አቡ ሩሐማ - Abu Ruhama
973 subscribers
784 photos
137 videos
22 files
911 links
➧«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»፡፡ (ማኢዳ፥3)
Download Telegram
የባይብል ጉዶች ክፍል ሰባት

ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 1:1
---
¹ ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር።
2: በአፉ መሳም ይሳመኝ፥
ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና።
Song of Solomon 1 አማ - መኃልየ
12: ንጉሡ በማዕዱ ሳለ፥
የእኔ ናርዶስ መዓዛውን ሰጠ።
13: ውዴ ለእኔ በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ፡
እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።

Song of Solomon 2 አማ - መኃልየ
4: ወደ ወይን ጠጁም ቤት አገባኝ፥
በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው።
5: በዘቢብም አጽናኑኝ፥
በእንኮይ አበረታቱኝ፥
በፍቅሩ ተነድፌ ታምሜያለሁና።
6: ግራው ከራሴ በታች ናት፥
ቀኙም ታቅፈኛለች።

ተፈላልገው ተገናኙ
መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 4 (አማርኛ 1954)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።…
³ ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ አፍሽም ያማረ ነው፤ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።…
ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥ በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።…
⁷ ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።…
⁹ እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፤ አንድ ጊዜ በዓይኖችሽ፥ ከአንገትሽ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 5 (አማርኛ 1954)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፤ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።
³ ቀሚሴን አወለቅሁ፤ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፤ እንዴት አሳድፈዋለሁ?
ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።🙈
⁵ ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፤ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 6 (አማርኛ 1954)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
አውከውኛልና ዓይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፤ ጠጕርሽ ከገለዓድ እንደ ወረደ እንደ ፍየል መንጋ ነው።
⁶ ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ ሁሉ መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን
እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 7 (አማርኛ 1954)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² አንቺ የመኰንን ልጅ ሆይ፥ እግሮችሽ በጫማ ውስጥ እንዴት ውቦች ናቸው! ዳሌዎችሽስ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ ዕንቍዎች ይመስላሉ።
³ እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት እንደ ተነጠጠ ጽዋ ነው፤ ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው።
ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ እንደ ሚዳቋ ግለገሎች ናቸው።
⁵ አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤ ዓይኖችሽ በሐሴቦን ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ እንደ ውኃ ኵሬዎች ናቸው፤ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አፋዛዥ እንደሚመለከት እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው።…
ወዳጄ ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!
⁸ ይህ ቁመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም የወይን ዘለላ ይመስላሉ።
⁹ ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፎችዋንም እይዛለሁ አልሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ የአፍንጫሽም ሽቱ እንደ እንኮይ ናቸው።…
¹¹ እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።
¹² ውዴ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ በመንደሮችም እንደር።
¹³ ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤ ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያ ውዴን እሰጥሃለሁ።

ይሄ ሁሉ ሲያማልላት የነበረው ይህን ፈልጎ ነበር አገኘ

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 8 (አማርኛ 1954)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² መርቼ ወደ እናቴ ቤት ባገባሁህ፥ በዚያም አንተ ባስተማርከኝ፤ እኔም ከመልካሙ ወይን ጠጅ ከሮማኔም ውኃ ባጠጣሁህ ነበር።
³ ግራው ከራሴ በታች በሆነች ቀኙም ባቀፈችኝ ነበር።…
¹⁰ እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፤ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ።


     ወንድም ሷቢር

የሐቅ መንገድ(The Path of Truth)
የአክሱምን ግፍ እንዴት እንታገለው.pdf
67.5 KB
ለዓመታት ስንጮህ፣ ብሶት ስናሰማና ስናለቅስ ኖረናል። አፋኝ አካላት ግን ጩኸት አያስፈራቸውም፤ የሚበረግጉት ድርጊታቸው "የኢኮኖሚና የፖለቲካ ዋጋ" ሲያስከፍላቸው ብቻ ነው! ታዲያ የአክሱምን መዋቅራዊ ጭቆና ለመስበር፣ ከስሜታዊነት ወጥተን በምን ዓይነት ሳይንሳዊና ተግባራዊ ስትራቴጂ መታገል አለብን?

​በዓለም ታሪክ ውስጥ አናሳና ተገፊ ማኅበረሰቦች፣ ጨቋኞቻቸውን ያንበረከኩባቸውን 4 በብዛት የሚታወቁ፣ የተፈተኑና እኛም በአጎራባች ክልሎች ሆነን በቀላሉ ልንተገብራቸው የምንችላቸውን "የማዕቀብና የሕግ ጦርነት" ስልቶች የያዘ አጭር የመፍትሔ ሰነድ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል። ይህ ጉዳይ ለሚያስጨንቀው ሁሉ መነሻ የውይይት ሀሳብ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

ንባቡ ቢበዛ 7 ደቂቃ ቢፈጅባችሁ ነው፤ የፒዲኤፍ ሰነዱ ከታች ባለው ሊንክ አውርዳችሁ በርጋታ አንብቡት። ሐሳቡን ካመናችሁበት ደግሞ... ለሌሎችም አጋሩት!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
t.me/Yahyanuhe
Forwarded from Seid Social (Seid)
ሙሀመድ አሊ ሀገራችን ካሏት በጣም ጥቂት አሳቢያን አንዱ ነው።
በርካታ ትውልድን እንዲጠይቅ እንዲመራመር የሚያደርጉ መፅሀፍቶችን ያበረከተልን ከማንበብና ከመፃፍ የማይወገደው ሙሀመድ ሀገራችን እሹሩሩ ብላ ልትይዘው የሚገባ ክስተት የሆነ ሰው ነበረ።

ግና ሙሀመድ የተወለደው ኢትዮጵያ ነው። ያውም በዚህ ዘመን!
ምሁራን የሚሸማቀቁባት ፤ መሀይሞች የማፈነጩባት ፤ አሮጋንትነት ከፍታን የሚወስንባት ፤ የሀሳብ ሰዎች የሚሸማቀቁባት አንገታቸውን የሚደፉባት በድህነት የሚቆራመዱባት ኢትዮጵያ ውስጥ!
ሌብነት የመለወጥ ፤ ማጥፋትን የሀያልነት ፤ በመንጋ መነዳትም የአዋቂነት መለያ ተደርጎ የሚታይባት ኢትዮጵያ !

ማሜን አላህ ይጠብቀው!
እኛም እንደ ህዝብ ማገዝ ማበርታት ካለብን ቅርብ ያሉት ሰዎች አቅጣጫ ይስጡን የቻልነውን እናበረታለን!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
🤔1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2018

በሙሰኛ ባለሥልጣናት እና ፖለቲከኞች ላይ "የሞት ቅጣት" እንዲደነገግ የሚል አጀንዳ ይዘው የቀረቡት እጩ !

" የሕዝብ ሀብት ዘረፋ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ መታየት ጀምሯል ! "


በሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ኮልፌ ቀራንዮ የምርጫ ክልል 24ን ወክለው በግል እጩነት ለሕ/ተ/ም/ቤት የቀረቡት ጠበቃና የሕግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ፤ ለከባድ የሙስና ወንጀል የሞት ቅጣት እንዲደነገግ የሚጠይቅ አጀንዳ ይዘው መቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ጠበቃ ወንድሙ በፖለቲካው መድረክ ለመሳተፍ የወሰኑበት ዋና ምክንያት፣ ፖለቲካው ሙሉ በሙሉ ለሕግ የበላይነት ተገዥ እንዲሆንና መንግስት የሚያወጣቸው ሕጎች ፖለቲከኞችን በሚመጥን መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

​በተለይም ሀገሪቱን እያመሰ ያለውን የሙስና ወንጀል ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት እጩው፤ በሙስናና በሕዝብ ሀብት ዝርፊያ የተሳተፉ የመንግስት ባለሥልጣናትን፣ ፖለቲከኞችንና ሌሎች ግለሰቦችን በሞት የሚያስቀጣ ሕግ እንዲወጣ አቋም ይዘዋል።

ጠበቃ ወንድሙ አቋማቸውን ለማስረዳት እንደ ቻይና እና ጃፓን ያሉ ሀገራት የሞት ቅጣትን ለሙስና ወንጀል እንደሚጠቀሙበት ያነሱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የህዝብ ሃብት ዘረፋ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ መታየት መጀመሩን በመተቸት ይህንን ለመግታት የሞት ቅጣት መፍትሔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ጠበቃው ከዚህ አጀንዳቸው በተጨማሪ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39 (1) " በማንኛውም ጊዜ እስከ መገንጠል " የሚለው እንዲሰረዝ ፤ እንዲሁም የቤተሰብ ሕግ ትዳርን በሚያከብር መልኩ እንዲሻሻል ለማድረግ እንደሚታገሉ አመልክተዋል።

​ተመራጭ ከሆኑ በምርጫ ክልላቸው ቋሚ ቢሮ በመክፈት በሳምንት አንድ ቀን የዜጎችን ጥያቄ በቀጥታ እንደሚቀበሉ ቃል የገቡት አቶ ወንድሙ ፤ ቀደም ሲል በሙያቸው ከ600 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ነፃ የጥብቅና አገልግሎት መስጠታቸውን አስታውሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ሰው እንዴት ኃጢኣቱ ይማርለት ዘንድ ኃጢአቱን ለሌላ ኃጢአተኛ ይናገራል? የንስሀ አባት ነገር ፈጽሞ ከህሊና የራቀ ነው..!

- https://t.me/Yahyanuhe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኳስ ትውልድን እየገደለ፣ መሳጂዶችን ባዶ እያደረገ ያለ ትልቅ በሽታ ሆኗል
የዒድ አል-አድሓ በዓልን ለማክበር ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚያመሩ ሙስሊሞች በቶሎ በመመለስ በሀገራዊ ምርጫው እንዲሳተፉ የፌዴራል መጅሊስ ጥሪ አቀረበ!

• ​ሀሩን ሚዲያ | ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ል

​የፌደራል መጅሊስ 1447ኛውን የዒድ አል-አድሓ (የአረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመላው የሙስሊም ማህበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

​የፌዴራል መጅሊሱ ም/ፕሬዚዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዒድ አል-አድሓ በዓል ታላቁ የሐጅ ሥርዓት የሚፈጸምበት፣ እንዲሁም የመከባበርና የመረዳዳት ወቅት መሆኑን ጠቅሰው የበዓሉን መንፈሳዊ ፋይዳ አብራርተዋል።

​በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በድምቀት የሚከበረው ይህ በዓል፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ያለንን ልዩ የመረዳዳት ባህል ይበልጥ በማጠናከር እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማገዝ ሊከበር እንደሚገባው አስገንዝበዋል። በዓሉን ስናከብር ሰላምና አንድነታችንን በማስጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ ያወሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማክበር ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች (ገጠር) የሚያመሩ ሙስሊሞች በቶሎ በመመለስ በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

​በሌላ በኩል የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ፤ በዓሉ በሙስሊሞች ዘንድ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች የሚከበር ደማቅ ዕለት መሆኑን አውስተዋል። አክለውም ነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) ለአላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ያሳዩትን ፍጹም ታማኝነት፣ መስዋዕትነትና ትዕግሥት የምናስታውስበት ታሪካዊ በዓል መሆኑንም በመግለፅ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ መልካም በዓልን ተመኝተዋል።

📅 ዙል-ሒጃ 8 ቀን 1447 ዓ.ሂ

© ሀሩን ሚዲያ
Eid Mubarek!
Iid Mubaarak!
ኢድ ሙባረክ!
የባዕድነትን ገጽታ በማውለቅ ተመሳስሎ መቅረብ (Indigenization)

​የማንኛውም ስውር ወረራ ታላቁ ስኬት የሚለካው፣ ተወራሪው ማህበረሰብ ወረራውን እንደራሱ የባህል አካል አድርጎ ሲቀበለው ነው። የሚሽነሪዎች እንቅስቃሴ በታሪክ ውጤታማ ከነበረባቸው መንገዶች አንዱ የባዕድነት መልኩን በመቀየር "ሀገር-በቀል" (Indigenization) የማድረግ ስልቱ ነው። ይህ ስልት የውጭ ጽንሰ-ሀሳቦችን በአካባቢው ቋንቋ፣ ዜማ፣ ባህላዊ ልብስ እና የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ በመክተት፣ ማህበረሰቡ አዲሱን ርዕዮተ-ዓለም ያለ ምንም ጥርጣሬ የራሱ አድርጎ እንዲቀበለው የማድረግ ረቂቅ ጥበብ ነው።

​በተለይም በኢትዮጵያ የወንጌላውያን እንቅስቃሴ ታሪክ ውስጥ እንደሚታየው፣ ባህላዊ የሙዚቃ ዜማዎችን እና የሀገር በቀል ስልቶችን ለስብከት አገልግሎት ማዋል ዋነኛ ስትራቴጂ ሆኖ አገልግሏል። ማህበረሰቡ በለመደው ቋንቋና ዜማ ሲነገረው፣ በባዕድ እና በሀገር በቀል አስተሳሰቦች መካከል ያለው ልዩነት ይደበዝዝበታል። ይህ ስልታዊ ውህደት፣ አንድ ማህበረሰብ ሳይነቃ በገዛ ልማዱ ማዕቀፍ ውስጥ አዳዲስ እሴቶችን እንዲያስተናግድ የሚያስገድድ ምሁራዊ ንድፍ ነው። ሃይማኖቱ ከውጭ የመጣ ቢሆንም፣ አቀራረቡ ግን የጓዳ እስኪመስል ድረስ በማላመድ የህዝቡን ስነ-ልቦና በቀላሉ መግዛት ተችሏል።

​በቀጣዩ ክፍል የምንዳስሰው አጀንዳ፡

የገጠር እና ከተማ ስልታዊ ክፍፍል - ምሁሩን በሃሳብ፣ ገጠሬውን በልማት የመቆጣጠር ስልትን በቀጣይ ክፍል - 12 ላይ በአላህ ፍቃድ እንመለከተዋለን።

​የመረጃ ምንጮች፦

• ​Temesgen Shibru Galla, "The Mission Thinking of the EECMY", 2011.

• ​Lamin Sanneh, "Translating the Message: The Missionary Impact on Culture".

​መረጃውን ሼር በማድረግ ማህበረሰባችንን እናንቃ! የእርስዎ ተሳትፎ ትውልድን ያነቃል!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe
የብሉይ ኪዳን ታቦት

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥145 ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼን እና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ مَّوْعِظَةً وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ

በዐረቢኛ “ለውሕ” لَوْح ማለት "ሰሌዳ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ለሙሣ ቃላትን በሰሌዳዎች ላይ ጽፎ እንደሰጠው በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
7፥145 ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼን እና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አልዋሕ" أَلْوَاح ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ለውሕ” لَوْح ለሚለው የብዙ ቁጥር ሲሆን "ሰሌዳዎች" ማለት ነው። በዐረቢኛ "ታቡት" تَّابُوت ማለት "ሳጥን" ማለት ነው፦
20፥39 ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ ጣይው፡፡ أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሳጥኑ" ለሚለው የገባው ቃል "አት ታቡት" التَّابُوت ነው። የጽላት ማስቀመጫ ሳጥኑ "ታቡት" تَّابُوت ተብሎአል፦
2፥248 ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሣ ቤተሰብ እና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ "ሳጥኑ" ሊመጣላችሁ ነው፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አለ» አላቸው፡፡ وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሳጥኑ" ለሚለው የገባው ቃል "አት ታቡት" التَّابُوت ሲሆን ሙፈሢሮች እንዳስቀመጡት በታቦቱ ውስጥ የሙሣ ቤተሰብ እና የሃሩን ቤተሰብ የተዉት "ቅርስ" ተብሎ የተቀመጠው ጽላት፣ የሃሩን በትር፣ መና ነው፥ ታቦቱን ከዳጎን ቤት ወደ አሚናዳብ ቤት ተሸክመው የወሰዱት መላእክት ናቸው።

እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ አቆጣጠር በ 1225 ድኅረ ልደት ላይ በንቡረ ዕድ ይስሐቅ የተቀነባበረ ክብረ ነገሥት የተባለው የታሪክ መጽሐፍ ይህ በሙሴ ዘመን የነበረው ታቦት በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን አክሱም ገብቶ እንደተቀመጠ ይናገራል፥ የአገራችን ሰዎች ይህንን ትርክት ተከትለው ዛሬ ላይ "አክሱም ጽዮን ማርያም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሙሴ ታቦት አለ" ብለው ያምናሉ። ማሩን አምርሮ ወተቱን አጥቁሮ መሞገት ከሐሰት ባለቤት የሚጠበቅ ቢሆንም ይህ ትርክት እልም ያለ ቅጥፈት መሆኑን የምትረዱት ከሰሎሞን ህልፈት 400 ዓመት በኃላ በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን ታቦቱ የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ ነበረ፦
2ኛ ዜና መዋዕል 35፥3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት ለያህዌህ ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ "ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት! ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም"።

የብሉይ ኪዳን ታቦት አራት ሰዎች በትከሻቸው የሚሸከሙት ግዙፍ ሳጥን እንጂ ዛሬ ላይ በየአድባሩ ያሉት ጣውላዎች ንድፍ የሆኑለት በአክሱም ጽዮን የተቀመጠው ባለ ሁለት ቅጥ አይደለም፥ ይህ የሙሴ ታቦት የሚሉት ከአክሱም ማርያም ለንግሥ የማያወጡበት ምክንያት ከብሉይ ኪዳን ታቦት ጋር የማይመሳሰል ስለሆነ ነው።
ቅሉ እና ጥቅሉ የቃል ኪዳኑን ታቦት የባቢሎን ንጉሥ ናቡነደፆርን እና ሰራዊቱን በ 606 ቅድመ ልደት ማርከው ወስደውታል፦
ዕዝራ ሱቱኤል 9፥22 "የቃል ኪዳናችን ታቦት" እንደ ተማረከች፥ ንዋየ ቅድሳታችን እንዳደፈ፥ ስማችን እንደ ረከሰ፥ ጌቶቻችን እንደ ተዋረዱ፥ ካህኖቻችን እንደ ተቃጠሉ፥ ሌዋውያኖቻችን እንደ ተማረኩ፥ ደናግሎቻችን እንደ ተገደሉ፥ ሚስቶቻችንን እንደ ቀሙን፥ ጻድቃኖቻችን እንደ ተጐተቱ፥ ጐልማሶቻችን እንደ ተገዙ፥ ወንዶች ልጆቻችን እንደ ተቀሙ፥ አርበኞቻችን እንደ ደከሙ አታዪምን?
Second Esdras 10፥22 The ark of our covenant has been plundered, our holy things have been polluted, and the name by which we are called has been almost profaned; our children[c] have suffered abuse, our priests have been burned to death, our Levites have gone into exile, our virgins have been defiled, and our wives have been ravished; our righteous men[d] have been carried off, our little ones have been cast out, our young men have been enslaved and our strong men made powerless.

"የቃል ኪዳናችን ታቦት እንደ ተማረከች"The ark of our covenant has been plundered" የሚለው ይሰመርበት! በዐማርኛው ዕዝራ ሱቱኤል እና በእንግሊዝኛው ዕዝራ ሱቱኤል የምዕራፍ ልዩነት እንዳለ ሆኖ ግዕዙ "ወተበርበረት ታቦተ ሕግነ" በማለት እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ይናገራል፥ ይህ ዘገባ የክብረ ነገሥት ትርክት አፈር ከድሜ የሚያስገባ ነው። በባቢሎን ምርኮ ዘመን ይህ የብሉይ ኪዳን ታቦት ተማርኮ ከዚያ በኃላ ጠፋ፦
ዕዝራ ሱቱኤል 9፥23 ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮን እንደጠፋች ቀረች፥ ከእሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን።

ይህ ዘገባ የክብረ ነገሥት ትርክት ዶግ አመድ የሚያደርግ ነው። ከባቢሎን ምርኮ በኃላ እስራኤላውያን "የያህዌህ የቃል ኪዳኑ ታቦት" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፣ ልብ አያደርጉትም፣ አያስቡትም፣ አይሹትም፣ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም፦
ኤርምያስ 3፥16 በዚያ ዘመን፦ "የያህዌህ የቃል ኪዳኑ ታቦት" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፣ ልብ አያደርጉትም፣ አያስቡትም፣ አይሹትም፣ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።

ቃልቻ እና ጉልቻ የተቀላቀለበት ይህ የብሉይ ኪዳን ታቦት ትርክት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ውዝግብ በማስነሳት የሚያራኩት ነው፥ ትግራይ መቀመጫ ያደረገው የኦርቶዶክስ ሲኖዶስ "አክሱም ቅድስት ከተማ ናት" ካለ ቅድሚያ ጽዮን ማርያም አጠገብ የተተከለውን የወንድ ኃፍረተ ሥጋ ቅርፅ የያዘውን ሐውልት ማፍረስ ይገባቸዋል። ፈጣሪ "የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ" ብሎአል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።

ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት ይህንን ካልን ዘንዳ ኢንሻ አሏህ በቀጣይ ጊዜ ስለ አዲስ ኪዳን ታቦት እንመለከታለን። አምላካችን አሏህ ከውዝግብ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ትግራይ መቀመጫ ያደረገው የኦርቶዶክስ ሲኖዶስ "አክሱም ቅድስት ከተማ ናት" ካለ ቅድሚያ ጽዮን ማርያም አጠገብ የተተከለውን የወንድ ኃፍረተ ሥጋ ቅርፅ የያዘውን ሐውልት ማፍረስ ይገባቸዋል። ፈጣሪ "የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ" ብሎአል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የጋና ፓርላማ ግብረሰዶማዊነትና ተግባራቱን የሚያስተዋውቅ የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ #ወንጀል የሚያደርግ ሕግ አጸደቀ።

በግብረሰዶማዊነት ተግባራት ውስጥ ተሳትፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በሦስት ዓመት እስራት እንደሚቀጣ ሕጉ ይደነግጋል።

ከዚህ በተጨማሪ በዚህ የተከለከለ ተግባር ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎችን የሚያውቅ ግለሰብ ለፖሊስ የመጠቆም ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል።

ማንኛውም የግብረሰዶማዊነት እንቅስቃሴ የሚደግፍ ወይም የሚያግዝ አካልም እስር እንደሚጠብቀው ተመላክቷል።

በሕጉ ላይ የግብረሰዶማዊ  እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ሰዎችን የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የሕግ፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የጤና ባለሙያዎች እንዳይካተቱ ተደርገዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ባለፈው ዓመት ወደ ሥልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ የሃይማኖት አባቶች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ ያሉ ሕጎችን እንዲያጠብቁ ጫና ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ሕጉን ያረቀቁት መጋቢ ጆን ንቲም ፎርዦር ፥ " ሕጉ የጋና ቤተሰብ እና ባህላዊ እሴቶች ይጠብቃል። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ለመከላከል የበለጠ ጠንካራ ፣ የበለጠ አካታች፣ የበለጠ ጥብቅ ያደርጋል " ብለዋል።

ጋና እ.አ.አ. በ2024 ተመሳሳይ ህግ ብታወጣም በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት አኩፎ አዶ ሳያጸድቁት በመቅረታቸው ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል።

ፕሬዚዳንት ማሃማ ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ ሕጉ እንዲጸድቅ እንደሚፈልጉ ተናግረው " ሁለት ጾታዎች ወንድ እና ሴት ብቻ በሚለው መርህ እና እሴት አምናለሁ። እና ጋብቻ በወንድ እና በሴት መካከል ብቻ ነው " ብለው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።

ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
⚠️ ምትማረው፣ ምትደክመው ስለዚች አለም ብቻ ከሆነ አደጋ ላይ ነህ…

ረሱል (🕌️) እንዲህ ብለዋል፦

 ﴿إنَّ اللهَ تعالى يُبغِضُ كلَّ عالِمٍ بالدنْيا، جاهِلٍ بالآخِرَةِ﴾

“የላቀው አላህ ስለ ዱኒያ ጉዳይ አዋቂ ሆኖ ሳለ ስለ አኼራው ጉዳይ የማያውቅ (መሃይም) የሆነን ሰው ይጠላዋል።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 1879

🟧🟧🟧🟧🟧

🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️Telegeram 📞 Whatsup

👤Facebook  📸Instagram

💬X 🎥Youtube 🎵Tik tok
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሁሌም ወቃሽ ከመሆን፣ እውነትንም መመስከር እንልመድ
===============================
✍️ ለዓመታት፣ በተለይም በሐጅ ጉዞ ወቅት፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚገጥመውን እንግልት እና መጉላላት ስንቃወም፣ መጅሊሱን ስንወቅስ
እና መፍትሄ ስንጠይቅ ኖረናል። የነበረው ክፍተት እና ብልሹ አሠራር እውነት ስለነበር፣ መውቀሳችንም ሆነ መተቸታችን ፍፁም ትክክል ነበር።

ነገር ግን... የዛሬው እውነታ ተቀይሯል! «ዘንድሮ በትክክል፣ በጥንቃቄና በምርጫ ምረጡት» ያልኳችሁ መጅሊስ፣ ይኸው ከምርጫው ዋዜማ ላይ በአንድ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን አኩርቶ አስመስክሯል። አል-ሐምዱ ሊላህ!

አዎ! የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ፣ በመካ በተካሄደው “ኺታሙሁ ሚስክ” በተሰኘው የሳዑዲ ሚስክ የዕውቅና መድረክ ላይ፣ የላቀ አፈፃፀም በማሳየት የአልማዝ (Diamond Award) ሽልማት አሸናፊ ሆኗል! 💎🇪🇹


🎁 በሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው የዘንድሮው "ምርጥ የሐጅ ልዑካን" (أفضل بعثات الحج) የሽልማት ሰንጠረዥ መሰረት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከማሌዥያ እና ከኢራቅ ጋር በመሆን የከፍተኛው ማዕረግ የአልማዝ (Diamond) ሽልማት አሸናፊ የሆነች ሲሆን፤ ከዚህ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የወርቅ (Gold) ሽልማቱን ቱርክ፣ ኮሞሮስ እና ጅቡቲ ሲያገኙ፤ በሦስተኛ ደረጃ የብር (Silver) ሽልማቱ ደግሞ ለግብፅ፣ ለኦማን እና ለሞሮኮ ተበርክቷል። በመጨረሻም የነሐስ (Bronze) ሽልማቱን ሲንጋፖር፣ ቱኒዚያ እና አልጄሪያ አሸንፈዋል። ይህ የደረጃ ሰንጠረዥ የሚያሳየው የሀገራችን መጅሊስ የሐጅ አፈፃፀም ከሌሎች በርካታ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደደረሰ እና ተወዳዳሪ መሆን እንደቻለ ነው!




▫️ ለዚህ ሽልማት ያበቋቸው ስኬቶች፦

ሑጃጆችን በጊዜ እና በተደራጀ መልኩ መመዝገብ፣

የሐጅ ተጓዦችን ቀድሞ በስልጠና
ማዘጋጀት (Proactive preparation)

በጥንቃቄ የተመራ የጤና አጠባበቅ እና፣

ለሑጃጆች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት (Efficient service delivery) መስጠታቸው ነው።

➡️ ዶ/ር ሙሐመድ ሷሊሕ ጀማል ይህን ዓለም አቀፍ ሽልማት ሲቀበሉ፣ ኢትዮጵያ በበጎ ስሟ ተጠርቷል። ይህ ትልቅ ድል ነው!


🔸ይህንን ስንል ማሽቃበጥ፣ አሊያም "አሁን መጅሊሱ 100% እንከን የለሽ ሆኗል" ማለት አይደለም። ዛሬም የሚስተካከሉ ክፍተቶች ይኖራሉ። ነገር ግን ከነ ክፍተታቸው፤ ትናንት የነበረውን የሐጅ ጉዞ እንግልት አሻሽለው ለዚህ ደረጃ ሲያደርሱ፣ Credit መስጠት እና ማድነቅ የኢስላም መርህ ነው።

ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ ተይሚይያህ 📍 እንዲህ ይላሉ፦
«والعدل أن تقبل من المحسن إحسانه، وتتجاوز عن المسيء إن تاب، ولا تبخس الناس أشياءهم»

«ትክክለኛ ፍትሕ ማለት፣ ከመልካም አድራጊው መልካምነቱን መቀበል፣ ከተሳሳተው ደግሞ ሲመለስ ማለፍ፣ እንዲሁም የሰዎችን የልፋት ዋጋ (ክሬዲት) አለመቀነስ ነው።»

Credit where credit is due  የጤናማ አዕምሮ መገለጫ ነው። ሁሌ ማሞካሸት ወይም ሁሌ ወቃሽና ከሳሽ መሆን፣ የነቀፋ ሱሰኝነት እንጂ ጤነኝነት አይደለም። ሲያጠፉ "ይህ ልክ አይደለም ብሎ በድፍረት ማረም፤ ሲያስተካክሉ ደግሞ «ጎበዞች፣ አላህ ይጨምርላችሁ» ብሎ ማድነቅ ሚዛናዊነት ነው።

ለዚህ ትልቁ መስካሪ ደግሞ የፌስቡክ ዲስኩር ሳይሆን... በፊት ሄዶ እንግልቱን ያየ እና ዘንድሮ ሄዶ ለውጡን ያጣጣመ ሑጃጅ ነው!


በድጋሚ ለመጅሊሱ የሐጅ እና ዑምራህ ዘርፍ (በተለይም ለፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ እና ለዶ/ር መሐመድ ሷሊሕ) እንኳን ደስ አላችሁ! አላህ የበለጠ የኡማውን ሐጃ ከማውጣት እና ከዚህም የላቀ ስኬት ያድርሳችሁ!


||
t.me/MuradTadesse
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር

የግንቦት ወር  (May) በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ግንዛቤ ወር በመባል ይታወቃል። ይህን አስመልክቶት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ሳምንታት በአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን የተዘጋጁ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ ነበር። እንሆ ዛሬ የመጨረሻው መልዕክት ተልኳል👇

አዕምሯችንም ይደክማል!

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን -የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት)

ብዙዎቻችን የአካላችንን ድካም በቀላሉ እንረዳዋለን ለምሳሌ እግራችን ሲደክም እንቀመጣለን፣ ትከሻችን ሲዝል ደግሞ ጋደም ብለን ለማረፍ እንሞክራለን። ነገር ግን አዕምሯችን የሰውነታችን ሁሉ መሪ ሆኖ 24 ሰዓት ያለእረፍት እንዲሠራ እናስገድደዋለን። አዕምሮ ልክ እንደ አካላችን ካልተንከባከብነውና ተገቢውን እረፍት ካልሰጠነው መድከሙ የማይቀር ነው።

በየቀኑ በኑሮና በሥራ ሩጫ ውስጥ ስንሆን አዕምሯችን " ደክሞኛል፣ እረፍት እፈልጋለሁ! " እያለ በተለያየ መንገድ ድካሙን ይገልፃል።

አንዳንዴ በእንቅልፍ ማጣት፣ አንዳንዴ የማተኮር አቅም በማጣት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለምክንያት ቶሎ በመበሳጨትና በስሜት መለዋወጥ ሊገለፅ ይችላል።

ታዲያ እነዚህን ምልክቶች እንደ ቀላል አይቶ ችላ ማለት ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል። የአዕምሮ ጤናን መጠበቅ የሚጀምረው ራስን ከማድመጥና ለራስ ጊዜ በመስጠት ነው።

ለአዕምሯችን ጊዜ መስጠትና ማሳረፍ ስንል ምን ማለታችን ነው?

- በቂ እንቅልፍ ወስደን አዕምሯችን ራሱን እንዲያድስ እድል በመስጠትና ከመተኛታችን በፊት ከስልክና ሶሻል ሚዲያ በመራቅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲያርፍ ማድረግ።

- ብቻችንን ከመብሰልሰል ከሰዎች ጋር ተገናኝቶ የውስጥን ጫና እና ጭንቀት ማውራት፤ ስሜትን ለምናምነው የቅርብ ሰው ወይም ለባለሙያ በማጋራት የአዕምሮን ሸክም በማውረድ።

- ከዕለት ተዕለት ጩኸት ራቅ ብሎ በንጹህ አየር እና በተፈጥሮ መካከል ጥቂት ደቂቃዎችን በማሳለፍ እንዲሁም ከአደንዛዥ እፆች ፣ ከጫት እንዲሁም ከአልኮል ጊዜያዊ መጠለያነት በመራቅ የአዕምሮን ጤና መጠበቅ እና መንከባከብ እንችላለን።


@tikvahethiopia