177 subscribers
144 photos
7 videos
12 files
40 links
Students'pic
Download Telegram
ስለ ልጆች አስተዳደግ መሠረታዊ ነጥቦች

ልጅን በባህሪ ማከም አስቸጋሪ የሚያደርገው ብዙ ጊዜ በሽታው ወላጅ ላይ ስለሆነ ነው። ወላጆች ደግሞ ችግሩ የነሱ መሆኑን ተረድተው ለመቀበል ብዙ ጊዜ ይቸገራሉ።
የወላጅ ትልቁ ኃላፊነት ልጅን ጨዋና ጎበዝ ተማሪ አድርጎ ማሳደግ ብቻ ሳይሆን ብልጥና ጠንቃቃም ማድረግ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ልጆችን እየተሳሳቱ እንዲማሩ ዕድል መስጠት ያስፈልጋል።

በትክክል ያላደጉ ልጆች እንዴት ጥሩ ወላጅ ሊሆኑ ይችላሉ? ሠዎች ሙዚቃና ስፖርት፣ እጅ ሥራና እርሻ ከልጅነታቸው ሲማሩ፤ ወላጅነትንና የትዳር አጋርነትን ግን በግምትና በመላምት የሚገቡበት መሆኑ አስገራሚ ነው። አውሮፕላን አብርሮ በማያውቅ ፓይለት በሚበር አውሮፕላን ውስጥ ማንም አይሳፈርም። ብዙ ልጆች የሚወለዱት ግን ትዳርና ቤተሰብ እንዴት እንደሚመራ በማያውቁ አዲስ ለማጆች ባቋቋሙት ቤት ውስጥ ነው።

ሴት ልጅ ካባቷ ተወዳጅነትንና አፍቃሪነትን፤ ከእናቷም ወዳጅነትንና ወላጅነትን ትወርሳለች ይባላል።
የራሳቸውን ውድቀት ደብቀው በልጆቻቸው ስሕተት ላይ አለንጋ የሚመዙ ወላጆች የራሳቸውን ስህተት በልጆቻቸው ይደግማሉ።
•
#ምንጭ :- "የተቆለፈበት ቁልፍ" በዶ/ር ምህረት ደበበ

በቅንነት ሼር ያድርጉ
JOIN || Telegram.me/Dr_MehretDebebe
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Mega 111
Forwarded from Mega 111
Forwarded from Mega 111
Mr Esbalew first of all I would like to thanx for everything , her name is Abigia kassahun grade one A student if you can post in the group page,thanx
Forwarded from Mega 111
Work out to leave stress and so
Forwarded from Ayalew Lisanework
Contacts(1).vcf
6.8 KB
ነጻ የስነ-ልቦና ምክር በኮሮና ወቅት

ጭንቀትና ፍርሃት ውስጥ ለገቡ ወገኖቻችን። ከስነ-አእምሮ ስፔሻሊስቶች፣ ሬዝደንት ዶክተሮችና ሳይኮሎጂስቶች*

አሁን በተለይ የኮሮና ታማሚዎች ቁጥር ማሻቀብን ተከትሎ ፍርሃትና ጭንቀት በብዙ ሰው ላይ መፈጠሩ አይቀርም። የስነ-ልቦና ጫናው እስከ ዘላቂ የአእምሮ ህመም ሊያደርስ ስለሚችል በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ራስን ማጥፋት፣ አደገኛ ነገሮችን የማድረግ አዝማሚያዎች በጣም ጨምረዋል። ብቸኝነትና ሥራ ፈትነት በራሱ ትልቅ ተጽእኖ አለው። የቤት ውስጥ የሴት ልጅ ጥቃት መጨመሩን እየሰማን ነው።

እናም ማንኛውም አይነት ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ድብርትና የመሳሰሉት ችግሮች እየተከሰቱባችሁ ያላችሁ ወገኖቼ ከላይ ካሉት የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎች #ስልክ አንዱን መርጦ በመደወል ምክርና ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

መልእክቱን እያጋሩ ለሌሎች ወዳጆቾ ያድርሱ። #Share

Via፦ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ

@melkam_enaseb
Forwarded from Hana Takele
Forwarded from Hana Takele
Estifanos Ashenafi.
Forwarded from Hana Takele
አስተማሪ አጭር ታሪክ .!


አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡

ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።

ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡

ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡

ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡

እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን
በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡
Forwarded from ESUBALEW JEMAL
ስሜታዊውና ምክንያታዊው

ስሜታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት የሚሰጥ ድንገተኛ ምላሽ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ምላሽ ውጤት ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ በተቃራኒው ምክንያታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት በቂ ጊዜ ወስዶ፣ ውጤቱን አውጥቶና አውርዶ ውጤቱን ከጅማሬ አይቶ ምላሽ መስጠት ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ ስታስብ መነሻህ ስሜታዊነት ይሁን ወይስ አእምሮህ ያሰበበትና አጥጋቢ ምክንያት ያለው ተግባር ለይተህ የማወቅን ልምምድ አዳብር፡፡ ይህንን መለማመድ ዘወትር በስሜት እየተነዳህ ውሳኔና እርምጃ ውስጥ ከመግባትና ውጤቱ አፍራሽ ከሆነ ሁኔታ ይጠብቅሃል፡፡

ለምሳሌ፣ ከዚህ በፊት ለነበረህ ገጠመኝ የሰጠኸውን ምላሽ አስብና ያንን ምላሽ የሰጠህበትን መነሻ አሳብ አጢነው፡፡ “ያነሳሳኝ ስሜት ነው ወይስ አእምሮዬን ተጠቅሜ በቂ ምክንያት አግኝቼ ነው?” የሚል የማስታወሻ ጽሑፎችን በመጻፍ ልዩነቱን ማየት ትችላለህ፡፡ እንዲህ አይነት ልምምዶችን በመደጋገም በማድረግ ስሜታዊ ልማዶችህን ቀስ በቀስ ልትቀርፋቸው ትችላለህ፡፡ አንዲት ደቂቃ በመታገስ የእለቱን የጋለ ስሜት ማሳለፍ ሲችሉ የመጣላቸውን የስሜት ንዝረት በማስተናገድ የሌላውንና የራሳቸውን ታሪክ ያበላሹ ሰዎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡

በየእለት የሰው ለሰው ግንኙነት መካከል በሚነሱ ነገሮች ሁሉ የሚፈነዱና ቁጣ ቁጣ የሚላቸው ሰዎች፣ በትዳርና በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ በስሜት በተናገሩት ንግግር ከተቆሳሰሉ በኋላ ለመወያየት የሚሞክሩ ሰዎች፣ በማሕበራዊውና በሃገር ደረጃ አንድን ነገር ገና ከመስማታቸው ስለሁኔታው በሚገባ ሳያጠኑና የምክንያታዊነት ሂደት ሳይከተሉ ለጥፋት የሚነሳሱ ሰዎች ምክንያታዊ ሳይሆኑ ስሜታዊ ሰዎች ናቸው፡፡

ምክንያታዊነት የበሳሎች መንገድ ነው፡፡ ምክንያታዊነት የአዋቂዎች ምርጫ ነው፡፡ ምክንያታዊነት ሚዛናዊ በራስ የመተማመን ደረጃ የደረሱና ከፍ ያሉ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡

ስሜታዊነት ጠባብነት ነው፡፡ ስሜታዊነት አርቆ ማሰብ ያለመቻል ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የመሸነፍና አቅም የማጣት ምልክት ነው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ከስሜታዊነት ወደ ምክንያታዊነት የመሸጋገርን ጉዞ እንድትጀምርና የግልህን፣ የቤተሰብህንና የሕብረተሰቡን ሕይወት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የምትሰራ ብልህ ሰው እንድትሆን ላበረታታህ፡፡
Forwarded from Yodit Negatu
የህፃናት አእምሮን እንጠብቅ!

(በዶ/ር ቤዛዊት ፀጋዬ እና በተማሪ አማኑኤል አዳነ) በመተባበር የተዘጋጀ

በዚህ ሰዓት 'ህፃናት' ከመቼውም ግዜ በላይ 'የወላጆችን' ትኩረት ይፈልጋሉ። በየቀኑ የሚያደርጉትን እንደ ከት/ቤት መቅረት ጋር አእምሮአቸውን ለማስተካከል የወላጆች ሚና ከፍተኛ ነው።

1. ስለኮሮና ቫይረስም ሆነ ሌሎች እየተፈጠሩ ስላሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲያውቁ እነሱ በሚረዷቸው ቃላቶች ማስረዳት

2. የሚኖራቸውን ጭንቀት እና ፍርሃት የሚገልፁበት አዎንታዊ የሆነ መንገድ ማሳየት ለምሳሌ:- ስዕል ፣ ፅሁፍ/ግጥም ፣ በተለያዩ የህፃናት ጨዋታዎች

3. በስልክ እና በተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ላይ የሚያጠፉትን ሰዓት በመገደብ ፣ ከእርስዎ ጋር ግዜ የሚያሳልፉበትን ሁኔታ መፍጠር

4. እነሱም እንደአዋቂ ጓደኛቸውን ስለሚናፍቁ በስልክ ፣ በቪድዮ በማገናኘት እንዲያወሩ ማድረግ ያስፈልጋል

በእርግጠኝነት ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል
Mr.Esubalew wishes a wonderful and a happy father's day for all fathers.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😷😷ለወላጆች በሙሉ😷😷
👩‍👧‍👧
ትምህርት ቤታችን የ2013ዓ.ም የጀማሪ ተማሪዎችን ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን እድሜያቸው 3 ዓመት ከ6ወር እና ከዛ በላይ የሆኑትን ልጆች ማስመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
🏠 ት/ቤቱ
"አንድ የደስታ በር ሲዘጋ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል፤ እኛ ግን በአብዛኛው የተዘጋዉ በር ላይ ለረዥም ጊዜ ከማፍጠጣችን የተነሳ የተከፈተልንን አዲሱን የደስታ በር አናየውም።" #ሔለን_ኬለር

እውነት ነው!
አብዛኛው እኛ ሰዎች የምንባል ፍጡር ካለፈው ህይወታችን ጋር ጥብቅ የሆነ ቁርኝት አለን በዚህ ምክንያት ከፊት ለፊታቸው የሚመጡትን አዳዲስ ዕድሎች አናያቸውም ስለዚህ በቀላሉ እናጣችዋለን።

በሮች በተለያዩ ሆኔታ ሊዘጉ ይችላሉ:: ግን ማሰብ ያለብን ሁልጊዜም ያሰብናቸው በሮች ቢዘጉም ሌሎች እልፍ ያልተዘጉ በሮች ወይም አዳዲስ ዕድሎች መኖራቸውን ነው፡፡

ምድራችን በአጋጣሚዎች የተሞላች ናት ወዳጄ! እነሱን መመልከት ከቻልን ማለት ነው፡፡ ሁሌም የወጠነው እቅድ አይሠራም። አንዳንድ ጊዜ ኪሳራና ውድቀት እናስተናግዳለን፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በፍቅር ግንኙነታችን ውስጥ ችግሮች ይፈጠራሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰዎች ገንዘባችንን ወይም ስራችንን ይነጥቁናል ወይም ሌሎች መራር የሆነ የህይወት ስንክል ያገኘን ይሆናል።

ከእኒዚህ ክስተቶች አንዱ ሲከሰትብን በፍጥነት የተዘጋው በር ላይ ትኩረት እናደርጋለን ግዜያችንም እንደዋዛ እናባክነዋለን፤ ውጤቱም ብስጭት እና ሀዘን ብቻ ይሆናል ማለት ነው።

ልብ ማለት ያለብን ግን በእነዚህ ክስተቶች ላይ ምንም ስልጣን የሌለን መሆናችንን ነው። ከተዘጋው በር ላይ አይናችንን ነቅለን ወደሌላ ማማተር ይኖርብናል ምክንያቱም ከአሮጌው እና ከምናቀው ወደ አዲሱ (ወደ ማናቀው) ተሻገርን አዱሱን መሞከር ወደፊት አሻግሮ ማየቱ ጠቃሚ ነውና!

#መልካም_ቀን!