ኢንስቲትዩቱ የ2019 አዲስ ዓመትን በማስመልከት ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ማዕድ ማጋራት አከናወነ።
======= SSGI =======
(ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም SSGI)
ኢንስቲትዩቱ ከምርምርና ልማት ስራዎቹ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለመቄዶንያ ሐረጋዊያን መርጃ ማዕከል፣ በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል እና በዋናው መስሪያ ቤት በጥበቃ ስራ ላይ ለተሰማሩ የፌዴራል ፖሊሶች አንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ስራ ባልደረቦች ሆነው በተለያዩ ጊዚያት እክል ለደረሰባቸው ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃግብር አካሂዷል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ ድጋፉን ያስረከቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ ሲሆኑ ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም የአዲስ ዓመት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ኢንስቲትዩቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈቱ የስፔስና ጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ ምርምሮችን ከማካሄድ ባለፈ፤ ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
ከምድር እስከ ህዋ …
SSGI

ለመላው የኢንስቲትዩቱ የስራ ባልደረቦች፣ የተቋማችን አጋር አካላት እና ኢትዮጵያዊያን
እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
መጪው 2019 ዓ.ም በሁሉም መስኮች የላቀ ስኬት የምናስመዘግብበት፧ በሥራችን ልቀን የምንገኝበት፣ የሠላም፣ የጤና፣ የስኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።
መልካም አዲስ ዓመት!

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲሳ ይልማ አዲሱን የ2019 ዓመት በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት፥
👍4❤2
ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ አዲስ ባለብዙ ተግባር ሳተላይት ይፋ አደረገች
********
የቻይና ተመራማሪዎች የህዋ ቴክኖሎጂን ወደ አዲስ ደረጃ የሚያሸጋግር ትልቅ ስኬት አስመዝግበዋል። ቀደም ሲል ሳተላይቶች የሚሰሩት አንድ የተወሰነ አገልግሎት ብቻ ቢሆንም (ለምሳሌ ምስል ማንሳት ብቻ ወይም የቴሌኮም መረጃ ማስተላለፍ)፣ አሁን ግን መገናኛን፣ ዳሰሳን፣ ማስላትን እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሂደትን በአንድ ላይ የሚያጣጥም ባለብዙ ተግባር ሥርዓት እውን አድርገዋል።
ለዚህ አዲስ ስኬት ማሳያ የሆነችው ፔጋሱስ 1 (PEGA-SUS1) የተሰኘችው 150 ኪሎ ግራም የምትመዝን ሳተላይት ናት።
ሳተላይቷ በሼንዘን የሚገኘው ፔንግቼንግ ላብራቶሪ፣ በቤጂንግ የሚገኘው ጋላክሲ ስፔስ የግል ኩባንያ እና ሌሎች የምርምር ተቋማት በጋራ የበለጸገች ሲሆን በቻይና የንግድ ሮኬት አማካኝነት ከሌሎች 8 ሳተላይቶች ጋር ወደ ህዋ ተልካለች።
የዚች ሳተላይት ዋና ልዩነቷ መረጃን ከህዋ ወደ መሬት ካወረደ በኋላ መተንተን ሳይሆን መረጃውን እዚያው ህዋ ላይ እያለች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ራሷ ማቀናበር መቻሏ ነው።
እንደ ጋላክሲ ስፔስ ከፍተኛ ቴክኒክ ባለሙያ ሬን ጂያዶንግ ገለጻ ለምሳሌ የደን ቃጠሎ ቢከሰት ሳተላይቷ የቃጠሎውን መኖር እና የጉዳቱን መጠን እዚያው ህዋ ላይ አጠናቅራ ዋናውን ውጤት ብቻ በፍጥነት ወደ መሬት ትልካለች።
ይህም ጥሬ ምስሎችን ሙሉ በሙሉ መላክ ስላይስፈልግ የማስተላለፊያ ጊዜን እና የመረጃ መጠንን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።

አዲሷ ፔጋሱስ 1 (PEGA-SUS1) ሳተላይት በአጠቃላይ ዘጠኝ ሳተላይቶችን እንደሚያካትት በተገለጸው ስብስብ ውስጥ የመጀመሪያዋ ፈር ቀዳጅ ናት።
በቀጣይም ለ6G ቴክኖሎጂ እና ለቻይና የሳተላይት ኢንተርኔት ፈጠራ ትልቅ መሠረት በመጣል ከመሬት እስከ ህዋ የሚዘልቅ የተቀናጀ የመገናኛ መረብ ለመገንባት መንገድ ትከፍታለች ተብሎ ተስፋ ተይዟል።
#SSGI EBC
#ChinaSpace #PEGASUS1 #SatelliteTechnology #GalaxySpace #SpaceInnovation

❤1
Forwarded from Ministry of innovation and technology (MinT)
ስትራይድ 2.0 (STRIDE 2.0)!!!
================
የኢትዮጵያን የ50 ዓመታት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ጉዞ እና የዲጂታላይዜሽን ስኬቶች የሚያከብር፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ዋና ዋና ብሔራዊ ስኬቶችን የሚቃኝ እንዲሁም ለሚቀጥሉት 50 ዓመታት አቅጣጫ የሚያስቀምጥ አገር አቀፍ ሁነት ነው።
ሁነቱ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. (እንደ ፈረንጀቹ አቆጣጠር ከሴፕቴምበር 29 እስከ ኦክቶበር 1 ቀን 2026) በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ይከናወናል።
ይህ ሁነት የሃሳቦች፣ የእድገት፣ የቴክኖሎጂ እና የመፃኢ እድሎች ማመላከቻና የባለራዕዮች መገናኛ ቦታ ይሆናል።
የ50 ዓመታት ጉዞ እና እድገት፤ የአምስት ዓመት ስኬት፣ ከዛሬ ውጥን የቀጣይ 50 ዓመታት ጉዞ ይጀምራል።
ይምጡ ይጎብኙን።
መግቢያ በነፃ!
ሁነቱ ለህዝብ ክፍት በሚሆንባቸው ሁለት ቀናት (በመስከረም 20 እና መስከረም 21) በጠቅላላው 750 ነፃ የጎብኚዎች መግቢያ ፈቃዶች (Passes) የተዘጋጁ ሲሆን፣ በየቀኑ 375 ነፃ ፈቃዶች የሚሰጡ ይሆናል።
ቦታ፦ አዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም
ቀን፦ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 21(ከሴፕቴምበር 29 እስከ ኦክቶበር 1)
አዘጋጅ፦ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
#STRIDE2 #EthiopiaSTI50 #InnovationForTheNext50 #DigitalEthiopia #ScienceTechnologyInnovation #MInT