የባህር ዳር አህሉሱና ዳዒዎች ገፅ
208 subscribers
1K photos
92 videos
16 files
448 links
በባህርዳርና አካባቢዋ በሱና ዑለሞችና ዳዒዎች የሚሰጡ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ገፅ ፤
Download Telegram
አዋሽ ባንክን እናመሰግናለን !!

አዋሽ ባንክ በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አማካኝነት ለ 25 ቤተሰቦች የተሟላ የአስቤዛ ድጋፍ አድርጓል፡፡

እርስዎስ ?

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባህርዳር  ቅርንጫፍ

ንግድ ባንክ
1000441566666

ሂጅራ ባንክ
1001318180001

ለበለጠ መረጃ : -
📱 0918711081
📱 0904947575
📱 0912491704
🌹 ልዩ የሙሃደራ ድግስ ለሴቶች 🌹

በባህር ዳር ከተማ

" አሏህን መፍራት "

🎙 ኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ

ሰኞ ግንቦት 28
/ 2015

ከጠዋቱ 03:30 ጀምሮ በነሲሓ መርከዝ ቀበሌ 14

አዘጋጅ:– ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ባህር ዳር ቅርንጫፍ
የምስራች

ልጅዎት ክረምትን እንዴት እንደሚሳልፉ አሳስቦዋታል ?

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ባህርዳር ቅርንጫፍ መፍትሔ አለው !!
እዩኝ፣ እዩኝ ማለት ደብቁኝ፣ ደብቁኝ ማለት ያመጣል
~
ባህሩ እኛ ተመቅኝተን ትኬት እንዳይሸጥላቸው እንዳደረግን አድርጎ እየከሰሰ ነው። በመጀመሪያ "በቁጭታችሁ ሙቱ!"፣ "ጩኸት በህመም ልክ ነው" እያላችሁ በፎከራችሁ ማግስት አሰናከላችሁብን ብላችሁ ማልቀስ ጥሩ አይደለም። ቢያንስ ሰንበትበት በሉ እንጂ። ይልቅ ካልተሳካ ማላከኪያ ሰበብ ከመፈለግ እውነተኛ ምክንያቱን ከራሳችሁ ዘንድ ፈልጉት። እንደኔ ጥቂት ነጥቦችን ብታስተውሉ መልካም ነው።
1ኛ፦ ለአንድ ቀን ደዕዋ 1000 ብር መጠየቅ ልክ ነው ወይ? በታዳሚው ቦታ ሆናችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።
2ኛ፦ ሚሊኒየም አዳራሽ ምን አንጠለጠላችሁ? በልካችሁ አትሞክሩም? ቢሳካስ ለአንድ ቀን አዳራሽ 810ሺ ብር፣ እንደገና ለሻይ ቡና 3.1 ሚሊዮን ብር ሌሎች ወጭዎችን ሳይጨምር ይሄ ብቻ አራት ሚሊዮን አካባቢ ብር ከማውጣት በተመሳሳይ መጠን ብዙ ስራ መስራት ይቻላል። ብዙ ሰው ያላቸው አካላት ጋር ትከሻ እየተለካኩ ሲንገዳገዱ ከማዘን በአቅም ልክ ማሰብ ይሻላል።
3ኛ፦ የራሳችሁ ጩኸት ሸውዷችኋል። ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚረብሸው ድምፃችሁ ስለ ራሳችሁ ቁጥር የተጋነነ ምስል እንድትይዙ አድርጓችኋል። ግርግር አይሸውዳችሁ። በሐጅማችሁ ሁኑ።
4ኛ፦ ኢኽላሳችሁን ፈትሹ። የቀስድ መበላሸት ብዙ ነገር ያበላሻል። እዩኝ፣ እዩኝ ማለት ደብቁኝ፣ ደብቁኝ ማለት ያመጣል። እነዚህን ነጥቦች በደንብ ብታጤኗቸው ለሌላ ጊዜ ይጠቅሟችኋል።
የአሁኗ ለቅሶ አላማ ከመንጋው ዘንድ ቁጭት ፈጥሮ መቀስቀስ ከሆነም ኒያችሁን አጥሩ። ያለ ኢኽላስ እንዲሁ ለእልህ የወጣ ገንዘብ ከአላህ ፊት ያስጠይቃል። ከዚህ በፊት እንዳደረጋችሁት ከሩቅ በእልህ ተጠራርታችሁ ዛሬን ብታሳኩ እንኳ የኋላ ኋላ ውርደት ያስከትላል። እልህና ኢኽላስ የተለያዩ ናቸው።
አንድ ነገር ግን አስረግጬ ልንገራችሁ! ቁጥራችሁ አሁን ካለውም የበለጠ እያነሰ ነው የሚሄደው። በተቃርኖ የተሞላ አካሄዳችሁን የታዘበ ሰው ይህንን ለመረዳት አይከብደውም። በሆይሆይታ ያሰለፋችኋቸው መንጋዎች ወደ ቀልባቸው ሲመለሱ ጊዜ እናንተ ከምትሾፍሩት የስሜት ባቡር እየተንጠባጠቡ ይወርዳሉ።
ማስታወሻ፡
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغۡیُكُمۡ عَلَىٰۤ أَنفُسِكُمۖ }
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው።" [ዩኑስ፡ 23]
{ وَلَا یَحِیقُ ٱلۡمَكۡرُ ٱلسَّیِّئُ إِلَّا بِأَهۡلِه }
"ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም።" [ፋጢር፡ 43]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
#challengebeforejumuah

እሄን ግሩፕ 10,000 ማድረስ እንዴት አቃተን?

የባህር ዳርና አካባቢዋ ሙስሊሞች ቁጥራችን እሄ ብቻ ነዉን?


በ3 ቀናት ውስጥ  ከጁሙዓህ በፊት 10,000 እናድርሰው !!

Join 👇👇👇

https://t.me/teeziya_bdr_muslims
የክረምት የዲን ኮርስ በባህር ዳር

ልጆችዎን መሰረታዊ የቁርአን ፣ የዓቂዳ፣ የሀዲስ፣ የፊቅህና የተርቢያ ትምህርቶች በክረምት ለማስተማር ፈጥነው ይመዝገቡ ፤

ለምዝገባ ከታች በተጠቀሱት ስልኮች ይደውሉ:-

0918393892/0918412322 ቀበሌ 14 ኖክ
0913646379/0918412322 ቀበሌ 7
0930703972/0918412322 አየር ጤና
0979621661/0918412322 ቀበሌ 14

https://t.me/merkezunabdr