📢 ለሁሉም የBiT ተማሪዎች ፓርላማ አባላት በሙሉ
ሁሉም የBit የተማሪዎች ፓርላማ አባላት ቅዳሜ ከምሽቱ 2:00 ሰዐት ስብሰባ ስለሚኖር የተማሪዎችህብረት ቢሮ እንድትገኙ እናሳስባለን ።
📅 ቀን: ቅዳሜ
⏰ ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
📍 ቦታ: ቢሮ ጥቁር 04
ሁሉም አባላት በሰዓቱ እንዲገኙ እና በንቃት እንዲሳተፉ እንጠይቃለን።
እናመሰግናለን።

❤3
📢 Announcement to All BiT Students’ Parliament Members
All BiT Students’ Parliament members are hereby informed that a meeting will be held on Saturday at 2:00 PM (night). You are kindly requested to attend at the Students’ Union Office.
📅 Date: Saturday
⏰ Time: 2:00 PM (Night)
📍 Venue: Office Block 04
All members are expected to be present on time and participate actively.

የተማሪዎች ህብረት፡ ያንተ ድምፅ፣ ያንተ መከታ፣ ያንተ ቤተሰብ!" 🤝❤️
ውድ የኢንስቲትዩታችን ተማሪዎች፤ 👨🎓👩🎓
የተማሪዎች ህብረት ቢሮ ዝም ብሎ የቢሮ ቁጥሮች ስብስብ አይደለም። የህብረቱ አባላትም ካንተ የተለዩ አይደሉም። እኛም እንደ አንተ፦
📚 ለፈተና እንጨነቃለን፤
🍔 ካፌ እንሰለፋለን፤
💡 የዶርም መብራት ሲጠፋብን ይጨንቀናል።
እኛ፣ እናንተ ነን! 🔄
ህብረቱ የቆመው ለጥቂቶች ሳይሆን ለሁላችንም ነው። ዓላማችን፦
🗣 ያንተን ድምፅ ለአስተዳደሩ በግልጽ ማሰማት፤
🛡 ያንተን መብት እና ጥቅም ማስከበር፤
🤝 በችግርህ ጊዜ ከጎንህ መሆን (በአካዳሚክስ፣ በጤና፣ በበጎ አድራጎት...)፤
🎉 የካምፓስ ህይወትህን በስፖርትና በመዝናኛ ማሳመር ነው።
ብቻህን አይደለህም! 🤗 ካንተ የምንፈልገው መጥተህ እንድታገኘን፣ ሃሳብህን እንድታካፍለንና አብረኸን እንድትቆም ነው።
ህብረቱ ያንተ ነው፤ አብረን እንልወጠው! 💪✨
#BiTStudentUnion #WeAreYou #StudentPower #CampusLife

👍18😁11❤9😭1
"አንድ ብር ለምን ትበቃለች? 🤔 ለአንድ ተማሪ ምሳ! 🍽"
ውድ ተማሪዎች፤ 👨🎓👩🎓
አንዲት ብር 🪙 ዛሬ ላይ ለብቻዋ ምንም የምትገዛው ነገር ላይኖር ይችላል። 🤷♂️🤷♀️ ነገር ግን የእኔ፣ የእንተና የእሷ አንድ ብር ሲደመር... ✨ የጓደኛችንን የቀትር ረሃብ ያስታግሳል፤ 😋 የህክምና ወጪውን ይሸፍናል! 🚑🏥
በግቢያችን ውስጥ በኢኮኖሚ ምክንያት ለከፋ ችግር የተጋለጡ፣ 🤗 የምሳ ሰዓት ሲደርስ የሚጨነቁና 😔 የታመሙ ተማሪዎች አሉ። እኛ እያለን ግን ማንም ተማሪ ተርቦ መማር የለበትም! 🚫🚫
መርሃ-ግብሩ ቀላል ነው፦ በወር አንዴ ብቻ 1 ብር 🪙 ለህብረቱ በጎ አድራጎት ዘርፍ እንለግሳለን። 🤝🤝
ያንተ 1 ብር ለብቻዋ ትንሽ ናት፤ 👇🪙
የሁላችንም 1 ብር ግን የብዙዎችን ህይወት ትታደጋለች። 🔄➕🪙🪙🪙➡️❤️🩹
በዚህ በጎ ተግባር በመሳተፍ የሰውነት ግዴታችንን እንወጣ። "ጥቂት ብር ለብዙዎች ፍቅር!" 🪙💖💖💖
📍 የልገሳ ቦታ፦ በየክላሱ ለሚመጡ የህብረቱ ተወካዮች 🚶♂️🚶♀️ ወይም በበጎ አድራጎት ዘርፍ ቢሮ (ቁጥር 03)። 🏢

👏7❤4
የሳጥንህ ጥግ... የወንድምህ መከታ! 🤝❤️
ውድ የኢንስቲትዩታችን ተማሪዎች፤ 👨🎓👩🎓
አንዳንድ ጊዜ በካምፓስ ህይወት ውስጥ ጎንህ ያለው ጓደኛህ በዝምታ 😶 የሚታገለው ትልቅ ችግር ሊኖር ይችላል። አንተ ጋ ተዘንግቶ የተቀመጠ አንድ ሸሚዝ 👕፣ ጥግ የያዘ አንድ ጫማ 👟 ወይም አንብበህ የጨረስከው አንድ መጽሐፍ 📚 ለሌላው የነገ ተስፋው ሊሆን ይችላል! 🌟
በዩኒቨርሲቲ ቆይታችን ውጤት (GPA) ብቻ ሳይሆን ሰብአዊነትንም ይዘን እንውጣ። 🎓❤️ ዛሬ ያንተን ትርፍ ለሌላው ክብር ስትሰጥ፣ የአንድን ተማሪ የትምህርት ጉዞ እያቀናህ ነው! ✨
ተማሪው እንዳይቸገር፦ የትምህርት መርጃ መጻሕፍትን እንለግስ። 📚✍️
ጓደኛችን እንዳይቆራመድ፦ የትርፍ አልባሳትንና ጫማዎችን እናካፍል። 👕👟🧤
"የሰጠኸው ያንተ ነው!" 🎁 ዛሬውኑ የቁምሳጥንህን ጥግ ፈትሽና ለአንድ ተማሪ ብርሃን ሁን። 💡✨
📍 የመለገሻ ቦታ፦ ቢሮ ቁጥር 03 (በጎ አድራጎት ዘርፍ) 🏢 ወይም በየብሎኩ ባሉ የልግስና ሳጥኖች። 📦🗳

❤7🥰1
📢 አስቸኳይ ማስታወቂያ፡ የሎከር ጥገናን በተመለከተ
በመኖሪያ ክፍል (Dormitory) ውስጥ የምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ፤
ከዛሬ ጀምሮ በየዶርሞቻችህይ የሚገኙ
የሎከር ቁልፎች ጥገና
ስለሚካሄድ፣ ጥገናው በሚከናወንበት ወቅት በየዶርሞቻችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ልብ ሊባሉ የሚገቡ ነጥቦች፦
ተገኝነት፦ ጥገናው በሚካሄድባቸው ሰዓታት ለተወሰነ ጊዜ በክፍላችሁ ለመገኘት ጥረት አድርጉ።
ቅሬታ ማቅረቢያ፦ የጥገና ሠራተኞች ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ ወይም ካጋጠሟችሁ፣ ወዲያውኑ ቢሮ ቁጥር 04 በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።
ተማሪዎች ለጥገና ሥራው አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ እንጠይቃለን።
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

❤7👍6
Dear All,
We are excited to invite you to the launching program of the Innovation Incubation Management System at the Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University. This event will take place at the Business Incubation and Techno-Entrepreneurship Center.
Join us as we unveil this innovative system designed to foster entrepreneurship and support budding innovators. Your presence will be greatly valued as we embark on this journey together.
Date: March 27/2026
Time: 8:00 LT/afternoon
Venue: Business Incubation and Techno-Entrepreneurship Center, Bahir Dar Institute of Technology (BiTec-BiT).

❤4👍2😭2🤔1
Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ
Photo
🕊 የፍቅር ስጦታ 🕊
"ደግነትዎ የሰውን ህይወት ይቀይራል፤ የእርስዎ እውቀት ለአንድ ተማሪ ብርሃን ነው!"
የተማሪዎች ህብረት በጎ አድራጎት ዘርፍ ያዘጋጀውን የልገሳ ጥሪ ይቀላቀሉ!
👕 ልብስና ጫማ፦ የቆየም ይሁን አዲስ በየ ብሎኩ በተቀመጡ ሳጥን ውስጥ ይጨምሩ
📚 የትምህርት ቁሳቁስ፦ ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ መጽሐፍት
✨ ችሎታና ዝንባሌ (Talent)፦ ማስተማር ወይም በበጎ ፈቃድ ማገልገል ለምትፈልጉ!
አድራሻ፦ ቢሮ ቁጥር 3 | ስልክ፦ 0964570244

❤1
❤️ GIFT OF LOVE ❤️
"In a world where many have so much, some have so little. 🌟 Your surplus can be the light of hope for someone's life! ✨"
Let's use what we have to give and make a difference. Join the great donation call organized by the Students' Union Charity Sector! 🤝✊
What can you donate? 👇
👕👟 Clothes and Shoes: Old or new (place them inside this box)
📚✏️| Educational Supplies: Notebooks, pens, books
🎓🧑🏫 Talent and Skill (Talent): For those who want to teach or volunteer!
Address: 🏢 Office Number 3 | Phone: 📞 0964570244
There is nothing greater than to give and make a difference! ❤️

❤2
🌟 የድል አጋማሽ! 🌟
ውድ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) ተማሪዎች፤
የፈተና ሳምንቱን ግማሽ መንገድ በጽናት ተጉዛችኋል። የቀሩትን ፈተናዎችም በተሻለ ትጋትና ትኩረት እንደምትወጡ አንጠራጠርም።
ድካማችሁ ለስኬት፣ ጥረታችሁ ለውጤት እንዲበቃ ምኞታችን ነው። የቀሩት ቀናት የድልና የደስታ እንዲሆኑላችሁ እንመኛለን!
በርቱ! የድል አክሊሉ ቅርብ ነው!
የBiT ተማሪዎች ህብረት
"ሁልጊዜም ለተማሪው ስኬት!"

😁7🙏4❤2😭2👍1
Business Incubation and Techno Entrepreneurship Center at Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University (BiTec-BiT-BDU) is pleased to announce the Health Hackathon 2026, a dynamic and collaborative event aimed at fostering innovation in the health sector.
This hackathon brings together students, researchers, innovators, developers, and entrepreneurs to design creative, practical, and technology-driven solutions to pressing healthcare challenges. Participants will have the opportunity to work in multidisciplinary teams, receive mentorship from experts, and transform their ideas into impactful product.

Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ pinned «🌟 የድል አጋማሽ! 🌟 ውድ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) ተማሪዎች፤ የፈተና ሳምንቱን ግማሽ መንገድ በጽናት ተጉዛችኋል። የቀሩትን ፈተናዎችም በተሻለ ትጋትና ትኩረት እንደምትወጡ አንጠራጠርም። ድካማችሁ ለስኬት፣ ጥረታችሁ ለውጤት እንዲበቃ ምኞታችን ነው። የቀሩት ቀናት የድልና የደስታ እንዲሆኑላችሁ እንመኛለን! በርቱ! የድል አክሊሉ ቅርብ ነው! የBiT ተማሪዎች ህብረት "ሁልጊዜም ለተማሪው…»
🌟 የካምፓስ ሕይወት፡ ከዲግሪ በላይ የሚገኝባቸው ወርቃማ ዕድሎች! 🌟
ውድ ተማሪዎቻችን፤ ዩኒቨርሲቲ መግባት ማለት ዝም ብሎ በክፍል ውስጥ መወሰንና የምረቃ ቀን መጠበቅ ብቻ አይደለም። ይህ ወቅት የሕይወታችሁ ትልቁ የለውጥ ምዕራፍ የሚጻፍበት ጊዜ ነው። ግቢ ውስጥ በቆይታችሁ ልታተርፏቸው የሚገቡ 5 ወርቃማ ነገሮች እነሆ፡
1. ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር (Networking) 🤝
ዛሬ አብሯችሁ ካፌ የሚሰለፈው ተማሪ ነገ የአገር መሪ፣ ትልቅ ተቋም መስራች ወይም የቅርብ የስራ ባልደረባችሁ ሊሆን ይችላል። ከተለያዩ አካባቢዎችና ባህሎች ከመጡ ልጆች ጋር የምታደርጉት ግንኙነት ለአስተሳሰባችሁ መነቃቃትን ከመፍጠሩም በላይ ለወደፊት የሥራ ዓለማችሁ ትልቅ ድልድይ ይሆናል።
2. የመሪነት ብቃትና የተግባቦት ክህሎት 🎤
በተማሪዎች ህብረት፣ በተለያዩ ክለቦችና በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ውስጥ በመሳተፍ ነገሮችን የማስተናገድ፣ ሰዎችን የማሳመንና ችግሮችን የመፍታት ብቃታችሁን የምታሳድጉበት ትልቁ ሜዳ ግቢ ነው። "Soft Skills" የሚባሉት እነዚህ ክህሎቶች ከቴክኒካዊ እውቀቱ ባልተናነሰ ለስኬታችሁ ወሳኝ ናቸው።
3. ራስን የማግኘት ጉዞ (Self-Discovery) 🔍
ከቤተሰብ ርቃችሁ በራሳችሁ መቆም ስትጀምሩ "እኔ ማን ነኝ? ምንስ ማድረግ እችላለሁ?" የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ትገደዳላችሁ። አዳዲስ ተሰጥኦዎችን የምታገኙበት፣ የዲጂታል እውቀታችሁን የምታሰፉበትና ጠንካራ ስብዕና የምትገነቡበት ወርቃማ ጊዜ አሁን ነው።
4. የፈጠራና የቴክኖሎጂ ዓለም 💻
ባላችሁበት ግቢ ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ክለቦች፣ የፈጠራ ማዕከላትና ውድድሮች (ለምሳሌ የE-sports ውድድሮች) የንድፈ-ሀሳብ እውቀታችሁን ወደ ተግባር የምትቀይሩባቸው ናቸው። አለም በቴክኖሎጂ በምትመራበት በዚህ ዘመን፣ ከክፍል ትምህርት ጎን ለጎን አዳዲስ ነገሮችን ከመሞከር ወደኋላ አትበሉ።
5. የማይረሱ ትዝታዎችና የህይወት ልምዶች ✨
ካምፓስ የደስታ፣ የፈተና፣ የጥናትና የጓደኝነት ድብልቅ ነው። በእያንዳንዱ ውድቀት ውስጥ ትዕግስትን፣ በእያንዳንዱ ስኬት ውስጥ ደግሞ ትጋትን ትማራላችሁ። እነዚህ የዛሬ ፈተናዎች ነገ በኩራት የምታወሯቸው ምርጥ ትዝታዎቻችሁ ይሆናሉ።
መልዕክታችን፡
"ዲግሪውን ይዛችሁ ብቻ ሳይሆን፣ እውቀቱን፣ ክህሎቱንና ሰብዕናውን ጨምራችሁ ውጡ!"
መልካም የትምህርትና የለውጥ ዘመን ይሁንላችሁ!
የተማሪዎች ህብረት ጽ\ቤት

👍19❤5😁4👏2😭2🔥1🤝1
የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ከባህር ዳር
ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ጽሕፈት ቤት
ባህር ዳር (መጋቢት 2018) —
በመጀመሪያ፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ጽሕፈት ቤት ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው በሙሉ እንኳን ለታላቁ የምረቃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ልባዊ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። ዛሬ የምታከብሩት ድል የዓመታት የልፋታችሁና የጥንካሬያችሁ ውጤት በመሆኑ ኩራታችን ላቅ ያለ ነው።
ይህ የምረቃ መርሃ-ግብር ከመደበኛው የትምህርት ስኬት ባለፈ፣ የተማሪዎች ህብረት አመራሮች በአካዳሚክ ዘርፍም ጭምር ያላቸውን ቁርጠኝነትና ብቃት በተግባር ያስመሰከሩበት ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ውሏል።
በዚህ በዓል ላይ የተገኙት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት አማረ ደጉ፣ በምረቃው ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡት አራት የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ያላቸውን ኩራት ገልጸዋል።
እነዚህ ተወካዮች፦
1️⃣አንተነህ ኑርልኝ
2️⃣ስለአባት ፈንታ
3️⃣ታምራት ታደለ
4️⃣ጥጋቡ ጫኔ
የተጣለባቸውን ከፍተኛ የተማሪዎች አገልግሎት ሃላፊነት እየተወጡ፣ በተመሳሳይ ሰዓት በትምህርታቸው እጅግ ከፍተኛ ውጤትና ማዕረግ (Great Distinction) ማስመዝገባቸውን ፕሬዝዳንቱ በደስታ ተናግረዋል።
"ዛሬ የተመረቁት የህብረታችን ተወካዮች፣ የተማሪዎች ህብረት በአገልግሎት ብቻ ሳይሆን በአካዳሚክ ደረጃም ቢሆን የተሻለና አርአያነት ያለው ስራ እንደሚሰራ ህያው ምስክሮች ናቸው፤" ሲሉ ፕሬዝዳንት አማረ ደጉ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ እነዚህ ወጣቶች "አመራርነት በትምህርት ላይ ጫና ይፈጥራል" የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት በመስበር ለሌሎች ተማሪዎች ትልቅ ተምሳሌት መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም፣ የተማሪዎች ህብረቱ ይህንን ድርብ ድል በማክበር ለተመራቂዎቹና ለቤተሰቦቻቸው መልካም ምኞቱን የገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም ህብረቱ በአካዳሚክና በአገልግሎት ዘርፍ ያለውን ጠንካራ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
ዘጋቢ፦ ቃለአብ ሰሙንጉስ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ

❤7👍1🔥1🏆1