South Radio And Television Agency
3.84K subscribers
11.8K photos
44 videos
3 files
3.69K links
South Radio and Television Agency
Download Telegram
to view and join the conversation
የሀዲያ ዞን ምክር ቤት የቀረቡለትን የምክር ቤቱን ዋናና ምክትል አፈጉባዔዎች ዕጩ ሹመት በሙሉ ድምፅ አጸደቀ
በዚሁ መሠረት ወይዘሮ እቴነሽ ሙሉጌታ ዋና አፈጉባኤ፤ አቶ ሳሙኤል በየነ ደግሞ ምክትል አፈጉባኤ ሆነው እንዲሠሩ ሹመታቸውን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ሹመት የተሰጣቸው አፈጉባኤዎችም ቃለ መሃላ በመፈጸም ከቀድሞ አፈጉባኤ የሥራ ርክክብ አድርገዋል።
ዘጋቢ፡ ኤርጡሜ ዳንኤል - ከሆሳዕና ቅርንጫፍ
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ190ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአሜሪካን ሀገር ዴንቨር፤ አውሮራና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሽብርተኛው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ190 ሺ በላይ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።
ዴንቨር፤አውሮራና የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቤይ ኤርያ ቀጥሎ 2ኛውን ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።
አምባሳደሩ እንደገለጹት ኢትዮጵያውያኑ በሽብርተኛው ህወሃት በግፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ190 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
በአሜሪካ ከወገን ለወገን የሚደረገው ድጋፍ እየጨመረ መሆኑንና በሌሎች ቦታዎችም ድጋፍ ለማካሄድ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝም አምባሳደሩ መናገራቸውን ኢዜአ በዘገባው አመላክቷል።
ዝግጅቱ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት፣ ለአርቲስት ተስፋዬ ሲማ እና ለለጋሾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 34ኛ መደበኛ ምክር ቤት ጉባኤና የሴት አመራሮች ኮከስ ምስረታ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል

መንግስት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚደግፍ የመምህራን ማህበር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከተቋቋመ ጀምሮ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በርካታ ተግባራትን ሲያከናው የቆየ አንጋፋ ማህበር ነዉ።

ማህበሩ 34ኛውን መደበኛ ጉባኤውን በአርባምንጭ ከተማ ባካሔደበት ወቅት የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ በንቲ እንዳሉት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በሀገራችን የትምህርት ስራ በተፈለገው ልክ እንዲሔድ ከማድረግ ባሻገር በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የማይዘነጋ ተግባር ተፈፅሟል።

አክለውም በ34ኛው ጉባኤ በርካታና ጠቃሚ ውሳኔዎችን ተሳታፊዎች እንደሚያስተላልፉ እምነታቸውን መሆኑን ጠቁመዋል።

የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጥናፉ አሰፋ በበኩላቸው የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን በሙያው የሚተማመን ዜጋ በማፍራቱ በኩል መምህራን ሚናቸውን በበለጠ እንዲጫወቱ ጠይቀዋል።

ማህበሩ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት ያደረገውን የማይዘነጋ ድጋፍም በመጠቆም።

የጋሞ ዞን አስተዳደር ልዩ አማካሪና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ሽመልስ ታደሰ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/pcb.1351426798649916/1351425328650063/
የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ አቶ ታመነ ታምርሶን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ መረጠ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 7ተኛ አመት የሥራ ዘመን 17ተኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ታመነ ታምርሶን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ መርጧል፡፡
በጉባኤው የዋና እና ምክትል አፈ ጉባኤዎችና የዋና አስተዳዳሪ ሹመትን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ሀላፊነት ሹመቶችን አጽድቋል።
የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ተኛ ዙር 7ተኛ አመት የሥራ ዘመን 17ተኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ሙሉነህ በላቸውን ዋና አፈ ጉባኤ፤ ወ/ሮ አስቴር ሰነቀን ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ በመምረጥ እንዲሁም አቶ ታመነ ታሚርሶን የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ሆነው እንዲቀጥሉ በድጋሚ መርጧል።
አዲስ የተመረጡ አፈ ጉባኤዎች የሰራ ርክብክብ አድርገዋል።
ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ታመነ ታሚርሶ በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች በኃላፊነት እዲያገለግሉ የተመረጡ ካቢኔ አባላትን ያቀረቡ ሲሆን ሀሳብ አስተያየቶች በምክር ቤቱ አባላት ተሰጥቶ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
የተመረጡ አመራሮች የመረጣቸውን ህዝብ በመካስ የሚያገለግሉበት ሊሆን እንደሚገባው ያሳሰቡት አቶ ታመነ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ወደ አመራርነት ማምጣት እና የሴቶችን ተሳትፎ ማጠናከር አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ሀላፊነት በመሠጠቱ መደሰታቸውን የገለጹት የጉባኤው ተሳታፊዎች እና የተመረጡ አመራሮች በቀጣይ ሌብነትን ሙሉ በሙሉ ከማጥፋት እና መልካም አስተዳር ከማስፈን አኳያ ሰፊ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ አወል ከድር - ከሳውላ ቅርንጫፍ
የሳይበር ጥቃት ወንጀል

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሳይበር ወንጀል ማለት የኮምፕዩተር ወንጀል ማለት ነው፡፡

ሳይበር ለሚለው ቃል የተለያዩ መዝገበ ቃላት በሰጡት ትርጉም ኮምፕዩተር እና የኮምፕዩተር ኔትዎርክ ማለት ነው፡፡

የሳይበር ጥቃት በሳይበር ክልል የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን የሳይበር ክልል ማለት ትስስር ያለው አለማቀፍ ኔትዎርክ ነው፡፡ የሳይበር ጥቃት ኮምፕዩተር፣ የኮምፕዩተር ስርአት ወይም የኮምፕዩተር ኔትዎርክን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማግኘት ሲሆን አላማውም ጉዳት ማድረስ ነው፡፡

የሚያደርሰውም ጉዳት ብልሽት፣ ማዛባት፣ ማስወገድ ወይም ኮምፑተሩን በመለወጥ ማጥፋት ማገድ ሲሆን በስርአት ውስጥ ያለ መረጃን ማዛባት ወይም መስረቅን ይጨምራል፡፡

የሳይበር ጥቃት አድራሾች የሳይበር ጥቃት የማጥቃት እስትራቴጂ ባለው በማንኛውም ሰው ወይም ቡድን ከየትኛውም ቦታ ሊሰነዘር ይችላል፡፡ ጥቃቱን የሚፈጽሙ ሰዎች የሳይበር ወንጀለኞች ወይም በተለምዶ ሃከሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

የሳይበር ጥቃት አድራሾች በመንግስታት በሚደገፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልሂቃን ቡድኖች እና መንግስትን የሚቃወሙ ሰዎች የሚፈጽሙት ነው፡፡

የመስኩ ባለሞያዎችም nation-state attackers እና hacktivists ሲሉ ይጠሯቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ከራሱ ከውስጠ ድርጅቱ ሰራተኞች በኩል የሚፈጸም የሳይበር ጥቃትም አለ፡፡ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/pcb.1351443041981625/1351442225315040/
“አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የሚያደላ አቋም ይዘዋል” - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የሚያደላ አቋም መያዛቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት፣መንግስታትና ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተዛባ አመለካከት መያዛቸውን ጠቅሰዋል።
ከአውሮፓ ህብረትም ለአሸባሪው ቡድን የሚያደላ ግልፅ አቋም የሚያራምዱ መኖራቸውን የገለጹት አምባሳደር ዲና፤ የተዛባና አድሏዊ አቋማቸውን ሆን ብለው የግል ፍላጎትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ መሆኑንም ተናግረዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ጫናቸውን ከመፍራት ይልቅ በጋራ ሆነው ለአገራቸው ህልውና መቆም አለባቸው ነው ያሉት።
አምባሳደር ዲና አክልውም የግብጽና ሱዳን ሰሞኑን እያካሄዱት ያለው ወታደራዊ ልምምድ ሉአላዊ መብታቸው መሆኑንም ጠቁመው፤ "ግብጽና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ብቻ ሳይሆን መዋሃድም ይችላሉ፤ ቀዩ መስመር በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ከመጡ ብቻ ነው" ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
''ህዝባችን ታገለግሉኛላችሁ ብሎ ድምጹን ብቻ ሳይሆን ተስፋም ጭምር ጥሎብናል'' - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ''ህዝባችን ታገለግሉኛላችሁ ብሎ ድምጹን ብቻ ሳይሆን ተስፋም ጭምር ጥሎብናል ''ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች ይህን ያሉት በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ እየተካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው።

"ለአዲስ ምዕራፍ ተልዕኮ ዝግጁ ነን" በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የውይይት መድረክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጨምሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በቅርቡ የተሾሙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በለውጥ ሂደት በርካታ ሳንካዎች አሉ ፤እነዚህን ሳንካዎች በጥንቃቄ በማለፍ ህዝብ የጣለብንን ሀላፊነት ለመወጣት ሁሉም አመራር በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ መስራት እንደሚገባው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

"የ6ኛው ክልላዊ እና ሀገራዊ ምርጫ አፈጻጸም ስኬቶች እና ተግዳሮቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " በሚል በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ ሙሁራን የተደረገ ዳሰሳዊ ጥናት ላይ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ዘገባ አመልክቷል።
የተከፈተብንን ጥቃት ለመመከት መፍትሄው የተደራጀ ንቅናቄ ነው! - የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተከፈተብንን ጥቃት ለመመከት መፍትሄው የተደራጀ ንቅናቄ ነው! ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫውም የሚከተለው ነው፡፡
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አሸባሪው የጁንታ ቡድን አለኝ የሚለውን ሃይል በማሰባሰብ በአፋርና በአማራ ክልሎች ባሉት ግንባሮች መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል። በዚህ ጥቃት በርካታ ንጹሃን ዜጎችን ገድሏል፤ ንብረት ዘርፏል፤ የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጋዝ አርከፍክፎ አቃጥሏል፤ በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ አድርጓል። የተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ እንዳይደርሳቸው አድርጓል። የሃሰት ፕሮፖጋንዳንም እንደ ዋነኛ መሳሪያው በመጠቀም ላይ ይገኛል።

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የአማራና አፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎች በመንጋ የመጣውን ጠላት ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመሆን በሚያኮራ መልኩ እየመከቱ ይገኛሉ። በተለይም ዘራፊው ቡድን በውጫሌ፣ ተሁለደሬ፣ ወረባቦ ደላንታና ጭፍራ ግንባሮች ጦርነት የከፈተ ቢሆንም የጸጥታ ሃይሉና የህብረተሰቡ የጋራ ጥምር ሃይል ይህንን ወራሪ ሃይልና ሰርጎ ገቦችን በጀግንነት እየመከተ ይገኛል። ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/a.402686300190642/1351487221977207/
የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በማዘመን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በማዘመን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጥሪ አቀረበ።

ጽ/ቤቱ የ2013 ዓመታዊ አፈጻጸምና የ2014 ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ምክክር እያደረገ ነዉ።
ጉባኤዉን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ግርማ በዞኑ የሚገኘዉን ሀብት በተገቢዉ በመሰብሰብ የአካባቢዉን ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ለማረጋገጥ መስራት ይገባል ብለዋል።

በተለይም ይህን ተግባር ስኬታማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ መታገዝና ቅንጅታዊ ስራን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት በዚሁ ዘርፍ ጠንካራ ትስስር እንዲኖራቸዉ እንደሚሰራም ተናግረዋል።ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/pcb.1351493848643211/1351493401976589/
የግብርና ሚኒስቴር የአዲስ ፕሮጄክት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) በግብርና ሚኒስቴር የአፈር ለምነት ዳይሬክቶሬት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያን ከተፈጥሮ ማዳበሪያ ጋር አጣምሮ በመስራት የአፈርን ለምነት በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን መጨመር የሚያስችል አላማን የያዘ ፕሮሳይለንስ” ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡

የፕሮጅክቱ አላማ አነስተኛ ማሣ ያላቸውን አርሶ አደሮች ሰው ሰራሽ ማዳበሪያን ከተፈጥሮ ማዳበሪያ ጋር አጣምረው በመጠቀም የአፈርን ለምነት በማሳደግ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ከማድረግ ጎን ለጎን ጥምር ግብርናን እንዲጠቀሙ እና ምርጥ ዘርን በማቅረብ እራሳቸውን በምግብ እንዲችሉ የሚያደረግ እንደሆነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

አዲሱ ፕሮጀክት በገንዘብ የሚደገፈው በአውሮፓ ህብረት ከጀርመን ልማት ትብብር ጋር በጋራ በመሆን በአምስት ክልሎች፡- በኦሮምያ፣ አማራ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ሲዳማ እና በትግራይ ክልል የሚተገበር እንደሚሆነ ተገልጿል፡፡
ደቡብ ኦሞ ዞን፣ አጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሰላምን በማስጠበቅ የህዝብ ለህዝብ ትስስር እና የጋራ ልማት ተጠቃሚነት ዙሪያ ይበልጥ እንደሚሰሩ አስታወቁ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) ደቡብ ኦሞ ዞን፣ አጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሰላምን በማስጠበቅ የህዝብ ለህዝብ ትስስር እና የጋራ ልማት ተጠቃሚነትን ይበልጥ አጠናክረው ለማስቀጠል እንደሚሠሩ የየዞኑ አስተዳዳሪዎች ገለጹ።

ሰሞኑን በህዝባዊ ውይይት ደቡብ ኦሞ ዞን የተገኙት የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደገለፁት የኮንሶ ህዝብና የደቡብ ኦሞ ማህብረሰብ ለዘመናት ተቻችለው የጋራ እሴቶቻቸውን ሲለዋወጡ የቆዩ ህዝቦች ናቸው።

ሁለቱም ዞኖች ስለሠላም በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውንም አስተዳዳሪው አንስተው አጎራባች ዞኖች እንደመሆናቸው መጠን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ በመቆም በወንድማማችነት መንፈስ ከትላንቱ ይልቅ አንድነቱ እንዲጠናከር እንደሚሠራ አቶ ዳዊት ገልፀዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አረጋ በበኩላቸው የደቡብ ኦሞ ዞን ህዝብ ከኮንሶ ህዝብ ጋር አብሮ የሚኖርና በአቃፊነት የሚታወቅ ነው ብለዋል።

በድንበር የሚገናኙና የህዝብ ለህዝብ ትስስሩ የጠበቀ በመሆኑ ይህንን አስተዳደሩ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

የአሌ ልዩ ወረዳ ለደቡብ ኦሞ ዞን አጎራባች እንደመሆኑ መጠን ልዩ ወረዳው በድንበር አካባቢ ለዘመናት አንዱ ከሌላው ህዝብ ጋር ግንኙነታቸውን ሲያሳልጡ መቆየታቸውም ተመላክቷል።

የጋራ ብልፅግና እንዲረጋገጥም ሁሉም አመራሮች አብረው እንደሚሠሩም አስታውቀዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አበራ - ከጂንካ ቅርንጫፍ
የጤና ሚኒስቴር በአፋር ክልል በአሸባሪው በዞን ህወሓት ጉዳት ላደረሰባቸው ጤና ተቋማት የህክምና መርጃ መሳሪያ ዛሬ ድጋፍ አደረገ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጤና ሚኒስቴር በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ጤና ተቋማት ስራ ማስጀመሪያ የሚውል 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የህክምና መርጃ መሳሪያ ድጋፍ አደረገ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተገኝተው ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የህክምና መርጃ መሳሪያዎቹን አስረክበዋል።

“በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በመደጋገፍና በአንድነት ማለፍ ይገባናል” ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

“በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በመደጋገፍና በአንድነት ማለፍ ይገባል” ያሉት ሚኒስትሯ፤ ለክልሉ የተሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።

ጤና ሚኒስቴር የህክምና መረጃ ቁሳቁስ ድጋፋ ያደረገው በክልሉ በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው አምስት የጤና ተቋማት ስራ ለማስጀመር መሆኑ ነው የተገለጸው።

የሚኒስቴሩ ድጋፍ የህክምና ተቋማቱ ወደ ስራ እንዲገቡና ድንገተኛና መደበኛ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ እገዛ እንደሚያደርግ ዶክተር ሊያ ጠቁመዋል።ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/pcb.1351514601974469/1351513691974560/
ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር በየዓመቱ 25ሺህ ወጣቶች ሥልጠና ይወስዳሉ


ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ፣ም (ደሬቴድ) በኢትዮጵያ ውጤት ተኮር ለሆነው ዘላቂ የሠላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት እንዲሁም ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ በየዓመቱ ለ25ሺህ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ያተኮረ ሥልጠና እንደሚሰጥ የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ።


ሥልጠናው አገሪቷ ካለችበት አዎንታዊ የሠላም ግንባታ ሂደት አንጻር ትልቅ ውጤት ያመጣል ተብሎ ይታሰባል።ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/a.402686300190642/1351528028639793/
ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ነገ እድሜያቸው ከ 5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት መሰጠት ይጀምራል


ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ነገ እድሜያቸው ከ 5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት መሰጠት ይጀምራል፡፡


ህጻናቱ ከዚህ ቀደም ቢከተቡም ባይከተቡም ክትባቱ ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት ቤት ለቤት በሚደረግ ጉብኝት ይሰጣል፡፡


የፖሊዮ ቫይረስ የህጻናትን እጅና እግር የሚያሽመደምድ ለሽባነት ብሎም ለሞት የሚዳርግ ተላላፊ በሽታ በመሆኑ ይህንን ጉዳት በዘላቂነት ለመከላከል ክትባቱ አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/a.402686300190642/1351553621970567/
የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያቤት የህጻናት ማቆያ ማዕከል አስመረቀ


ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያቤት የህጻናት ማቆያ ማዕከል አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡


የህጻናት ማቆያ ማዕከል መገንባት ለተቋም ውጤታማነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ እና ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡


የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ከበደ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግሯ በተቋማችን ሴቶች ያለባቸውን ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት የተሻለ የስራ አካባቢን ለመፍጠርና ለልጆቻቸውም ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ ማቆያ ለመገንባት ቀና የሆነ አመራር በመኖሩ በዛሬው ዕለት የተመለከታችሁትን የህጻናት ማቆያ ለመስራት ችለናል ማለታቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በትስስረ ገፁ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡


ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው የህጻናት ማቆያ ማዕከላት የሴት ሰራተኞችንና የህጻናትን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ ባሻገር ሴት ሰራተኞች በተሰማሩበት የስራ መስክ ይበልጥ ውጤታማና ተወዳዳሪ በመሆን ሃገራቸውን እንዲያበለጽጉ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
የኢፌዲሪ አየር ኃይል ሴት የሰራዊት አባላት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ማሟላት ላልቻሉ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ)የኢፌዲሪ አየር ኃይል ሴት የሰራዊት አባላት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ማሟላት ላልቻሉ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ የተደረገው በተቋሙ ለሚሰሩና በአንስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የሲቪል ሰራተኛ ተማሪ ልጆች ነው።

የአየር ኃይል ኢንዶክትርኔሽን ዳይሪክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ተሾመ በዳዳ "አየር ኃይል የተሰጠውን ግዳጅና ተልዕኮ በታላቅ ጀግንነት ከመፈፀም ባሻገር ከራስ በፊት ለህዝብ የሚለውን ወርቃማ እሴቱን በመላበስ ለህዝባችን ፈጥኖ ደራሽ መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ጠቁመው ፣ ሴት የሰራዊት አባላቱም ያደረጉት ድጋፍ የዚህ ማሳያ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የአየር ኃይል ሴቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ኮ/ል አገሬ ዘመነ በበኩላቸው ፣ "ሴት የሰራዊት አባላት በግንባር ተሰልፈው ግዳጃቸውን በላቀ ብቃት ከመወጣታቸው በተጨማሪ የህብረተሰባችንን ችግሮች በመጋራት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ እንደመጡ ጠቅሰው የዛሬው ድጋፍም የሰራዊት አባላቱ በራሳቸው ተነሳሽነት ያደረጉት በጎ ተግባር መሆኑን መግለጻቸው ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ድረገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በሚዲያ ተቋማት ላይ የሚሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸዉ ተገለጸ

በሀገራችን ባሉ የሚዲያ ተቋማት ላይ የሚሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸዉ ተገልጿል።

አገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን አስመልክቶ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከትላንት ጀምሮ ከሚዲያ ተቋማት ለመጡ ለድረ-ገጽ፣ ለማህበራዊ ሚዲያ እና ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሙያተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የሳይበር ደህንነት ትንተና ባለሞያ አቶ ጋሹ አባተ በዛሬው ዕለት ለተገኙት ሰልጣኞች በሳይበርና የሳይበር ደህንነት፣ የሚዲያ ተቋማት ላይ ስለሚከሰቱ የሳይበር ጥቃቶች ፣ አጋላጭ መንገዶች እንዲሁም የመከላከያ ዘዴዎች ላይ ያተኮ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡
ተቋሙ የሚዲያ ተቋማት ላይ ትኩረት ያረገ ስልጠና መዘጋጀቱ በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚዲያ ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የተነሳ ስልጠናው መዘጋጀቱን አቶ ጋሹ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው የተካፈሉ የዘርፉ ሙያተኞች ሳይበር እና የሚዲያ ስራ የማይነጣጠሉ በመሆናቸው በሳይበር ደህንነት እና በሚዲያ ተጋላጭነት ዙሪያ የተሰጣቸው ስልጠና በዘርፉ የሚኖራቸውን የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ለመቀነስ አይነተኛ አስተዋጾ እንዳለው መገለጹን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮ በባይደዋ የተሰማራው የሴክተር ሶስት አሚሶም እና ድጋፍ ሰጭ የሰራዊት አባላት በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ለጅግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡


ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) በርክክቡ ወቅት የተገኙት ኮሎኔል ጋታው የጠዳው የሴክተር ሶስት ዘመቻ ሃላፊ 45 ሺ 670 ዶላር እና 97 ሺ 200 የኢትዮጵያ ብር በድምሩ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ በመከላከያ ሰራዊቱ የድጋፍ ማሰባሰቢያ አካውንት ገቢ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡


በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮ የተሰጣቸውን ግዳጅ ከመወጣት ጎን ለጎን ለህልውና ዘመቻው መሳካት ስላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ለመስጠት መዘጋጀቱን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ለመስጠት መዘጋጀቱን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ከጥቅምት 12 እስከ 15 ድረስ የሚቆየውን የፖሊዮ ክትባት ዘመቻን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ዋና ሀላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናትን ለመከተብ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆናቸው ህጻናት ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም ይህን ክትባት ይወስዳሉ ብለዋል።ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/pcb.1351595505299712/1351594908633105/
ከመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት የተሰጠ መግለጫ


ጠላት በመረጠው የውጊያ ስልት ከፍተኛ ኪሳራ እያስተናገደ ይገኛል

አሸባሪው ህወሃት የትግራይን ህዝብ ከህፃን እስከ አዋቂ ለወረራ በማንቀሳቀስ ያለ የሌለ ኃይሉን በወሎ መርሳ አቅጣጫና በሃራ ጭፍራ በኩል አሰማርቷል።

ሃገር የማፍረስ ህልሙን የገበሬ አዝመራን አጭዶ ከመውሰድና ንብረት ከመዝረፍ እንዲሁም ከማውደም በተጨማሪ ፣" ከፍተኛ የሰው ብዛትና የሃገር ሃብት አለበት" ብሎ በመረጠው የሐይቅ አቅጣጫን ተከትሎ ለመግባት በሁሉም ግንባር ኃይሉን አሰባስቦ ውጊያ ከፍቷል።

ጠላት ህዝቡን ያሰለፈው በዋናነት በሶስት አሰላለፍ ከፍሎ ነው። የመጀመሪያው ፣ በግንባር የሚዋጋና በሰው ኃይል የበላይነት ወስዶ ፍላጎቱን ለማሳካት እየጣረ ሲሆን ፤ ሁለተኛው ፣ የቅርብ ድጋፍ ሰጭ ሆኖ የሚተካ፣ ቁስለኛ የሚያነሳ፣ የህዝብ ሃብት ዘርፎ የሚያሸሽ እና የሚያወድም ሆኖ የተደራጀ ነው። ሶስተኛው ፣ ለቀጣይ ግዳጅ ተዘጋጅቶ የሚጠብቅ አድርጎ ህዝቡን የቡድን ፍላጎቱ ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንዲሆን ወደ ጦርነት ማግዶታል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/a.402686300190642/1351605381965391/