አቡ ሩሐማ - Abu Ruhama
973 subscribers
783 photos
137 videos
22 files
910 links
➧«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»፡፡ (ማኢዳ፥3)
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከቲክቶክ መንደር የተገኘ

በራሳቸው አንደበት እንደሚመሰክሩት "ኢየሱስ ፍጡር ነው" ብሎ ያምነው የነበረው ማህበረሰብ 96% የነበረ ሲሆን "ፈጣሪ ነው" ብሎ የሚያምነው ህዝብ ደግሞ 4% ብቻ ነበር።

ዋናው ጥያቄ ይህ ሁሉ ክርስቶስን እከተላለሁ ይል የነበረ ክርስቲያን "ኢየሱስ ከአምላክ የተላከ ፍጡር እንጅ አምላክ አይደለም" ብሎ እንዲያምን ያደረገው ምንድን ነበር? የሚለው ነው።
👍3
"...አንድ ጊዜ አንድ የእምነት መምህር ሰብስቦ ሲያስተምረን “እየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው ነው” አለን፡፡ ከዚያ፤ “እየሱስ ፍጹም ሰው የሆነው ደግሞ እኛን ከአዳም የኃጢአት እዳ ሊያድነን ነው” አለን።
ልናምን ስለሄድን የኔ ተግባር ማመን ነበር የወጣትነት ቅንነት ስለነበረኝ፤ ግን አልቻልኩም፡፡

"አምላክ ሰው ከሆነ ሰውም ወደ አምላክነቱ ከተመለሰ እኛስ ከአንዱ ባሕሪ ወደ ሌላው ወይም ሁለቱንም የሰው መሆንንና አምላክ የመሆን ጸጋ አለን ወይ በአምሳሉ ስለፈጠረን?” ብዬ ጠየቅሁ፡፡ ከመምህሩ ይልቅ አብረውኝ የሚማሩት ከፋቸው። መምህሩ በትዕግሥት እንደ ሳማ በምትለበልብ ቃል፤ "አትፈላሰፍ!" አሉኝ።

"እኔ የማደርገውን እናንተም ማድረግ ትችላላችሁ ብሏልኮ በአስተምህሮቱ " ብዬ ትንሽ ለእምነት አብረውኝ ለነበሩት ስነግራቸው በአንድ ላይ አጉረመረሙብኝ። ከዚያ ወዲህ ጥያቄዎቼን በውስጤ አዳፍኜ ማዳመጥ ብቻ መረጥሁ..."

/ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ የሚሳም ተራራ፥ ገፅ 60/
👍4
የንባብ ግብዣ
•════•════•
➾ እግዚአብሔር እንደ ኀያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንአትን ያስነሣል ይጮሃል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል። ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ዝም ብዬም ታግሻለሁ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮሃለሁ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።
❨ትንቢተ ኢሳያስ 42፥13-14❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
😁2
Forwarded from እናት
አምላክን  ሁለት  ሰዎች  በደሉት
ምን አደረጉት  አትሉኝም?

አንዱ ሰውዬ (አዳም) አምላክ አትባላ ያለውን በላ
ሌላኛው ሰውዬ (የአምላክ ገዳይ) ደግሞ አምላክን ገደለው

የኔ ጥያቄ  አምላክን ይበልጥ የበደለው የትኛው ነው?🤔
2
▣ ክርስቲያኖች የዘነጉት ህግ ▣
ወንድ ልጅ ሱሪውን አሳጥሮ መልበስ
• ════•════•
⓵.‹‹ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን (የሚሸፍነውን) ሰው እጠላለሁ፥ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ፥እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።›› ❨ትንቢተ ሚልኪያስ 2፡16❩
⓶.ኢየሱስም እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ረዣዥም ልብስ ለብሰው መዞርን፥በገበያም ሰላምታን፥በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፊዎች ተጠበቁ
የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።›› ❨ማርቆስ12፡38-40❩

۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1
▣ የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርዓን አስተምህሮት ▣
• ════•════•
በክትን እስራኤላዊ ላልሆነ ወገን ወይንም ለመጻተኛ(ምፅዋት ጠያቂ) ስጡ
የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት
አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥የበከተውን ሁሉ አትብላ ይበላው ዘንድ በአገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ትሰጠዋለህ፥ወይም ለእንግዳ ትሸጠዋለህ።የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል። ❨ኦሪት ዘዳግም 14፥21❩
●*●*●*●*●*️●*️●
የቁርዓን አስተምህሮት
▣ መልካምንና ለራስህ የምትወደውን ምፅዋት ስጡ ▣
✺يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا كَسَبْتُمْ وَمِمَّا أَخْرَجْنَا لَكُم مِّنَ الْأَرْضِ ۖ وَلَا تَيَمَّمُوا الْخَبِيثَ مِنْهُ تُنفِقُونَ وَلَسْتُم بِآخِذِيهِ إِلَّا أَن تُغْمِضُوا فِيهِ ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٌ
✒️እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያም ለእናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ፡፡ መጥፎውንም (ለመስጠት) አታስቡ፡፡ በእርሱ ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እንጂ የማትወስዱት ስትኾኑ ከእርሱ (ከመጥፎው) ትሰጣላችሁን አላህም ተብቃቂ ምስጉን መኾኑን ዕወቁ፡፡ ❨በቀራ፥267❩

۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2
ውሸት ጥሩ አይደለም!

"ማተብህን በአንገትህ እሰረው" አይልም፦
ምሳሌ 6፥20-22 ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ሁልጊዜም በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።

"በአንገትህም እሰረው" የሚለው ማተብን ሳይሆን "የአባትህ ትእዛዝ እና የእናትህን ሕግ" ነው። በአንገት መታሰር እማሬአዊ ሳይሆን ፍካሬአዊ መሆኑን ለማወቅ "ሁልጊዜም በልብህ አኑረው" ይላል። ማተብ ልብ ውስጥ እንዴት ይኖራል? ማተም ይመራልን? ይጠብቃልን? ያነጋግራልን? "ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል" የሚለው የአባትህ ትእዛዝ እና የእናትህን ሕግ ነው። ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፦
ምሳሌ 6፥23 ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom
👍2
ቡሄ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

መጣና መጣና
ደጅ ልንጥና፤
መጣና ባመቱ
እንዴት ሰነበቱ፣
ክፈት በለዉ በሩን
የጌታዬን፣
ክፈት በለዉ ተነሳ
ያንን አንበሳ፣
መጣሁኝ በዝና
ተዉ ስጠኝ ምዘዝና።
እየተባለ ሆያ ሆዬ በልጅነት ያለ ዕውቀት ሙሥሊሙ ከክርስቲያኑ ጋር ተደባልቆ የክርስቲያን ሠው ሥራሽ በዓል ሲያከብር አድጓል። "ቡሄ" ማለት "ገላጣ" "የተገለጠ" ማለት ነው፥ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይህ ዕለት "ቡሄ" ተባለ። ኢየሱስ ሦስቱን ተከታዮች ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፦
ማቴዎስ 17፥1 *ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው*።

ይህ ተራራ የትኛው ተራራ እንደሆነ በባይብል አልተጠቀሰም። አንዳንድ ምሁራን አርሞንኤም ነው ይላሉ፥ የእኛዎቹ ታቦር ነው ይላሉ። "ደብር" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ተራራ" ማለት ነው፥ የደብር ብዙ ቁጥር "አድባር" ሲሆን "ተራሮች" ማለት ነው። "ደብረ-ታቦር" ማለት "የታቦር ተራራ" ማለት ነው፥ ይህ ቡሄ በዓል ደብረ-ታቦር ይባላል።
በባይብል የተራራው ስም የለም፣ ይህ እለት ነሃሴ 13 ነው የሚል የለም፣ ይህንን ቀን አክብሩ የሚል የለም፣ በዚህ ቀን ዳንኪራ ሆያ ሆዬ አድርጉ የሚል የለም። ይህ ሁሉ ሰው ሠራሽ ሕግ ነው። በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ቡሄ ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ በመስጠት እና ችቦ በማብራት በዓሉን ያከብራሉ። ይህ ሁሉ ከንቱ እዚሁ የሚቀር ምድራዊ ነገር ነው። ይህንን የክርስትና ሰው ሰራሽ በዓል ሙሥሊሙ ባለማወቅ ሲያከብረው ኖሯል። ይህ ስህተት ነው። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ቡሄ የአገር ባህል ይመስለን ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አይደለም። ይህንን በዓል መልእክተኛው ያልሰጡን ዕቡይ ተግዳሮት መሆኑን ዐውቀን መሳተፍ የለብንም። የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል፥ ይህን ለማድረግ አስረግጦ እና ረግጦ መረዳትና ማስረዳት ይጠበቅብናል። ያኔ የኢሥላም ልዕልና ለካፊሩን የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ኢንሻላህ ይሆናል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍3
የቁርዓን ትንቢት
•════•════•
▣ የፈርዖን በድን ከኤርትራ ባሕር እንደሚወጣ አስቀድሞ መነገር ▣

እንደሚታወቀው አላህ በሙሣ ዘመን ለፈርዖን እና ለቤተሰቡ
ማስጠንቀቂያ ተሰጧቸው ነበር፦
ፈርዖን እና ቤተሰቡ ከአላህ የመጣውን መልእክት ሲያስተባብሉ እና
የእስራኤልን ልጆች ሊያጠፉ ሲመጡ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ፦
➵የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና
ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው
ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት
በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ*፡፡ አምላካችን አላህ ለፈርዖን፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን
ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" አለው፦ ❨ዩኑስ፥90❩

አምላካችን አላህ "እናወጣሃለን" ብሎ በተናገረው መሠረት የፈርዖን በድን ከኤርትራ ባሕር
እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1975 ድኅረ-ልደት አውጥቶታል።
ይህን የማውጣቱ መርሐ-ግብር የፈጸሙት ዶክተር ሞሪስ ሞካየ ናቸው።

የፈርዖን በድንን ይቱብ ላይ ማየት ይቻላል፦
https://youtu.be/-dxDmbgEdcc

(ምንጭ፦ ወሒድ ዑመር የቁርዓን ትንቢት ከሚል ፅሁፍ ላይ የተመረኮዘ)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
የሐጃጆች የኢሕራም ልብሶችና ከሐጃጆች የሚጠበቁ ሕግጋቶች
• ════•════•
➢‹‹ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ
የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛው አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ
ጊዜ ከበግ ጠጉር አንዳች ነገር በለያቸው አይሁን። በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፤ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚያወዛም ነገር አይታጠቁም። ወደ ውጫኛውም አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን
ያውልቁ፤ በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውጥ ያኑሩ፤ ሕዝቡን በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላውን ልብስ ይልበሱ።›› ❨📓ትንቢተ ሕዝቅኤል 44፡17-19❩

❒ ማብራቱቱ ቃል በቃል መተርጎም ስለሚሆን
የተወሰነ ብቻ ነካ አድርጌ ልለፍ። ስለ ሐጃጆች አልባሰት ተጠቃሏል።
በውስጠኛውም አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ ከበግ ጠጉር
መጠምጠሚያ ይሁን፤ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን። ወደ
ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ እነዚህን
በሙሉ የሙስሊም ሐጃጆች አልባሳት ናቸው። እንዲሁም ከሐጃጆች የሚጠበቁ
ሥርዓቶችን ነው። አሁንም ተጨማሪ ማብራራያ አለ። ወደ ውጭኛውም
አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ።
በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑሩ፤ ሕዝቡን በልብሳቸው እንዳይቀድሱ
ሌላውን ልብስ ይልበሱ። ….ሌላ ልብስ ለብስው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ። ሐጃጆች
ሌላ ልብስ በሐጅ በውስጠኛውም አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ
ከበግ ጠጉር መጠምጠሚያ ይሁን፤ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ
ይሁን።›› የሐጃጆች ሌላ ልብስ በሐጅ ጊዜ የሚለብሱት ልብስ የኢሕራም ልብስ
በመባል ይታወቃል።
❨ምንጭ፦ከብርሃን ነፀብራቅ ብርሃንን ለሚናፍቅ ሰልማን ካሳ (ገ/እግዚአብሔር)
ገፅ 167-168❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1
ኢየሱስ ሙስሊም ነው።
إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ
(ዒሳም)
«አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» (አላቸው)፡፡ (ኣሊ-ኢምራን:51❩
4
የዒሣ ኪታብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥30 ሕፃኑም፦ አለ «እኔ የአሏህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

"ኪታብ" كِتَاب የሚለው ቃል "ከተበ" كَتَبَ ማለትም "ጻፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጽሐፍ" ማለት ነው፥ "ከተበ" كَتَبَ የሚለው የግሥ መደብ "ቃለ" قَالَ ማለትም "አለ" ወይም "ከለመ" كَلَّمَ ማለትም "ተናገረ" በሚል ይመጣል፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጦም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጻፈ" ለሚለው የገባው ቃል "ኩቲበ" كُتِبَ ሲሆን "ተነገረ" "ተባለ" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ቁርኣን ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ልብ የወረደ ቃል ነው፦
26፥194 ከአስጠንቃቂዎቹ ነቢያት ትኾን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِينَ
2፥97 እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት መጻሕፍት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ይህም ቃል ወሕይ ነው፥ ወሕይ وَحْي የሚለው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰٓ ማለትም "ገለጠ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ግልጠት "ግህደት"revelation" ማለት ነው። ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ልብ የወረደው ኪታብ ወሕይ እንጂ በወረቀት የተጻፈ ቂርጧሥ አይደለም፦
7፥2 ይህ ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ كِتَابٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ
4፥113 አሏህ በአንተ ላይ መጽሐፍን እና ጥበብን አወረደ፡፡ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ

"ቂርጧሥ" قِرْطَاس ማለት "ብራና" "ወረቀት" "ክርታስ" ማለት ሲሆን ቁርኣን በተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ላይ በወረቀት የተጻፈ መጽሐፍ ሆኖ ቢወርድ ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፦
6፥7 በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድን እና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَابًا فِي قِرْطَاسٍ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

ይህን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ ለዒሣ የሰጠው ኪታብ ኢንጂል ነው፥ ይህም ኢንጂል ወሕይ እንጂ ቂርጧስ አይደለም፦
57፥27 የመርየምን ልጅ ዒሣንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ
19፥30 ሕፃኑም፦ አለ «እኔ የአሏህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

"ቃለ" قَالَ የሚለው አላፊ ግሥ "የቁሉ" يَقُولُ በሚል መጻኢ ግሥ እንደሚመጣ ሁሉ "አታኒይ" آتَانِي የሚለው አላፊ ግሥ "ሠዩዑቲይ" سَيُؤْتِي በሚል መጻኢ ግሥ የመጣ ነው፥ ስለዚህ ለዒሣ ኪታቡል ኢንጂል በጎልማሳነት እንደተሰጠው ጉልኅ ማሳያ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "ለኢየሱስ የተሰጠው መጽሐፍ የለም" የሚሉት አንደኛ "መጽሐፍ" የሚለውን ቃል "ወረቀት" በሚል ስለሚረዱት፣ ሁለተኛ በባይብል ለኢየሱስ ተጽፎ የተሰጠው መጽሐፍ ስለሌለ እና ሦስተኛ እርሱ የጻፈው መጽሐፍ ስለሌለ ነው፥ ቅሉ ግን ባይብል "መጽሐፍ" የሚለው በብራና፣ በወረቀት፣ በክርታስ፣ በደንገል፣ በሸክላ ወይም በቁስ ላይ የሚጻፍ ነገር ብቻ ሳይሆን "ቃልን" ለማመልከትም ይመጣል፦
ሕዝቅኤል 3፥1 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ! ያገኘኸውን ብላ፤ ይህን መጽሐፍ ብላ! ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር" አለኝ።
ሕዝቅኤል 3፥2 አፌንም ከፈትሁ መጽሐፉንም አጐረሰኝ።
ሕዝቅኤል 3፥3 እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ! አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ" አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።

ሕዝቅኤል በልቶ ለእስራኤል ቤት የተናገረው መጽሐፍ ወረቀት ሳይሆን ቃል ከሆነ ለኢየሱስ አምላኩ ቃል ሰጥቶታል፦
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ "ሰጠኝ"።
ዮሐንስ 17፥8 "የሰጠኸኝን ቃል" ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት።

"የሰጠኸኝን ቃል" የሚለው ይሰመርበት! ስለዚህ በቁርኣኑ ላይ "መጽሐፍን ሰጥቶኛል" የሚለው የአሏህ ትረካ ስሙር ነው። ይህ የተሰጠው ቃል የኢየሱስ የራሱ ሳይሆን የላከው ስለሆነ ወደ አምላኩ ሲጸልይ በሁለተኛ መደብ "ቃልህ" በማለት አስረግጦ እና ረግጦ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ "ቃልህን" ሰጥቻቸዋለሁ።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ "የእኔ አይደለም"።

እንዲናገር ለኢየሱስ የተሰጠው ቃል የራሱ ሳይሆን የላከው ከሆነ በሥረ መሠረት ወንጌል ማለት ከላኪው አምላክ ለተላኪው መልእክተኛ የተሰጠ ግልጠት ነው፦
ሉቃስ 4፥17 ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና።
ማርቆስ 1፥14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የአምላክን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ። Καὶ μετὰ τὸ παραδοθῆναι τὸν Ἰωάνην ἦλθεν ὁ Ἰησοῦς εἰς τὴν Γαλιλαίαν κηρύσσων τὸ εὐαγγέλιον τοῦ Θεοῦ
ማርቆስ 1፥15 ዘመኑ ተፈጸመ የአምላክም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፡ "በወንጌልም እመኑ" አለ። καὶ λέγων ὅτι Πεπλήρωται ὁ καιρὸς καὶ ἤγγικεν ἡ βασιλεία τοῦ Θεοῦ· μετανοεῖτε καὶ πιστεύετε ἐν τῷ εὐαγγελίῳ.

ኢየሱስ የተቀባው ወንጌልን እንዲሰብ ነው፥ ይህ ወንጌል ከአምላኩ የተሰጠው የአምላክ ወንጌል ነው። "በወንጌል እመኑ" ያለውም ከአምላኩ የተሰጠውን ቃል እንጂ እከሌ እከሌን ወለደ የሚለውን የትውልድ እና የታሪክ መጽሐፍ አይደለም፥ ስለዚህ ቁርኣን ኢንጂል የሚለውን የዒሣ ኪታብ በኣራቱ የታሪክ ዘገባዎች ውስጥ በቅሪት ደረጃ ፍንጭ ይሰጠናል። ተግባባን መሰለኝ? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች
ክፍል 13
• ════•════•
13. ይጠበቅ የነበረው ኤልያስ መጥምቁ ዮሐንስ ነበረ ወይንስ አልነበረም?

📌ይጠበቅ የነበረው ኤልያስ መጥምቁ ዮሐንስ ነበረ
‌✽ እነዚያም ሲሔዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ዠመረ፥እንዲህም አለ፦ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችኹ...ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።›› (ማቴዎስ 11፡7-14)
በተመሳሳይ
‌✽ ‹‹ ደቀ፡መዛሙርቱም፦እንግዲህ፡ጻፊዎች፦ኤልያስ፡አስቀድሞ፡ሊመጣ፡ይገ፟ባ፟ዋል፡ስለ፡ምን፡
ይላሉ፧ብለው፡ጠየቁት።ኢየሱስም፡መልሶ፦ኤልያስማ፡አስቀድሞ፡ይመጣል፡ዅሉንም፡ያቀናል፤
ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥ኤልያስ፡ከዚህ፡በፊት፡መጣ፤የወደዱትንም፡ዅሉ፡አደረጉበት፡እንጂ፡አላወቁትም፤
እንዲሁም፡ደግሞ፡የሰው፡ልጅ፡ከነርሱ፡መከራ፡ይቀበል፡ዘንድ፡አለው፡አላቸው።በዚያን፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡
ስለ፡መጥምቁ፡ስለ፡ዮሐንስ፡እንደ፡ነገራቸው፡አስተዋሉ።›› ❨ማቴዎስ 17፡10-13❩
●*●*●*●*●*️●*️●
📌ይጠበቅ የነበረው ኤልያስ መጥምቁ ዮሐንስ አልነበረም
‌✽ ‹‹አይሁድም፦አንተ፡ማን፡ነኽ፧ብለው፡ይጠይቁት፡ዘንድ፡ከኢየሩሳሌም፡ካህናትንና፡ሌዋውያንን፡
በላኩበት፡ጊዜ፥የዮሐንስ፡ምስክርነት፡ይህ፡ነው። መሰከረም፡አልካደምም፤እኔ፡ክርስቶስ፡አይደለኹም፡
ብሎ፡መሰከረ።እንኪያስ፡ማን፡ነኽ፧ኤልያስ፡ነኽን፧ብለው፡ጠየቁት፦አይደለኹም፡አለ፦ነቢዩ፡ነኽን፧
አይደለኹም፡ ብሎ፡መለሰ።›› ❨ዮሐንስ ወንጌል 1፡19-21❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
ለወትሮውም በማይስማሙ ባል እና ሚስት ውስጥ ልጅ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፦ "እኛ ከምንድነው የተፈጠርነው?

አባት፦ "የፈጣሪ የእጆቹ ሥራ ነን፥ መጀመሪያ አዳምን ከአፈር አበጀው"

ልጅ እናቱ ጋር ይሄድና፦ እማ እኛ ከምንድነው የተፈጠርነው?

እናት ሆዬ፦ "እኛ የመጣነው ከዝንጀሮ ነው፥ ቀስ በቀስ በዝግመተ ለውጥ ነው"

ልጅ አባቱ ጋር ይሄድና እናቴ እኮ "ሰው የመጣው ከዝንጀሮ በዝግመተ ለውጥ ነው" አለችኝ።

አባት፦ "እርሷ የነገረችህ የእነሱን ቤተሰብ ነው"

ምንጭ ፓፕይ ዘተዋሕዶ
አርጋለችን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ናቸው፥ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ድንግል ማርያም ነሐሴ 15 ወይም 16 ቀን "ወደ ሰማይ አርጋለች" ተብሎ በካቶሊክ፣ በመለካውያን ኦርቶዶክስ እና በጽብሓውያን ኦርቶዶክስ ይታመናል፥ ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ ያሉት የቤተክርስቲያን አበው ስለ ማርያም ድንግልና፣ ንጽህና፣ ምስጋና ይናገሩ እንጂ ስለ አማሟቷ ምንም የተናገሩት ነገር የለም። ቅሉ ግን ከ 505 እስከ 571 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ኢትዮጵያዊ ያሬድ እና ከ 675 እስከ 749 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የደማስቆ ዮሐንስ ስለ ማርያም እርገት"assumption" ተናግረዋል፥ ነገር ግን ባይብል ላይ ስለ ማርያም እርገት ይቅርና ስለ አሟሟቷ ምንም ሽታው የለም። ይህ አላዋጣ ሲላቸው፦ "ቁርኣን ማርያም እና ልጇ እንዳረጉ ይናገራል" ብለው አረፉት፥ እንደ ጓያ ነቃይ የፊት ለፊቱን ብቻ በመመልከት "ይደግፈናል" ብለው የሚናገሩለት ጥቅስ ይህ ነው፦
23፥50 የመርየምን ልጅ እና እናቱንም ተአምር አደረግናቸው፥ የመደላደል እና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው፡፡ وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً وَآوَيْنَاهُمَا إِلَىٰ رَبْوَةٍ ذَاتِ قَرَارٍ وَمَعِينٍ

እዚህ አንቀጽ "አስጠጋን" ለሚለው የገባው ቃል "አወይና" آوَيْنَا ነው እንጂ "ረፈዕና" رَفَعْنَا አይደለም፥ ሲቀጥል "ረብዋህ" رَبْوَة ማለት "ከፍተኛ ስፍራ" ማለት ሲሆን ዝናብ እና ፍሬ ያለበትን የአትክልት ቦታ ያመለክታል፦
2፥265 የእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግ እና ለራሳቸው እምነትን ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች "ከፍተኛ ስፍራ" ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَآتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ከፍተኛ ስፍራ" ለሚለው የገባው ቃል "ረብዋህ" رَبْوَة መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ከፍተኛ ስፍራ በሌላ አንቀጽ "ሩቅ ስፍራ" ተብሏል፦
19፥22 ወዲያውኑም አረገዘችው፡፡ በእርሱም (በሆዷ ይዛው) ወደ "ሩቅ ስፍራ" ገለል አለች፡፡ فَحَمَلَتْهُ فَانتَبَذَتْ بِهِ مَكَانًا قَصِيًّا

እዚህ ሩቅ ስፍራ መደላደል የሆነ ፍራፍሬ እና ምንጭ የሆነ ወንዝ ያለበት ነው፦
19፥24 ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት፦ "አትዘኝ! ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል"፡፡ فَنَادَاهَا مِن تَحْتِهَا أَلَّا تَحْزَنِي قَدْ جَعَلَ رَبُّكِ تَحْتَكِ سَرِيًّا
19፥25 የዘምባባይቱንም ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዣት! በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ وَهُزِّي إِلَيْكِ بِجِذْعِ النَّخْلَةِ تُسَاقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا

ሢሠልስ ቀደምት ሠለፎች ሆኑ የእነርሱ መንሃጅ ያላቸው ሙፈሢሮች ያስቀመጡት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 23፥50
"አል አውፊ እንደተረከው ኢብኑ ዐባሥ እንዲህ አለ፦ "የመደላደል እና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው" በሚለው "ምንጭ" የተባለው "የሚንቦሎቦል ውኃ" ሲሆን ይህም ወንዝ የላቀው አሏህ፦ "ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል" በማለት ያወሳው ነው። رواه العوفي ، عن ابن عباس في قوله : ( وآويناهما إلى ربوة ذات قرار ومعين ) ، قال : المعين الماء الجاري ، وهو النهر الذي قال الله تعالى : ( قد جعل ربك تحتك سريا )

ስለዚህ "ቁርኣን ማርያም እና ልጇ እንዳረጉ ይናገራል" የሚለው ጥራዝ ነጠቅ ወሬ ያልሰከነ እና የደፈረሰ ስሑት ሙግት ነው። ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአሏህ አንቀጾች የማያምኑት ናቸው፥ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፦
16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ናቸው፥ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ትሪሙርቲ

“ትሪሙርቲ” त्रिमूर्ति በሳንስክሪት ቋንቋ “ሥላሴ” ማለት ነው፥ ከላይ ያለው የሂንዱ ሥላሴ “ብራህማ፣ ቪሽኑ እና ሲቫ” ናቸው።
1. ብራህማ ፈጣሪ አምላክ ሲሆን ሁለቱን መለኮታዊ አካላት ቪሽኑን እና ሲቫን ላኪ ነው፣
2. ቪሽኑ በየዘመናቱ ስጋ እየለበሰ የሚወለድ አቫታር ነው። እስከ ዛሬ 9 ጊዜ ተወልዷል፥ ማትስያ፣ ኩርማ፣ ቫራሃ፤ ናራሲማ፣ ቫማና፣ ፓራሹራማ፣ ራማ፣ ክሪሽና፣ ቡድሃ እና ወደፊት ይወለዳል ብለው የሚጠብቁት ካልኪ ነው፣
3. ቪሽኑ የማይታ መንፈስ ሲሆን የአማልክቱ(የመላእክት) ገዢ ነው።

በስተ-ግራ በኩል የምትመለከቱት ደግሞ የግብጽ ሥላሴ "ኦስሪስ፣ አይሲስ እና ሆረስ" ናቸው።

በስተ-ቀኝ በኩል የምትመለከቱት ደግሞ የክርስትና ሥላሴ "አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ" ናቸው።

በሂንዱ፣ በግብጽ እና በክርስትና ያሉት ሥላሴ እነዚህ ሦስት አካላት በማንነት ሦስት በምንነት አንድ ናቸው ተብሎ ይታመናል። ማን ከማን ኮረጀ? መልሱን ለኅሊና!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom
የባይብል ግጭቶች
ክፍል 14
የአብያም እናት ማናት? የማንስ ልጅ ናት?
•════•════•
A. እናቱ መዓካ ናት፣ የአቤሴሎም ልጅ ናት

★በኢየሩሳሌምም ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም መዓካ የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች።
❨1ኛ ነገሥት 15፥2❩
●*●*●*●*●*️●*️●
B. እናቱ ሚካያ ናት፣ የኡርኤል ልጅ ናት

★ ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፥ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። ❨2ኛ ዜና መዋዕል13፥2❩

ጥያቄው፦የአብያ እናት ማን ናት? መዓካ ወይስ ሚካያ? የማንስ ልጅ ናት? የአቤሴሎም ልጅ ወይስ የኡርኤል ልጅ?
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1
የዘረኝነት ደረጃ በኢስላም

✽ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏... أَنْتُمْ بَنُو آدَمَ وَآدَمُ مِنْ تُرَابٍ لَيَدَعَنَّ رِجَالٌ فَخْرَهُمْ بِأَقْوَامٍ إِنَّمَا هُمْ فَحْمٌ مِنْ فَحْمِ جَهَنَّمَ أَوْ لَيَكُونُنَّ أَهْوَنَ عَلَى اللَّهِ مِنَ الْجِعْلاَنِ الَّتِي تَدْفَعُ بِأَنْفِهَا النَّتْنَ ‏”‏

➵አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦" ...እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤ ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል።"(አቢ ዳውድ 43፥344)
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትንቢቶች
• ════•════•
ከፈተና ራስን መጠበቅ የሚቻልበት መንገድ

➵አንድ ጊዜ
እንዲህ በማለት የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቅኳቸው ፦"ይላል ሁዘይፋ 'እኛ የኖርነው በዘመነ ድንቁርና(ጃሂሊያ) ና በሰይጣናዊ ድርጊቶች ተተብትበን ነው። ከዚያም አላህ ይህንን ሃይማኖት (ኢስላምን) ለእኛ በመስጠት ፀጋውን ሞላልን። ከዚህ መልካም ነገር በኋላ ሌላ መጥፎ ነገር ይከሰታልን?' እርሳቸውም። 'አዎ' አሉ። እኔም 'ከዚያ መጥፎ ሁኔታ በኋላ ጥሩ ሁኔታ ይከሰታልን?
በማለት ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም :- አዎን ይመጣል ሆኖም ግን በጭጋግ የተሸፈነ ነው' አሉኝ። 'ይህ ጭጋግ(መጥፎ ሁኔታ) ምንድን ነው?' አልኳቸው። 'እኔ ካመጣሁት ሌላ የሆነ ነገርን በማምጣት ሕዝቦችን የሚመሩ ሰዎች ይከሰታሉ። ከእነርሱ ድርጊቶች አንዳንዶቹን ልታጸድቁላቸው ብትችሉም ሌሎቹን ግን ውድቅ ታደርጉባቸዋላችሁ።' 'ከዚያ መልካም ነገር በኋላስ ሌላ መጥፎ ሁኔታ ይፈጠራልን?' ስል ጠየቅኳቸው። 'አዎን ከጀሃነም ደጃፍ ላይ ሆነው ሰዎችን የሚጠሩ ይመጣሉ ጥሪያቸውን የተቀበለ ሁሉ ወደዚያው ውስጥ ይጣላል።' አሉኝ። 'የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለእነዚህ ሰዎች በሚገባ ይግለፁልን?' አልኳቸው 'እነርሱ ከእኛው መካከል የሆኑና የእኛኑ ቋንቋ የሚናገሩ ናቸው።' አሉ። 'እነዚህ ሁኔታዎች በእኔ የሕይወት ዘመን ካጋጠሙኝ ምን እንዳደርግ ይመክሩኛል?' አልኳቸው። የዑማውን ጀምዓ(ህብረት) ና ኢማማቸውን (መሪያቸውን) ተከተል' አሉኝ። 'ጀምዓም ሆነ ኢማም ከሌለስ?' በማለት ጠየቅኳቸው። 'እንደዚያ ከሆነ ከእነዚህ ቡድኖች ራስህን አግልል። ሌላው ቀርቶ የዛፍ ስሮችን መብላት ቢኖርብህ እንኳን እንደዚያ እያደረግክ ሞት እስኪመጣብህ ድረስ ተጠባበቅ' አሉ። ❨ቡኻሪ ዘግበውታል❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
የኢየሱስና ጳውሎስ አስተምህሮቶች ይስማማሉን?
የኢየሱስ አስተምህሮ
የሙሴ ህግ አልተሻረም
⓵.እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣኹ አይምሰላችኹ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣኹም።እውነት እላችኋለሁ፥ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢኾን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።
❨ማቴዎስ 5:17-20❩
●*●*●*●*●*️●*️●
የጳውሎስ አስተምህሮ
⓵.ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለ ሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች። ❨ዕብራውያን 7:18❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13