አቡ ሩሐማ - Abu Ruhama
971 subscribers
784 photos
137 videos
22 files
911 links
➧«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»፡፡ (ማኢዳ፥3)
Download Telegram
ተጸጸተ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አሏህ አንድ ነገር ከመከሰቱ፣ ከመሆኑ፣ ከመደረጉ፣ ከመከናወኑ በፊት ያለውን ሩቅ ነገር እና አንድ ነገር ከተከሰተ፣ ከሆነ፣ ከተደረገ፣ ከተከናወነ በኃላ ያለውን ግልጹን ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፦
64፥18 ሩቁን ነገር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

"አማሬ ኲሉ" ማለት "ሁሉን ዐዋቂ" ማለት ነው፥ መለኮት "ሁሉን ዐዋቂ" ነው። በባይብል አንዱ አምላክ "ሁሉን ዐዋቂ" ነው፦
1 ዮሐንስ 3፥20 አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና "ሁሉንም ያውቃል"። ὅτι μείζων ἐστὶν ὁ Θεὸς τῆς καρδίας ἡμῶν καὶ γινώσκει πάντα.

ቅሉ ግን አንድ ማንነት በሠራው ሥራ ከተጸጸተ ያንን ሥራ ከመሥራቱ በፊት ስለማያውቅ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። ለምሳሌ፦ ሰው በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፦
ዘጸአት 13፥17 አምላክ፦ "ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው እና ወደ ግብፅ እንዳይመለስ" ብሎአልና። אָמַ֣ר אֱלֹהִ֗ים פֶּֽן־יִנָּחֵ֥ם הָעָ֛ם בִּרְאֹתָ֥ם מִלְחָמָ֖ה וְשָׁ֥בוּ מִצְרָֽיְמָה׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንዳይጸጽተው" ለሚለው የገባው ግሥ " ፐን ዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው። የእስራኤል ሕዝብን የፈርዖንን ሠራዊት ሰልፍ ባየ ጊዜ ከግብፅ መውጣቱ ጸጽቶት ወደ ግብፅ መመለስ ከከጀለ በመውጣቱ ይጸጸት ነበር፥ የእስራኤል ሕዝብን ሰው ስለሆነ የወደፊቱን ሰማያውቅ በሠራው ሥራ ሊጸጸት ስለሚችል ፈጣሪ እንዳይጸጸቱ መክሯቸዋል። ሰው የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስላልሆነ በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፥ የሰው ተቃራኒ አምላክ ደግሞ የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስለሆነ በሚሠራው ሥራ አይጸጸትም፦
ዘኍልቍ 23፥19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ አምላክ ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። לֹ֣א אִ֥ישׁ אֵל֙ וִֽיכַזֵּ֔ב וּבֶן־אָדָ֖ם וְיִתְנֶחָ֑ם
1 ሳሙኤል 15፥29 የእስራኤል ኃይል አይዋሽም አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና። וְגַם֙ נֵ֣צַח יִשְׂרָאֵ֔ל לֹ֥א יְשַׁקֵּ֖ר וְלֹ֣א יִנָּחֵ֑ם כִּ֣י לֹ֥א אָדָ֛ם ה֖וּא לְהִנָּחֵֽם׃

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መጸጸት" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ከዚያ በተቃራኒው ያህዌህ በሠራው ሥራ እንደተጸጸተ ባይብሉ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 6፥6 ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም እጅግ አዘነ። וַיִּנָּ֣חֶם יְהוָ֔ה כִּֽי־עָשָׂ֥ה אֶת־הָֽאָדָ֖ם בָּאָ֑רֶץ וַיִּתְעַצֵּ֖ב אֶל־לִבֹּֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጸጸተ" ለሚለው የገባው ግሥ "ይዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው፥ ያህዌህ የተጸጸተ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ነው። የሠሩትን ወንጀል ዓይቶ "ከመነሻው ሰው መፍጠር አልነበረብኝም" ብሎ በሠራው ሥራ ተጸጸተ፥ መጸጸት ለሁሉን ዐዋቂ አምላክ የተገባ ባሕርይ አይደለም።
በእርግጥ "ናኻም" נָחַם የሚለው ቃል "ተጸጸተ" ብቻ ሳይሆን "አዘነ" "ራራ" "አጽናና" "ረዳ" "ተቆጣ" የሚል ፍቺ ይኖረዋል፥ ይህንን ይዘን፦
፨"ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አዘነ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ራራ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አጽናና"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ረዳ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ተቆጣ"
ትርጉም ይሰጣልን? እራሱ በሠራው ሥራ ማዘን፣ መራራት፣ መጽናናት፣ መርዳት፣ መቆጣት ትርጉም አይሰጥም፥ ነገር ግን እራሱ በሠራው ሥራ ተጸጽቷል። ይህ የፈጣሪ ባሕርይ በፍጹም አይደለም፥ "አምላክ ይጸጸት ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም" "እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም" ከሚሉት አናቅጽ ጋር ከመጋጨት አልፎ በመላተም ይፋጫል። የሚያሳዝነው "ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ" ብሎ የሚነግረው ያህዌህ ወይም ሙሴ ሳይሆን ማንነቱ በውል የማይታወቅ ሰው ነው፥ ይህ ውሉ የማይታወቅ ሰው ንግግር ይዘን እንደ አምላክ ቃል መሞገት አግባብ አይደም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍1
በመስቀሉ ላይ ያለው እባብ ከፓጋኑ ሰይጣን ጋር ምን ያህል እንደሚመሳሰል ተመልከቱ። የኦርቶዶክስን ገድላት እና ድርሳናት ጉድ ለማየት በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/orthox
😨2
መልዕክት
• ════•════•
✺ إِن يَعْلَمِ اللَّهُ فِي قُلُوبِكُمْ خَيْرًا يُؤْتِكُمْ خَيْرًا مِّمَّا أُخِذَ مِنكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

➳ ...«አላህ በልቦቻችሁ ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከእናንተ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» (አንፋል:70)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2
ስርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 11:የአትናቲዎስ ቅዳሴ
""ሕፃንን" "ከአባቱ ወገብ" #አውጥተህ ወደ #ሴት #ማሕፀን #የምትልከው #ሆይ..."
"ሕፃንን" የሚለውን ልብ ይበሉ ሕፃን ልጅ እንደ ክርስትና እና ባይብል አስተምሮ ከአባቱ ወገብ #ወጥቶ #ወደ እናቱ ማህፀን ገብቶ ከዛ ከእናቱ ማህፀን እንደሚወጣ ያስተምራል።
ይሄ እውነት ነው?
ከመቼ ጀምሮ ነው "ሕፃን" ልጅ ከኣባት ወገብ ተነስቶ ከዛ ወደ ሴት ማህፀን ገብቶ ከሴት ማህፀን መውጣት የጀመረው??

ባይብልም በሰፊው አላብራራውም እንጂ ልጆች ከኣባት ወገብ እንደሚወጡ በዚህ መልኩ ይናገራል...
“ለጌዴዎንም ብዙ ሚስቶች ነበሩትና "ከወገቡ" "የወጡ" #ሰባ #ልጆች ነበሩት።”
— መሳፍንት 8፥30

ቁርኣን ግን በዚህ መልኩ ትክክለኛውን የፅንስ(ልጅ) አፈጣጠር ይነግረናል
49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ

"ኑጥፋህ” نُّطْفَة ማለት "የፍትወት ፈሳሽ"sexual fluid" ማለት ነው፥ ይህምም የፍትወት ፈሳሽ የወንዱ የዘር ሕዋስ"sperm cell" እና የሴቷ የእንቁላል ሕዋስ"egg cell" ነው፦
76፥2 *እኛ ሰዉን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንሆን ”ቅልቅሎች” ከሆኑ “የፍትወት ጠብታ” ፈጠርነዉ*፤ ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ። إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

ብዙ መጨመር ቢቻልም እንዳይረዝም ይኼ በቂ ነው።
✍️ሰለምቴው ወድማቹ ሙስጠፋ ነኝ
@Alfurqan12b
@Alfurqan12b     
ወሰላሙ አለይኩም
የእግዚአብሔር ባህሪያት በባይብል
• ════•════•
⓵.እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልካል
➵ስለዚህም ፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል። ❨2ኛ ተሰሎንቄ 2፥11-12❩

⓶. እግዚአብሔር ጨለማን ይልካል
ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ። ❨መዝሙር 104፥28❩

️⓷.እግዚአብሔር ሰዎች የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል፦
➵እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ የሰማይንም ጭፍራ አሳልፎ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው። ❨የሐዋርያት ሥራ 7፥42❩

⓸.እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦

➵ ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን ዛሬ ድረስ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል። ❨ሮሜ 11፥8❩
➵እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል። ❨ኢሳይያስ 29፥10❩

⓹. እግዚአብሔር ክፉን መንፈስን ይልካል

➵ የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ *ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው። ❨1ኛ ሳሙኤል 16፥14❩
➵ በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው። ❨1ኛ ሳሙኤል 18፥10)
➵ እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ። ❨መሣፍንት 9፥23❩

⓺.እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ደስ ይለዋል፦
➵እግዚአብሔርም በጎ ያደርግላችሁ ዘንድ ያበዛችሁም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ሲያፈርሳችሁም ደስ ይለዋል ትወርሷትም ዘንድ ከምትገቡባት ምድር ትነቀላላችሁ። (ዘዳግም 28፥63)
- *- * *- * -*- * -*
* ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ

۞ (አላህ) ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው፡፡ (አንዓም:100)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1👎1
ከዚህ በፊት "ከሚገርመኝ ነገራቸው ውስጥ አንዱ አስካሪውን መጠጥ "ቅዱስ ጊዮርጊስ" ብለው መሰየማቸው ነው። ሃይማኖት ያለው ሰው እንዴት ይህን ለጤናም፣ ለማህበረሰብም ጠንቅ የሆነ ቆሻሻ አተላ "ቅዱስ" ብሎ ይጠራል?!" ብዬ ፅፌ ነበር።
አሁን "ይነሳል ቅዱሱ፣ ከጠርሙሱ" የሚል ዘመቻ ሳይ ትዝ አለኝ። "መጠጡ በእምነት ክልክል ካልሆነ ምን ችግር አለው? " የሚል ጥያቄ ግን አጥጋቢ ምላሽ የሚያገኝ አይመስለኝም።
የሚገርመው ደግሞ ዘመቻቸውን በቁጭት ለማድመቅ "መሀመድ ቢራ የሚባል አለወይ?" ሲሉ ነው። ምኑን ከምኑ ነው የምታወዳድሩት? በሙሐመድ አስተምህሮ'ኮ አስካሪ መጠጥ ሐራም ነው። መጠጣት የሚያስገርፍ ወንጀል ነው። እናንተስጋ? መፅሀፉ የሚለው "ድሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ።ጕስቁልናውንም ከእንግዲህ አያስብ" ነው። (ምሳ 31፤7-8)
ለማንኛውም ለቀጣይ ዘመቻ የሚሆን ርእስ ላስታውሳችሁ። "ቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤትም" ስሙን እንዲቀይር ተንቀሳቀሱ። እንደ መፅሀፉ አስተምህሮት "ዘፋኝ መንግስተ ሰማያት አይገባም።"
ቅዱስ ዮሐንስ (St John) የሚል መጠጥም ያለ መሰለኝ። ቡናም በኢ.ኦ.ቤ.ክ "ሐራም" ነው። ለማስታወስ ያክል ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
👍3
ጥያቄያችን ለክርስቲያኖች
. * . * . * . * . * . * . * .
የሙሴ ህግ ተሽሯል ወይስ አልተሻረም?

የሙሴ ህግ ተሽሯል
⓵.ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለ ሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች። ❨ዕብራውያን 7:18❩
●*●*●*●*●*️●*️●
የሙሴ ህግ አልተሻረም
⓵.እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣኹ አይምሰላችኹ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣኹም።እውነት እላችኋለሁ፥ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢኾን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።
❨ማቴዎስ 5:17-20❩


۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👎1
የንባብ ግብዣ
በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኀጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል። ስለ ምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም እንዲሁ ይሰድቡናልና፥አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና። (ሮሜ 3፥7-8❩
ለአስተዋዮች ብቻ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
▣ ባሏ የሞተባት ሴት ደረጃ በክርስትና ▣
      •════•════•
⓵. ልጄ ሆይ፥ስለ ምን ጋለሞታ ሴት ትወዳ፟ለህ የሌላዪቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ።
❨መጽሐፈምሳሌ 5፡20❩
⓶. ጋለሞታ ሴት የጠለቀች ዐዘቅት ናትና፥ሌላዪቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናትና።
እንደ ሌባ ታደባለች ወስላታዎችንም በሰው ልጆች መካከል ታበዛለች። (መጽሐፈ ምሳሌ 23፥27-28)
⓷. ‹‹ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤
በክርስቶስ ላይ ተነስተው ሊቀማጠሉና ሊያገቡ ይወዳልሉና።›› ❨1ኛ ጢሞቲዎስ 5፥11❩
⓸. ‹‹ለአምላክ የተቀደሰ ነው ጋለሞታን ሴት ወይንም
የረከሰችውን አያግባ ወይንም ከባልዋ የተፋታችውን አያግባ።›› ❨ዘሌዋውያን 21፥7❩
⓹. "ስለተሳልኸው ስእለት ሁሉ የጋለሞታዪቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደእግዚአብሔር ቤት አታቅርብ ሁለቱም በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።" ❨ዘዳግም 23፥18❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"መጠጥ እር. ኩስ ነው ማለት ሃጢአት ነው።"
ይሄው ቄስ ሌላ ቪዲዮ ላይ "ወይን ቅዱስ ነው" ይላል።
.
"ይነሳል ቅዱሱ
ከጠርሙሱ" የሚለው ዘመቻ ውሃ በላው ማለት ነው።
ጠርሙሱ የያዘው መጠጥ ቅዱስ ነው ማለት አይደል? መቼም
"ይነሳል ቅዱሱ
ከቅዱሱ" አይባል ነገር።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
👍1
ድሃ እና ሃብታም
~
በመፅሀፍ ቅዱስ ከአስካሪ መጠጥ አንፃር ለድሀዎች ያለው ህግ ለሃብታሞች ካለው የተለየ ነው።
1- ለድሃዎች፦
(ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፤ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድሕነቱንም ይርሳ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ፡፡) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፡6)
2- ለሃብታምስ?
(ለነገሥታትና ለሀብታምና ለመሳፍንትም፦ አስካሪ መጠጥ በፍፁም አይገባም፥ ልሙኤል ሆይ፥ ነገሥታት የወይን ጠጅ_ይጠጡ_ዘንድ_አይገባም።) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፥4)

ለምን? ለድሃው የተፈቀደው ድህነቱን እንዲረሳ ነው። ሃብታሙ ከዚህ ችግር ነፃ ነው።

በመጽሀፉ መሰረት መስከር እንጂ መጠጣት አልተከለከለም። እሺ መጠጣት ከተፈቀደ መጠኑ ምን ያህል ነው? አንዳንዶች እንደሚሉት መለኪያ አይደለም። ይልቁንም ጉዳዩ ለጠጪው የተተወ ይመስላል። እስከሚረካ ድረስ።
(ወዳጄ ሆይ ጠጪ እስክትረኪ ድረስ ጠጪ፡፡) (መኀልዬ መኀልዬ ዘሰለሞን 5፡1)

ግራ የሚገባው መጽሀፉ ነብያት ሰክረው ወንጀል ፈፀሙ ሲል ነው። ለምሳሌ፦

* የፈጣሪ ነቢይ ኖህ ሰክሮ ራቁቱን ሆነ። (ዘፍጥረት 9:20-21)
* በአስካሪ የወይን ጠጅ ስካር ምክንያት ውዱ የእግዚአብሄር ነቢይ ሎጥ ከወለዳቸው ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ሰክሮ ልጆቹ ከአባታቸው ከነቢዩ ሎጥ ዲቃ .ላ ጸነሱ። (ዘፍጥረት 19፡30-36)
* አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ። አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው። (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 13፥28)

እንደ ኢስላም አስተምህሮት ግን ነብያት ከእንዲህ ዓይነት ሃጢአት ፍፁም እና የተጠበቁ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
🔖ሀላችሁም እረኞች ናችሁ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿كُلُّكُمْ رَاعٍ، وَكُلُّكُمْ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ،﴾

“ሁላችሁም እረኞች (ጠባቂዎች) ናችሁ በምትጠብቁት ነገር ደግሞ ትጠይቃላችሁ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5200

https://t.me/ASselefiyehcom7777/4127
🔘 የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች ️🔘
      ▣  ክፍል 8
ወይን ጠጅ መጠጣት የተፈቀደ ወይስ ክልክል?
        📌 የተፈቀደ
️❶እግዚአብሔር፡ሥራኽን፡ተቀብሎታልና፥ኺድ፤እንጀራኽን፡በደስታ፡ብላ፥የወይን፡ጠጅኽንም፡በተድላ፡
ጠጣ። ❨📓መጽሐፈ መክብብ:9:7❩

❷የእኽልም፡ቍርባን፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፡የኾነ፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡
ዱቄት፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡ለእሳት፡ቍርባን፡ይኹን፤የመጠጡም፡ቍርባን፡የወይን፡
ጠጅ፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡ይኹን።  ❨📓ዘሌዋውያን 23፥13❩

  በሌላ ቦታ ደግሞ
  📌 የተከለከለ
❶ የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጣት፡ኀያላን፡የሚያሰክረውንም፡ለማደባለቅ፡ጨካኞች፡ለኾኑ፤
...ወዮላቸው! (📙️ትንቢተ ኢሳያስ:5:22-23)

❷ የወይን፡ጠጅ፡ከሚጠጡ፡ጋራ፡አትቀመጥ፡ለሥጋም፡ከሚሣሡ፡ጋራ። ❨📗መጽሐፈ ምሳሌ 23፥20❩

❸ ሥጋን፡አለመብላት፡ወይንንም፡አለመጠጣት፡ወንድምኽም፡የሚሰናከልበትን፡አለማድረግ፡መልካም፡ነው። (📘ሮሜ 14፥21)
️..........
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2
Forwarded from የመዳን መንገድ (ኢብኑ-ያሲር ሸሪዓዊ የውይይት መድረክ Chanel📚📚)
መፅፍ ቅዱስ ኢትዮጵያዊያን ግደሉ እደሚል ያውቁ ኑሮዋል

ጥያቄ ለክሪስቲያን ወገኖች

“እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።”
— ሶፎንያስ 2፥12

ጥያቄያችን አምላክ ገድሎናል ወይስ ገና ሊያስገድለን ነው መልስ እንሻለን

?
ሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ ነኝ

ጆይን በሉ⤵️⤵️
t.me/Alfurqan12b
t.me/Alfurqan12b
👍2
ይድረስ ለክርስቲያን ሴት ሰባኪያን
➣ ሴት፡በነገር፡ዅሉ፡እየተገዛች፡በዝግታ፡ትማር፤
ሴት፡ግን፡በዝግታ፡ትኑር፡እንጂ፡ልታስተምር፡ወይም፡በወንድ፡ላይ፡ልትሠለጥን፡አልፈቅድም።
አዳም፡ቀድሞ፡ተፈጥሯልና፥በዃላም፡ሔዋን፡ተፈጠረች። የተታለለም፡አዳም፡አይደለም፥ሴቲቱ፡ግን፡ተታላ፟፡በመተላለፍ፡ወደቀች። (1ኛ ጢሞቲዎስ፡2፥11-14)
ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና። ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።
(1ኛ ቆሮንቶስ 14:34-35)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
ዋቄፈና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አላህ መለኮት ነው፤ “መለኮት” ማለት ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ ማለት ነው፤ እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢና ሕያው መለኮት ነው፤ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እኛ ሙስሊም አላህ ስናመልከው እርሱን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ውስጥ እና በእርሱ ነቢይ ሐዲስ ውስጥ በተቀመጠልን መስፈርት ብቻ ነው። ይህንን ካወቅን ስለ ዋቄፈና ደግሞ በግርድፉና በሌጣው እንይ።

“ዋቄፈና” የሚለው ቃል “ዋቃ” ማለትም “አምላክ” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን የእምነቱ ስም ነው፤ ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፤ “ኢሬቻ” ማለት “ምስጋና” ወይም “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለትም “ቤተ-አምልኮ” ውስጥ በጭፈራዎቹና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው፤ ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው። ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፤ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው፤ “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል። “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፤ ይህ በዓል በአመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ-ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል። እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ-ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፤ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእስልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም፥ ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፤ እነርሱም ባወጡት ሰው ሰራሽ አምልኮ ያመልኩታል፤ ይህ ደግሞ ቢድዓ ነው፤ እዚህ አምልኮ ውስጥ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሃይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ሺርክ ነው፤ በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፤ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ነው? እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፤ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ከእነዚህ ሁለት በዓል ውጪ ሌሎች በዓላት ተቀባይነት የላቸውም፤ ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም”* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
*ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል*። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። *ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩምና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሃ ወደ አላህ ተመለሱ። አላህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ስለ ዋቄፈና ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Mulugeta Jaleta Gobenooromo; Indiginious Religion: Anthroplogical Understanding of Waaqeffanna-Nature Link, With Highlight on Livelihood in Guji Zone, Adola Redde and Girja Districts, A thesis submitted to the department of Social Anthropology, College of Social Science Addis Ababa University, June 2017,
2. Census (PDF), Ethiopia, 2007,
3. Workinesh Kelbessa, Traditional Oromo Attitudes towards the Environment, Social Science Research Report Series.

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Forwarded from የመዳን መንገድ (ኢብኑ-ያሲር ሸሪዓዊ የውይይት መድረክ Chanel📚📚)
መጠጥ መጠጣት ከጤና አንፃርና እስልምና ክርስትና በመጠጥ ጉዳይ ምን ይላሉ?

ከጤና አንፃር


1) ልብ:- የአልኮል መጠጥ ማዘውተር የልብ ጡንቻዎችን በማዳከም የደም ፍሰት መዛባትን ያሰከትላል፡፡ በአልኮል መጠጥ ብዛት የሚከሰት የልብ ሕመም የትንፋሽ ማጠር፤ የተዛባ የልብ ምት፤ ድካም፤ የማያቋርጥ ሳልን ያስከትላል በተጨማሪም ለደም ግፊት እና ለድንገተኛ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ይዳርጋል፡፡

2) አንጎል:- የአልኮል መጠጥ በአንጎል ላይ መልዕክት መተላለፍን ያዘገያል፡፡ አልኮል መጠጥን ማዘውተር የተለያዩ የአንጎል ክፍሎችን ስለሚጎዳ የባሕርይ ለውጦችን እንደ መደበት፤ ጭንቀት እና የመርሳት ችግር የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

3) ጉበት:- የምግብ መፈጨት፣ ንጥረ ነገሮችን ማከማቸት፣ ኢንፌክሽን የመቆጣጠር እና መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት የማስወገድ ተግባርን የሚያከናውን የሰውንት ክፍል ነው፡፡ ታድያ አልኮልን የምናዘወትር ከሆነ በጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እናደርሳለን፡፡

4) ኩላሊት:- የአልኮል መጠጥ በብዛት መውሰድ በኩላሊት የሥራ ሂደት ላይ መዛባትን ስለሚፈጥር በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች መመጣጠንን በመረበሽ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ለከፍተኛ የደም ግፊት መጠን መጨመር ይዳርጋል፡፡ ኩላሊትንም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ይዳርጋል፡፡

5) ቆሽት:- ልክ እንደ አንጎል ሁሉ ከፍተኛ አልኮልን መውሰድ የቆሽትን ሥራ ያዛባል፡፡ ቆሽት የሚያመነጫቸው ኤንዛየምዎች(Enzymes) በውስጡ እንዲጠራቀም በማድረግ ቆሽት እንዲቆጣ ያደርጋል፡፡ ይህም የሆድ ሕመምን፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ የልብምት መጨመር ተቅማጥና ትኩሳት ያስከትላል፡፡ የቆሽት መቆጣት በሚቆይ ጊዜ የቆሽትን ሥራ ስለሚያስተጓጉል ለስኳር ሕመም አልፎም ለሞት ይዳርጋል፡፡

የአልኮል መጠጥ መጠጣት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችም ጉዳቶችን ስለሚያስከትል ለጤንንትዎ ሲሉ እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡ [ምንጭ ከዶክተሮች ፔጅ]

መጠጥ በክርስትና

" ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፤ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።" (1ኛ ጢሞቴዎስ 5:23)
" ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድሕነቱንም ይርሳ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ፡፡" (መጽሐፈ ምሳሌ 31፡6)

መጠጥ በእስልምና

«አዕምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሀል ከሁለቱም ውስጥ ታላቅ ሀጢአትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው። ግን ሐጢዐታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው፤ ….» (አል በቀራህ 219)

አቡደርዳዕ(ረ.ዐ ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- "ወይን አትጠጡ ለሁሉም የሸይጧን ቁልፍ ነውና" (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

አነስ ቢን ማሊክ(ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል:- ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከወይን ጋር ግንኙነት ያላቸውን አስር ሰዎችን ረገሙ፡- ወይንን የጠመቀን፣ ያሸገን(የሞላ)፣ የጠጣን፣ ያቀበለን፣
የተቀበለን፣ ያቀረበን፣ የሸጠን፣ ከክፍያው የተጠቀመን፣ የገዛንና ያመረተን ሰው ረግመዋል» (ቲርሚዚና 2776 ኢብን ማጃህ ዘግበውታል)

አላህ እንዲህ ይላል «ሸይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፣
አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው። ታዲያ እናንተ(ከነዚህ) ተከልካዮች ናችሁን (ተከልከሉ)» (አል ማኢዳህ 91)

እንግዲ ልብ ይበሉ የኢስላም አስተምህሮ(ትእዛዛት) ለመጪው አለም ጥቅም ብቻ ሳይሆን ላለንበት የዱንያ ህይወትም ጭምር የሚስማማ ያለው ድንቅ እምነት ነው።
✍️ሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ ነኝ

ጆይን በሉ⤵️⤵️
t.me/Alfurqan12b
t.me/Alfurqan12b
ወሰላሙ አለይኩም
1