Sunset Hiking
3.57K subscribers
248 photos
4 videos
2 files
46 links
🌄 Sunset Hiking Ethiopia
Feeling burned out from city life?
We organize safe, guided sunset hikes to help you reset, breathe, and reconnect with nature and people.
🥾 Weekly hikes
🌅 Stunning sunset views
📍 Addis & nearby destinations
👉 Upcoming hikes here
Download Telegram
Channel created
°°° Hiking ወደ ድንባሮ °°°

ቦታ፡- ደብረሲና ድንባሮ(144 ኪ.ሜ)
ቀን፡- ታህሳስ/5/2012(እሑድ)

* እሑድ ታህሳስ እምስት ከመዲናችን ከአዲስ አበባ ተነስተን 140 ኪ.ሜ በመኪና ከተጓዝን በኋላ ከ4-10 ኪ.ሜ በእግር ጉዞ፣ ድንባሮ(የሚሊኒክ መስኮት)፡፡

* በአቀማመጥ 9°45'00.7"N 39°38'47.7"E የሆነው ይህ ቦታ በተራሮች የተከበበ እንዲሁም የተለያዩ ምንጮች የፈለቁበት ሲሆን እጅግ ውብ ተፈጥሮና ለአይን ማራኪ የሆነ ቦታ ነው፡፡

"ጥቅል ፓኬጅ"

★ ደርሶ መልስ የትራንስፖርት አገልግሎት ጨምሮ።
★ ስናክ
★ የታሸገ ውኃ
★ አምስት ፕሮፌሽናል ፎቶ የሚያነሱ ፎቶ ግራፈሮች
★ የምሳ ግብዣ ከአዝናኝ ጫዎታዎች ጋር


♦ የጉዞ ወጪ፡- 300 ብር
♦ የመነሻ ቦታ፡- ፒያሳ(ጣይቱ ሆቴል)

@sunsethiking
@sunsethiking
የሚኒሊክ መስኮት
ይህ ቦታ ከደ/ብርሃን ከተማ ወደ ሰሜን አቅጣጫ በሚወስደው የአስፖልት መንገድ 40 ኪ.ሜትር ያክል እነደተጓዙ አንዲት ጥድና ጅብ ዋሻ የሚባሉ አካባቢዎች እንደደረሱ ወደ ቀኝ በመታጠፍ ወደ ከፍታ ተራራ በመውጣት የሚያገኙት ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ይህንን ቦታ “የምኒልክ መስኮት” አንዴም “ገማሳ ገደል” በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህ ቦታ በጣም ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከአመት አመት ልምላሜ የማያጣውና በአረንጓዴ ሸማ እንደተሸፈነ ጌጥ ተፈጥሮ ውበት ያለበሰችው አስደናቂ ሥፍራ ነው፡፡
ከተፈጥሮአዊ ውበቱ ጋር ተዳምሮ በአካባቢው ያለው እንደ ጭስ ጧት ከማታ የሚግተለተለው ጉምና ነፋሻማ አየር ሁልጊዜ የማይሰለችና አስደሣች ስፍራ ያደገርዋል፡፡ በዚህ ስፍራ ነው እንግዲህ ሆን ተብሎ የታቀደና በተዋጣለት መሀንዲስ ተከርክመው የተሰሩ የሚመስሉት ግራና ቀኝ እንደምስል ቀጥ ብለው የሚገኙትን ተራሮች ከነ ግርማ ሞገሣቸው የሚያገኙት፡፡ በዚህ ቀዳዳ ወደ ምስራቅ ቁልቁል አሻግረው ሲመለከቱ ያላሰቡትንና ያልጠበቁትን ክስተት ይመለከታሉ፡፡ የይፋት ቆላማ መንደሮች፣ ኢትዮጵያን ለሁለት ከፍሎ የሚያልፈው ትልቁ ስምጥ ሸለቆ ፣ የአፋር ክልል በርሃማ ቦታዎችና የአዋሽ ወንዝ በሰልፍ ተኝተው በአግራሞት ለመመልከት ያስችልዎታል፡፡ ይህ የሚሆነው ታዲያ ከገደሉ በር እንደ እጣን ጭስ እየተጥመለመለ የሚወጣው ነጭ ጉም እና የአካባቢውን ቀዝቃዛ አየር እየሳቡ ነው ፡፡
አፄ ምኒልክ በንግስና ዘመናቸው ወደ አያታቸው ንጉስ ሣህለ ስላሴ የትውልድ ቦታ ወደ ሆነችው ሰላድንጋይ ከተማ ለተለያዩ ጉዳዩች ሲሄዱና ሲመለሱ በዚህ ስፍራ በመገኘት ትልቁ የስምጥ ሸለቆ የሚያልፍባቸውን አካባቢዎችና የአዋሽን ወንዝ በተመለከቱ ጊዜ እጅግ ከመደነቃቸው የተነሣ በተደጋጋሚ በቦታው እየተገኙ ይመለከቱ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ የአካባቢው ነዋሪዎችም የዚህን ስፍራ መጠሪያ ስም የምኒልክ መስኮት የሚል ስያሜ ሰጥተውት እስከ አሁን ድረስ በዚሁ ስያሜ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ሥፍራው የወፍ ዋሻን ደን ከፊል ገጽታ ከስሩ የያዘ ሁልጊዜ ለምለም የማይለየው በመሆኑ በርካታ ዝንጀሮዎች፣ ሺኮኮዎችና ገደሉን እንደመጠለያ አድርገው የሚኖሩ በርካታ የአእዋፍ ዝርያዎች የሚገኙበት መሆኑ ደግሞ የቱሪስት መስህብነቱን ይበልጥ ማራኪና አስደናቂ ያደርገዋል፡፡
Please join our telegram group:- @sunsethike
የእግር ጉዞ(Hiking) ማለት በተፈጥሮአዊ አካባቢዎች ፣ ብዙውን ጊዜ በተራራማ ወይም በሌላ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ውስጥ መጓዝን የሚያመለክት ከቤት ውጭ ያለ እንቅስቃሴ ነው።

የእግር ጉዞ(Hiking) የእግር ጉዞ ብቻ ሳይሆን በብስክሌት መጓዝ፣ ሸርታቴ(መንሸራተት)፣ በፓራሹቶች መብረርንም የሚያካትት ነው፡፡

የእግር ጉዞ(Hiking) ጥቅሞች ምንድ ናቸው?
በተለያዩ ጥናቶች ለማረጋገጥ እንደተቻለው የእግር ጉዞ(Hiking) አካላዊ ጤንነት፣ ለአእምሮ ጤንነት እንዲሁም ማህበራዊ ሕይወታችን ትልቅ ጥቅም ይሰጣል፡፡

አካላዊ ጤንነት
1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከፍ ያደርገዋል
የእግር ጉዞ ብቻ በሰዓት 440 እስከ 550 ካሎሪ ሊቃጠል ይችላል፡፡ በአማካኝ 75 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሰው ለ 3 ሰዓታት የእግር ገዞ ቢያደርግ 1200 ካሎሪ ሊያጥል ይችላል፡፡
2. የደም ግፊትን ያሻሽላል ፣ የልብ ድካም አደጋን ይቀንሳል፡፡
3. የስኳር በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ይረዳል
4. መገጣጠሚያዎችን ያረጋጋል እንዲሁም ሚዛንን ያሻሽላል
5. የመተንፈሻ አካልን ያሻሽላል
6. የጀርባ ህመም ያስታግሳል

ለአእምሮ ጤንነት
1. የፈጠራ ችሎታን ይጨምራል
2. የእግር ጉዞ ደስተኞች እንድንሆን ያደርገናል
3. የእግር ጉዞ ማድረግ አዕምሮን ነጻ ያደርጋል እንዲሁም ጭንቀትን ይቀንሳል
4. ከተፈጥሮ ጋር መግባባት(ግንኙነትን) ይፈጥራል
5. የበለጠ ለጋስ ያደርገናል

ማኅበራዊ
1. አዳዲስ ጓደኞችን ለምፍራት ይረዳል
2. የህብረትን ስሜት ይፈጥራል
3. ከሰው ጋር ለመነጋር ግዜ ይገኛል
4. በጊዜው ከሰው ለምኖር እንማራለን፡፡
Captured by Architect, Photographer and Art Director #Argene markos in 2007
@dinbaro
👉 ቦሌ፣ 22፣ ስታዲዮም አከባቢ ላላቹ 0927983591

👉 ሜክሲኮ፣ ፒያሳና አዲሱ ገበያ አከባቢ ላላቹ 0901927999

👉 ጀሞ፣ ቤቴል፣ መገናኛና ጋርመንት አከባቢ ላላቹ 0921484549

👉 ፈረንሳይ፣ ጉራራና ቤላ አከባቢ ላላቹ 0919296071

👉 የካአባዶ፣ ጉርድሾላና ሰሚት አከባቢ ላላቹ +251910554965

👉 4ኪሎ፣ 6ኪሎና ካሳንቺስ አከባቢ ላላቹ 0919266760

ደውላቹ ማግኘት ትችላላቹ

እንዲሁም 5ኪሎ ከቤሄራዊ ሙዚየም ፊትለፊት #ተስፋ ቡና ቲኬቱ ይገኛል

@sunsethiking
@sunsethiking
join our group @sunsethike
Sunset Photographers
በፋና ቲቪ ወደ ምንሄድበት የሚሊኒክ መስኮት የቀረበ ዘጋቢ ፊልም https://www.youtube.com/watch?v=Kq7cg3viu04
Hello beautiful sunset hikers, we are glad to tell you that, we've #finished our dinbaro spots. This happened because of our wonderful and perfect group participants, without you it was difficult to imagine the whole. For those of you that we didn't get tickets we're really sorry, we packed only small spot. I hope we hike together the upcoming next journey.


Look deep into nature and you will understand everything better. "AE"

@sunsethiking
@sunsethiking
የጉዞው እለት ምን ላድርግ?

❗️❗️ተጓዞች ምን ያድርጉ❗️❗️

1. ቲኬቱ እንዳይለያቹ
2. ነገ ታህሳስ 5 ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 1 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል እንገናኝ( 1 ሰዓት መኪናው ከጣይቱ ሆቴል ይነሳል)
3.የምንጓዝበት ቦታ በጣም ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ ቅዝቃዜን ያማከለ ልብስ ይልበሱ።
4. ቀላልና ጠንካራ የጉዞ ጫማዎች ይልበሱ።
5. ኮፍያ ወይም ቆብ (ግድ አይደለም)
6. የእጅ ጓንት (ግድ አይደለም)
7. ሚፈልግ ሰው የራሱን ምግብ ማምጣት ይችላል

❗️ጥቅሎች❗️

1. የትራንስፖርት አገልግሎት
2. ስናክ
3. ውኃ
4. ፎቶ ግራፍ
5. የምሳ ግብዣ
6. ጉዞውን መምራት እና ማስተባበር
7. የተጓዡን ደኅንነት መከታተል
8. በእለቱ የሚኖሩ አዝናኝ ጨዋታዎችን ማዘጋጀት

@sunsethiking
@sunsethike
As written by our beloved brother @Sa_mee
#Sunset hiking is proudly brought to you by SOCHI Pvt. Ltd. Co
Portuguese bridge hike
Venue: Tayitu Hotel
Meet time: 12:00 LT
Date: Sunday, Jan/5/2020
Fee: 300 birr
"Package"
~ Transportation.
~ Snack
~ Canned water
~ photography
~ including Lunch
We'll be selling tickets starting from tomorrow morning 8 AM.
We will not accept Order that comes before 8 AM.