አቡ ሩሐማ - Abu Ruhama
971 subscribers
784 photos
137 videos
22 files
911 links
➧«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»፡፡ (ማኢዳ፥3)
Download Telegram
የንባብ ግብዣ
በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኀጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል። ስለ ምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም እንዲሁ ይሰድቡናልና፥አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና። (ሮሜ 3፥7-8❩
ለአስተዋዮች ብቻ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
▣ ባሏ የሞተባት ሴት ደረጃ በክርስትና ▣
      •════•════•
⓵. ልጄ ሆይ፥ስለ ምን ጋለሞታ ሴት ትወዳ፟ለህ የሌላዪቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ።
❨መጽሐፈምሳሌ 5፡20❩
⓶. ጋለሞታ ሴት የጠለቀች ዐዘቅት ናትና፥ሌላዪቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናትና።
እንደ ሌባ ታደባለች ወስላታዎችንም በሰው ልጆች መካከል ታበዛለች። (መጽሐፈ ምሳሌ 23፥27-28)
⓷. ‹‹ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤
በክርስቶስ ላይ ተነስተው ሊቀማጠሉና ሊያገቡ ይወዳልሉና።›› ❨1ኛ ጢሞቲዎስ 5፥11❩
⓸. ‹‹ለአምላክ የተቀደሰ ነው ጋለሞታን ሴት ወይንም
የረከሰችውን አያግባ ወይንም ከባልዋ የተፋታችውን አያግባ።›› ❨ዘሌዋውያን 21፥7❩
⓹. "ስለተሳልኸው ስእለት ሁሉ የጋለሞታዪቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደእግዚአብሔር ቤት አታቅርብ ሁለቱም በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።" ❨ዘዳግም 23፥18❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"መጠጥ እር. ኩስ ነው ማለት ሃጢአት ነው።"
ይሄው ቄስ ሌላ ቪዲዮ ላይ "ወይን ቅዱስ ነው" ይላል።
.
"ይነሳል ቅዱሱ
ከጠርሙሱ" የሚለው ዘመቻ ውሃ በላው ማለት ነው።
ጠርሙሱ የያዘው መጠጥ ቅዱስ ነው ማለት አይደል? መቼም
"ይነሳል ቅዱሱ
ከቅዱሱ" አይባል ነገር።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
👍1
ድሃ እና ሃብታም
~
በመፅሀፍ ቅዱስ ከአስካሪ መጠጥ አንፃር ለድሀዎች ያለው ህግ ለሃብታሞች ካለው የተለየ ነው።
1- ለድሃዎች፦
(ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፤ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድሕነቱንም ይርሳ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ፡፡) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፡6)
2- ለሃብታምስ?
(ለነገሥታትና ለሀብታምና ለመሳፍንትም፦ አስካሪ መጠጥ በፍፁም አይገባም፥ ልሙኤል ሆይ፥ ነገሥታት የወይን ጠጅ_ይጠጡ_ዘንድ_አይገባም።) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፥4)

ለምን? ለድሃው የተፈቀደው ድህነቱን እንዲረሳ ነው። ሃብታሙ ከዚህ ችግር ነፃ ነው።

በመጽሀፉ መሰረት መስከር እንጂ መጠጣት አልተከለከለም። እሺ መጠጣት ከተፈቀደ መጠኑ ምን ያህል ነው? አንዳንዶች እንደሚሉት መለኪያ አይደለም። ይልቁንም ጉዳዩ ለጠጪው የተተወ ይመስላል። እስከሚረካ ድረስ።
(ወዳጄ ሆይ ጠጪ እስክትረኪ ድረስ ጠጪ፡፡) (መኀልዬ መኀልዬ ዘሰለሞን 5፡1)

ግራ የሚገባው መጽሀፉ ነብያት ሰክረው ወንጀል ፈፀሙ ሲል ነው። ለምሳሌ፦

* የፈጣሪ ነቢይ ኖህ ሰክሮ ራቁቱን ሆነ። (ዘፍጥረት 9:20-21)
* በአስካሪ የወይን ጠጅ ስካር ምክንያት ውዱ የእግዚአብሄር ነቢይ ሎጥ ከወለዳቸው ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ሰክሮ ልጆቹ ከአባታቸው ከነቢዩ ሎጥ ዲቃ .ላ ጸነሱ። (ዘፍጥረት 19፡30-36)
* አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ። አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው። (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 13፥28)

እንደ ኢስላም አስተምህሮት ግን ነብያት ከእንዲህ ዓይነት ሃጢአት ፍፁም እና የተጠበቁ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
🔖ሀላችሁም እረኞች ናችሁ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿كُلُّكُمْ رَاعٍ، وَكُلُّكُمْ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ،﴾

“ሁላችሁም እረኞች (ጠባቂዎች) ናችሁ በምትጠብቁት ነገር ደግሞ ትጠይቃላችሁ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5200

https://t.me/ASselefiyehcom7777/4127
🔘 የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች ️🔘
      ▣  ክፍል 8
ወይን ጠጅ መጠጣት የተፈቀደ ወይስ ክልክል?
        📌 የተፈቀደ
️❶እግዚአብሔር፡ሥራኽን፡ተቀብሎታልና፥ኺድ፤እንጀራኽን፡በደስታ፡ብላ፥የወይን፡ጠጅኽንም፡በተድላ፡
ጠጣ። ❨📓መጽሐፈ መክብብ:9:7❩

❷የእኽልም፡ቍርባን፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፡የኾነ፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡
ዱቄት፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡ለእሳት፡ቍርባን፡ይኹን፤የመጠጡም፡ቍርባን፡የወይን፡
ጠጅ፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡ይኹን።  ❨📓ዘሌዋውያን 23፥13❩

  በሌላ ቦታ ደግሞ
  📌 የተከለከለ
❶ የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጣት፡ኀያላን፡የሚያሰክረውንም፡ለማደባለቅ፡ጨካኞች፡ለኾኑ፤
...ወዮላቸው! (📙️ትንቢተ ኢሳያስ:5:22-23)

❷ የወይን፡ጠጅ፡ከሚጠጡ፡ጋራ፡አትቀመጥ፡ለሥጋም፡ከሚሣሡ፡ጋራ። ❨📗መጽሐፈ ምሳሌ 23፥20❩

❸ ሥጋን፡አለመብላት፡ወይንንም፡አለመጠጣት፡ወንድምኽም፡የሚሰናከልበትን፡አለማድረግ፡መልካም፡ነው። (📘ሮሜ 14፥21)
️..........
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2
Forwarded from የመዳን መንገድ (ኢብኑ-ያሲር ሸሪዓዊ የውይይት መድረክ Chanel📚📚)
መፅፍ ቅዱስ ኢትዮጵያዊያን ግደሉ እደሚል ያውቁ ኑሮዋል

ጥያቄ ለክሪስቲያን ወገኖች

“እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።”
— ሶፎንያስ 2፥12

ጥያቄያችን አምላክ ገድሎናል ወይስ ገና ሊያስገድለን ነው መልስ እንሻለን

?
ሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ ነኝ

ጆይን በሉ⤵️⤵️
t.me/Alfurqan12b
t.me/Alfurqan12b
👍2
ይድረስ ለክርስቲያን ሴት ሰባኪያን
➣ ሴት፡በነገር፡ዅሉ፡እየተገዛች፡በዝግታ፡ትማር፤
ሴት፡ግን፡በዝግታ፡ትኑር፡እንጂ፡ልታስተምር፡ወይም፡በወንድ፡ላይ፡ልትሠለጥን፡አልፈቅድም።
አዳም፡ቀድሞ፡ተፈጥሯልና፥በዃላም፡ሔዋን፡ተፈጠረች። የተታለለም፡አዳም፡አይደለም፥ሴቲቱ፡ግን፡ተታላ፟፡በመተላለፍ፡ወደቀች። (1ኛ ጢሞቲዎስ፡2፥11-14)
ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና። ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።
(1ኛ ቆሮንቶስ 14:34-35)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
ዋቄፈና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አላህ መለኮት ነው፤ “መለኮት” ማለት ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ ማለት ነው፤ እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢና ሕያው መለኮት ነው፤ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እኛ ሙስሊም አላህ ስናመልከው እርሱን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ውስጥ እና በእርሱ ነቢይ ሐዲስ ውስጥ በተቀመጠልን መስፈርት ብቻ ነው። ይህንን ካወቅን ስለ ዋቄፈና ደግሞ በግርድፉና በሌጣው እንይ።

“ዋቄፈና” የሚለው ቃል “ዋቃ” ማለትም “አምላክ” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን የእምነቱ ስም ነው፤ ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፤ “ኢሬቻ” ማለት “ምስጋና” ወይም “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለትም “ቤተ-አምልኮ” ውስጥ በጭፈራዎቹና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው፤ ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው። ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፤ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው፤ “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል። “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፤ ይህ በዓል በአመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ-ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል። እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ-ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፤ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእስልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም፥ ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፤ እነርሱም ባወጡት ሰው ሰራሽ አምልኮ ያመልኩታል፤ ይህ ደግሞ ቢድዓ ነው፤ እዚህ አምልኮ ውስጥ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሃይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ሺርክ ነው፤ በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፤ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ነው? እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፤ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ከእነዚህ ሁለት በዓል ውጪ ሌሎች በዓላት ተቀባይነት የላቸውም፤ ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም”* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
*ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል*። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። *ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩምና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሃ ወደ አላህ ተመለሱ። አላህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ስለ ዋቄፈና ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Mulugeta Jaleta Gobenooromo; Indiginious Religion: Anthroplogical Understanding of Waaqeffanna-Nature Link, With Highlight on Livelihood in Guji Zone, Adola Redde and Girja Districts, A thesis submitted to the department of Social Anthropology, College of Social Science Addis Ababa University, June 2017,
2. Census (PDF), Ethiopia, 2007,
3. Workinesh Kelbessa, Traditional Oromo Attitudes towards the Environment, Social Science Research Report Series.

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Forwarded from የመዳን መንገድ (ኢብኑ-ያሲር ሸሪዓዊ የውይይት መድረክ Chanel📚📚)
መጠጥ መጠጣት ከጤና አንፃርና እስልምና ክርስትና በመጠጥ ጉዳይ ምን ይላሉ?

ከጤና አንፃር


1) ልብ:- የአልኮል መጠጥ ማዘውተር የልብ ጡንቻዎችን በማዳከም የደም ፍሰት መዛባትን ያሰከትላል፡፡ በአልኮል መጠጥ ብዛት የሚከሰት የልብ ሕመም የትንፋሽ ማጠር፤ የተዛባ የልብ ምት፤ ድካም፤ የማያቋርጥ ሳልን ያስከትላል በተጨማሪም ለደም ግፊት እና ለድንገተኛ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ይዳርጋል፡፡

2) አንጎል:- የአልኮል መጠጥ በአንጎል ላይ መልዕክት መተላለፍን ያዘገያል፡፡ አልኮል መጠጥን ማዘውተር የተለያዩ የአንጎል ክፍሎችን ስለሚጎዳ የባሕርይ ለውጦችን እንደ መደበት፤ ጭንቀት እና የመርሳት ችግር የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

3) ጉበት:- የምግብ መፈጨት፣ ንጥረ ነገሮችን ማከማቸት፣ ኢንፌክሽን የመቆጣጠር እና መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት የማስወገድ ተግባርን የሚያከናውን የሰውንት ክፍል ነው፡፡ ታድያ አልኮልን የምናዘወትር ከሆነ በጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እናደርሳለን፡፡

4) ኩላሊት:- የአልኮል መጠጥ በብዛት መውሰድ በኩላሊት የሥራ ሂደት ላይ መዛባትን ስለሚፈጥር በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች መመጣጠንን በመረበሽ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ለከፍተኛ የደም ግፊት መጠን መጨመር ይዳርጋል፡፡ ኩላሊትንም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ይዳርጋል፡፡

5) ቆሽት:- ልክ እንደ አንጎል ሁሉ ከፍተኛ አልኮልን መውሰድ የቆሽትን ሥራ ያዛባል፡፡ ቆሽት የሚያመነጫቸው ኤንዛየምዎች(Enzymes) በውስጡ እንዲጠራቀም በማድረግ ቆሽት እንዲቆጣ ያደርጋል፡፡ ይህም የሆድ ሕመምን፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ የልብምት መጨመር ተቅማጥና ትኩሳት ያስከትላል፡፡ የቆሽት መቆጣት በሚቆይ ጊዜ የቆሽትን ሥራ ስለሚያስተጓጉል ለስኳር ሕመም አልፎም ለሞት ይዳርጋል፡፡

የአልኮል መጠጥ መጠጣት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችም ጉዳቶችን ስለሚያስከትል ለጤንንትዎ ሲሉ እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡ [ምንጭ ከዶክተሮች ፔጅ]

መጠጥ በክርስትና

" ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፤ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።" (1ኛ ጢሞቴዎስ 5:23)
" ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድሕነቱንም ይርሳ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ፡፡" (መጽሐፈ ምሳሌ 31፡6)

መጠጥ በእስልምና

«አዕምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሀል ከሁለቱም ውስጥ ታላቅ ሀጢአትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው። ግን ሐጢዐታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው፤ ….» (አል በቀራህ 219)

አቡደርዳዕ(ረ.ዐ ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- "ወይን አትጠጡ ለሁሉም የሸይጧን ቁልፍ ነውና" (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

አነስ ቢን ማሊክ(ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል:- ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከወይን ጋር ግንኙነት ያላቸውን አስር ሰዎችን ረገሙ፡- ወይንን የጠመቀን፣ ያሸገን(የሞላ)፣ የጠጣን፣ ያቀበለን፣
የተቀበለን፣ ያቀረበን፣ የሸጠን፣ ከክፍያው የተጠቀመን፣ የገዛንና ያመረተን ሰው ረግመዋል» (ቲርሚዚና 2776 ኢብን ማጃህ ዘግበውታል)

አላህ እንዲህ ይላል «ሸይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፣
አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው። ታዲያ እናንተ(ከነዚህ) ተከልካዮች ናችሁን (ተከልከሉ)» (አል ማኢዳህ 91)

እንግዲ ልብ ይበሉ የኢስላም አስተምህሮ(ትእዛዛት) ለመጪው አለም ጥቅም ብቻ ሳይሆን ላለንበት የዱንያ ህይወትም ጭምር የሚስማማ ያለው ድንቅ እምነት ነው።
✍️ሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ ነኝ

ጆይን በሉ⤵️⤵️
t.me/Alfurqan12b
t.me/Alfurqan12b
ወሰላሙ አለይኩም
1
حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏

ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል። (ሡነን ኢብኑ ማጃህ : 210)
ምን አገናኛቸው?
• ════•════•
▣ ከንፈር መንከስና ክፋት መፈፀም ምን አገናኛቸው?

➢ ዐይኑን የሚዘጋ ጠማማ ዐሳብን ያስባል ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል። (መጽሐፈ ምሳሌ16፥30)
●*●*●*●*●*️●*️●

▣ ዘይትን መውደድና ባለፀጋ አለመሆን ምን አገናኛቸው?
➾ ተድላን የሚወድ፟ ድሃ ይሆናል፥የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድ፟ ባለጠጋ አይሆንም።
(ምሳሌ 21፥17❩

●*●*●*●*●*️●*️●
▣ የተጠላች ሴት ባል ማግኘትና የምድር መናወጥ ምን አገናኛቸው?

➳ በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥አራተኛውንም ትሸከም ዘንድ አይቻላትም። ባሪያ በነገሠ ጊዜ ሰነፍም እንጀራ በጠገበ ጊዜ፥ የተጠላች ሴት ባል ባገኘች ጊዜ፥ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ። ❨ተግሳጽ 6፥21-23❩

۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
ኑ ከነብዩ ﷺ ማእድ ተቋደሱ!
~
ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የሆኑ ሰዎች፡ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በቂያማ ቀን ጌታችንን እናየዋለን?” በማለት ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ጥያቄ አቀረቡ። የአላህ መልእክተኛም ﷺ፡ “ጨረቃ ሙሉ በሚሆንበት በወሩ 14ኛው ቀን ላይ ጨረቃን ከማየት ትቸገራላችሁን?” ብለው ጠየቁ። “በጭራሽ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሉ። ፀሐይንስ ከስሯ ዳመና ሳይኖር (ለማየት) ትቸገራላችሁን?” ሲሏቸው “በጭራሽ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሉ። በዚህ ጊዜ (ነብዩ ﷺ) እንዲህ አሉ፡-
“እንግዲያው በርግጥም ልክ እንደዚሁ አላህንም ታዩታላችሁ! የቂያማህ ቀን አላህ ሰዎችን ይሰበስብና ‘የሆነን ነገር ሲያመልክ የነበረ እሱኑ ይከተል’ ይላል። ከዚያም ፀሀይን ሲያመልክ የነበረ ፀሀይን ይከተላል። ጨረቃን ሲያመልክ የነበረ ጨረቃን ይከተላል። ጣኦታትን ሲያመልክ የነበረ ጣኦታትን ይከተላል። ይህቺ ህዝብ ግን ከነ ሙና .ፊቋ ትቀራለች። ቀድመው ያውቁት በነበረው ሳይሆን በሌላ ቅርፅ (ሱራ) የላቀው አላህ ይመጣቸውና ‘እኔ ጌታችሁ ነኝ’ ይላቸዋል። እነሱም ‘ኧረ ካንተ በአላህ እንጠበቃለን! እኛ ጌታችን እስከሚመጣን ድረስ ይሄው ነው ቦታችን። ሲመጣን ደግሞ እናውቀዋለን’ ይላሉ። ይህኔ የላቀው አላህ ቀድመው በሚያውቁት ቅርፁ ይመጣቸውና፡ ‘እኔ ጌታችሁ ነኝ’ ይላል። እነሱም ‘አንተ ጌታችን ነህ’ ይላሉ። ከዚያም ይከተሉታል።

በጀሀነም ጀርባዎች ላይ ድልድይ (ሲራጥ) ይዘረጋል። እኔና ህዝቦቼ መጀመሪያ የሚያቋርጡት እንሆናለን። በዚያን ቀን መልእክተኞች እንጂ ማንም ሌላ አይናገርም። የመልእክተኞችም ንግግር ያኔ፡ ‘ጌታዬ ሆይ ሰላም አርገው! ሰላም አርገው!’ የሚል ነው። ጀሀነም ላይ ልክ እንደ ቀንጠልፋ እሾህ ያሉ መንጠቆዎች አሉ። ቀንጠልፋ አይታችኋል?’
‘አዎ’ አሉ።
ከዚያም እንዲህ አሉ፡- ‘እነሱ ልክ እንደ ቀንጠፋ እሾህ ናቸው። ባይሆን የግዝፈት መጠናቸው ምን እንደሚያክል አላህ እንጂ ማንም አያውቅም። ሰዎችን በስራዎቻቸው ይጠልፋሉ። ከነሱ በስራው የሚተርፍ አማኝ አለ። ከነሱ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ የስራውን የሚያገኝ አለ።
ከዚያም በባሪያዎቹ መካከል ያለውን ፍርድ ሲጨርስ ከእሳት ጓዶችም በእዝነቱ ሊያወጣ የፈለገውን በፈለገ ጊዜ፣ ‘ላኢላሀ ኢለላህ’ ከሚሉት በአላህ ምንም ያላጋራውን፣ የላቀው አላህ ሊያዝንለት የፈለገውን እንዲያወጡ መላእክትን ያዛል። በእሳት ውስጥም ያውቋቸዋል። የሚያውቋቸው በሱጁድ ምልክቶቻቸው ነው። የኣደምን ልጅ የሱጁድ ቦታዎቹ ሲቀር እሳቷ ትበላዋለች። የሱጁድ ቦታን እንዳትበላ በጀሀነም እሳት ላይ ክልክል አድርጎባታል። ሰዎቹ በርግጥም ተቃጥለዋል። የህይወት ውሃ በላያቸው ላይ ይፈሰስባቸዋል። ከሱም ቦይ ተሸክሞት የመጣው ደለል ጋር እንደምትበቅል ቡቃያ ይበቅላሉ።

ከዚያም የላቀው አላህ በባሪያዎቹ መካከል ያለውን ፍርዱን ሲጨርስ ፊቱ ወደ እሳት የዞረ ሰው ይቀራል። ሰውየው መጨረሻ ጀነት የሚገባው የጀነት ሰው ነው። እናም፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ፊቴን ከእሳቷ አዙርልኝ? ሽታዋ አሰቃየኝ! ወላፈኗም አቃጠለኝ!’ እያለ አላህ የፈቀደውን ያክል አላህን ይለምናል። ከዚያም የላቀውና ከፍ ያለው አላህ፡ ‘ይህን ካደረግኩልህ ሌላ ላትጠይቅ ቃል ትገባለህ?’ ይለዋል። ‘ከዚህ ውጭ አልጠይቅም’ ይላል። አላህ የፈለገውን ያክል (ሌላ ላይጠይቅ) ለጌታው ቃል ይገባል። ማጠናከሪያም ያስቀምጣል። ከዚያም አላህ ፊቱን ከእሳቷ ያዞርለታል።
ከዚያም ወደ ጀነት ሲዞርና ሲመለከታት ጊዜ አላህ የፈቀደውን ያክል ዝም ይላል። ከዚያ ግን፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ወደ ጀነት በር አቅርበኝ?’ ይላል። አላህም፡ ‘ከሰጠሁህ ውጭ ላትጠይቅ ቃልኪዳንና ማጠናከሪያዎችን አልሰጠህም ነበር? ወዮልክ የኣደም ልጅ! ምንኛ ቃል አፍራሽ ነህ?!’ ይለዋል። ሰውየውም፡ ‘ጌታዬ ሆይ!’ እያለ አላህን ይለምናል። ከዚያም ‘ይህን ካደረግኩልህ ሌላ ላትጠይቅ ቃል ትገባለህ?’ ይለዋል አላህ። ‘በክብርህ ይሁንብኝ! ሌላ አልጠይቅም’ ይላል። አላህ የፈለገውን ያክል ለጌታው ቃል ይገባል። ማጠናከሪያም ያስቀምጣል። ወደ ጀነት በርም ያቀርበዋል። ጀነት በር ላይ ሲቆም ጊዜ ጀነት ትከፈትለታለች! በውስጧ ያሉትን መልካም ነገሮችንና ደስታዎችን ያያል። አላህ የፈቀደውን ያክልም ዝም ይላል። ከዚያም፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ጀነት አስገባኝ?’ ይላል። አላህም፡ ‘ከሰጠሁህ ውጭ ላትጠይቅ ቃልኪዳንና ማጠናከሪያዎችን አልሰጠህም ነበር? ወዮልህ የኣደም ልጅ! ምንኛ ቃል አፍራሽ ነህ?!’ ይለዋል። ሰውየውም፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ከፍጡሮችህ የመጨረሻ እድለ-ቢሱ አልሁን!’ እያለ የላቀውና ከፍ ያለው አላህ በሱ እስከሚስቅ ድረስ ይለምናል። አላህ በሱ ከሳቀ በኋላ፡ ‘ጀነትን ግባ’ ይለዋል። ከገባ በኋላ ደግሞ አላህ፡ ‘(ያሻህን) ተመኝ’ ይለዋል። ከዚያም (ምኞቱ አልቆበት) አላህ፡ ‘ይህም አለ’፣ ‘ይህም አለ’ እያለ እስከሚያስታውሰው ድረስ ጌታውን ይለምናል። ይመኛልም! ምኞቶቹ ሲያልቁበት ጊዜ አላህ፡ ‘ያን (የተመኘኸውን) እና አምሳያውን (ተሰጥቶሀል)’ ይለዋል።”

አቡ ሁረይራ ይህን ሲተርኩ አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ አብረው ነበሩ። ነገር ግን ምንም አይመልሱም ነበር። አቡ ሁረይራ አላህ ለሰውየው፡ “ያን (የተመኘኸውን) እና አምሳያውን (ተሰጥቶሀል)” እንደሚለው ሲናገሩ ግን (አቡ ሰዒድ)፡ “ ‘ከሱው ጋር #አስር አምሳያውን’ ነው የተባለው” አሉ። አቡ ሁረይራ፡ “እኔ ግን ‘ያን (የተመኘኸውን) እና አምሳያውን’ የሚለውን ብቻ ነው የያዝኩት” ሲሉ። አቡ ሰዒድ ደግሞ፡ “እኔ ግን ‘ከሱው ጋር አስር አምሳያውን’ የሚለውን ከአላህ መልእክተኛ ﷺ እንደያዝኩኝ እመሰክራለሁ” አሉ። አቡ ሁረይራ፡ “ይሄ ሰውየ ነው ከጀነት ሰዎች መጨረሻ ጀነትን የሚገባው” አሉ። [አልቡኻሪይ፡ 806] [ሙስሊም፡ 469]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች
      ክፍል 17
  .• ════•════•
  📌የበከተውን ለመጻተኛ ስጥ
➢አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥የበከተውን ሁሉ አትብላ ይበላው ዘንድ በአገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ትሰጠዋለህ፥ወይም ለእንግዳ ትሸጠዋለህ።
❨ዘዳግም 14፥21❩
      .*.*.*.*.*.*.*.
📌ለራስህ የማትወደውን ለማንም አታድርግ
➢ለራስህ የጠላኸውን ለማንም ለማን አታድርግ።
❨ጦቢት 4፥15❩

۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/sunah13
Forwarded from zakir
ጥንታዊ የሆነው የዓረብኛ ቋንቋ ሰዋሰው (ነሕው) እና  ሶርፍ እንደ ጥንቱ ዛሬም ሳይቀየር የቋንቋው አካል ሆነው ይገኛሉ።
ዛሬ ዘመናዊ አረብኛ የሚናገር ሰው በቀላሉ ከዛሬ 1400 አመታች በፊት የነበረውን ቁርአን መረዳት ይችላል። ይህ አይነቱ ልዩ ባህሪይ ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንጅ ለሌሎቹ ነቢያት የታደለ ጉዳይ አይደለም! ለዓለም መድህን የመጣው ቁርአን ጥንትም እንደነበረው ዛሬም በዛው ገፅታው ላይ ይገኛል፤ ወደፊትም በዚሁ መልክ ተጠብቆ ይቆያል።

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው። እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን።” (አል-ሂጅር 15፤9)
Forwarded from A B Y @ROSSE
የሀገራችን ክርስትያን ወገኖቻችን ሆይ:-

መስቀል መከበር እንዳለበት ለእትዮጵያውያን ክርስትያኖች ብቻ ነውንዴ የተገለጠለቸው?

ለሌሎች ሀገር ክርስትያኖች የመስቀል መከበር መች ነው የሚገለጥላቸው?

ደሞ መስቀል ለናንተ ሚናቹ ነው?

ሀይላቹህ ወይስ ጠላታቹህ?

ለምንድነው ወደ አመድነት የምትቀይሩት?
👍4
ከተወሰኑ አመታት በፊት የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጋዜጠኛዋ በአክሱም ጽዮን ስለሚገኘው "የሙሴ የቃል ኪዳኑ ታቦት" አንስታ ጠይቃቸው ነበር። ታቦቱ በአክሱም ለመገኘቱ "እንደ ፓትርያርክ እርስዎ አይተውታል ወይ?" ብላ ጠየቀቻቸው፤ እሳቸውም ሲመልሱ "አባቶቻችን አይተውታል፣ በእርግጥ እኔ እስካሁን አላየሁትም" አሉ። መስቀል በመጣ ቁጥር "መስቀሉ እስካሁን ኢትዮጵያ ነው ያለው" የሚለውን ንግግር ስሰማ የሳቸው ንግግር ትዝ ይለኛል።