Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ
2.56K subscribers
1.01K photos
10 videos
76 files
314 links
ማንኛውንም የትምህርት ነክ ጉዳዮችን በውክልና እናስጨርሳለን።
👉 ቴምፖራሪ ዲግሪ
👉ኦረጅናል ዲግሪ
👉ኦፊሻል ማስላክ
👉ኦተንቲኬሽን
👉Medium of instruction አና ሌሎችንም ጉዳዮችን ባሉበት ሆነው ማስፈፀም ይችላሉ።
👇 ቅርንጫፎቻችን
1. ባህር ዳር
2.ጎንደር
3.ደብረ ታቦር
4.ደብረ ማርቆስ
5.አዲስ አበባ

ለበለጠ መረጃ👉905906455/924682247 ይደውሉ።
Download Telegram

🔴The first phase of the WiSE-BiT program has been successfully completed and this is the company visit session in the Askuala Link.

💥💥💥💥💥💥💥💥💥

🔴የWiSE-BiT የኮምፒውቲንግ ተማሪዎች ፕሮግራም የመጀመሪያ ምዕራፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ይህም የአስኳላ ሊንክ (Askuala Link) የድርጅት ጉብኝት ሂደት ነው።

1
📢 የመረብ ኳስ (Volleyball) አፍቃሪዎች በሙሉ!

​በግቢያችን በቅርቡ የሚጀመረውን አጓጊ የቮሊቦል ውድድር በጋራ ለማሳካት የእናንተን እገዛ እንፈልጋለን!

ውድድሩ በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ በአዘጋጅ ኮሚቴነት ተሳታፊ በመሆን የድርሻችሁን ለመወጣት የምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

​የምዝገባ ዝርዝር፦
​ቦታ፦ የተማሪዎች ህብረት ቢሮ ቁጥር 03 (በአካል በመገኘት)

​የምዝገባ ማብቂያ ቀን፦ እስከ አርብ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም

​የስፖርት ቤተሰብ በመሆን አሻራችሁን ለማሳረፍ ይህ መልካም አጋጣሚ ነው፤ ቀድማችሁ በመመዝገብ ዝግጅቱን አብረን እናድምቅ!

​የተማሪዎች ህብረት ስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍ
1
Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ
📢 የመረብ ኳስ (Volleyball) አፍቃሪዎች በሙሉ! ​በግቢያችን በቅርቡ የሚጀመረውን አጓጊ የቮሊቦል ውድድር በጋራ ለማሳካት የእናንተን እገዛ እንፈልጋለን! ውድድሩ በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ በአዘጋጅ ኮሚቴነት ተሳታፊ በመሆን የድርሻችሁን ለመወጣት የምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ​የምዝገባ ዝርዝር፦ ​ቦታ፦ የተማሪዎች ህብረት ቢሮ ቁጥር 03 (በአካል በመገኘት) ​የምዝገባ…
📢 Attention All Volleyball Enthusiasts!

​We are excited to announce that a Volleyball Tournament is coming soon to our campus! To make this event a huge success, we are looking for passionate and committed students to join the Organizing Committee.

​If you have a love for the game and want to contribute to our campus sports culture, come and register to be part of the team.

Registration Details:
Venue: Students' Union Office, Room 03 (In person)

Deadline: Until Friday, March 20, 2026 (11/07/2018 E.C.)

​Don't miss this chance to lead and be part of an amazing sporting event!

Students' Union - Sports & Entertainment Executive
1
🌟 የችሎታ ማሳያ መድረክ፦ የBiT የኪነ-ጥበብ ምሽት (Talent & Open Mic Night) 🌟

​በውስጥህ የታፈነ ጥበብ አለ? በግጥም፣ በሙዚቃ ወይስ በኮሜዲ ሰዎችን የማስደሰት ልዩ ችሎታ አለህ? እንግዲያውስ መድረኩ ያንተ ነው!

​የተማሪዎች ህብረት የስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍ ለግቢው ማህበረሰብ ድንቅ የጥበብ ምሽት ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ ይገኛል። ችሎታችሁን ለጓደኞቻችሁ እና ለታዳሚው ለማሳየት የምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ የጥበብ ቤተሰብ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።
​የተሳታፊዎች ዘርፍ፦

🎤 ግጥም (የራስዎ ድርሰት ወይም ተወዳጅ ስራዎች)
🎸 ሙዚቃ (ድምጽ፣ መሳሪያ ወይም ባንድ)

😂 ኮሜዲ/በቀልድ (Stand-up comedy)

🎭 ማንኛውም ሌላ ልዩ ተሰጥኦ

​እንዴት መሳተፍ ይቻላል?

ችሎታችሁን ለማስገምገም እና ለመመዝገብ በአካል የተማሪዎች ህብረት ቢሮ በመገኘት ይመዝገቡ።

📍 ቦታ፦ የተማሪዎች ህብረት ቢሮ ቁጥር 03

📅 የምዝገባ ጊዜ፦ በስራ ሰዓት

​የBiT መድረክ ያንተን ድምጽ እና ጥበብ ይጠብቃል! መጥተህ ተሳተፍ፣ አብረን እንዝናና!

​የተማሪዎች ህብረት ስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍ
1
Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ
🌟 የችሎታ ማሳያ መድረክ፦ የBiT የኪነ-ጥበብ ምሽት (Talent & Open Mic Night) 🌟 ​በውስጥህ የታፈነ ጥበብ አለ? በግጥም፣ በሙዚቃ ወይስ በኮሜዲ ሰዎችን የማስደሰት ልዩ ችሎታ አለህ? እንግዲያውስ መድረኩ ያንተ ነው! ​የተማሪዎች ህብረት የስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍ ለግቢው ማህበረሰብ ድንቅ የጥበብ ምሽት ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ ይገኛል። ችሎታችሁን ለጓደኞቻችሁ እና ለታዳሚው ለማሳየት…
🌟 BiT’s Got Talent: Open Mic & Talent Night! 🌟

​Do you have a voice that needs to be heard? A poem that needs to be shared? Or a joke that can light up the entire campus? The stage is calling YOUR name!

​The Students’ Union Sports & Entertainment Executive is thrilled to announce an upcoming Talent Night and Open Mic session. We are creating a platform for the BiT community to witness the incredible artistic depth of our students.
​We are looking for:
🎤 Poetry & Spoken Word: Share your verses and stories.
🎸 Music & Vocals: Solo singers, instrumentalists, or acoustic bands.
😂 Stand-up Comedy: Bring your best punchlines and humor.
🎭 Diverse Talents: Magic, beatboxing, or any unique performance!
​How to Participate:
​We want to see what you've got! To ensure a high-quality show for the campus, we are holding talent screenings for all interested performers.
📍 Venue: Students’ Union Office, Room 03
🕒 Registration: Visit us in person during office hours to register and showcase a snippet of your talent.

Don’t just watch the stars—be one! Come show the BiT community what you are made of.

Students’ Union - Sports & Entertainment Executive
🎮 BiT E-Sports Championship: የቨርቹዋል ሜዳው ጀግና ማን ነው?

🎮
​የእግር ኳስ ፍቅር በሜዳ ላይ ብቻ አያበቃም! የተማሪዎች ህብረት የስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍ ከተለመደው የስፖርት ውድድር ለየት ባለ መልኩ ታላቅ የቪዲዮ ጌም (Video Game) ውድድር አዘጋጅቶላችኋል።

​በ FIFA እና PES (eFootball) ችሎታዬ ወደር የለውም የምትሉ የጌሚንግ አፍቃሪዎች በሙሉ፣ ብቃታችሁን የምታሳዩበትና የBiT የኢ-ስፖርት ሻምፒዮን የምትሆኑበት መድረክ ተዘጋጅቷል።

የውድድሩ ዘርፎች፦
FIFA 2024/25
PES / eFootball

እንዴት መሳተፍ ይቻላል?
ለመመዝገብ እና ስለ ውድድሩ ህጎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በአካል ቢሮ ድረስ ብቅ ይበሉ።
📍 ቦታ፦ የተማሪዎች ህብረት ቢሮ ቁጥር 03
📅 የምዝገባ ማብቂያ፦እሁድ 13/07/2018

የቁጥጥር (Controller) ንጉስ ማን እንደሆነ የምናይበት ጊዜው አሁን ነው!


🎮 BiT E-Sports Championship: Who is the King of the Virtual Pitch? 🎮

​The beautiful game isn't just played on the field anymore! The Students’ Union Sports & Entertainment Sector is bringing you the ultimate Video Game Tournament.

​Calling all gamers, tacticians, and controller wizards! It’s time to take your skills from the dorm room to the big stage. Come and compete to be the first-ever BiT E-Sports Champion.

Tournament Categories:
FIFA 24/25
PES / eFootball

How to Join:

Ready to prove you’re the best? Register now and get the full tournament rules.

📍 Venue: Students’ Union Office, Room 03 (In person)

📅 Registration Deadline: 13/07/2018

Grab your controller. Claim your glory. May the best gamer win!

Students’ Union - Sports & Entertainment Sector
🔥61
🌟 የክህሎት ልውውጥ (Skill Share) ዘመቻ፦ እውቀትዎን ለሌሎች ያጋሩ! 🌟

​"ያወቁትን ማሳወቅ፣ የያዙትን ማካፈል ፍጹም በጎነት ነው!"

​የተማሪዎች ህብረት የበጎ አድራጎት ዘርፍ በግቢያችን ውስጥ አዲስ እና ድንቅ የሆነ የክህሎት ልውውጥ መድረክ ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ ይገኛል። ይህ መርሃ-ግብር ተማሪዎች ያላቸውን ልዩ ተሰጥኦ እና እውቀት ለጓደኞቻቸው በነጻ የሚያካፍሉበት ልዩ አጋጣሚ ነው።

​እርስዎስ ምን ማስተማር ይችላሉ?

💻 የኮምፒውተር ጥገና እና የሶፍትዌር አጠቃቀም

🎨 ስዕል፣ ዲዛይን ወይም የፈጠራ ስራዎች

🗣️ የቋንቋ ክህሎት (እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ ወዘተ...)

🛠️ ሌሎች ማንኛቸውም ጠቃሚ የቴክኒክ ወይም የሙያ ክህሎቶች

​ለምን ይሳተፋሉ?

​እውቀትዎን በማጋራት ሌሎችን ለመርዳትና በጎነትን ለማስፋፋት።

​የማስተማር እና የመግባባት ክህሎትዎን ለማሳደግ።

​ከህብረቱ የሚሰጠውን የእውቅና ሰርተፍኬት ለማግኘት።

​እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ያላችሁን ክህሎት ለሌሎች ለማጋራት ፍላጎቱ ያላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦
📍 ቦታ፦ የተማሪዎች ህብረት ቢሮ ቁጥር 03

ስልክ 0964570244

📅 ጊዜ፦ በስራ ሰዓት

​አሻራዎን ያሳርፉ፤ እውቀትዎን ያጋሩ!


🌟 Skill Share Campaign: Share Your Talent, Empower Your Peers! 🌟

​"Knowledge increases by sharing, not by saving."
​The Students’ Union Charity Sector is launching an exciting Skill Share Campaign at BiT! We are looking for talented students who are willing to volunteer their time to teach their fellow students valuable skills.

​What skills are we looking for?

💻 Computer Maintenance & Software Skills

🎨 Arts, Sketching, & Graphic Design

🗣️ Language Proficiency (English, French, Arabic, etc.)

🛠️ Any other technical or creative expertise!

​Why Join?

​To experience the joy of giving and support your community.

​To improve your leadership and communication skills.

​To receive a Certificate of Appreciation from the Students’ Union.

​How to Sign Up:

If you are passionate about sharing what you know, come and register at:

📍 Venue: Students’ Union Office, Room 03

📅 Time: During office hours
​Be a mentor. Be a volunteer. Make a difference!
6
Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ
https://forms.gle/Ysutq7waoCB8JePg8
🔔 ነገ ይጀምራል፡ የጤናዎ ባለቤት ይሁኑ! 🔔
የBiT የምግብ ቤቶችና የላውንጆች የጽዳት ደረጃ ምዘና (Hygiene Rating)
የተማሪዎች ህብረት የጤና ዘርፍ የተማሪዎቻችንን ጤና ለመጠበቅ እና የምግብ አገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ አዲስ አሰራር ይዞላችሁ ቀርቧል። ከነገ ጀምሮ በየምግብ ቤቱ በሚለጠፉት QR Codes አማካኝነት ድምጽዎን መስጠት ይችላሉ!

ለምን መሳተፍ አለብዎት?
🧼 ለጽዳት፦ የሚመገቡበት ቦታ ንጽህናው የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ።

🍲 ለጥራት፦ የሚቀርብልዎ ምግብ ጥራትና ጣዕም እንዲሻሻል ለማድረግ።

👮 ለተጠያቂነት፦ ደካማ አገልግሎት የሚሰጡ ካፌዎች እንዲታረሙ ለማድረግ።

🏆 ለእውቅና፦ በንጽህናቸው አርአያ የሆኑ ካፌዎችን ለማበረታታት።

እንዴት ነጥብ ይሰጣሉ? (ቀላል 3 እርምጃዎች)
📲 በየካፌውና ላውንጁ የተለጠፈውን QR Code በስልክዎ ስካን ያድርጉ።

⭐️ ለጽዳት፣ ለምግብ ጥራትና ለአቅራቢዎች ስነ-ምግባር ከ 1 እስከ 5 ኮከብ ይስጡ።

Submit የሚለውን በመጫን ድምጽዎን ያሳውቁ።

ምን ታሳቢ ይደረጋል?
📍 የአካባቢ እና የጠረጴዛዎች ንጽህና

🍽 የሳህን፣ የማንኪያ እና የብርጭቆዎች ጽዳት

🥼 የአቅራቢዎች አለባበስ (ጋውን እና የፀጉር መሸፈኛ)

🤝 የአቀባበል እና የንግግር ስነ-ምግባር

"የእርስዎ አንድ ሬቲንግ (Rating) ለጤናማ ግቢ መሰረት ነው!"

የተማሪዎች ህብረት - የጤና ዘርፍ
9
Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ
🔔 ነገ ይጀምራል፡ የጤናዎ ባለቤት ይሁኑ! 🔔 የBiT የምግብ ቤቶችና የላውንጆች የጽዳት ደረጃ ምዘና (Hygiene Rating) የተማሪዎች ህብረት የጤና ዘርፍ የተማሪዎቻችንን ጤና ለመጠበቅ እና የምግብ አገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ አዲስ አሰራር ይዞላችሁ ቀርቧል። ከነገ ጀምሮ በየምግብ ቤቱ በሚለጠፉት QR Codes አማካኝነት ድምጽዎን መስጠት ይችላሉ! ለምን መሳተፍ አለብዎት? 🧼 ለጽዳት፦ የሚመገቡበት…
🔔 STARTS TOMORROW: TAKE CHARGE OF YOUR HEALTH! 🔔
BiT Cafeteria & Lounge Hygiene Rating System
The Students’ Union Health Sector is launching a brand-new initiative to ensure your safety and upgrade the quality of food services on campus. Starting tomorrow, your feedback will directly determine the ranking of every cafe and lounge at BiT!

Why Should You Participate?
🧼 For Cleanliness: To ensure your dining environment is spotless and sanitary.

🍲 For Quality: To push for better food taste, freshness, and standards.

👮 For Accountability: To hold poorly managed cafes responsible for their services.

🏆 For Excellence: To reward and encourage cafes that maintain high standards.

How to Rate? (3 Simple Steps)
📲 SCAN: Use your phone to scan the QR Code posted at the entrance or on the tables of any cafe/lounge.

⭐️ RATE: Give your stars (1 to 5) for environment, food hygiene, and staff conduct.

SUBMIT: Click submit to make your voice heard in seconds!

What Are You Rating?
📍 Cleanliness: Tables, floors, and general dining area hygiene.

🍽 Sanitation: How clean the plates, spoons, and glasses are.

🥼 Staff Standards: Use of aprons, hairnets, and overall grooming.

🤝 Professionalism: The courtesy and behavior of the service providers.

"Your Rating is your power. Use it for a healthier BiT!"

Students’ Union — Health Executive
1
Invitation for Socialization Workshop
.....................................
ATI in partinership with Bahir Dar University prepare half day workshop on AgriLearn Digital Learning Platform Socialization Workshop, To socialize and promote AgriLearn Digital Learning Platform in Amhara region and strengthen integration of the platform in the implementation of ADEY and other ATI initiatives, thereby expanding digital learning access in the region.
5
📢 ለሁሉም የBiT ተማሪዎች ፓርላማ አባላት በሙሉ

ሁሉም የBit የተማሪዎች ፓርላማ አባላት ቅዳሜ ከምሽቱ 2:00 ሰዐት ስብሰባ ስለሚኖር የተማሪዎችህብረት ቢሮ እንድትገኙ እናሳስባለን ።

📅 ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
📍 ቦታ: ቢሮ ጥቁር 04

ሁሉም አባላት በሰዓቱ እንዲገኙ እና በንቃት እንዲሳተፉ እንጠይቃለን።

እናመሰግናለን።
📢 Announcement to All BiT Students’ Parliament Members
All BiT Students’ Parliament members are hereby informed that a meeting will be held on Saturday at 2:00 PM (night). You are kindly requested to attend at the Students’ Union Office.
📅 Date: Saturday
Time: 2:00 PM (Night)
📍 Venue: Office Block 04
All members are expected to be present on time and participate actively.
1
🎭 ከአንጋፋው አርቲስት ጌትነት እንየው ጋር፦

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የአገራችንን የጥበብ ባለውለታ አንጋፋው አርቲስት ጌትነት እንየውን በመጋበዝ ልዩ ምሁራዊ መድረክ አዘጋጅቶላችኋል።

በኢትዮጵያ የቴአትር እና የሥነ-ጽሑፍ ጉዞ ላይ ትኩረቱን የሚያደርገው ይህ መድረክ፣ ለጥበብ አፍቃሪያንና ለዘርፉ ተማሪዎች የማይታለፍ አጋጣሚ ነው።

🗓 ቀን፦ መጋቢት 09/2018 ዓ.ም
🕒 ሰዓት፦ ከሰዓት በኋላ 8:00 (2:00 PM)
📍 ቦታ፦ ፔዳ ካምፓስ፣ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኦዲቶሪየም አዳራሽ

ተጋባዦች፦
የዩኒቨርሲቲው ፋኩልቲ ተማሪዎችና መምህራን
የጥበብ ባለሙያዎች
ማንኛውም የሥነ-ጽሑፍና የቴአትር አፍቃሪ ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ኑ፣ ስለ ጥበብ እንወያይ!
የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍና ቴአትር ታሪክ ካለፉበት አንደበት እንስማ።

#BahirDarUniversity #BDU #GetnetEnyew #EthiopianLiterature #EthiopianTheatre #ArtAndCulture #ባህርዳርዩኒቨርሲቲ #ጌትነትእንየው
1
The Bahir Dar Institute of Technology-Bahir Dar University's Business Incubation and Techno-Entrepreneurship Center (BiT-BDU-BiTec), in partnership with the Entrepreneurship Development Institute (EDI), is pleased to announce an upcoming Entrepreneurship Training Workshop.
This six-day intensive program is designed for individuals who aspire to enhance their entrepreneurial skills. Participants who are selected and successfully complete the training will have the opportunity to advance to the Training of Trainers (TOT) program.
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdalbQFGY4u0Q-vO_3QWSWRIqhEpMdOJCn-JS2ogQfc_sugGQ/viewform?usp=publish-editor
1
ማስታወቂያ
                                                                                                                            
ቀን: 09/07/2018 ዓ.ም

ከ ተማሪዎች ኅብረት የጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ

ጉዳዩ፦ "የጽዱ ዶርም" ፕሮጀክት መጀመርን ማሳወቅ

የተማሪዎች ኅብረት የጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ የተማሪዎችን የመኖርያ አካባቢ ምቹና ጤናማ ለማድረግ ታልሞ በተቀረጸው "የጽዱ ዶርም" ፕሮጀክት ከነገ ጀምሮ በይፋ ስራ ይጀምራል። በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች የሚከተሉትን ነጥቦች አውቃችሁ ተግባራዊ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡-

የጽዳት ግዴታ እያንዳንዱ ተማሪ የሚኖርበትን የመኝታ ክፍል (Dormitory) በየቀኑ የማጽዳትና የመንከባከብ ኃላፊነት አለበት።

የክትትል ስራ የኅብረቱ የጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ ከዩኒቨርሲቲው የሚመለከታቸው አመራሮች ጋር በመሆን በየዕለቱ ድንገተኛና መደበኛ የክትትል ስራዎችን ያከናውናል።

አስተዳደራዊ እርምጃ፦ በተደረገው የክትትል ስራ ወቅት የዶርሙን ጽዳት ባልጠበቀና ቸልተኛ ሆኖ በሚገኝ ተማሪ ላይ የዩኒቨርሲቲውን መመሪያ ተከትሎ አስፈላጊው የዲሲፕሊንና የአስተዳደር እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

👉 ጤናማና ጸዳ ያለ ግቢ ለመፍጠር ለምናደርገው ጥረት የተማሪዎች ትብብር ወሳኝ ነው።

"ንጹህ አካባቢ ለተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት !"

የተማሪዎች ኅብረት የጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ


                ANNOUNCEMENT
           
                    Date: March18, 2026

From: Students' Union General Service Affairs

Subject: Announcing the launch of the "Clean Dorm" Project

The Students' Union General Service Affairs, in its commitment to ensuring a healthy and conducive living environment, is officially launching the "Clean Dorm" project starting tomorrow. Therefore, all students are strictly required to adhere to the following directives:

Sanitation Duty: Every student is responsible for maintaining the cleanliness and hygiene of their assigned dormitory room daily.

Daily Inspection: The General Service Affairs, in collaboration with the concerned University management bodies, will conduct daily inspections to ensure standards are met.

Administrative Measures: Any student found neglecting the cleanliness of their dormitory or failing to comply with the project standards will face necessary disciplinary and administrative actions as per the University’s legislation.

👉 Your cooperation is vital in building a clean and vibrant campus community.

"A Clean Environment for a Better Academic Journey !"

Students' Union General Service Affairs
15😁12👍2
📢 ለሁሉም የBiT ተማሪዎች ፓርላማ አባላት በሙሉ

ሁሉም የBit የተማሪዎች ፓርላማ አባላት ቅዳሜ ከምሽቱ 2:00 ሰዐት ስብሰባ ስለሚኖር የተማሪዎችህብረት ቢሮ እንድትገኙ እናሳስባለን ።

📅 ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
📍 ቦታ: ቢሮ ጥቁር 04

ሁሉም አባላት በሰዓቱ እንዲገኙ እና በንቃት እንዲሳተፉ እንጠይቃለን።

እናመሰግናለን።
3
📢 Announcement to All BiT Students’ Parliament Members
All BiT Students’ Parliament members are hereby informed that a meeting will be held on Saturday at 2:00 PM (night). You are kindly requested to attend at the Students’ Union Office.
📅 Date: Saturday
Time: 2:00 PM (Night)
📍 Venue: Office Block 04
All members are expected to be present on time and participate actively.
ድል ለደጋፊው... ተስፋ ለወገኑ!"

​በሜዳው ላይ የአርሰናል እና ሲቲ ፍልሚያ... በክበባችን ደግሞ የፍቅር እና የመረዳዳት ምሽት!
የአንድ ጨዋታ ክፍያ ለብዙዎች ተስፋ ይሆናል።

​እሁድ ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ በ DSTV እንገናኝ። የሚከፍሉት እያንዳንዱ ሳንቲም ለርዳታ አገልግሎት ይውላል።

ይምጡ፣ ይደሰቱ፣ ይርዱ!
11👍1