St.Paul's Hospital Millennium Medical College
18.7K subscribers
1.95K photos
23 videos
12 files
458 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Social distancing & hand washing at a clinic in Kenya: two of the most effective ways to stop the spread of #COVID19.
If you are pregnant, you can help protect yourself against COVID-19 by:

✔️Washing your hands frequently
✔️Keeping space between yourself and others
✔️Avoiding touching your eyes, nose and mouth
✔️Practicing respiratory hygiene
የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) የተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
Join new WHO interactive chatbot on Viber to get accurate information about COVID-19 in multiple languages: https://vb.me/82e535
የዱከም ነዋሪ የሆኑት የ65 ዓመት ሴት በሌላ ተጓዳኝ ሕመም ምክንያት በሆስፒታላችን ለአንድ ቀን ቆይተው ነበር፡፡ይሁን እንጂ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት በማሳየታቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ አንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚዋ በአሁኑ ሰዓት በኮተቤ ኤካ ሆሰፒታል ቀጣይ ሕክምናቸውን አንዲከታተሉ ተልከዋል፡፡
ለታማሚዋ የሕክምና አገልግሎትን ሲሰጡ ከነበሩ በርካታ የጤና ባለሙያዎች መካከል ፡ በወቅቱ አስፈለጊውን አልባሳት (PPE) አልተጠቀምንም ወይም አጠቃቀማችን በቂ አይደለም ያሉ ሰባት ባለሙያዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ባለሙያዎች መካከል ሁለቱ ታማሚዋን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡
እኝሁ ሴት በ ዛሬው የጤና ጥበቃ ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ የተገለጹት 44ኛዋ ታማሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
Please checkout our new film " Pregnancy and COVID 19"
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ተግባራት
**********

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ተግባራት ይፋ ሆናዋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች ያሉት ጉዳዮች የተከለከሉ መሆናቸውን በአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ላይ ተገልጿል።

1. ለሀይማኖታዊ ወይም ማህበራዊ አላማ፣ ለመንግስታዊ ወይም ፖለቲካዊ ስራ ወይም ሌላ መሰል አላማ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግስት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና በማናቸውም ቦታ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው፤

2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ባሉ ንዑሳን ኮሚቴዎች ስብሰባ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

3. ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ክልክል ነው፣

4. ማንኛውም ሀገር-አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በማንኛውም ጊዜ ከተሸከርካሪው ወንበር ብዛት 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤

5. ማናቸውም የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ታክሲ፣ አውቶቡስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤

6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ሾፌሩን ሳይጨምር ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤

7. የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከዚህ በፊት ሲጭን ከነበረው አቅሙ 25% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤

8. የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ከወንበር ቁጥሩ 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ ተከለከለ ነው፤

9. ማንኛውንም ታራሚን ወይም ተጠርጣሪን በአካል በመገኘት በማረሚያ ቤት ወይም ፖሊስ ጣቢያ መጠየቅ ክልክል ነው፤ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በፖሊስ ጣቢያ ለሚገኝ ተጠርጣሪ፣ ከተጠርጣሪው ጋር በአካል ሳይገናኙ ስንቅ ማድረስን አይከለክልም፤

10. በጭፈራ ቤቶችና በመጠጥ ቤቶች ማናቸውንም የመጠጥና መዝናኛ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤

11. በማናቸውም ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤

12. የሲኒማ፣ ቲያትርና በአንድ ቦታ ብዙ ሰዎችን የሚያሰባስቡ መሰል የመዝናኛ አገልግሎቶችን መስጠት ክልክል ነው፣

13. ሆቴሎች፣ ካፌዎች ወይም ምግብ ቤቶች አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሶስት ሰው በላይ እንዲቀመጥ ማድረግ የተከለከለ ሲሆን ተገልጋዮች በሚቀመጡባቸው ጠረጴዛዎቹ መካከል ያለው ርቀትም ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤ ሆኖም ተገልጋዮች የሚገለገሉት በጠረጴዛ ላይ ካልሆነ በመካከላቸው የሚኖረው ርቀት ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤በድንበር አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች በኩል ወደ ሀገር ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጪ መውጣት የተከለከለ ነው፣

14. .በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በኬላዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፤

15. ለዚሁ አላማ ከተቋቋመው ኮሚቴ ወይም በተመሳሳይ መልኩ በክልሎች ደረጃ በሚቋቋሙ ንዑስ ኮሚቴዎች ወይም ተመሳሳይ አደረጃጀቶች አማካኝነት ፈቃድ ከተሰጠው ሰው ውጪ በማንኛውም የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣን ወይም ባለሙያ ኮቪድ-19ኝን በተመለከተ የፌዴራል ወይም የክልል መንግስትን ወክሎ መግለጫ መስጠት የተከለከለ ነው፣

16. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11 የተመለከተው ክልከላ ቫይረሱን አስመልክቶ የወጡ ህጎችን በተመለከተ የሚደረግ የሙያ ትንተናን ወይም በህክምና ባለሙያዎች የሚደረጉ ማብራሪያዎችን ወይም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየእለቱ የሚሰጡ መረጃዎችን አይመለከትም፤

17. ማንኛውም የመኖሪያም ሆነ የንግድ ድርጅት ቤት አከራዮች በተከራዩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ ወይም የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ ነው፤

18. ማናቸውም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሰራተኞችን የሚያስተዳደሩ የግል ድርጅቶች በስራቸው ያሉ ሰራተኞችን የስራ ውል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው ስርአት ውጪ ማቋረጥ የተከለከለ ነው፣

19. ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋም በትምህርት ቤት ወይም በሌላ ማናቸውም ቦታ አስተማሪና ተማሪዎች በአካል ተገናኝተው መማር ማስተማር ስራ እንዲሰራ ማድረግ ወይም ማስተማር የተከለከለ ነው፤

20. ማንኛውም ሁለትና ከዚያ በላይ ሰው በመሆን የሚጫወቱባቸውን ጨዋታዎች፣ ማጫወትም ሆነ መጫወት የተከለከለ ነው፤

21. ማናቸውንም የስፖርት ውድድሮች ወይም የቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተከለከለ ነው፤

22. የህፃናት ማጫዎቻ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፣

23. ማንኛውም ሰው የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከሁለት የአዋቂ እርምጃዎ በታች በሆነ ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ የተከለከለ ነው፡፡

24. መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንደ መብራት ሀይል፣ ከውሃ አቅርቦት ጋር ግንኙነት ያለው ስራ የሚሰሩ ተቋማት ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የህክምና ተቋማት፣ ባንኮች፣ ከምግብ አቅርቦት ጋር ግንኙት ያለው ስራ የሚሰሩ ተቋማት፣ የጽዳት ስራዋችን የሚሰሩ ተቋማትና ባለሙያዎች፣ ከድንገተኛ ና የእሳት አደጋ መከላከል ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ ተቋማት፣ ከጥበቃና ደህንነት ጋር የተያያዙ ድርጅቶች እና ተቋማት በማንኛውም መልኩ ስራን አለመስራተ ማቋረጥ ማስተጓጎል እና መሰል ተግባራትን መፈጸም የተከለከለ ነው፤

25. የደረቅና የፈሳሽ ጭነት አገልግሎትን፣ የምርት ስራን፣ የእርሻ ስራን ወይም የግንባታ ስራን ማቋረጥ፣ ማሰተጓጎል ወይም አለመስራት የተከለከለ ነው፣

26. ኮቪድ-19ኝና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ማህበረሰቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርግና በማህበረሰቡ ላይ ስነ-ልቦናዊ ጫና የሚፈጥር ማናቸውንም መረጃ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ህክምና መመሪያ /The NATIONAL COMPREHENSIVE #COVID19 MANAGEMENT HANDBOOK / ታትሞ ለንባብ ቀርቧል::

ይህም ወረርሺኙን በመቆጣጠር ሂደት ለፖሊሲ አውጪዎች ፣ ለህክምና እና ለህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች በሁሉም ደረጃ የሚያገለግል መመሪያ ነው::

መመሪያውን ከስር ባለው ሊንክ ማግኘት ይችላሉ::http://www.moh.gov.et/ejcc/am/NATIONAL%20COMPREHENSIVE%20COVID19%20MANAGEMENT%20HANDBOOK
WHO Health Alert on COVID-19 is now active on Messenger 👉 messenger.com/t/WHO
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።
St. Paul’s Hospital Millennium Medical College is converting the city main Convention Center, The Addis Ababa Millennium hall, into a 1,000 bed hospital.
The Addis Ababa Millennium hall will become SPHMMC’s an emergency hospital treating coronavirus patients and is the first biggest facility in the country.
The Millennium hall sprawls across 87,000 sqm of landscape with an indoor space of 19,000 sqm offering huge expo hall stretched up to 5000sqm.
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኮቪድ-19 ህመምተኞች እንዲሆን በሚሌኒየም አዳራሽ የተዘጋጀውን የህክምና ማዕከል ጎበኙ። በጉብኝታቸው ወቅት እንደተገለጸው አዳራሹ አንድ ሺህ አልጋዎችን የሚይዝና በትልቅ ሆስፒታል ደረጃ ዝግጁ የሚሆን ነው፡፡ የህክምና ማዕከሉ በአጠቃላይ 1 ሺህ ሰራተኞች ይኖሩታል፡
ዶ/ር አብርሃም ፍሳሐዬ “The Art of living Dreams.” (Story of becoming an OB-GYN) በሚል ዛሬ መጽሐፋቸውን አስመርቀዋል ፡፡ ከኤርትራ የአጠቃላይ የሕክምና ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ በስደት መጥተው የማሕፀንና ጽንስ ትምህርት የስፔሻሊስት ትምህርታቸውን እንዴት እንዳጠናቀቁና ችግርን አልፈው ሕልማቸውን ማሣካት እንደቻሉ በመጽሐፋቸው ገልፀዋል ፡፡ በሕይወት ታሪካቸው ላይ ተመስርቶ የተጻፈው የሐኪሙ መጽሐፍ ዋና ጭብጡ ዓላማን ዳር ለማድረስ የተከፈለ መስዋእትነትን ነው፡፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ 146 ገጾች ያሉት ነው ፡፡
ዶር አብርሃም ማህፀንና ጽንስ ሕክምና ስፔሻሊስት የተመረቁ ሲሆን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው፡፡