St.Paul's Hospital Millennium Medical College
18.7K subscribers
1.96K photos
23 videos
12 files
458 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
World Prematurity Day
የዓለም የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ
የሚወለዱ ሕፃናት ቀን
የዓለም የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ሕፃናት ቀን መሠረታዊ እውነታዎች
ህዳር 8 የዓለም የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ህጻናት ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በዓለም ደረጃ በየአመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህጻናትን በተመለከቱ ጉዳዩች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል፡፡
የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ ማለት ምን ማለት ነው?
አንድ ህፃን የእርግዝና 37ኛ ሣምንት ከመጠናቀቁ በፊት ከተወለደ የመወለጃ ቀኑ ሳይደርስ ተወልዷል ይባላል፡፡
የችግሩ ስፋት ምን ያህል አሳሳቢ ነው?
በዓለም፡
• በየዓመቱ ከ 15 ሚሊየን በላይ ህፃናት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ ይወለዳሉ፡፡
• በየዓመቱ ከ 1 ሚሊየን በላይ የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት ይሞታሉ፡፡
• የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ ለተለያዩ የአካልና የአዕምሮ ጉዳቶች ይዳርጋል፡፡
• የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ እድሜያቸው ከ 1 ወር በታች ለሆኑ ህፃናት ቁጥር አንድ ሞት ምክንያት ነው፡፡
• በዓለም ላይ የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ እየጨመረ ነው፡፡
• ዝቅተኛ የገቢ መጠን ባላቸው ሀገራት ውስጥ የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ከተወለዱት ጋር ሲነፃፀር የመሞት እድላቸው 10 እጥፍ ነው፡፡
ኢትዮጵያ፡
• በዓመት 320,300 ህፃናት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ ይወለዳሉ::
• ከ10 በሕይወት ከሚወለዱ ህፃናት አንዱ የመወለጃ ቀኑ ሳይደርስ ይወለዳል፡፡
• የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ እድሚያቸው ከ 1 ወር በታች ለሆኑ ህፃናት ቁጥር አንድ የሞት ምክንያት ነው፡፡
ምክንያቱስ?
የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ በአብዛኛው ምክንያቱ በውል አይታወቅም፡፡ ብዙ መውለድ፣ የስኳር ህመም፣ በቤት ውስጥ በከሰል ወይም በእንጨት ማብሰል፣ የደም ግፊት እና ሌሎች ህመሞች አጋላጭ ሁኔታዎች ናቸው ተብሎ ይታመናል፡፡
መከላከል ይቻላልን?
የቤተሰብ እቅድ መጠቀም፣ ሴቶችን ማብቃት እና የቅድመ-ወሊድ ክትትል ማድረግ የመወለጃ ቀን ሳይደርስ የመወለድን እድል ይቀንሳል::
የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናትን ሊያጋጥሙአቸው የሚችሉ ዋና ዋና ችግሮች ምን ምን ናቸው? አስፈላጊው እንክብካቤ በወቅቱ ካልተደረገላቸው የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት ለሚከተሉት ችግሮች ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡
የሰውነት ሙቀት፡ የሰውነታቸውን ሙቀት መጠበቅ ስለማይችሉ በቀላሉ በቅዝቃዜ ምክንያት ለህልፈተ- ሕይወት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ መጥባት፡ ጡት ለመጥባት ሊቸገሩ ስለሚችሉ ተጨማሪ እገዛ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ የእናት ጡት ወተትን አልቦ በስኒ በማጠጣት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡ ህመም፡ በአብዛኛው በሽታን የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ በህመም ይጠቃሉ፡፡ አዕምሮ፡ በቀለሉ የአዕምሮ ጉዳት ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ አይን፡ የአይን ብርሃንን የማጣት ጉዳት ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ የመተንፈሻ አካላት ችግር፡ የሳንባ አለመዳበርን ተከትሎ የሚከሰት የአተነፋፈስ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ሞት እና ጉዳትን መቀነስ ይቻላል? አዎ! ቀላልና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ በማይጠይቅ ህክምና እና እንክብካቤ 75 በመቶ የመወለጃ ቀን ሳይደርስ ከመወለድ ጋር የተያያዘ የህጸናት ሞትን ማስቀረት ይቻላል ፡፡
ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተከሉትን ያካትታሉ፡፡
• በጤና ተቋማት መውለድ፣
• የቅድመ ወሊድ እና የድህረ ወሊድ ክትትል ማድረግ፣
• ለጨቅላ ህጻናት ህመሞች በአፋጣኝ ህክምና መሻት፣
• በጤና ባለሙያ የታዘዘን ህክምና እና እንክብካቤ በአግባቡ መተግበር፡፡

የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህጻናት በወደፊት ሕይወታቸው ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ?
አዎ ! ምክንያቱም እነ አይዘክ ኒውተን (የሂሳብ፤ የፊዚክስ እና የስነ ከዋክብት ተመራማሪ)፤ አልበርት እንስተይን (የፊዚክስ ተመራማሪ) ስቲቪ ወንደር (ዘፋኝ፤ የዘፈን ግጥም ደራሲ እና አዘጋጅ) እና ቻርልስ ዳርዊንን የመሳሰሉ አንቱ የተባሉ የአለማችን ስኬታማ ሰዎች የተወለዱት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ ነበር፡
To ERMP 2022 Applicants
____________

Information including Instructions for the ERMP 2022 Exam, exam hubs, and the location of exam halls for each hub is available on the Ministry website. Follow the link below:
https://www.moh.gov.et/site/ermp-announcements
የሐዘን መግለጫበኮሌጃችን ከ12 ዓመታት በላይ በምግብ ማደራጃ ክፍል ክፍል በአስተባባሪነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወ/ት ቆንጂት ተክሌ ባደረባቸው ሕመም ሲረዱ ቆይተው ህዳር 14/2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተልይተዋል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ማሕበረሰብም ለቤተሰባቸው፣ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናት ይመኛል፡፡
Join us for a Professorship Speech
Prof. Mahteme Bekele
Date: Dec 20, 2022
Venue: EPHI
SPHMMC , Department of Psychiatry keep producing New vibrant Psychiatrists to heal the nation. Congratulations On your well deserved success
ባልደረባችን ሲስተር ኢየሩሳሌም ክንፈ
ስለ ኤች. አይ.ቪ.ኤድስ መረጃዎችን እንዲህ ይናገራሉ፡፡
SPHMMC Dermatovenereology graduates, 2022
         በሚያስነጥሱበት በሚያስሉበት እንዲሁም ከባድ ነገር በሚያነሱበት ጊዜ የሽንት ማምለጥ ችግር  ላለባቸዉ ወይም ሽንት  መቆጣጠር ለሚያስቸግራቸው እናቶች በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከህዳር 28 እስከ ጥር  5 ድረስ ባሉ የስራ  ቀናት የህክምና አገልግሎት በእናቶች ተመላላሽ ህክምና ክፍል ስለሚሰጥ ችግሩ ያለባችሁ እናቶች የ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡                                          
St. Paul's Hospital Millennium Medical College-Center for Professional and Institutional Development invites you to join a virtual seminar on 'Principles of Stoma and Advanced Wound Care'.

Speaker: Dr. Feven Moges, M.D., Stoma and Wound Care Specialist

Duration: 1 hr.

Date: Friday, December 9th, 2022

Starting time: 3: 00 PM (9:00 PM Local Time)

Register here: https://zoom.us/webinar/register/WN_L3iHvTELSu6soPvGcJXMbA

Zoom
ባልደረባችን ዶር ጴጥሮስ ብሩ ከታካሚያቸው ይህን የመሠለ የምሥጋና ደብዳቤ አግኝተዋል።
ዶር ጴጥሮስ ከአንገት በላይ ሕክምና ክፍል ይሠራሉ።
Internal Medicine graduates of St. Paul, 2022.