St.Paul's Hospital Millennium Medical College
19K subscribers
1.97K photos
23 videos
12 files
458 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ነጻ ሕክምና
የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ላለባቸው፣ዕድሜያቸው 3 ወርና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሕጻናት ኮሌጃችን ዳይሬክት ኤይድ ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ነጻ ሕክምና ይሰጣል፡፡
በተጨምሪም የጣት አበቃቀል እና መዛባት ችግር ያለባቸውም ሕጻናት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት በ976 በመደወል ወላጆች ተራ ማስያዝ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ST. PAUL'S HOSPITAL MILLENIUM MEDICAL COLLEGE
OFFICE OF THE REGISTRAR
Call for Application, post graduate programs 2023/2024 academic year.
All students will join the college after satisfactorily passing the Graduate Admission Test (GAT) that will be administered by MoE, Written and Oral exams will be given by the hosting department. The date will be notified on social media pages.

School of Nursing: MSC programs
1. Critical Care Nurse Practitioner (Nursing Residency Type)
2. MSc in Parademic Science
4. Cardiothoracic Surgery Nursing
5. MSc in Cardiovascular Nursing
6. Master of Science in Neonatal Nursing ( Residence type )
7. Master of Science in Clinical Oncology Nursing(Residence type)
School of Medicine: MSC Programs
1. Medical Microbiology
2. Respiratory Therapy
3. Medical Radiologic Technology
a. Computed Tomography and Magnetic resonance imaging Pathway
b. Ultrasonography Pathway
c. Radiography fluoroscopy and Mammography Pathway
d. Interventional Radiologic Technology Pathway
4. Clinical Embryology

School of Public Health
Ph.D. in Public Health
MPH programs
1. Health communication and promotion (regular and weekend)
2. Public Health Nutrition (regular and weekend)
3. General Public Health (regular and weekend)
4. Epidemiology (regular and weekend)

Application period is from August 11 to September 13/2023 GC

For the detail on the Admission Criteria and registration visit the link https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement
የጤና ምርመራ ያድርጉ -ነጻ!
ቦታ:-ራስ ኃይሉ ስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል።
ከነሐሴ 11-17/2015
" በጎነት ለጤናችን " በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የክረምት የበጎ ፍቃድ የጤና አገልግሎት  ነጻ ምርመራ  ዛሬ  የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶር ደረጄ ዱጉማ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በሚቆየዉ ነጻ የሕክምና ምርመራ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ መጥቶ የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚችል በመክፈቻው ላይ ተገልጿል፡፡
ለምን አመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ አለብን?
አመታዊ የጤና ምርመራ በተለያየ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች የሚደረግ እና ለአንድ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው።
እድሜ እና ፃታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና ከዛም በላይ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች አሉ። እነዚህን ምርመራዎች መረዳት እና መቼ መጠየቅ እንዳለብዎት ማወቅ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያግዝዎታል። እንደ ካንሰር ፤የልብ ህመም፤ስትሮክ ፤የኩላሊት ህመም፤የስኳር ህመም፤የደም ግፊት መጨመር እና አንዳንድ በቅድመ ጥንቃቄ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን ህመሞች ለመቆጣጠር ቀደም ብሎ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ታዲያ የጤናዎን ሁኔታ ለማወቅ ለምን ወደ እኛ አይመጡም? በራስ ኃይሉ የስፖርት ማዘውተሪያ እንገኛለን። ምርመራው ደግሞ ነጻ ነው።
ኡሁን ምንም ዓይነት ሕመም ስሜት ላይሰማዎት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ በሽታዎች ምልክታቸው በውል የምንገነዘበው አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ የበሽታው ሰስር ሳይሰድ አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡ በተለያየ የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች የሚያደርጉት የጤና ምርመራ ለአንድ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ ያስችላቸዋል፡፡
ታዲያ እርስዎ ወረፋ ሣይጠብቁ፡ ካርድ ሳያወጡ፡ ምንም ሳይከፍሉ ለምን የጤና ምርመራ አያደርጉም? ፈቃድዎ ከሆነ መድሐኔያለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደተጃ ትምህርት ቤት ዝቅ ብሎ በሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ተገኝተው የጤና ምርመራ እንዲያድርጉ ጋብዘንዎታል፡፡