Forwarded from S•A•R•A•H
الحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي عَلَّمَ بِالقَلَمِ.
Pure joy and passion poured into crafting these Islamic art pieces.
@Sarah_Creative

Forwarded from ስለ ቀልባችን
ከአቡ ሁረይራ (ረድየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
❝ ትጥበት አድርጎ ወደ ጁምዓ የመጣ፣ ከዚያም የተገራለትን ያህል(ሱና ሶላት) የሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ ኹጥባውን እስኪጨርስ ዝም ብሎ ያዳመጠ፣ በመቀጠልም አብሮት የሰገደ ሰው፤ በዚያች ጁምዓ እና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል ያለው እንዲሁም ተጨማሪ የሶስት ቀናት (ወንጀሉ) ይማርለታል።❞
◇ሰሒሕ ሙስሊም 857
t.me/Sle_qelbachn1
❝ ትጥበት አድርጎ ወደ ጁምዓ የመጣ፣ ከዚያም የተገራለትን ያህል(ሱና ሶላት) የሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ ኹጥባውን እስኪጨርስ ዝም ብሎ ያዳመጠ፣ በመቀጠልም አብሮት የሰገደ ሰው፤ በዚያች ጁምዓ እና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል ያለው እንዲሁም ተጨማሪ የሶስት ቀናት (ወንጀሉ) ይማርለታል።❞
◇ሰሒሕ ሙስሊም 857
t.me/Sle_qelbachn1
Forwarded from S•A•R•A•H
A new journey ✨️
Some of my summer achievements ✨️ Alhamdulillah for everything ✨️
اللهم بارك لها وزدها!
"وَأَنْ لَيْسَ لِلإِنْسَانِ إِلا مَا سَعَى"
"And that man can have nothing but what he strives for." (Surah An-Najm 53:39)

❤4
Forwarded from ስለ ቀልባችን
የዱሃ ሶላት...
ነቢዩ (ﷺ) እንዳስተማሩን በሰውነታችን ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች ያሉ ሲሆን፣ በየቀኑ በሰላም ለተንቀሳቀሰበት ለእያንዳንዱ
መገጣጠሚያችን ምስጋናና ሰደቃ ማቅረብ ይጠበቅብናል።
ይሁን እንጂ የአላህ እዝነት ሰፊ ነውና—በረፋድ ሰዓት የምንሰግዳት ሁለት ረከዓ የዱሃ ሶላት ብቻዋን ለእነዚህ ሁሉ 360
መገጣጠሚያዎች እንደ ሙሉ ሰደቃና ምስጋና ሆና በቂ ሆና ትተካለች።
የመስገጃ ወቅቱም ፀሐይ ወጥታ ከፍ ካለችበት (ረፋድ) ጀምሮ እስከ ዙህር ጥቂት ደቂቃዎች እስኪቀረው ድረስ ነው። በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥተን ይህችን ውድ ሶላት በማዘውተር የሰውነታችንን ጤና ጸጋ እናመስግን!
--

❤1
Forwarded from TENBIHAT AASTU MUSLIM SISTERS ASSEMBLY (Admin)
✍ኢላሂ! አመፅኩህ እንጂ አልካድኩህም፤ ወንጀል ላይ ወደቅኩ እንጂ ከፍቅርህ ክልል አልወጣሁም። እግሮቼ ወደ ኃጢአት ሲራመዱ፣ልቤ ግን «አትሂድ»እያለች ትጮሃለች። አካሌ በስሜት ሲሸነፍ፣ መንፈሴ ግን በአንተ ናፍቆት እንደታመመች አንተ ታውቃለህ።
☝️ኢላሂ! ወንጀልን የተዳፈርኩት አንተን ንቄ፣ ቅጣትህን አቅልዬ፣ ወይም ስልጣንህን ተጋፍቼ አይደለም። ጌታዬ ሆይ! እኔ ማለት እኮ የሸይጧን ተንኮል እና የነፍስያዬን ግፊት መቋቋም ያቃተኝ ደካማ ፍጡር ነኝ።
...... ባንተ ፊት መቆም እያማረኝ፣ የዱኒያ ማዕበል ጠለፈኝ። ወደ ብርሃንህ መምጣት እየፈለግኩ፣ የጨለማ ገመድ ጎተተኝ። ጌታዬ...ሸይጧን አሸነፈኝ…ጌታዬ ነፍስያየ አሸነፈችኝ።
☝️ኢላሂ! ወንጀሌን አይተህ «ሂድ ከደጃፌ» ብትለኝ ወዴት እሄዳለሁ? ብትቀጣኝ ፍትህህ ነው፤ ብትምረኝም እዝነትህ ነው።
ኢላሂ…ወንጀለኛ ነኝ... ግን ያንተው ደካማ ባሪያ ነኝና ማረኝ!
©