St.Paul's Hospital Millennium Medical College
19K subscribers
1.97K photos
23 videos
12 files
458 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን ወለደች
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ  አንዲት  የ30 ዓመት ዕድሜ ያላት ሴት  በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን  በትናትናው እለት ከቀኑ  7፡00  ሠዓት በሰላም ወልዳለች፡፡
ከአሶሳ ከተማ ሆሰፒታል ከፍተኛ ሕክምና እንድታገኝ የተላከችው ይህች እናት ከዚህ ቀደም ሁለት ልጆች የነበራት ሲሆን አሁን ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡ እናቲቱ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት ስለተከሰተባትና  የአራት ሕጸናት እርግዝና በመሆኑ ነው ወደ ኮሌጁ በʻሪፈርʻ  የተላከችው፡፡
የቀዶ ሕክምናውን  በመሪነት  ያከናወኑት ዶር ሩት  ሰለሞን እንደገለጹት  ቀዶ ሕክምናወ 31 ደቂቃ መፍጀቱን ገልጸው፡ አራቱም አራቱም ሕጻናት የተወለዱት በ31 ኛ ሳምንታቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡  በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉም ብለዋል፡፡ የሕጻናቱ ክብደት መጠንም ጥሩ መሆኑንንም ገልጸዋል፡፡
እናቲቱ በአነስተኛ የሸቀጣቀጥ ንግድ ስራ  የተሰማራች ሲሆን ባለቤቷ ደግሞ  ሾፌር  ነው፡፡ ሁለቱም ወላጆችም አራት ልጆች ለማግኘት ፈጽሞ አለማሰባቸውን ገልጸው ነገር ግን የእግዚአብሔር ስጦታ በመሆኑ ደስተኛ ነን ብለዋል፡፡
ይህን ቀዶ ሕክምና በተባባሪነት የመሩት ዶር ጌታ መሳይ ሞላ ሲሆኑ በተጨማሪም ነርሶች ፡ ሚድ ዋይፎች እና የአንስቲስት ባለሙያዎችም አብረው ሰርተዋል፡፡
በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን  መውለድ  ከ500 ሺህ እናቶች መካከል አንድ ጊዜ የሚያጋጥም እንደሆነ ይነገራል፡፡

Quadruplets Delivered Safely at St. Paul’s Hospital
A 30-year-old mother from Assosa has safely delivered quadruplets at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College in Addis Ababa. The babies were born at 31 weeks via a carefully managed delivery due to the mother’s pre-eclampsia. This was her fourth pregnancy; she already has two children.
Led by Dr. Ruth Solomon and assisted by Dr. Getamesay Mola, a skilled medical team ensured a safe delivery. All four premature babies are stable and being cared for in the neonatal intensive care unit (NICU).
“The successful delivery was due to teamwork and timely care,” said Dr. Ruth Solomon. The mother and babies are under close observation and improving well.
The father, a driver in Assosa, thanked the team for their dedication. St. Paul’s continues to lead in high-risk maternal and newborn care in Ethiopia.