አቡ ሩሐማ - Abu Ruhama
971 subscribers
784 photos
137 videos
22 files
911 links
➧«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»፡፡ (ማኢዳ፥3)
Download Telegram
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
✺ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ ❨📓ኣሊ-ኢምራን፥103❩
●*●*●*●*●*️●*️●*️●
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
➢ ደግሞም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኛዎች፥በምድራችሁም ውስጥ ከወለዷቸው በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ከዘራቸው ውስጥ ባሪያዎችን ግዙ ርስትም ይሁኑላችሁ።
ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ይወርሷቸው ዘንድ ተዉአቸው ከነርሱም ባሪያዎችን ለዘለዓለም ትወስዳላችሁ ነገር ግን፥የእስራኤልን ልጆች ወንድሞቻችሁን በጽኑ እጅ አትግዟቸው።
📘ሌዋውያን 25:45-46❩
ከአቡ ሁረይራ (رضيﷲ عنه) እንደተወሳው
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿كُلُّ أُمَّتي يَدْخُلُونَ الجَنَّةَ إِلّا مَن أَبى، قالوا: يا رَسُولَ اللَّهِ، وَمَن يَأْبى؟ قالَ: مَن أَطاعَنِي دَخَلَ الجَنَّةَ، وَمَن عَصانِي فقَدْ أَبى.﴾
“ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር። ማነው ጀነት ግባ ተብሎ እምቢ ሚለው አንቱ የአላህ መልዕክተኛ? እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ። እኔን ያመፀኝ ደግሞ እሳት ገባ።”
📙️ቡኻሪ ዘግበውታል: 7280❩
የሰውን ስጋ መመገብ ይፈቀዳልን?
            መጽሐፍ ቅዱስ
              ይፈቀዳል!

➩ የወንዶችና፡የሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ሥጋ፡አበላቸዋለኹ፥ዅሉም፡ጠላቶቻቸውንና፡ነፍሳቸውን፡የሚሹት፡
በሚያስጨንቋቸው፡ጭንቀትና፡መከበብ፡የባልንጀራዎቻቸውን፡ሥጋ፡ይበላሉ። (📓ትንቢተ ኤርምያስ 19:9)
● "አበላቸዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! አስበው አምላክ የሰውን ሥጋ ለዛውም የገዛ የአብራክ ክፋይ ልጅ መብላት ከመፍቀዱ አልፎ ማስበላቱ
.*.*.*.*.*.*.*.
           አይፈቀድም
➺እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ ❨📓ሁጅራት፥12❩
●ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ክልክል ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ክልክል ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል:-
➩ ነብዩ ሙሐመድ እንዲህ ብለዋል "ﷺ"
እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። ❨📓ኢብኑ ማጃህ 6፥184❩
➺፦ ነብዩ "ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"።  (📓አቢ ዳውድ 43፥ 106)
የወሒድ ዑመር ፅሁፍ ላይ የተመረኮዘ
●*●*●*●*●*️●*️●*️●
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
💩1
ወሒድ ክርስትናን ለቆ ኢስላምን ከተቀበለበት አሳማኝ ምክንያቶች ውስጥ ለናሙና ያክል
ኢስላምን ሊዋጋ መጥቶ በቁርኣን ተማረኮ የሰለመው ወንድማችን አጠር ያለ ታሪክ
ስለ ኡስታዝ ወሒድ የማታውቁ ካላችሁ ስለራሱ በ 7 ደቂቃ ውስጥ እንዴት እንደሰለመ ገልፆበታል። አዳምጡት

የኡስታዝ አቡሃይደር ቻናል ለምትፈልጉ👇

https://t.me/abuhyder

የኡስታዝ ወሒድ ቻናል ምትፈልጉ👇

https://t.me/Wahidcom
👍4👎1
ሴቶች ባያውቁ ማንን ይጠይቁ?
•════•════•
ባሎቻቸውን ይጠይቁ
መጽሐፍ 'ቅዱስ'
➱ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ። ❨📘1ኛ ቆሮንቶስ 14፥35❩
❒ጥያቄዎች
1. ባሎቻቸውን ይጠይቁ ተብሎ ከተገደበ
ባል የጥያቄውን መልስ ባያውቅና ከባል ውጪ የሚያውቅም ቢኖርስ?
2.ባሎቻቸውን ያላገቡና ለጋብቻ ያልደረሱስ ወይም ጋለሞታዎችስ ማንን ይጠይቁ?
3. ከባል ውጪ ያለው ባዕድ ያልሆነውን የቅርብ ዘመዷ ወንድሟ፣እህቷ፣አባቷ፣እናቷ...
የመሳሰሉትን የጥያቄውን መልስ የሚያውቁት ከሆኑ ብትጠይቅስ ምን ችግር ይኖረዋል?
●●●●●️●️●️●
አዋቂዎችን ይጠይቁ
ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
➵ የማታውቁም ብትኾኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡ (📙ነህል:43)
●*●*●*●*●*️●*️●*️●
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
💩1
✺قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ
➵ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ ❨📓ኑር:30)
•════•════•
➩ አታመንዝር፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችዃል። እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥ወደ፡ሴት፡ያየ፡ዅሉ፡የተመኛትም፡ያን፡ጊዜ፡በልቡ፡ከርሷ፡ጋራ፡ አመንዝሯል። ቀኝ፡ዐይንኽም፡ብታሰናክልኽ፡አውጥተኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ሙሉ፡ሰውነትኽ፡በገሃነም፡ከሚጣል፡ይልቅ። ከአካላትኽ፡አንድ፡ቢጠፋ፡ይሻልኻልና።
(📓ማቴዎስ 5፥27-30)
●*●*●*●*●*️●*️●*️●
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
▣ የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች ▣
ክፍል 10
10. ምን ያህል የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር?
A. 2000 (ሁለት ሺሕ) የባዶስ መስፈሪያ
➵"ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር።ሁለት ሺሕም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።" ❨መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ 7፥26❩
●*●*●*●*●*️●*️●*️●
ነገር ግን በሌላ ቦታ
B. 3000 (ሶስት ሺሕ)የባዶስ መስፈሪያ
➵"ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር፥እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር ሦስት ሺሕም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።"❨ዜና መዋዕል ካልዕ 4፥5❩
ጥያቄው:-ሁለት ሺህ ወይንስ ሶስት ሺህ የባዶስ መስፈሪያ?
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
۞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:- "አትጠላሉ፤ አትመቀኛኙ፤ጀርባ አትሰጣጡ፤የአላህ ባሪያዎች ወንድማማቾች ሁኑ።" ❨📙️ሶሂህ ቡኻሪ፥ 6076❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
የንባብ ግብዣ
➢ በዚያችም ቀን ቅዱስ ሚካኤል የመንፈስ ቅዱስ ዕውቀቱ ወደ ኃዘን ይወስደኛል ያበሳጨኛል ብሎ ለቅዱስ ሩፋኤል መለሰለት። ❨📓መጽሐፈ ሔኖክ 19፥1❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
የነቢዩ ሎጥ ደረጃ በመጽሐፍ 'ቅዱስ'ና በቁርዓን
•════•════•
መጽሐፍ ቅዱስ
➵በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት ታላቂቱም ገባች፥ከአባቷም ጋራ ተኛች ርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፦እንሆ፥ትናንት ከአባቴ ጋራ ተኛሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከርሱ ጋራ ተኚ፥ከአባታችንም ዘር እናስቀር። አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት ታናሺቱም ገብታ ከርሱ ጋራ ተኛች። የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።
❨ኦሪት ዘፍጥረት 33-36❩
●*●*●*●*●*️●*️●
۞ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَت تَّعْمَلُ الْخَبَائِثَ ۗ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمَ سَوْءٍ فَاسِقِينَ
وَأَدْخَلْنَاهُ فِي رَحْمَتِنَا ۖ إِنَّهُ مِنَ الصَّالِحِينَ
➵ ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ ከዚያችም መጥፎ ሥራዎችን ትሠራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው፡፡ እነሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና፡፡ በችሮታችንም ውስጥ አገባነው፡፡ እርሱ ከመልካሞቹ ነውና፡፡ ❨አንቢያ፥74-75❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
የመጽሐፍ 'ቅዱስ' ግጭቶች
ክፍል 11
• ════•════•
11. ይሁዳ እየሱስን አሳልፎ ሲሰጠው ለምልክትነት ስሞት ነበርን?
📌 ስሞታል
➢‹‹አሳልፎ የሚሰጠውም፦የምስመውእርሱነው ያዙት ብሎ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር።ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና፦መምህር ሆይ፥ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው።"
❨ማቴዎስ 26፡48-49❩
• ════•════•
📌አልሳመውም(እየሱስ ራሱ ማንነቱን ገልጾላቸዋል)
➢‹‹ኢየሱስም፥የሚመጣበትን ሁሉ ዐውቆ ወጣና፦ማንን ትፈልጋላችኹ አላቸው።
የናዝሬቱን ኢየሱስን ብለው መለሱለት። ኢየሱስ፦እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከነርሱ ጋራ ቆሞ ነበር።›› ❨ዮሐንስ 18፥4-5❩

۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍2🤣1
ሁለተኛ ኮርስ
፩:3 የጠፉ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሉምን?


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ
እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

قُلْ مَنْ أَنزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَاٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ ۖ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا ۖ وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوا أَنتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ

6፥61 እንዲህ በላቸው፡- «ያንን ብርሃን እና ለሰዎች መሪ ኾኖ *ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው? የወደዳችኋትን ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፤ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ

وَتُخْفُونَ كَثِيرًا
ብዙውንም ትደብቃላችሁ በሚለው ይሰመርበት ለሙሴ በተሰጠው መፅሐፍ እንዴት እንደደበቁትና የኢየሱስ መፅሐፍ እንዴት እንደደበቁት
እናያለን።

Dr. Stevan Davies: ዴቪስ ስለ ጠፉት የኢየሱስ አባባሎች በሰፊው የጻፈ የአዲስ ኪዳን ምሁር ነው። “የኢየሱስ የጠፉ አባባሎች” በተሰኘው መጽሐፋቸው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያልተካተቱ ነገር ግን በሌሎች ምንጮች ሊገኙ የሚችሉ ብዙ የኢየሱስ ንግግሮች እንዳሉ ተከራክሯል።

ለምሳሌ

ክርስቲያኖች በ 387 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ ከወንጌላት የቶማስ፣ የይሁዳ፣ የጴጥሮስ፣ የያዕቆብ፣ የበርናባስ፣ የፊሊጶስ፣ የበርተሎሞዎስ፣ የመቅደላዊት ማርያም የተባሉትን ወንጌላትን ቀንሰዋል።

እነኚህ መፅሐፍቶች የት ይገኙ ይሁን?

“For I have not spoken of myself; but the Father which sent me, he gave me a commandment, what I should say, and what I should speak.”
  — John 12፥49 (KJV)

he gave me a commandment, በሚለው ይሰመርበት ትዕዛዝ የተሰጠው ከአባቱ መሆኑን "but the Father which sent me" ሲለን ለኢየሱስ የተሰጠው መፅሐፍ አሁን በእጅ የተፃፈ ሰይሆን አምላክ የሰጠው ነው።ለዚህም “የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።”
  — ዮሐንስ 17፥8

“የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና" በሚለው ይሰመርበት የተሰጠው ቃል የሰው እጅ የልገባበት ስሆን ያንን ቃል ለሀዋሪያቶች ስሰጣቸው እነርሱም ተቀበሉት፥።

ኢየሱስ እየሰበከ የነበረው የተሰጠውን ወንጌል እንጂ ቧሃላ ማቴዎስ, ማርቆስ, ዩሀንስ, ሉቃስ የፀሐፉት ወንጌል አይደለም ምክንያቱም እነኚ ወንጌሎች ከኢየሱስ እርገት ቦሃላ ነው
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉት አራቱ ወንጌላት የተጻፉት በተለያየ ጊዜ ሲሆን በሊቃውንት ዘንድ ግምታቸው ይለያያል። 

የማርቆስ ወንጌል፡-  በ65-70 ዓ.ም
የማቴዎስ ወንጌል፡-  በ80-90 ዓ.ም
የሉቃስ ወንጌል፡-   በ80-85 ዓ.ም
የዮሐንስ ወንጌል፡-  በ90-100 ዓ.ም
በአንዳንድ ሙሁራኖች መሰረት እንዲህ ተብለው ይታመናል።

እኛም ይሄንን ተንተርሰን እየሱስ እያስተማረበት የነበረው ወንጌል ማርቆስ 1፥14-15 ላይ የተጠቀሰው
አሁን ያለውን የነ የማርቆስ የማቴዎስ የሉቃስ የዮሐንስ ሰይሆን የራሱ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ነው።
ለዚህም ነው እንዲህ የሚለው
"-- ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።”
  — ማርቆስ 1፥14-15
የኛ ጥያቄ የኢየሱስ ወንጌል ይት ይኑር ይሁን?

የጴጥሮስ ወንጌል
- የቶማስ ወንጌል
ወንጌል ማርያም
- ሚስጥራዊ የማርቆስ ወንጌል
- የእውነት ወንጌል
- የባርናባስ ወንጌል
እነኚህ ወንጌላት ይት ይኑሩ ይሁን?

የሙሴ መፅሐፍ
አይሁዳውያን ለሙሳ የተሰጠውን መጽሐፍ በመከፋፈል ኦሪት ዘፍጥረት፣ ኦሪት ዘጸአት፣ ኦሪት ዘኁልቁ፣ ኦሪት ዘሌዋውያን፣ ኦሪት ዘዳግም በማለት ከፋፍለውታል፤ እነርሱም የማይመቻቸውን አፓክራፋ ማለት ድብቅ በማለት በመቀነስ ደብቀውታል፤

የሙሴ መፅሐፍ ግን በአራት ተከፋፍለው አነበረም።
ምክንያቱም ለሙሴ እግዚአብሔር ፅፎ እንደሰጣው ዘጸአት 24፥12 ላይ ተፅፎላቸዋል

“እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው።”
  — ዘጸአት 24፥12

ስማቸው በባይብል ውስጥ ተጠቅሰው አሁን የማይገኙ የጠፉ የባይብል ክፍሎች

ምሳሌ 1 የእግዚአብሔር የጦርነት መፅሐፍ

“ስለዚህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥”
  — ዘኍልቁ 21፥14

ምሳሌ 2 የእስራኤል የነገሥታት የታሪክ መፅሐፍ

“የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ እንዴት እንደ ተዋጋ፥ እንዴትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።”
  — 1ኛ ነገሥት 14፥19

ምሳሌ 3 የያሻር መፅሐፍ

“ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።”
  — ኢያሱ 10፥13

ምሳሌ 4 የአይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ

“የቀረውም የአብያም ነገር፥ ያደርገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በአብያምና በኢዮርብዓምም መካከል ሰልፍ ነበረ።”
  — 1ኛ ነገሥት 15፥7

ምሳሌ 5 የሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ

“የቀረውም የሰሎሞን ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ጥበቡም፥ እነሆ፥ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።”
  — 1ኛ ነገሥት 11፥41

ምሳሌ 6 በአዶ ራእይ የተጻፈ መፅሐፍ

“የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በኦሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ የተጻፈ አይደለምን?”
  — 2 ዜና 9፥29

ምሳሌ 7 በፋርስ ነገሥታት ታሪክ የተፃፈው መጽሐፍ

“የኃይሉና የብርታቱም ሥራ ሁሉ ንጉሡም እስከ ምን ድረስ እንዳከበረው የመርዶክዮስ ክብር ታላቅነት፥ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?”
  — አስቴር 10፥2

ምሳሌ 8 ኢሳይያስ የፃፈው መፅሀፍ


“የቀረውንም የፊተኛውንና የኋለኛውን የዖዝያንን ነገር ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ጽፎታል።”
  — 2 ዜና 26፥22

ምሳሌ 9 የሳሙኤል መፅሐፍ

“ሳሙኤልም የመንግሥቱን ወግ ነገረ፥ በመጽሐፍም ጻፈው፤ በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው።”
  — 1ኛ ሳሙኤል 10፥25

ዶ/ር ባርት ዲ ኤርማን፡ ኤርማን የአዲስ ኪዳን ምሁር እና የጽሑፍ ሃያሲ ሲሆን ስለጠፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በሰፊው ጽፏል። በ"Lost Christianities" በተሰኘው መጽሃፉ ውስጥ በእምነት መጀመሪያዎቹ መቶ ዘመናት ውስጥ ብዙ የተለያዩ የክርስትና ስሪቶች እንደነበሩ እና በመጨረሻም አዲስ ኪዳን የሆኑት ጽሑፎች ከትልቅ ታሪክ ውስጥ ትንሽ ክፍል ብቻ እንደሆኑ ይከራከራሉ.

ጥብቅ ማሳሰቢያ
እዚህ የምንለቃቸው ፁሁፎች
edit አድርጎ መጨመርም ሆነ መቀነስ የተከለከተ ነው።


📕 ወንድም አምዳላ ናሲር
የተኛውም አይነት  ሀሳብ ካለዎት
  👉ሀሳብ መስጫ👈
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇
https://t.me/comparativeRelgion/517
👍2
የመጽሐፍ 'ቅዱስ' አስተምህሮት
ለምጻም እርኩስ ነው።
• ════•════•
★ ለምጻም ሰው ነው ርኩስ ነው ካህኑ፦በርግጥ ርኩስ ነው ይለዋል ደዌው በራሱ ነው።የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ከንፈሩንም ይሸፍን ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል። ደዌው ባለበት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆናል እርሱ ርኩስ ነው ብቻውን ይቀመጣል መኖሪያውም ከሰፈር በውጭ ይሆናል።
📓ዘሌዋውያን 13፥44-46❩

۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1👎1
ሑዘይፋህ ኢብኑል የማን ለአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አልኳቸው ይላሉ፦"እኛ በክፋት ውስጥ ነበርን። አላህ ይህንን ኸይር (ኢስላምን) አመጣልን። ከዚህ ኸይር በኋላ ክፋት ይኖራልን?" "አዎ" አሉ። "ከዚያስ ክፋት በኋላ መልካም ነገር ይኖራልን?" ስላቸው "አዎ" አሉ። "እንዴት ?" ስላቸው "ከኔ በኋላ በመመሪያዬ የማይመሩ፣ በሱናየም የማይጓዙ መሪዎች ይመጣሉ። በነሱም ላይ ልቦቻቸው የሸይጧን አካላቸው ደግሞ የሰው የሆኑ ሰዎች ይነሱባቸዋል" አሉ። ሑዘይፋ ረዐ "እንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ከደረስኩኝ ምን ላድርግ ?" ሲላቸው "አሚሩን ትሰማለህ፣ ለሱም ትታዘዛለህ፣ ጀርባህ ቢመታህም ገንዘብህን ቢነጥቅህም እንኳ" አሉ። (ሙስሊም ዘግበውታል:4891)
የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች
     ክፍል 12
• ════•════•➵
📌️ይሁዳ ኢየሱስን በመክዳቱ ያገኘውን ገንዘብ ምን አደረገው?
●*●*●*●*●*️●*️●
    በብሩ መሬት ገዛበት
➤‹‹ ይህም፡ሰው፡በዐመፅ፡ዋጋ፡መሬት፡ገዛ፥በግንባሩም፡ተደፍቶ፡ከመካከሉ፡ተሰነጠቀ፥አንዠቱም ዅሉ
ተዘረገፈ›› ❨የሀዋርያት ስራ 1፥18❩
.*.*.*.*.*.*.*.
  በቤተ መቅደስ ጣለው
➤ ‹‹ብሩንም፡በቤተ፡መቅደስ፡ጥሎ፡ኼደና፡ታንቆ፡ሞተ።›› ❨📓ማቴዎስ 27፡5❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዋሰዋዊ ስህተቶች
  • ════•════•
   ️🔘 ሰው ወይም ሴት ️🔘
⓵.እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ የናዝራዊነት ስእለት ቢሳል፦...(📓ዘኁልቁ 6፥2)
      ●*●*●*●*●*️●*️●
⓶.ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ በድንጋይ ይውገሯቸው ደማቸው በላያቸው ነው።
(📓ዘሌዋውያን 20፥27)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
1
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
• ════•════•
️ሸይጣን በመጽሐፍ"ቅዱስ"እና ቁርዓን አስተምህሮት
📌️ የመጽሐፍ"ቅዱስ" አስተምህሮት
ሰይጣን እንደ የፈጣሪ ስልጣን ተፎካካሪ
➵ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!
አንተን በልብህ፦ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ።ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥በልዑልም እመሰላለሁ አልህ።
(📓ትንቢተ ኢሳያስ 14፡12-14)
●*●*●*●*●*️●*️●
️ የቁርዓን አስተምህሮት
📌️ ሸይጣን ተፎካካሪ ያልሆነ አመፀኛ ፍጥረት

قَالَ رَبِّ فَأَنظِرْنِي إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
➵«ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝም» አለ፡፡ (📓ሷድ፥79)
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1
▣ የነብያት ሃይማኖት ▣
•════•════•
ኢስላም
📌️ ኢስላም የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ነው።
⓵. ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡ ❨ሹራ፥13❩

⓶. ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ(ኢየሱስ) የማርያም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ።
ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው እናቶቻቸው ይለያያሉ፤ ነገር ግን ሃይማኖታቸው ኢስላም አንድ ነው። ❨📙ቡኻሪ 60፥113❩
●*●*●*●*●*️●*️●
ክርስትና
ነብያት ክርስቲያን አልነበሩም። ክርስትና የተጀመረው ከኢየሱስ እርገት በኋላ ነውና።
በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ። ❨📗የሐዋርያት ስራ 11፥26❩
۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞ ۞
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/sunah13
👍1