስታርት ያድርጉት ምናልባት ስልክዎቫይረስ ከሌለው ይህኛው አማራጭ በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉነ ፕሮግራሞችን ላያመጣይችላል
5.ስልኮን አጥፍተው የድምፅ መቀነሻው ይጫኑና እሲከበራ አይልቀቁ በዚህን ጊዜ ስልኮ ሴፍ ሞድ የሚል ፅሁፍ ያመጣልናል: ይህ የሚጠቅመን አልጠፋም ያሉ የቫይረስ አፕሊኬሽኖችን ከሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ በቀላሉ ለማጥፋት ነው::
6.የተለያዩ anti-virus application መጠቅም።
ይህ ትምህርት ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ላይክ እና ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ እናመሰግናለን
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም እና ዩቲዩብ ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://youtube.com/channel/UCxuKs2nEKmHaur3Z05MSvrg

Telegram channel

t.me/taducom
👍1
ስዊፍት/SWIFT ምንድነው?
ሰሞኑን አሜሪካ እና አጋር የአውሮፓ ሀገራት በዓለም የንግድ ታሪክ ከኢራን
በመቀጠል የተወሰኑ የሩሲያ ባንኮች የስዊፍት ስርአትን እንዳይጠቀሙ
አግደዋል። ጦርነቱ የማይቆም ከሆነም ሩሲያን ሙሉ በሙሉ ከስርአቱ
ለማስወጣት ዝተዋል።
ለመሆኑ ስዊፍት/SWIFT ምንድነው?
SWIFT የሚለው ቃል ምህጻረ-ቃል ሲሆን የሚወክለው Society of
Worldwide Interbank Financial Telecommunications የሚለውን
ነው። ይህ ስርአት በቤልጂየም ውስጥ እ.ኤ.አ. በ1973 የተመሠረተ ተቋም
ነው። የስዊፍት ስርአት ፋይናንስ ነክ መረጃዎች በፍጥነት፣ በአስተማማኝ ሁኔታ
እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በአለም ላይ በሚገኙ 200 ሀገራት ውስጥ ያሉ
11,000 ባንኮች እንዲላላኩ ያስችላል። ስዊፍት ባንኮችን ተክቶ ለደንበኞች
ገንዘብ የሚያስቀምጥ ተቋም አይደለም። ከእዚያ ይልቅ ባንኮች እርስ በእርስ
የሚያደርጉትን ፋይናንሺያል ትራንዛክሽኖችን የተመለከቱ ፋይናንስ ነክ ምስጢራዊ
መልእክቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ያቀባብላል። በአጭሩ የአለም አቀፍ ባንኮች
አስተማማኝ Gmail በመሆን ያገለግላል።
ለምሳሌ ያህል ባንኮች የመተማመኛ ሰነዶች/Letter of Credits ለመከፈት፣
የገንዘብ ዝውውር ትእዛዛትን ለማስተላለፍ፣ ገንዘባቸውን ካስቀመጡባቸው
ባንኮች ወደሌላ ባንክ እንዲዘዋወር ለማዘዝ፣ ለላኪዎች ክፍያ እንዲከፈል ገንዘብ
ያስቀመጡባቸውን ባንኮች /Correspondent Banks/ ለማዘዝ፣ ላኪዎች
ወደውጭ ሀገር ለላኳቸው ምርቶች ክፍያ ለመቀበል፣ ትልልቅ ኮርፖሬሽኖች
የከበሩ ማእድናትና የአክሲዮን ግዢዎችን ለመፈጸም የSWIFT ስርአትን
በመሣሪያነት ይጠቀማሉ።
የሩሲያ ባንኮች ከSWIFT ስርአቱ ተቆረጡ ማለት የሩሲያ የአለም አቀፍ ንግድ
ላይ ከፍተኛውን ጫና ይፈጥራል። ሩሲያ ከስዊፍት ስርአቱ ተገለለች ማለት
የሩሲያ ባንኮች ወደ ድንጋይ ዘመኑ የቴሌግራም እና የፋክስ ስርአት ለመመለስ
ይገደዳሉ። ሩሲያ SWIFTን የሚተካ ስርአት ብታበጅም የSWIFTን ያህል
ቅቡልነት ለማግኘት አመታትን መፍጀቱ አይቀሬ ይሆናል። አስከዛው ኢራን
ከSWIFT ስርአት የተሰረዘች ጊዜ የወጪ ንግዷ በ2/3 እንደቀነሰው ሁሉ የሩሲያ
የወጪ ንግድም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ አይቀሬ ይኾናል።
SWIFTን የሚቆጣጠሩት የG-10 ሀገራት ማእከላዊ ባንኮች ሲሆኑ እነዚህም
ሀገራት ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኢጣልያ፣ ኔዘርላንድ፣ ዩናይትድ
ኪንግደም፣ አሜሪካ፣ ስዊዘርላንድ እና ስዊዲን ናቸው። የእነዚህን ሀገራት
ማእከላዊ ባንኮች በበላይነት የሚመራው የቤልጅየሙ ማእከላዊ ባንክ ነዉ
@Tilahun Girma Ango
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ
እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን
አሳዩኝ።
# ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል
https://youtube.com/channel/UCxuKs2nEKmHaur3Z05MSvrg
የኮዲንግ ስሞችና ምስሎቻቸው